ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Postby password » Tue Aug 12, 2014 4:46 am

ቢተወደድ wrote:ሰሞኑን በተስፋዬ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች: ትክክለኛ ማንነቱን እያወጡት ይገኛሉ:: ጽሁፎቹን አንብበሀቸው ከሆነ; አስተያየትህን ልታካፍለን ትወዳለህን?ተስፋዬ , የቡርቃ ዝምታ ላይ ለሰነዘርኩት አጭር ትችት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታ መርጧል ... ስለዚህ እሱን ዋርካ ስር ካላየሁት በቀር ላነሳው አልፈቀድኩም ... በተረፈ ለዘገየው ምላሼ ይቅርታ እጠይቃላሁ.....

ፓስ ....
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Postby ምክክር » Tue Aug 12, 2014 9:25 am

password wrote:
ቢተወደድ wrote:ሰሞኑን በተስፋዬ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች: ትክክለኛ ማንነቱን እያወጡት ይገኛሉ:: ጽሁፎቹን አንብበሀቸው ከሆነ; አስተያየትህን ልታካፍለን ትወዳለህን?ተስፋዬ , የቡርቃ ዝምታ ላይ ለሰነዘርኩት አጭር ትችት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታ መርጧል ... ስለዚህ እሱን ዋርካ ስር ካላየሁት በቀር ላነሳው አልፈቀድኩም ... በተረፈ ለዘገየው ምላሼ ይቅርታ እጠይቃላሁ.....

ፓስ ....


ውድ ፓስ: ሠላምታ
ተስፋዬን ዋርካ ላይ እንዴት ለይተህ ልትመነጥረው ትችላለህ? እኔ ነኝ ተስፋዬ ቢልህ እንኳ!
ቡርቃን በተመለከተ: ተስፋዬ ዋርካ ጥላ ሥርም ሆነ ገለጥ ባለው በገሀዱ ዓለም አይገጥምህም:: ስለዚህ አርኪ ና አመርቂ አስተያየትህን ብትችረን ምናለ?

ተስፋዬ አማርኛችንን ሰርቆ: ማንነታችንን አጨማልቆ: በባዕድ አገር ቢኖርም ተደብቆ: ዋርካ ላይ በድፍረት ራሱን አሳውቆ: አይገጥምህም በድፍረት ዘልቆ:: :)

ሠላም
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 438
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re:

Postby ቢተወደድ1 » Thu Sep 01, 2016 2:07 pm

ይሄን የዞረበት ሰው ብዙ እዳናቃችሁት ልትሞቱ ነው፡፡ ለኔ ግን የጭቃ እሾህ ነው፡፡ ሆላንድ አንድ አሁን ስሙ የተረሳኝ ሰው አብረው ይኖሩ እንደነበርና ሚስጥሩን በሙሉ አውጥቶ አጋልጦታል፡፡ ሊንኩን ሳገኘው አመጣላቹና እናንተው ትፈርዳላቹህ፡፡
ለመሆኑ የኦሮሞ ዜግነት እንደተቀበለ ታውቃላቹህ? ዮ ቲዩብ ፈልጉት፡፡

እባካችሁን wrote:ደራሲው ከዚህ በፊት የፃፋቸውን መፅሀፍት የማንበብ እድል አላገኘሁም። ይህንን ግን ሙሉ ገፆቹን አንብቤ ጨረስኩ። በርግጥም ድንቅ የትረካ ችሎታ አለው። ከፃፈው ታሪክም ሀገራችን በእንዴት ያሉ ወሮበሎች ስር እንዳለች በግልፅ መረዳት ይቻላል። ሆኖም በኔ ግምት እርሱም ካስር አመት ላላነስ ጊዜ አንጀቱን ሲያርስ የነበረና ወያኔዎችም እንደሸንኮራ አገዳ እኝክ አርገው ሊተፉት ሲሉ ነው የወጣው። ከመገፋቱ በፊት ዘለለ ማለት እደፍራለሁ። ወደስደትም የወጣው ከበቂ ዝግጅት በኋላ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ያም ሆኖ ማንም የማይነጥቀው ድንቅ የስነፅሁፍ ችሎታ አለውና ወደፊትም ብዙ ይፅፋል ብዬ እገምታለሁ።
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 488
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Postby password » Fri Dec 15, 2017 10:34 am

ቡርቃ በቡድን እንደተደረሰና ኪነጽሁፋዊ ዘየ እንደሚጎድለው ቀድም ብለን ዋርካ ሥነጽሁፍ ክፍል ውስጥ ተወያይተንበት ነበር። አሁን ውስጥ አዋቂዎች ጉዱን አውጥተውታል።

በኔ እምነት ቡርቃው የእንድ ደራሲ ስራ አይደለም። ቡርቃን በተመስጦ ያዳመጠ አንባቢ የተራኪው ድምጽ ከምዕራፍ ምዕራፍ ሲለዋወጥ ያስተውላል ። በተለይ የመጀመሪያው ክፍል ላይ ያለው ቋንቋና ሀሳብ እንደ ተስፋዬ በአማርኛ ተናጋሪዎች መሐል ያደገ ሰው ሊጠቀምበትና ሊታስበውም የማይቻለው ሆኖ ነው ያገኘሁት። ምናልባት በሌላ ሰው የተጀመረና ማጣፊያው ሲያጥር ወደ ተስፋዬ የተወረወረ ስራ ይሆናል ብዬም እገምታልሁ። ደራሲ ተስፋዬ በብሄረሰቦች መሃል የሚያስከትለውን ውዝግብና በራሱም ላይ የሚያመጣውን ጣጣ ሳይገነዘብ ችሎታውን ለማስመስከር፣ ትኩርት ለመሳብና ዝናን ለማግኘት ሲል ወይም በድርጅታዊ ስራ ታዝዞ የተፈናጠጠበት የሌላ ሰው ወይም ቡድን ጅምር ስራ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምትም አለኝ።"
የሚል አስተያየት 2014 ላይ በዚሁ ርዕስ ሥር ተሰጥቶ ነበር።

አክቲቪስት ቶሎሳ ኢብሳ የሚለው አለው፥ (at 45 min)
https://www.facebook.com/Thomasti1/videos/1558896680859275/?fref=mentions
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby password » Sun Aug 12, 2018 2:09 pm

password wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:[/u]
ጎበዝ እስከ 62 ገጽ ድረስ አነበብኩት .....ምቀኛ አትበሉኝ እንጂ ይሄ መጽሀፍ ተብዬው ተራ የእድር ደብተር የመሰለ ማመልከቻ ምኑም አልጣመኝም ...እውነተኛ ታሪክ አይባል ...ከእውነት እጅጉን የራቀ ነው ...ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ደሞ እንዳይባል በተራ አሉባልታዎች የተሞላ ነው ...
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...ምናልባት በትግሪኛ ጽፈው ካልሆነ ለማለት ነው..ጽፈው ከሆነ እኔ ትግሪኛ ስልማልችል አላነበብኩት ይሆናል ...
ሆነ ቀረ ደራሲው ተብዬው ከኢትዮጲያ ህዝብ የዘረፈውን ገንዘብ በደቡብ አፍሪካ ከመጨረሱ በፊት ዘመድ ካለው ወደ ጠበል ምናምን ውሰዱትና ሻል ሲለው እውነቱን ይጽፍ ይሆናል .....
ፓኑ አባ ፈርዳ
ኢትዮጲያዊ


ኢትዮጵያ ትቅደም በጣም ክቡር መፈክር ነው። ብዙ ትርጉም አለው. እርግጥ ናዚ ጀርመኒም ''ጀርመን ትቅደም'' ይል ነበር። ኢትዮጵያ ትቅደም ግን በመንፈሱም ሆነ በዐላማው ከጀርመኑ የተለየ ነበር። አንተ በየትኛው መንፈስ እንደጠቀስከው አላውቅም..

የየካቲትን ህዝባዊ ንቅናቂ ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች መጨቆናቸውንና መገፋታቸውን ሲገልጹ፣ ሁሉም በየፊናው ይህ ይገባኛል፣ ያ ይሰጠኝ፣ እንዲህ ይደረግልኝ፣ እገሌ ይነሳልኝ፣ እገሌ ይታስር በሚለበት ወቅት አገር ወዳዶች ተነስትው፣ እንዴ ሁሉም ለኔ ለኔ ሲል አገር እኮ ተረሳች። የራሳችንን ትተን ለሀገር የሚበጀውን እናድርግ። አገርን እናስቀድም። ኢትዮጵያ ትቅድም አሉ። ህዝብም ተቀበለው። በአንድ ወቅት ምልዐተህዝቡ የዘመረው መፈክር ነበር። ያን መሰለኝ አባ ፈርዳ ፊርማ ያረከው።

ያን ከሆነ ያልገባህ ነገር ይታየኛል። በየካቲቱ ኢትዮጵያ ትቅደም የጎሳ ልዩነቶች አይታወቁም። አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ውራጌ፣ ቤንሸንጉል የሚባል ክልል አልነበረም። ኢትዮጵያ ትቅደም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ብቻ ማመን ነበር። ልክ ኦባማ ጥቁር አሜሪካዊ፣ ነጭ አሜሪካዊ ወዘተ የሚባል ነገር የለም። there is only the united states of america. እንዳለው፣ ኢትዮጵያ ትቅደም ማለት የኢትዮጵያዊያን አንድነት ፍጹምነት ማለት ነበር። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ያነገቡ ወጣቶች በፖለቲካ አለመግባበት እርስ በርስ በጥይት ሲሞሻለቁ እንኩዋን በአመለካከት እንጂ በጎጥ ተለየይተው አልነበረም። ኢትዮጵያ ትቅደም አራማጆች ተዳመተወል ግን በኢትዮጵየዊነት ለኢትዮጵያ ነበር።

እና
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...

ስትል አልገባኝም።

ከዚህ አባባል ጀርባ ያለው ጥላቻና ብሽቀጥ ይገባኛል። ከመሬት ተነስተህ እንዲህ አላልክም። በስልጣን ላይ ያለው፣ በትግርኛ ተናጋሪዎች የበላይነት የተገነባው ስርዓት በግል ያደረሰብህ በደል ይኖራል። በአገርም ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሊሰማህ ይችላል። ይሁን እንጂ ከላይ የተከተበው ሀረግ ካንተ የሚጠበቅ አይደለም። ይህን ማንም ቢጽፈው ቀጥተኛ መልስ አልሰጥበትም ነበር፣ ከአንተ፣ ወራሽን ካስነበብከንና የኢትዮጵያ ትቅደምን መንፈስ ያውቃል ከምንለው ደራሲ በፍጹም አይጠበቅም።

አባ ፈርዳ፣ የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ እኮ አሁን ደረስ ያለ ይመስለኛል። በጎጥ ያልተከፋፈልች አንድ ኢትዮጵያ የምናይበት ዘመን እኮ ሩቅ አይደለም። ከቀይ ባህር አስከ ተፈሪ በር ያለ ህዝብ በእንድ ብሄራዊ መዝሙር፣ በአንድ ባንዲራና በአንድ መንግስት በስላም፣ በፍቅርና በአንድነት የሚኖሩበት ዘመን እውን እስኪሆን በእውነት ይህ ትውልድ አያልፍም። ታዲያ ያ ክቡር የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ በሂደት እየደከም መምጠቱን በአንተ ስመለከት ልቤ ይደማል።

ለመታረም ባለህ ድፍረት በመተማመን
ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Postby password » Sun Aug 12, 2018 2:14 pm

ዋርካ ውስጥ ስንት ተፃፈ!

አባ ፈርዳ፣ የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ እኮ አሁን ደረስ ያለ ይመስለኛል። በጎጥ ያልተከፋፈለች አንድ ኢትዮጵያ የምናይበት ዘመን እኮ ሩቅ አይደለም። ከቀይ ባህር አስከ ተፈሪ በር ያለ ህዝብ በአንድ ብሄራዊ መዝሙር፣ በአንድ ባንዲራና በአንድ መንግስት በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት የሚኖሩበት ዘመን እውን እስኪሆን በእውነት ይህ ትውልድ አያልፍም
ታዲያ ያ ክቡር የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ በሂደት እየደከመ መምጣቱን በአንተ ስመለከት ልቤ ይደማል።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 3 guests