የዲማ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ውጪ ሀገር

Postby ምረቱ » Sun Nov 09, 2008 3:25 am

ውጪ ሀገር

ነገሩን ለማያቅ ውጪ የሚባለው ስሙ ቢያስደስትም
ውስጡ ለቄስ ይሁን እንደስሙ አይደለም
ብዙ ቢባልለት አኗሪ አንቀባሮ
የተወለወለ ቢያስመስል ብርሌ ገጽን አሳምሮ
ባይታይ ነው እንጂ ብዙው ከውስጥ ጠቁሮ
በደስታ ደህይቶ ይኖራል እሮሮ
አይ የውጭ አገር ኑሮ!!!

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ዋናው » Sun Nov 09, 2008 3:29 pm

ሠላም ምረቱ...
ሠሞንኛ የዋርካ ቀሽም አቢዮት በተነሳሳበት ጊዜ ሆኖ'ንጂ እቺ ቤት ሸላይ ናት:: የባለ ስድስት የወል ቤት የበዛበት ስንኞች ከዋርካዊያን ገጣሚዎች ዘንድ ብዙ ጊዜ አይታይም.... እናም ያንተይቱ ስንኝ ሹረባ የጥበቡን ዘርፍ መልክ አብዝቶ ከማቆንጀትም .... (ቀሽት) ነው::

ቃላት ይርቡልህ ብያለው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ምረቱ » Sun Nov 30, 2008 5:32 am

ዋናው wrote:ሠላም ምረቱ...
ሠሞንኛ የዋርካ ቀሽም አቢዮት በተነሳሳበት ጊዜ ሆኖ'ንጂ እቺ ቤት ሸላይ ናት:: የባለ ስድስት የወል ቤት የበዛበት ስንኞች ከዋርካዊያን ገጣሚዎች ዘንድ ብዙ ጊዜ አይታይም.... እናም ያንተይቱ ስንኝ ሹረባ የጥበቡን ዘርፍ መልክ አብዝቶ ከማቆንጀትም .... (ቀሽት) ነው::

ቃላት ይርቡልህ ብያለው


ሰላም ዋናው:

እግዜር ይስጥልኝ ለአስተያየቱ:: አማርኛ (ለመጻፊያ የሚሆነው ማለቴ ነው) እንደቁምጣ እያጠረብኝ እኮ ነው:: በዚያ ላይ አማተርነቱም አለ:: የሆነ ሆኖ ግን የምጫጭረው ነገር መናገር የፈለኩትን ካደረሰልኝ ለኔ ስርግ እና ምላሽ ነው:: ዋናው መልዕክቱ ስለሆነ:: ታንኪው አጌይን!

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የኅሊና ዕዳ

Postby ምረቱ » Sun Nov 30, 2008 6:13 am

ኢትዮጵያ ኑሮ የመወደዱ ነገር እዚህ ዋርካ ላይ አልፎ አልፎ ይነሳል:: በሌሎች የዜና ማሰራጫዎችም አየዋለሁ:: የችግሩን ክብደት ድሮውንም እረዳዋለሁ:: ያሳስበኝማል:: የዛሬ ሁለት ሳምንት አካባቢ ወደ ቤት ስልክ ደውየ ስለሰፈራችን ሰዎች ተራ በተራ ጠይቄ ብዙዎቹ በምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳሉ ገባኝ እና ሙድ ሪሴሺን ሲጫወትብኝ ከረመ:: ባጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ እየሆነ ካለው ነገር የተለየ ነገር እንደማይጠብቃቸው ባውቅም አገሬን ሳስብ በፍጥነት ትዝ ስለሚሉኝ ሁኔታቸው ሰላም ነሳኝ::

ይቺን ግጥም በግድ ሞከርኩአት:: ሌላ ጊዜም እቀጥልባት ይሆናል::


የኅሊና ዕዳ:

መቼም ኅሊና የሚባል ነገር ካለ
ለቀናት መዘንጋት የሌለበት ያልተከፈለ ዕዳ አለ::

እናት ለልጁ የሚሆነውን የሆነች
ተበድራ ተቀድማ ያስተማረች
እናታችን ኢትዮጵያ ...
ዛሬም በቀን ጎደሎ በጣዕር ተይዛለች::

ያኔ የኔታ ቤት ተዘልቆ አቡጊዳ
አስኮላም ተገብቶ ሌላ ለማወቅ ስንሰናዳ
እሱም ሽው ብሎ አልቆ
የበረታውም ኮሌጅ ዘልቆ
ባለው ላይ ብዙ ጨምሮ
ተፈትሾ መተንተን መቻሉ ያወቀውን አብጠርጥሮ
ካባ ለብሶ ምሎ ሲሊውን ሊይዝ...
ድንቁርናን ሊመታው አጠንክሮ

ያስተማረችንም በሌላት አቅሟ
እናታችንም ኢትዮጵያችን እማማ
ችግሯን አምቃ እንባዋን አደራርቃ
የደረሱላትን ልጆችዋን መርቃ
የሀዘን እንባዋ ደርቆ እንዳትኖር ትንሽ እንኳ ስቃ
እስከዛሬ እንደ ጂረት የፈሰሰው እንባ እንዳይበቃ
ዛሬም ኢትዮጵያችን አለች ቀን ጎሎባት ተይዛ በሀዘን ሲቃ
ምን ይብቃ??!!

ያሁኑ ይባስ! የፊጥኝ ተቀፍድዶ የታሰረ
እንዳይበላ ተፈርዶበት ተከንትሮ ያደረ
በቀን አንዴም አፉን ያልሻረ
እሱን እያየች...
መኖር ከተባለ እናታችን ኢትዮጵያ ዛሬም አለች
በእንባ እየታጠበች::

መቼም ኅሊና የሚባል ነገር ካለ
መዘንጋት የሌለበት ያልተከፈለ ዕዳ አለ::

ካብራኳ የወጣ ጐፈሬ ዛሬ ጸጉሩን ተከርክሞ
አምሮበት ሺክ ብሎ በሱፍ ተሸልሞ
ከዘመኑ ሰዱቃውያን ጋር ገጥሞ
""በነፃ-ገበያ"" ቅኝት ይደለቃል እየመታ አታሞ
ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ...
ማን ከልካይ አለበት ይናገራል ደሞ

"" ኢትዮጵያማ አድጋለች
የነብስ-ወከፍ ገቢ በእጥፍ ጨምራለች""

ህልቆ መሳፍርት የሌለውን
በየቤቱ በነብስ ወከፍ በራብ ሆዱ የሚጮኸውን
እንጀራ ቁም ነገር ሆኖ እሱን ያጣውን
ተመቸኝ ብሎ ""በአድጎአል"" ውሸት መጀቦን

ህሊና የሚባል ነገር ካለ
መዘንጋት የሌለበት ያልተከፈለ ዕዳ አለ::

ያለ ነጋሪት ጋዜጣ
ይመስላል አዲስ አዋጂ የወጣ
እናታችን ኢትዮጵያ ታስራ ተቀፍድዳ
ታውጆባታል እንድትቀበር በሰዱቃዊ ቆዳ

ለወንበዴ አላጨበጭብም ያለው ቂም ተይዞበት
እሚበላው አሳጥተው በራብ አለንጋ ሲገርፉት
ያን ኩሩ ህዝብ ለዱቄት ሲያሰልፉት
ከዚህ በላይ! አወረዱ እንጂ መዐት!

መቼም ኅሊና የሚባል ነገር ካለ
ያልተከፈለ ዕዳ አለ.....

ምረቱ

ህዳር 20, 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የተዳፈነ ግለት

Postby ምረቱ » Sat Dec 27, 2008 6:00 am

የተዳፈነ ግለት

በልብ አዳራሽ ውስጥ ሲግም የነበረ
""ነገን"" በማስታጎል የተጠረጠረ
ውስጥን የሚያሞቀው ያ የልብ ግለት
መጋሉን እንዲያቆም ያኔ ተፈርዶበት
እሳትነቱ ተዳፍኖ
ያላባቱ መሬት ሆኖ
ውሉን ሳይስት ኖሮ ኖሮ...የጠፋ መስሎ
እንደገና ጋመ ባይነ-ግቡ መለሎ!

ምረቱ
Last edited by ምረቱ on Thu Mar 26, 2009 1:04 am, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sat Feb 14, 2009 4:30 am

ደሞ መጣ ይኼ ጠኔ
ዳግም አንገቱን ደፋ ወገኔ?
Last edited by ምረቱ on Sun Nov 08, 2009 8:21 pm, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Fri Mar 20, 2009 1:45 am

"ኮመን ሴንስ"

መነገጃ ተብሎ በተሰበሰበ
ውስጡ ሳይፈተሽ ብዙ በከረመ
በታጀለ ሀሳብ እየተዘገመ;
አላዘግምም ያለ ትቺቱን ሲያሰላ
በሚያዘግመው ብሶ ስለታሙን ሀሳብ...
ሊያስመስል የተላ
ወርቃማውን ሀሳብ ደርሶ ሲገዳዳር
"በኮመን ሴንስ" ፊት ሊያደርገው ባይተዋር
ከዚያው ከታጀለው ምክንያት ሲደረደር
ምነው! ...ቁርጡን 'ሚናገር ያሳብ ሚዛን ቢኖር
ደንደሳም "ኮመን ሴንስ" በቀለለ ነበር::

ምረቱ ኮምን ሴንስ ቋቅ ሲለው የጻፈው ነው
ቶሮንቶ, መጋቢት 12, 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

The power of beauty

Postby ምረቱ » Sat Mar 21, 2009 12:59 am

ውበት እንደ ካቴና


በተሰጣት እየፈካች; እያማረች
የማይገራ ልብ እንቢተኛ ነብስ ካሰረች
ውበት በርግጥ ካቴናም ነች

እንደ ወፈ ሰማያት
...ህልቆ መሳፍርት
አገር ምድር ሔዋን በሞላበት
ወዳጂ አካል(ልብ) አንደዋዛ ካቴና ገብቶለት
ነብስ ላላት ነብስ ታማኝ እስረኛ ከሆነላት
በርግጥ ውበት ካቴናም ናት !!

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Wed Mar 25, 2009 2:41 am

ዘመነ ጭልፊት

ቀናዒ ልቦና
አስተዋይ ህሊና
ጭልፊት መሪ ሆኖ
ማዕረጉን አጣና;
ጆቢራም በዛና
ዐይን ባይን ሆነ
ድንገት አዘናግቶ
መሞጭለፍ ሆነና;
የሰው ልጂ መለያ
ፈጣሪ የሰራው
በራሱ አምሳያ
በጎ ስራ; ፍቅር ሞቶ;
እንዳይን ጠፍቶ
እኩይ ግብር; ጭካኔ
በሰው ልጂ እሳቤ ግዛቱን አስፋፍቶ
የፈጣሪም አምሳል ተረስቶ;
በሰላም አገር ሳይጠር; ሳይጠና ቆሪሩ
እኩይ ግብር; ውሸት ብሶ በፈራሚው; በባለወንበሩ
ሲያጋፍር ስርቆቱን ሳይነቃነቅ ከመንበሩ
ሕግም ጥላ ሆኖላቸው ሕዝብ ሲመዘብሩ
ጭራሽ በሰረቀዉ; ለሚሰርቅበትም ማይረጉ
ያገር ልጆች ጠባቂ ወታደር ሲደረጉ
ሌባነቱን እንዲረሱ ሆነው;ታጥቀው ለሌባ ሲያደገድጉ
""የለም! ይኼ ሌባ ነው ያሉ"" ሲገደሉ; ሲወገሩ
በጠራራ ፀሀይ በሐሩሩ
ሌቦች ሲሾሙ;ሲከበሩ
ምን ሊያሳስት!
ይኼማ ነው ዘመነ ጭልፊት!!
ኤሎሄ ለሚል ኤሎሄ 'ሚልበት::

ሕብረት ሙሾ ታውርድ
ጎበዝ ግን ይነሳ
እንባዋን በመጥረግ
ዘመኑን ለመናድ
ሞጭላፋ እንዲቀጣ
በሰረቀው ነገር መጀነኑ ቀርቶ
በውል እንዲዋረድ!!

ምረቱ,

መጋቢት 16, 2001, ዓ. ም
ቶሮንቶ
Last edited by ምረቱ on Sun Apr 12, 2009 1:05 am, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ሰው መሳይ በሸንጎ

Postby ምረቱ » Fri Apr 03, 2009 1:31 am

ሰው መሳይ በሸንጎ

ለቀማኛ ወሮበላ ያደረ
እደሚለብሰው ካባ ህሊናውን ያጠቆረ
እውነት ዘብጥያ ሲጣል አብሮ በመንፈስም ያሰረ
ሱፉን ከካባ አስማምቶ
ከሱፍ መልስ ያለውን
ስብዕናውን አጨቅይቶ
ህሊናውን በሳስቶ; አድርጎ ቡትቶ
የሚበይንበት ወንበር ላይ ሲያዪት ተጎልቶ
ሰው መሳይ በሸንጎ
ፍርድ አዋቂ;አሳቢ በጎ
እሱ የሚቀመጥበትን ወንበር ሲያሽከረክር
ከላይ ግን ሲያሽከረክሩት
... እንደፈለጉት ሆኖ እንዲያድር
ሲያስብሉት ጥቁሩን ነጭ;ነጩን ጥቁር
የፍትህ ቅጣንባር ጠፍቶበት ሲደናገር
ምነው ራሱን እንኩአን ቢሽር
ውስጡን ኮስኩሶት ከሌባ;ለሌባ ማደር!!
ግን እሱም የሱ አይደል; አለበት ወታደር::

መጋቢት 24, 2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ሁለት ሞት

Postby ምረቱ » Sun Apr 05, 2009 5:12 am

ሁለት ሞት:

አገር ጥሎ ተኮብልሎ
ከኑሮ ወጥመድ ላይመለጥ
ክልብ ሆኖ ላየ...ከፀሀይ በታች...የሚለውን አስቦ
አንደኛው ከሌላው ብዙ ለማይበልጥ
እንዲህ ሊኖር ፍዳ ተከፍሎ
አነሰም አደገም የነበረን; የወንዝን ጥሎ
እለት ተለት እየተንከባለሉ እንደ አለሎ

ደሞ ይነገራል ...
ስም አይሞት ይባላል...
ይኼው ሞቶ በቁም ተቀብሮ
በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሂሳብ
ሰው ሲኖር ከመጠሪያው ተሰውሮ
ቀሪ ሀብቱን ስሙን ቀይሮ
ስም የማይገዛ ከሆነ
እንደምንስ ሊሸጥ ተወሰነ?
ግን ብዙ ሰው አለው ""ምን አለበት?!""
እኔ ግን አልኩት ሁለት ሞት

መጋቢት 27, 2001 ዓ.ም
Last edited by ምረቱ on Fri Apr 10, 2009 4:19 am, edited 2 times in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Thu Apr 09, 2009 4:20 am

የፍትሕ አርበኛ

የፍትህ ተሟጋች አርበኛ
ተገኝታ ቆፍጣና እንስት ዳኛ
ልጓሙን አጥብቃ ይዛ
በፍርሀት በብረት; ሳትገዛ
አላስነካም ብላ ፍትህን በዋዛ
በነጻነት ስለፍትህ ስትበይን
ስለእውነት ሳታጋንን
ሆኖባቸው የራስ ምታት
ለሚገዙት ""በእንተ ሰማዕታት""...
በዱላ; በብረት
የጎሪጥ ሲያዩአት
ገባትና የፍትህ መሰረት መናጋት;
በቆይታ መሰረት ልታጸና; ልታደላድል
በሴት አቅሟ ገባች ወደ ትግል::

ጥሊያንን እንደተፋለሙት የእናት አርበኞች
ወኔዋ ሳይከዳት; ሳትል ፍንክች
ልክ ልክ ስለተናገረች
በውሸት እና በብረት እንደገና ታሰረች
እንደምን የታደለች!!
ለእምነቷ -በእምነት የጸናች
ስንቱንስ እንስት ለትግል አነሳሳች!!
እኔ አልኩአት የሴት ወንድ-የእውነት አገልጋይ
ይጠብቅሽ ኤልሻዳይ!!!

ለብርቱካን ሚዴቅሳ,
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

"ፍቅር እድሜና ፆታ አይለይም'

Postby ምረቱ » Wed Apr 15, 2009 1:54 am

እንዲህም አለ:

በእንተ ፍቅር የተራቡ
በእንተ ፍቅር የጠገቡ
ነው ይኼ መከተቡ:

ድሮ...
ለነገ ዕጣ ፋንታ ስኬት
ዘዴ ብልሀት ሲዶለት
ከጂስም* -ከሰራ አከላት
"ልብ' ተግሳጽና ቁጣ ደርሶት
ጭንቅላትን "በሽምደዳ' ለማገዝ
በየቤተ-መጽሐፍቱ ሲዋትት
ልብ እንደ ""ልብ"' ሳይጫወት ፊት ተነስቶ
የአካል-የሕይወት መዘውር እንዳልሆነ ነገር ተዘንግቶ
የመውደድ ቅዋው**ደክሞ ሳስቶ
""ነገ"" አዳምኖ በሳለው ገጽ ፈዞ
በማያውቀው "ነገ" ታዞ
ለማያውቀው"'ነገ"" ተክዞ
ከነማፍቀሩ ተቀብሮ""በነገ"" ተገንዞ
ትንሽ እንኳ ሳይዘከር ተትቶ
አሁን(ነገ ዛሬ ሆኖ) ከዘመን በኍላ ትንሳዔ አግኝቶ
የመውደድ ኃይሉም አገርሽቶ
ቢወድ አንዲት ድማም
የለዛ ባለጠጋ ሀብታም
በግርማዋ ከልብ ተስቦ
ቢፈልግ ሊያወራት ቀርቦ
ሰኔና ሰኞ; "'አንተን አላውቅ; ፍቅርም አልፈልግ"" ተባለ
እንዲህም አለ
መተያየት; መነጋገር ማንን ገደለ?!
የኔ ፍቅር;
የልቤን ጥጋጥግ መሀሉም ሳይቀረው እያተራመሰ
እንጥል የምታህል ትንሽ እንኳ ፍቅር ልቧ ካልደረስ
በኔ 'ሚንቀለቀል የፍቅር ነበልባል ትንሽም ካልታያት
""የሷ ባይሆን ብዬ"" አሁን ጠረጠርኩት
እንግዲህ አምላክ ባርኮ ለሌላዋ ይስጣት!!
~~~~~ ~~~~~ ~~~~~


መፍቻ:
*ጂስም- ሰውነት
**ቅዋው- አቅሙ

(ጊዜያቸውን ላይብራሪ ለላይብራሪ ላቃጠሉ; ለተሸወዱ; ፍቅር ለተራቡም; ፍቅር ለጠገቡም ይሁን)

ሚያዚያ 7, 2001 ዓ.ም
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ!

Postby ምረቱ » Sun Apr 19, 2009 2:58 am

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
....
በአብይ ኃይል ወስልጣን

... አሰሮ ለሰይጣን!

አጋዞ ለአዳም
ሰላም
ንዜእሰ
ኮነ
ፍስሀ ወሰላም!!

መልካም የትንሣዔ በዕል ይሁንላችሁ!!
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sat Apr 25, 2009 1:32 am

የሰፈሬ እናቶች:

የደግነት ድካ
የቸርነት ዋርካ
የሰፈሬ እናቶች
እነኚያ ደጋጎች
የማምላክ ወዳጆች
ምንም ሳይኖራቸው
ዐመል ሆኖባቸው
ለሰፈር ልጃቸው
ይፈታል እጃቸው::
"" የኔ ልጂ በሞቴ አፈር ስሆንልህ
እንዴት እድርጌ እንደሰራሁት ብታይ እኔ እናትህ
እፈር ስሆንልህ?!
እንዲያው ምን ሆነህ ነው ትንሽ ብትቀምስ
ጥሩ ድቁስ
እንጀራውም ትኩስ
ቆንጆ ሽሮም አለ ካንጀትህ እንዲደርስ
ምነው ደስ ቢለኝ የልቤ ቢደርስ?! ""
መስጠት እኮ ነው የልባቸው
ለወደዷቸው ልጆቼ ላሉአቸው!

በጎን ዘንበል ብለው
ዐመዱን ተታከው
"'እፍ"" እያሉ 'ሚያነዱት እሳት
ፊታቸውን እንደጉልቻው ድንጋይ ጠብሶት
ጥላሸት ፊታቸው ላብ ቸፍ ብሎበት
ኑሮ የገደላቸውን 'ረስተውት
ከመጤፍ ሳይቆጥሩት
""አፈር ስሆንልህ ብላልኝ ይሉኛል""
እኔን እንዲሞቀኝ እንደዛ ጠቋቁረው
ጻዕዳ ፍቅራቸውን ይደርቡልኛል::
ልክ እንደ ትልቅ ሰው ካንጀት ያከብሩኛል
ከወዴት ይገኛል?!
እንዲህ ያለ ሐገር;
እንዲህ ያለ ፍቅር;
እግር እስኪነቃ ሲኬድንኳ ቢኖር::

እንደ አለመታደል
እነዚያን እናቶች
ባይኔ ሳላያቸው
""አረፉ"" ይሉኛል
አንድ ቀን ሳያርፉ
ሲለፉ ላለፉ!

የሰፈሬ እናቶች
እነኚያ ደጋጎች
የማምላክ ወዳጆች
አምላክ ይክፈላቸው
መሬት ይቅለላቸው!!!


በሞት ለተለዪ ሁለት ጎረቤት እናቶች የተቋጠረ

ሚያዚያ 16, 2001 ዓ.ም
Last edited by ምረቱ on Sun Jun 12, 2011 2:36 am, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests