የዲማ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ምረቱ » Fri Mar 05, 2010 6:25 am

ቶድ wrote:በቅድሚያ የከብረ ሰላምታ ለዲማ!!!!!

""ፍቅር እስከ መቃብር"" በታላቁና ስመ ጥሩ ደራሲ በዶክተር አዲስ አለማየሁ ..... በዲማ ጊዮርጊስ ዙሪያ ህይወትና ነፍስ ሲዘራበት ............ ዛሬ ደግሞ የታላቁን የአድዋን ድል በማስመልከት በተከበሩትና እጅግ በጣም በምናፈቅራቸው በእነዛ ስመ ጥር ቅድመ አያቶቻችን ስለተከፈለልን መስዋትነት ገድል ..... ባህሉንና ታሪኩን በሚወደውና በሚያከብረው በውድ ወንድማችን በዲማ ...... ""ነፍስና ህይወት"" በተዘራበት የግጥም መድብል የአድዋ ምድርና እንዳያልፉ ሆነው ስላለፉት ውድ ሰማዕታት አያቶቻችን ነፍስና ህይወት ሲዘሩ በማንበቤ ....... ከታላቁ አድናቆቴ ባሻገር ..... የዲማ ስም አሰያየሙ ... ""በተፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ"" ..... ተጨማሪ ህይወት የመዝራቱ ሚስጥር እንቆቅልሽ እንዲሆንብኝ እየጋበዘኝ ነው::

ወንድም ዲማ እጅግ በጣም ግሩም ግጥም ነውና የምትጽፈው ....... በርታ!!!!! በዚሁ ቀጥልበት!!!!!! ባሕላችንና ታሪካችንንም ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ..... የአንተን መሰል ወገን መፈጠሩ እሰየው የሚያስብል ነው!!!!!

በዚህም አጋጣሚ የታላቁን የአድዋን ድል በዓል በማስመልከት ለሁሉም ወገኖቻችን የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ..... የዛሬ 114 ዓመት ገደማ .... ውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን በዘርና በሐይማኖት ሳይከፋፈሉ ... በታላቁ በአድዋ ምድር ላይ ..... ከአራቱም የሐገራችን መዓዘናት በመሰባሰብ ስለከፈሉት መስዋትነት ...... የአድዋ ምድርና በተለይም የአድዋ ተወላጆቿ ስለኢትዮጵያ አንድነት እጅግ በጣም የከበደ ሀላፊነት ሊሰማቸው እንዲገባ ከፖለቲካ እጅግ በጣም የነፃ መልክቴን አስተላልፋለሁ:: እንደዚህም ስል ለአድዋ ልጆች ብቻ የተለየ መልክት ላስተላልፍ ፈልጌ ወይንም የአድዋ ልጆች የሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ውለታ አለባቸው ለማለት ሳይሆን ...... ወይንም በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የአድዋ ልጆች ናቸው ለማለት ፈልጌ አይደለም .... ወይንም ሌላው ኢትዮጵያዊ ምንም ተሰሚነት የለውም ለማለት ሳይሆን ወይንም ለአድዋ ልጆች ከሌላው ወገኖቼ የተለየ ብልጫ ለመስጠትም ሳይሆን (ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ነው!!!!! ምንም ጥርጥርም የለውም!!!!!!) ..... የታላቁ የአድዋ ድል የታሪክ መፃፊያ ደብተሩ የአድዋ ምድር መሆኑዋና ....... በአድዋ ላይ ስለተከፈለው መስዋትነት ...... እያንዳንዱ ውድ ወገናችን በዘር .. በፆታ ... በሀይማኖት ሳይከፋፈል ..... ከእያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ .... አንተ ትብስ እኔ ትብስ ተባብሎ ታሪክ የሰራበት አጋጣሚ ነበርና ...... ዛሬም!!!!!!!! አሁንም ቢሆን!!!!!!!! እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ!!!!!! ይህንን በዓል በማስመልከት በዘር የመከፋፈል ፖለቲካውን በመተው ....... በተለይም ነገ ለምንወልዳቸው ውድ ልጆቻችን መርዝ አዘል የቤት ስራ እንዳንሰጣቸው ....... አንድነታችንን ጠበቅ!!!!!!!!!! የምናደርግበት አጋጣሚ እንዲሆን ከአደራ ጋር መልእክቴን ለእያንዳንዱ ወገናችን በዚህ አጋጣሚ አስተላልፋለሁ::


ሰላም ቶድ:

ጊዜህን ወስደህ በማንበብህ እና ለማበረታት በመጻፍህም ምስጋናየ ይድረስህ:: እኔ ስለ እውነት ለመናገር ጸሀፊ አይደለሁም:: እዚሁ ዋርካ ላይ ነው ግጥም መሞከር የጀመርኩት:: እኔ የሞካከርኩአቸው ነገሮች እንዲህ እንደ ግጥም ታይተው በግጥም ሂሳብ ከተያዙ እንደኔ እንደኔ ግጥም መጻፍ ተሰጥኦ አይደለም ወደሚለው ሀሳብ አደላለሁ:: ምክንያቱም የምጽፋቸውን ግጥሞች እየፈጠርኩአቸው ሳይሆን የሚሰማኝን ነገር በግጥም መልክ ለመፃፍ ስሞክር ነው ግጥም የሚሆነው:: ግጥም ከተሰጥኦነቱ ይልቅ የውስጣዊ ስሜት መግለጫነቱ ይጎላብኛል:: (በርግጥ አዋቂዎች እንደሚሉት የጥበብ ተግባሩ ይኸው ነው::) አንተ እንደታዘብከኝ እንደአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን ባህል በጣም እወዳለሁ:: እዚህ ውጭ ሀገር የወጣነው በተለያየ የባህል ተጽዕኖ እና ጫና (በተለይ ይኽ የፖፕ ካልቸር በሚባለው )ምክንያት ብዙ ሰው የሞተበትን እና ብዙም ያልተበረዘውን የባህል እሴታችንን እንዳናጣ የሚልም ስጋት ይሰማኛል:: እና የመጻፍ አቅሙ እና ጊዜው ቢኖረኝ በዚያ ላይ በስፋት ብጽፍ እንዴት ደስ ባለኝ:: መንግስትም የተቃዋሚ ፖርቲዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ አቋም ቢኖራቸው እያልኩ ሁሉ እመኛለሁ:: ለዘመናት ብዙ ሰው ያለቀበት ጉዳይ ነው::

ዲማ የሚለው ስም ...ከኢትዮጵያ ከወጣሁ በኁላ ከአንድ ሩሲያዊ ጋር በተያያዘ አንድ ጓደኛየ ያወጣው ስም ነው:: የሩሲያዊው ስም ከእኔ ጋር ሞክሼ ስለነበረ እና ሰውየው ዲማ ስለሚባል የኔም ስም በዛው ዲማ ሆነ:: ነገሩ የፍቅር እስከመቃብሩን ታሪክ ስላስታወሰኝም ጭምር ተቀበልኩት::ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የጌትነት እንየው ልክ ነጋሪ ግጥም!

Postby ምረቱ » Thu Mar 11, 2010 12:36 am

ለማንነታቸው ዋጋ የሚሰጡ; የራሳቸውን የባህል እሴት ጠንቅቀው የሚያውቁ ኢትዮጵያውን በዘመናዊነት ሰም በተጠቀለለ የባዕድ ባህል ማስፋፊያ መሳሪያ አይሆኑም!! የባህልም አርበኛ አለው:: ይህች የጌትነት እንየው ግጥም በፖፕ ባህል ያልማለለ እና የምዕራብ ባህል ማስፋፊያ መሳሪያ የማይሆን ; ማንነቱን የሚያከብር የባህል አርበኛ ትውልድ በእኛም ዘመን እውን ይሆን ይሆን ወይ የሚል ጥያቄ አጫረብኝ! ሊንኩን ከታች ተመልከቱ

http://www.quatero.net/archives/7817


ሌላ የጌትነት እንየው ድንቅ ስራ : በታሪክ የነበረው ኢትዮጵያዊነት ይኼ ነው!
http://www.ethiotube.net/video/8004/Art ... lay-Zeleke

ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

እንኳን አደረስን!!!

Postby ምረቱ » Sun Apr 04, 2010 6:58 am

ክርስቶስ ተንስኣ እም ሙታን
በአብይ ኃይል ወ ሥልጣን
ኣሰሮ ለሰይጣን
አጋዞ ለዓዳም
ሰላም ንዜዕሰ
ኮነ ...ፍስሀ ወሰላም

መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ!!!

ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የገጣሚ ነብዩ መኮነን አሪፍ ግጥም

Postby ምረቱ » Fri May 21, 2010 5:36 am

የገጣሚ ነብዩ መኮነን የምትመስጥ ግጥም ላካፍል------

አገር ያለፍቅር -ፍቅርም ያለአገር

መቼም ጮኸው ካልዘመሩት ; ነጻነት ቃሉ አይሰማ
ባንዲራው የሰማይ ችካል; የፀሐይ እግር ኅብር-አርማ
ከቶም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ ሀገር
ነብስ የለሽ ስጋ ነውና; እርሻ ያለ-ፍሬ መከር
ጀግና በልቡ እንደሚዳኝ; በመንፈሱ ጽናት ካስማ
አገር ያለ ፍቅር ጠበል; ፍቅር ያለ አገር ሙቅ ማማ
ከቶ አንዱም ያለ አንዱ አይለማ!
የልብ ወኔ ንዝረትኮ; የአበው በገና ነው ምቱ
ወትሮም የሸንጎ ተውኔቱ; ጥበብ ፋኖ ነው ቅኝቱ!
ማተብ እንደክራር ሲከር; ቃኝው አርበኛ ነው ጎምቱ!
ያ ነው የነፃነት ዕፁ; የሀገር ፍቅር ዕውነቱ::
ለዚህ ነው ጥበብ መቆሟ; ለሰው ልጂ ለሚሟገቱ!
ዱሮም ከሰቆቃ አንጀት ነው; ኃያል ዜማ
________________________ የሚወለድ
በአርበኝነት ጥበብ ላንቃ; ያገር ፍቅር እሳት ሲነድ!

ከዛሬ ስልሳ ዓመት በፊት ...
አገር ተወረረችና; በነጭ አረመኔ መዓት
ሞትና ስደት አጠጠ; አንዱ ዘመን ጣር በዛበት::
መቼም ሰው ጠላቱን አይመርጥ; የባላንጣም ቦቃ
___________________________ __የለው
በተለይ ባገር የመጣ; የአገር ክንድ ነው'ሚቀምሰው::
የሀቅ ዐይኗ ተደንቁሎ; የሰላም ብሌን ተጓጉጦ
የአውሮፖ ግፍ እንደጎሽ ግት ; አመፃው እንደጉድ
________________________________ፈጦ
አበሻ ሰቆቃው መጥቆ ;መከራ ሌት ከቀን ባርቆ
ሳቅ እንደዘላለም ርቆ
ጣሊያን ባመጣው ፍዳ አሣር ;በበላዔ-ሰብ ትናጋ
ጦቢያ ባንድ ልብ ደምቶ; ከጠላት ግንባር ሊላጋ
ከፋሺስት ጥርስ ሊወጣ; ከግፉ መንጋ መንጋጋ
አንድም ቅኔ; አንድም ወኔ : ነፃነት ፋና ፍለጋ
አንድም ምሬት; አንድም እሬት; በህይወት
________________________ተውኔት አለንጋ
አንድም ፊድል; አንድም ገድል: የግፍ ምዕራፍ
____________________________እስኪዘጋ
ጥበብን ማተብ አረጋት; የአርበኛ ልቡን ሲያተጋ
መቼም መከራ ዳር አያውቅ
አንዱ ጠላት ከዚያ ዘልቆ; አንዱ ጠላት ከዚህ ፈልቆ
ፋሺስትና ባንዳ ፈልቶ; የወራሪ ግፉ ልቆ
ዕምነት እንደቅሌት አዋይ; እንደ እራፊ ተበጫጭቆ
ስንቱ በደል እንደባህር;ስንቱ ዕንባ ከኅዋ መጥቆ ...
አንድነት እንደሩቅ ዋይታ; በሚስጥር ጎራ ለጎራ;
በሙሾው ዋልታ ለዋልታ
በመቀነት በዝናር ድግ; በዱር ትንፋሽ -በሹክሹክታ
ነበር; እስኪነጋ ጀንበር::
ፋኖ የልቡን አታሞ; በአጥንቱ ቋር እየመታ
ነብሱን ከቸነከረበት; የነፃነት ጎለጎታ
በደሙ ስርየት ሊያመጣ; በእልሁ ድሆ አፍታ ካፍታ
ሰንደቅ አላማ እንደግማድ;ተሸክሞ ነው የረታ::
ጠላት ባንድ ፊት ሲባረር;ባንዳ ባንድ ፊት ሲወገር
አገር በኪን አፍ ሲመሰክር
ፍቅር በጥበብ ሲዘከር
ኪነት እንደኩራት እርሾ
ቴያትር እንደጎበዝ ማሾ
መራር ያገር ፍቅር ዜማ
ከመድረኩ ዱር ሲያሰማ
ሽቅብ ሲል እስከነፃነት
ቁልቁል ሲል እስከአማን መሬት
ቃሉን በቃናው ልጎ; ዳንሱን ሶምሶማ አድርጎ
ጦር ውስጥ በደሙ ሠርጎ
ትውልድን ለዛሬ አበቃ; ስንቱ በጥበቡ ኮርቶ
አይሰው ተሰውቶ; እስከ ንጋት ጎሁ ሞቶ!
ያ ነው ያገር ፍቅር ማለት; የጥቁርም አህጉር ፀጋ
ማንም የማይሽረው ምትሀት; ደም ያጠራው ታሪክ ዋጋ
መከራ አሳር ሲቀበል; አርበኛ ገድሉን ሲሰራ
ጣልያንን "" ጣል -ያን!"" እያለ ;ጥልያንን ""ጥል-ያኔ!""
_____________________________________እያለ
አንዱ ጎራው ጥበብ ነበር; የአገር የሽመናው ስራ
እየታየው የንጋት ጎህ; በደም የተቀባው ሸራ
ያው ታሪኩን ቀልሞበታል; የውሎ ገድሉን ደመራ::
ፈርሶ የመገንባቱ ....ወድቆ የመነሳቱ
ይኸው ነው የታሪኩ ጽንስ ;የሀገር ፍቅር እትብቱ!!
እናም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ አገር
ደሞም ያለጥበብ አጋር
ለአፍታም ለዝንተ-ዓለምም
አንዱ ያላንዱ አይኖርም::
አገር ቢሉ ፍቅር ነው
ፍቅርም ቢሉ አገር ነው
አገር -ፍቅርም ይኼው ነው!


ሐምሌ 1993 ዓ.ም
(ለሀገር ፍቅር ዳግም ልደት)

ከስውር ስፌት ገጽ 50-52.
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የገጣሚ ነብይ መኮነን ግጥም

Postby ምረቱ » Tue May 25, 2010 1:46 pm

የአህጉሬ የምጫ ዜማ

ይህ የአፍሪካ ምርጫ...
ይህ የአፍሪካ ምርጫ...
ከጦርነት ማዶ ; ያለብን ፍጥጫ
የአመታት ሩጫው ; የአገር የአህጉሩ
ፈትሉም ድሩም ማጉም ; አንድ ነው ድውሩ::
በግርፍ;
በድርድር;
ተቃኝቷል ክራሩ::

ከሩቅም ከቅርብም ሁልጊዜ እሚሰማ
አለው ልዩ ግርማ
ስልቱ;ቅኝት ምቱ የአህጉሩ ዜማ!
እንደፀበል ፍቱን ;
ግጥሙ ፈልቆ ፈልቆ;
ቤት መቶ ላይ -ታቹ
በተደጋጋሚ ;
""ተጭበርብሯልኮ""
የሚል ነው አዝማቹ!!

ሚያዚያ 19 1999 ዓ.ም
( ለናይጄሪያ እና ለሚመለከተው ሁሉ)

ከስውር ስፌት ገጽ 54.

ከገጣሚ ነብይ መኮነነ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Re: የገጣሚ ነብዩ መኮነን አሪፍ ግጥም

Postby ዋኖስ » Thu May 27, 2010 7:26 pm

ሰላም ምሕረቱ:

የገጣሚ ነብይ መኮንን ሥራዎች በሲዲም በብዙ አጋጣሚዎች አዳምጨአለሁ: አንብቤአለሁ አይቻለሁም:: የማይሰለቹ: የማይጠገቡ በመሆናቸዉ ሁሌም እንደ አዲስ ኃሳብ እንደ አዲስ ግጥም አነባቸዋለሁ:: እናም ያረኩኛል::ያስደስቱኛልም::

አመሰግናለሁ

ዳሞት ከዳሞት ::ምረቱ wrote:የገጣሚ ነብዩ መኮነን የምትመስጥ ግጥም ላካፍል------

አገር ያለፍቅር -ፍቅርም ያለአገር

መቼም ጮኸው ካልዘመሩት ; ነጻነት ቃሉ አይሰማ
ባንዲራው የሰማይ ችካል; የፀሐይ እግር ኅብር-አርማ
ከቶም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ ሀገር
ነብስ የለሽ ስጋ ነውና; እርሻ ያለ-ፍሬ መከር
ጀግና በልቡ እንደሚዳኝ; በመንፈሱ ጽናት ካስማ
አገር ያለ ፍቅር ጠበል; ፍቅር ያለ አገር ሙቅ ማማ
ከቶ አንዱም ያለ አንዱ አይለማ!
የልብ ወኔ ንዝረትኮ; የአበው በገና ነው ምቱ
ወትሮም የሸንጎ ተውኔቱ; ጥበብ ፋኖ ነው ቅኝቱ!
ማተብ እንደክራር ሲከር; ቃኝው አርበኛ ነው ጎምቱ!
ያ ነው የነፃነት ዕፁ; የሀገር ፍቅር ዕውነቱ::
ለዚህ ነው ጥበብ መቆሟ; ለሰው ልጂ ለሚሟገቱ!
ዱሮም ከሰቆቃ አንጀት ነው; ኃያል ዜማ
________________________ የሚወለድ
በአርበኝነት ጥበብ ላንቃ; ያገር ፍቅር እሳት ሲነድ!

ከዛሬ ስልሳ ዓመት በፊት ...
አገር ተወረረችና; በነጭ አረመኔ መዓት
ሞትና ስደት አጠጠ; አንዱ ዘመን ጣር በዛበት::
መቼም ሰው ጠላቱን አይመርጥ; የባላንጣም ቦቃ
___________________________ __የለው
በተለይ ባገር የመጣ; የአገር ክንድ ነው'ሚቀምሰው::
የሀቅ ዐይኗ ተደንቁሎ; የሰላም ብሌን ተጓጉጦ
የአውሮፖ ግፍ እንደጎሽ ግት ; አመፃው እንደጉድ
________________________________ፈጦ
አበሻ ሰቆቃው መጥቆ ;መከራ ሌት ከቀን ባርቆ
ሳቅ እንደዘላለም ርቆ
ጣሊያን ባመጣው ፍዳ አሣር ;በበላዔ-ሰብ ትናጋ
ጦቢያ ባንድ ልብ ደምቶ; ከጠላት ግንባር ሊላጋ
ከፋሺስት ጥርስ ሊወጣ; ከግፉ መንጋ መንጋጋ
አንድም ቅኔ; አንድም ወኔ : ነፃነት ፋና ፍለጋ
አንድም ምሬት; አንድም እሬት; በህይወት
________________________ተውኔት አለንጋ
አንድም ፊድል; አንድም ገድል: የግፍ ምዕራፍ
____________________________እስኪዘጋ
ጥበብን ማተብ አረጋት; የአርበኛ ልቡን ሲያተጋ
መቼም መከራ ዳር አያውቅ
አንዱ ጠላት ከዚያ ዘልቆ; አንዱ ጠላት ከዚህ ፈልቆ
ፋሺስትና ባንዳ ፈልቶ; የወራሪ ግፉ ልቆ
ዕምነት እንደቅሌት አዋይ; እንደ እራፊ ተበጫጭቆ
ስንቱ በደል እንደባህር;ስንቱ ዕንባ ከኅዋ መጥቆ ...
አንድነት እንደሩቅ ዋይታ; በሚስጥር ጎራ ለጎራ;
በሙሾው ዋልታ ለዋልታ
በመቀነት በዝናር ድግ; በዱር ትንፋሽ -በሹክሹክታ
ነበር; እስኪነጋ ጀንበር::
ፋኖ የልቡን አታሞ; በአጥንቱ ቋር እየመታ
ነብሱን ከቸነከረበት; የነፃነት ጎለጎታ
በደሙ ስርየት ሊያመጣ; በእልሁ ድሆ አፍታ ካፍታ
ሰንደቅ አላማ እንደግማድ;ተሸክሞ ነው የረታ::
ጠላት ባንድ ፊት ሲባረር;ባንዳ ባንድ ፊት ሲወገር
አገር በኪን አፍ ሲመሰክር
ፍቅር በጥበብ ሲዘከር
ኪነት እንደኩራት እርሾ
ቴያትር እንደጎበዝ ማሾ
መራር ያገር ፍቅር ዜማ
ከመድረኩ ዱር ሲያሰማ
ሽቅብ ሲል እስከነፃነት
ቁልቁል ሲል እስከአማን መሬት
ቃሉን በቃናው ልጎ; ዳንሱን ሶምሶማ አድርጎ
ጦር ውስጥ በደሙ ሠርጎ
ትውልድን ለዛሬ አበቃ; ስንቱ በጥበቡ ኮርቶ
አይሰው ተሰውቶ; እስከ ንጋት ጎሁ ሞቶ!
ያ ነው ያገር ፍቅር ማለት; የጥቁርም አህጉር ፀጋ
ማንም የማይሽረው ምትሀት; ደም ያጠራው ታሪክ ዋጋ
መከራ አሳር ሲቀበል; አርበኛ ገድሉን ሲሰራ
ጣልያንን "" ጣል -ያን!"" እያለ ;ጥልያንን ""ጥል-ያኔ!""
_____________________________________እያለ
አንዱ ጎራው ጥበብ ነበር; የአገር የሽመናው ስራ
እየታየው የንጋት ጎህ; በደም የተቀባው ሸራ
ያው ታሪኩን ቀልሞበታል; የውሎ ገድሉን ደመራ::
ፈርሶ የመገንባቱ ....ወድቆ የመነሳቱ
ይኸው ነው የታሪኩ ጽንስ ;የሀገር ፍቅር እትብቱ!!
እናም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ አገር
ደሞም ያለጥበብ አጋር
ለአፍታም ለዝንተ-ዓለምም
አንዱ ያላንዱ አይኖርም::
አገር ቢሉ ፍቅር ነው
ፍቅርም ቢሉ አገር ነው
አገር -ፍቅርም ይኼው ነው!


ሐምሌ 1993 ዓ.ም
(ለሀገር ፍቅር ዳግም ልደት)

ከስውር ስፌት ገጽ 50-52.
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: የገጣሚ ነብዩ መኮነን አሪፍ ግጥም

Postby ምረቱ » Tue Jun 08, 2010 7:10 am

ዋኖስ wrote:ሰላም ምሕረቱ:

የገጣሚ ነብይ መኮንን ሥራዎች በሲዲም በብዙ አጋጣሚዎች አዳምጨአለሁ: አንብቤአለሁ አይቻለሁም:: የማይሰለቹ: የማይጠገቡ በመሆናቸዉ ሁሌም እንደ አዲስ ኃሳብ እንደ አዲስ ግጥም አነባቸዋለሁ:: እናም ያረኩኛል::ያስደስቱኛልም::

አመሰግናለሁ

ዳሞት ከዳሞት ::ምረቱ wrote:የገጣሚ ነብዩ መኮነን የምትመስጥ ግጥም ላካፍል------

አገር ያለፍቅር -ፍቅርም ያለአገር

መቼም ጮኸው ካልዘመሩት ; ነጻነት ቃሉ አይሰማ
ባንዲራው የሰማይ ችካል; የፀሐይ እግር ኅብር-አርማ
ከቶም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ ሀገር
ነብስ የለሽ ስጋ ነውና; እርሻ ያለ-ፍሬ መከር
ጀግና በልቡ እንደሚዳኝ; በመንፈሱ ጽናት ካስማ
አገር ያለ ፍቅር ጠበል; ፍቅር ያለ አገር ሙቅ ማማ
ከቶ አንዱም ያለ አንዱ አይለማ!
የልብ ወኔ ንዝረትኮ; የአበው በገና ነው ምቱ
ወትሮም የሸንጎ ተውኔቱ; ጥበብ ፋኖ ነው ቅኝቱ!
ማተብ እንደክራር ሲከር; ቃኝው አርበኛ ነው ጎምቱ!
ያ ነው የነፃነት ዕፁ; የሀገር ፍቅር ዕውነቱ::
ለዚህ ነው ጥበብ መቆሟ; ለሰው ልጂ ለሚሟገቱ!
ዱሮም ከሰቆቃ አንጀት ነው; ኃያል ዜማ
________________________ የሚወለድ
በአርበኝነት ጥበብ ላንቃ; ያገር ፍቅር እሳት ሲነድ!

ከዛሬ ስልሳ ዓመት በፊት ...
አገር ተወረረችና; በነጭ አረመኔ መዓት
ሞትና ስደት አጠጠ; አንዱ ዘመን ጣር በዛበት::
መቼም ሰው ጠላቱን አይመርጥ; የባላንጣም ቦቃ
___________________________ __የለው
በተለይ ባገር የመጣ; የአገር ክንድ ነው'ሚቀምሰው::
የሀቅ ዐይኗ ተደንቁሎ; የሰላም ብሌን ተጓጉጦ
የአውሮፖ ግፍ እንደጎሽ ግት ; አመፃው እንደጉድ
________________________________ፈጦ
አበሻ ሰቆቃው መጥቆ ;መከራ ሌት ከቀን ባርቆ
ሳቅ እንደዘላለም ርቆ
ጣሊያን ባመጣው ፍዳ አሣር ;በበላዔ-ሰብ ትናጋ
ጦቢያ ባንድ ልብ ደምቶ; ከጠላት ግንባር ሊላጋ
ከፋሺስት ጥርስ ሊወጣ; ከግፉ መንጋ መንጋጋ
አንድም ቅኔ; አንድም ወኔ : ነፃነት ፋና ፍለጋ
አንድም ምሬት; አንድም እሬት; በህይወት
________________________ተውኔት አለንጋ
አንድም ፊድል; አንድም ገድል: የግፍ ምዕራፍ
____________________________እስኪዘጋ
ጥበብን ማተብ አረጋት; የአርበኛ ልቡን ሲያተጋ
መቼም መከራ ዳር አያውቅ
አንዱ ጠላት ከዚያ ዘልቆ; አንዱ ጠላት ከዚህ ፈልቆ
ፋሺስትና ባንዳ ፈልቶ; የወራሪ ግፉ ልቆ
ዕምነት እንደቅሌት አዋይ; እንደ እራፊ ተበጫጭቆ
ስንቱ በደል እንደባህር;ስንቱ ዕንባ ከኅዋ መጥቆ ...
አንድነት እንደሩቅ ዋይታ; በሚስጥር ጎራ ለጎራ;
በሙሾው ዋልታ ለዋልታ
በመቀነት በዝናር ድግ; በዱር ትንፋሽ -በሹክሹክታ
ነበር; እስኪነጋ ጀንበር::
ፋኖ የልቡን አታሞ; በአጥንቱ ቋር እየመታ
ነብሱን ከቸነከረበት; የነፃነት ጎለጎታ
በደሙ ስርየት ሊያመጣ; በእልሁ ድሆ አፍታ ካፍታ
ሰንደቅ አላማ እንደግማድ;ተሸክሞ ነው የረታ::
ጠላት ባንድ ፊት ሲባረር;ባንዳ ባንድ ፊት ሲወገር
አገር በኪን አፍ ሲመሰክር
ፍቅር በጥበብ ሲዘከር
ኪነት እንደኩራት እርሾ
ቴያትር እንደጎበዝ ማሾ
መራር ያገር ፍቅር ዜማ
ከመድረኩ ዱር ሲያሰማ
ሽቅብ ሲል እስከነፃነት
ቁልቁል ሲል እስከአማን መሬት
ቃሉን በቃናው ልጎ; ዳንሱን ሶምሶማ አድርጎ
ጦር ውስጥ በደሙ ሠርጎ
ትውልድን ለዛሬ አበቃ; ስንቱ በጥበቡ ኮርቶ
አይሰው ተሰውቶ; እስከ ንጋት ጎሁ ሞቶ!
ያ ነው ያገር ፍቅር ማለት; የጥቁርም አህጉር ፀጋ
ማንም የማይሽረው ምትሀት; ደም ያጠራው ታሪክ ዋጋ
መከራ አሳር ሲቀበል; አርበኛ ገድሉን ሲሰራ
ጣልያንን "" ጣል -ያን!"" እያለ ;ጥልያንን ""ጥል-ያኔ!""
_____________________________________እያለ
አንዱ ጎራው ጥበብ ነበር; የአገር የሽመናው ስራ
እየታየው የንጋት ጎህ; በደም የተቀባው ሸራ
ያው ታሪኩን ቀልሞበታል; የውሎ ገድሉን ደመራ::
ፈርሶ የመገንባቱ ....ወድቆ የመነሳቱ
ይኸው ነው የታሪኩ ጽንስ ;የሀገር ፍቅር እትብቱ!!
እናም አገር ያለፍቅር; ፍቅርም ያለውድ አገር
ደሞም ያለጥበብ አጋር
ለአፍታም ለዝንተ-ዓለምም
አንዱ ያላንዱ አይኖርም::
አገር ቢሉ ፍቅር ነው
ፍቅርም ቢሉ አገር ነው
አገር -ፍቅርም ይኼው ነው!


ሐምሌ 1993 ዓ.ም
(ለሀገር ፍቅር ዳግም ልደት)

ከስውር ስፌት ገጽ 50-52.


ሠላም ዋኖስ

በቅድሚያ ለመመልስ ስለዘገየሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ:: የገጣሚ ነብይ መኮነን ስራዎች እውነትም የሚገርሙ ናቸው:: እኔም እንዳንተ ደጋግሜ ነው ያነበብኳቸው:: ስውር ስፌት ከምትለው መጽሀፉ ውስጥ ባገኘሁት ኢሜይል አድራሻው አድናቆቴን አስታላልፌአለሁ:: በፍቅር እና በሀገር ጉዳይ ላይ የገጠማቸው ግጥሞች በጣም ይመስጡኛል:: ከስውር ስፌት ሌላ የምታውቀው ስራው ካለህ የት እንደማገኘው ብትጠቁመኝ ደስ ይለኛል::
አመሰግናለሁ
ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ስብሀት ገ/እግዚያብሄር

Postby ምረቱ » Tue Jun 08, 2010 7:14 am

ብዙም የስብሀት ገ/እግዚያብሄር አድናቂ አይደለሁም:: ነገር ግን በዚህ ክሊፕ ላይ ስለ ሀዘን ባህላችን የሰጡት ሀሳብ ትክክለኛ እና ወደውስጣችን መውሰድ ያለብን ነገር ነው:: "" leave me alone"" የሚባል የፈረንጂ አስተሳሰብ በማህበረሰባችን ውስጥ ስር እንዳይሰድ ያስፈልጋል::

http://www.ethiotube.net/video/9507/Eth ... -Egziabher
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

መልካም አዲስ ዓመት!!!

Postby ምረቱ » Wed Sep 08, 2010 12:16 am

መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ!!! አምላካችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ሲዘምር አየነው!

Postby ምረቱ » Mon Jan 24, 2011 8:09 am

የሚጠፋ መስሎት እንደ ጉም የሚተን
ያገር ፍቅር በኖ ሕዝብ የሚበታተን
ቋንቋን ተገን አርጎ ሀገር ሲሸነሽን
ጭፍራ ሲያሰማራ
ወገን ሊያስፈራራ
ሰው ባገሩ እንዳይኮራ
ሀገሩን ረስቶ ዘሩን እንዲያወራ
ባንዲራ ሲቀየር
ለምን የሚለውም ሲጣል ወደ እስር
ዘዴ ቢቀያየር ...
በርሀብ በርዛት በኑሮ ቢረግጠው
ወይ ፍንክች...!
ወገን እንደሆነ ተመልሆ ያው ነው
ክልጂ እስከአዋቂ
ኢትዮጵያን ሲያስባት
ሲዘምር አየነው:: !!


ባለፈው ሳምንት የተከበረውን የጥምቀት በዓል በኢንተርኔት ካየሁ በኍላ የተሰማኝን ስሜት ለማንጸባረቅ ነው::
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ቡል ዶዘር

Postby ምረቱ » Mon Jan 24, 2011 8:19 am

ሲነገር ስንሰማ ...
የድሮ ወታደር
አለኝታ ነበር ለሀገር::

የዛሬ ወታደር
...አገር አፍራሽ
ከወንበር የማይገፈትር
የዘረኞች አለኝታ
ራሱ ሀገር አፋራሽ ቡል ዶዘር!


ጥር 2003, ቶሮንቶ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

እስከመቼ

Postby ምረቱ » Sun Jan 30, 2011 7:51 am

ተሸክሞ የብሶት ቁልል
ችጋርና ርሀብ ቤቱን ሰርቶ
ቁራሽ ምኞት ሆኖ አርፎ
በፈረቃ እየተበላ ስንቱ
በየቤቱ ራሱን ስቶ
ቁራሽ ፍለጋ ተከልቶ
ቀየውን መንደሩን ትቶ;
ከሁለት ያጣ እንዲሉ
ቁራሹም ጠፍቶ ላመሉ
ቀየውንም ቁራሹንም እየተራበ
ጉደኛ አሳዳሪ...
""ዕድገት"" አለ እያለ ከበሮ ደረበ::

"" ህዳሔ አለ ...ዕድገት አለ
አስፋልት ተነጠፈ
ጥርጊያ መንገድ ተደለደለ
ለዕድገት ተብሎ..
ለአረቡ; ለቻይናው; ለህንዱ መሬት ታደለ
ዕድገት አለ:: ""

እንዲህ አይነት ፌዝ እየሰማ
አበሽ ልቡ እየደማ
በረሀብ የሚፈጀው
ረሀብ እና ባርነት ያደረጀ 'ሚታገሰው
እስከመቼ ነው?!

የ""አትንኩኝ"" ባይነት መንፈስ
ነጻነት ባበቀለበት ምድር
ዛሬ "አትንኩኙን" ማን ቀጠፈው
ማን ቀላቀለበት ከአፈር::

ምነው አበሽ ዝምታ አበዛ አንገቱን ሰበረ
"'ከመናገር ደጃዝማቺነት ይቀራል"" ተረስቶ
ስለምን ለዘራፊ አሳዳሪ አቀረቀረ??

ኧረ እንደልማድህ አበሽ
ኑር እንደ አባት አደሩ
ችጋር; ባርነት ለሚደግስ
እስከመቼ እሺሩሩ??ጥር 2003 ቶሮንቶ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Re: እስከመቼ

Postby Senayte » Thu Feb 03, 2011 3:13 am

ምረቱ wrote:ተሸክሞ የብሶት ቁልል
ችጋርና ርሀብ ቤቱን ሰርቶ
ቁራሽ ምኞት ሆኖ አርፎ
በፈረቃ እየተበላ ስንቱ
በየቤቱ ራሱን ስቶ
ቁራሽ ፍለጋ ተከልቶ
ቀየውን መንደሩን ትቶ;
ከሁለት ያጣ እንዲሉ
ቁራሹም ጠፍቶ ላመሉ
ቀየውንም ቁራሹንም እየተራበ
ጉደኛ አሳዳሪ...
""ዕድገት"" አለ እያለ ከበሮ ደረበ::

"" ህዳሔ አለ ...ዕድገት አለ
አስፋልት ተነጠፈ
ጥርጊያ መንገድ ተደለደለ
ለዕድገት ተብሎ..
ለአረቡ; ለቻይናው; ለህንዱ መሬት ታደለ
ዕድገት አለ:: ""

እንዲህ አይነት ፌዝ እየሰማ
አበሽ ልቡ እየደማ
በረሀብ የሚፈጀው
ረሀብ እና ባርነት ያደረጀ 'ሚታገሰው
እስከመቼ ነው?!

የ""አትንኩኝ"" ባይነት መንፈስ
ነጻነት ባበቀለበት ምድር
ዛሬ "አትንኩኙን" ማን ቀጠፈው
ማን ቀላቀለበት ከአፈር::

ምነው አበሽ ዝምታ አበዛ አንገቱን ሰበረ
"'ከመናገር ደጃዝማቺነት ይቀራል"" ተረስቶ
ስለምን ለዘራፊ አሳዳሪ አቀረቀረ??

ኧረ እንደልማድህ አበሽ
ኑር እንደ አባት አደሩ
ችጋር; ባርነት ለሚደግስ
እስከመቼ እሺሩሩ??

ጥር 2003 ቶሮንቶ


ሄይ ዲማ

ስሞኑን ሰሉዋ በዕርህ በየቦታው በትጋት በስራላይ ናት .....
:wink: . በርታ ....!!!!
" Every problem has a solution. If it doesn't ,it isn't a problem but a fact ,and you must learn to live with it."
Senayte
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 241
Joined: Thu Nov 18, 2004 5:00 am
Location: Lieville.....

ሚስጥረ ልብ

Postby ምረቱ » Mon Mar 07, 2011 7:52 am

ሚስጥረ ልብ !

እንደ ባሊና ኳስ ልብ እየነጠረ
ከሰው አልመከረ;
እግር አልተነሳ; ወሰን ተሻገረ::

""ምን ለመሆን ነው
የሰው ነገር ...የሰው
ሲሆን እያወከው?! ""
ብየ ብጠይቀው
ዝም አይነቅ ዝም!
መንጠሩን ግን አላቆመም::

ነጥሮ ነጥሮ እንደገና መሬት ደረሰ
መሬቱ ላይ መሬት ሆኖ ቀረ ዝምታ ነገሰ
ትንሽ ቆይቶ ደሞ ተላወሰ
የታየውን ....ተነፈሰ

"" እንደኖርኩት ...እንደማውቀው
ልብ በዋዛ አይመታም
ወደላይ አይጉንም
መሬት ላይ አይነጥርም::
እንዲህ የሚጉነው
እንዲህ የሚነጥረው
የመታው ቢለይ ነው!""
ሲል ቢነግረኝ
የልብ ንጥረቱ ና ስደቱ ገባኝ::

ከስደትም የተሰደደ ልብን ለሚያውቁ

ምረቱ ዘ ብሄረ የጁ!

የካቲት 27, 2003, ቶሮንቶ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የልብ እግር ሲሰበር ...ሲሽር

Postby ምረቱ » Tue Jun 14, 2011 1:54 am

የልብ እግር ሲሰበር
ዓላማ ፣ ተስፋ ፣
ፍላጎት ፣ ሀሴት ፣ ምኞት
ሕይወት አልባ ይሆናሉ ::
ሲሽር እንደ አዲስ ነብስ ይዘራሉ::
ህብረት ይፈጥራሉ
መሰናክል ይዘላሉ::
ግና ሰባራ ልብ የሚያራምደው
...ወጌሻው
የጽናት እና የእምነት ትብብር ነው::

ምረቱ

ሰኔ 7 2003
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests