ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተስፋዬ ገ/አብ

Postby yekolo » Sun Feb 22, 2009 4:39 pm

I've read his book, የቡርቃ ዝምታ, and I can tell you that it was pure garbage. Not only interms of content but also literary style.

ለሎቹንም መጣጥፎቹን አንበቤያለሁ... ከብርሀኑ ዘሪሁን ጋር ማወዳደር is a huge exaggeration if not a crime.
yekolo
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Sun Feb 22, 2009 4:31 pm

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Feb 25, 2009 10:43 am

password wrote:በተስፋዬ ገ/አብ የተደረሰው ''የጋዜጠኛው ማስታወሻ'' የተሰኘው መጽሀፍ

ተስፋዬ ... ብርሀኑ ያበረታታኝ ነበር ... ይላል ...

ገጽ 75 ላይ ደርሼአለሁ ... ብርሀኑ ላካ ተኪውን አዘጋጅቶልን ኖሯል ...

ጉርም ትረካ .... አስደናቂ ዘገባዎች ... ውብ ስነጽሁፍ

እያነበብኩት ነው ... ስጨርስ እመለሳለሁ ....

PDF የተሰራጨውን የምታነቡ የዚህን ድንቅ ደራሲ ድካም አትዘንጉ

በርድ መጽሀፉን አግኝተሻል ?.
እንደ ልቦለድ ልብ የሚሰቅል ..
እንደ ትሩዝ ግጥሞች ቀልብ የሚስብ ... አንብቢው

ፓስ ይቅርታ በስህተት ተሰርዞ ነበር
ጎበዝ እስከ 62 ገጽ ድረስ አነበብኩት .....ምቀኛ አትበሉኝ እንጂ ይሄ መጽሀፍ ተብዬው ተራ የእድር ደብተር የመሰለ ማመልከቻ ምኑም አልጣመኝም ...እውነተኛ ታሪክ አይባል ...ከእውነት እጅጉን የራቀ ነው ...ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ደሞ እንዳይባል በተራ አሉባልታዎች የተሞላ ነው ...
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...ምናልባት በትግሪኛ ጽፈው ካልሆነ ለማለት ነው..ጽፈው ከሆነ እኔ ትግሪኛ ስልማልችል አላነበብኩት ይሆናል ...
ሆነ ቀረ ደራሲው ተብዬው ከኢትዮጲያ ህዝብ የዘረፈውን ገንዘብ በደቡብ አፍሪካ ከመጨረሱ በፊት ዘመድ ካለው ወደ ጠበል ምናምን ውሰዱትና ሻል ሲለው እውነቱን ይጽፍ ይሆናል .....
ፓኑ አባ ፈርዳ
ኢትዮጲያዊ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Feb 25, 2009 10:56 am

ይድረስ ለ
የጋዜቴኛው ማስታወሻ ደራሲ ተብዬው .......
መቀሌን በ13ኛው ክፍለ ዘመን እንደተቆረቆረች ስትነግረን ....መቀሌን ከአክሱምና አዶሊስ ጋር ልታዛምድ መጣርህ በልከፋ ነበር ...ግን ግን ቄሱን ንጉስ ካሳ ጥርሶን 600 አመት ወደ ኋላ ጎትተህ ማቅረብህ ግን ቅሌታም ያስብልሀል ...አንዳንዴ እያሰብክ ጻፍ
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby password » Wed Feb 25, 2009 2:18 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:[/u]
ጎበዝ እስከ 62 ገጽ ድረስ አነበብኩት .....ምቀኛ አትበሉኝ እንጂ ይሄ መጽሀፍ ተብዬው ተራ የእድር ደብተር የመሰለ ማመልከቻ ምኑም አልጣመኝም ...እውነተኛ ታሪክ አይባል ...ከእውነት እጅጉን የራቀ ነው ...ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ደሞ እንዳይባል በተራ አሉባልታዎች የተሞላ ነው ...
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...ምናልባት በትግሪኛ ጽፈው ካልሆነ ለማለት ነው..ጽፈው ከሆነ እኔ ትግሪኛ ስልማልችል አላነበብኩት ይሆናል ...
ሆነ ቀረ ደራሲው ተብዬው ከኢትዮጲያ ህዝብ የዘረፈውን ገንዘብ በደቡብ አፍሪካ ከመጨረሱ በፊት ዘመድ ካለው ወደ ጠበል ምናምን ውሰዱትና ሻል ሲለው እውነቱን ይጽፍ ይሆናል .....
ፓኑ አባ ፈርዳ
ኢትዮጲያዊ

ኢትዮጵያ ትቅደም በጣም ክቡር መፈክር ነው። ብዙ ትርጉም አለው. እርግጥ ናዚ ጀርመኒም ''ጀርመን ትቅደም'' ይል ነበር። ኢትዮጵያ ትቅደም ግን በመንፈሱም ሆነ በዐላማው ከጀርመኑ የተለየ ነበር። አንተ በየትኛው መንፈስ እንደጠቀስከው አላውቅም..

የየካቲትን ህዝባዊ ንቅናቂ ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች መጨቆናቸውንና መገፋታቸውን ሲገልጹ፣ ሁሉም በየፊናው ይህ ይገባኛል፣ ያ ይሰጠኝ፣ እንዲህ ይደረግልኝ፣ እገሌ ይነሳልኝ፣ እገሌ ይታስር በሚለበት ወቅት አገር ወዳዶች ተነስትው፣ እንዴ ሁሉም ለኔ ለኔ ሲል አገር እኮ ተረሳች። የራሳችንን ትተን ለሀገር የሚበጀውን እናድርግ። አገርን እናስቀድም። ኢትዮጵያ ትቅድም አሉ። ህዝብም ተቀበለው። በአንድ ወቅት ምልዐተህዝቡ የዘመረው መፈክር ነበር። ያን መሰለኝ አባ ፈርዳ ፊርማ ያረከው።

ያን ከሆነ ያልገባህ ነገር ይታየኛል። በየካቲቱ ኢትዮጵያ ትቅደም የጎሳ ልዩነቶች አይታወቁም። አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ውራጌ፣ ቤንሸንጉል የሚባል ክልል አልነበረም። ኢትዮጵያ ትቅደም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ብቻ ማመን ነበር። ልክ ኦባማ ጥቁር አሜሪካዊ፣ ነጭ አሜሪካዊ ወዘተ የሚባል ነገር የለም። there is only the united states of america. እንዳለው፣ ኢትዮጵያ ትቅደም ማለት የኢትዮጵያዊያን አንድነት ፍጹምነት ማለት ነበር። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ያነገቡ ወጣቶች በፖለቲካ አለመግባበት እርስ በርስ በጥይት ሲሞሻለቁ እንኩዋን በአመለካከት እንጂ በጎጥ ተለየይተው አልነበረም። ኢትዮጵያ ትቅደም አራማጆች ተዳመተወል ግን በኢትዮጵየዊነት ለኢትዮጵያ ነበር።

እና
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...

ስትል አልገባኝም።

ከዚህ አባባል ጀርባ ያለው ጥላቻና ብሽቀጥ ይገባኛል። ከመሬት ተነስተህ እንዲህ አላልክም። በስልጣን ላይ ያለው፣ በትግርኛ ተናጋሪዎች የበላይነት የተገነባው ስርዓት በግል ያደረሰብህ በደል ይኖራል። በአገርም ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሊሰማህ ይችላል። ይሁን እንጂ ከላይ የተከተበው ሀረግ ካንተ የሚጠበቅ አይደለም። ይህን ማንም ቢጽፈው ቀጥተኛ መልስ አልሰጥበትም ነበር፣ ከአንተ፣ ወራሽን ካስነበብከንና የኢትዮጵያ ትቅደምን መንፈስ ያውቃል ከምንለው ደራሲ በፍጹም አይጠበቅም።

አባ ፈርዳ፣ የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ እኮ አሁን ደረስ ያለ ይመስለኛል። በጎጥ ያልተከፋፈልች አንድ ኢትዮጵያ የምናይበት ዘመን እኮ ሩቅ አይደለም። ከቀይ ባህር አስከ ተፈሪ በር ያለ ህዝብ በእንድ ብሄራዊ መዝሙር፣ በአንድ ባንዲራና በአንድ መንግስት በስላም፣ በፍቅርና በአንድነት የሚኖሩበት ዘመን እውን እስኪሆን በእውነት ይህ ትውልድ አያልፍም። ታዲያ ያ ክቡር የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ በሂደት እየደከም መምጠቱን በአንተ ስመለከት ልቤ ይደማል።

ለመታረም ባለህ ድፍረት በመተማመን
ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby password » Wed Feb 25, 2009 2:37 pm

Postby Janamora » Wed Feb 25, 2009 2:56 pm

ፓን ሪዚኮ እንደጻፈ(ች)ው:
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...አባ ፈርዳ ዱለቻው::
ደራሲ ለመሆን ከዋሸራ መምጣት አለብህ እንዴ? ስብሀት ገ/እግዚአብሄር ትውልዱ የት ነው?? ሳስብህ ደረትህና መቀመጫህ ላይ ጸጉር ያበቀልክ ጭላዳ ዝንጀሮ ትመስለኛለህ:: ሰላም::
The Lion was silent but, The rats were roaring
Janamora
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 97
Joined: Tue Oct 28, 2008 8:45 pm

Postby early_bird ! » Wed Feb 25, 2009 3:51 pm

Janamora wrote:ፓን ሪዚኮ እንደጻፈ(ች)ው:
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...አባ ፈርዳ ዱለቻው::
ደራሲ ለመሆን ከዋሸራ መምጣት አለብህ እንዴ? ስብሀት ገ/እግዚአብሄር ትውልዱ የት ነው?? ሳስብህ ደረትህና መቀመጫህ ላይ ጸጉር ያበቀልክ ጭላዳ ዝንጀሮ ትመስለኛለህ:: ሰላም::

ጃንአሞራ..........
ኡፍፍ............አንጀቴን አራስክልኝ............................... :D :D :D

ፓስሻ....ሰላምታዮ ይድረስህ ንፍቅ ብለህኝ ነበር በ ሰላም ነው? :)
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby መሰማማት » Wed Feb 25, 2009 11:26 pm

ጋዜጠኛው የዶርዜውን አንጋፋ ቃለመጠይቅ አቅርቦላቸው የመለስ ልጅ አፏን የፈታቸው በእንግሊዝኛ ነው ለምን በትግርኛ አላስተማራትም እኛን ልጆቻችሁን በቋንቋችሁ በዶርዝኛ አስተምሩ እያለ:: ልጆቻችን በደርዝኛ የምናስተምራቸው ሸማኔ እንዲሆኑ ነው ? ሂድና ለመለስ ዜና እኛ ልጆቻችን በየትም የኢትዮጵያ ክፍል ሰርተው መኖር እንዲችሉ በአማርኛ ነው የምናስተምራቸው..........የምትለውን ምልልስ አጣቁሙኝ ባካችሁ...ፈልጌ ፈልጌ ላገኛት አልቻልኩም..ናዝሬት ላይ መሰለኝ ያነበብኳት
Twenty years from now you will be more disappointed by the things that you didn't do than by the ones you did do. So throw off the bowlines, sail away from the safe harbor, catch the trade winds in your sails, Explore, Dream, Discover.
መሰማማት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 290
Joined: Mon Aug 20, 2007 6:37 am

Postby ሀዲዱ » Thu Feb 26, 2009 12:08 am

ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ

ሳስብህ ......................... ጭላዳ ዝንጀሮ ትመስለኛለህ :?: ................ አባባልህ ታስቃለች :: .................... አንዳንዴ እንዲህ ፈገግ እድርጉን

ሀዲዱ

Janamora wrote:ፓን ሪዚኮ እንደጻፈ(ች)ው:
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...
አባ ፈርዳ ዱለቻው::
ደራሲ ለመሆን ከዋሸራ መምጣት አለብህ እንዴ? ስብሀት ገ/እግዚአብሄር ትውልዱ የት ነው?? ሳስብህ ደረትህና መቀመጫህ ላይ ጸጉር ያበቀልክ ጭላዳ ዝንጀሮ ትመስለኛለህ:: ሰላም::
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
ሀዲዱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 891
Joined: Fri Jul 13, 2007 8:58 pm
Location: Here

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby የጋሽ ለማልጅ » Thu Feb 26, 2009 5:39 am

ሀዲዱ wrote:የማንን እንደሆነ ትዝ ባይለኝም ይህ ፅሁፍ ሌላ የሆነ ሰው አፃፃፍ ስታይል ያስታውሰኛል ቂቂቂቂቂቂቂ

password wrote:በተስፋዬ ገ/አብ የተደረሰው ''የጋዜጠኛው ማስታወሻ'' የተሰኘው መጽሀፍ

ተስፋዬ ... ብርሀኑ ያበረታታኝ ነበር ... ይላል...

ገጽ 75 ላይ ደርሼአለሁ ... ብርሀኑ ላካ ተኪውን አዘጋጅቶልን ኖሯል...

ጉርም ትረካ .... አስደናቂ ዘገባዎች ... ውብ ስነጽሁፍ

እያነበብኩት ነው... ስጨርስ እመለሳለሁ....

PDF የተሰራጨውን የምታነቡ የዚህን ድንቅ ደራሲ ድካም አትዘንጉ

በርድ መጽሀፉን አግኝተሻል?.
እንደ ልቦለድ ልብ የሚሰቅል..
እንደ ትሩዝ ግጥሞች ቀልብ የሚስብ ... አንብቢው

ፓስ

በሳቅ. ሀዴዱ አስተዋይ ታዛቢ ነህ ወንዳታ.!, እኔም አሁን ገና ተገለጠልኝ. ሰውየው እራሱን ሲያጃጅል በ 3ዳይሜንሽን ይጫወታልና. ባንዱእ ዘርጣጭ በሊዬላው ፊልምና መጣህፍ ሀያሲ በሶስተኛው አሽቃባጭ ሴት ሆኖ ብቻውን ድራማ ይሰራል. ጥንብ ሻቢያ
የጋሽ ለማልጅ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Sun Feb 08, 2009 8:05 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Feb 26, 2009 9:17 am

Janamora wrote:ፓን ሪዚኮ እንደጻፈ(ች)ው:
ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...አባ ፈርዳ ዱለቻው::
ደራሲ ለመሆን ከዋሸራ መምጣት አለብህ እንዴ? ስብሀት ገ/እግዚአብሄር ትውልዱ የት ነው?? ሳስብህ ደረትህና መቀመጫህ ላይ ጸጉር ያበቀልክ ጭላዳ ዝንጀሮ ትመስለኛለህ:: ሰላም::

ጥጋበኛ ኣጋዘን ...የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል ...አሉ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Feb 26, 2009 9:28 am

password wrote:

ለነገሩ እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ...

ስትል አልገባኝም።

ከዚህ አባባል ጀርባ ያለው ጥላቻና ብሽቀጥ ይገባኛል። ከመሬት ተነስተህ እንዲህ አላልክም። በስልጣን ላይ ያለው፣ በትግርኛ ተናጋሪዎች የበላይነት የተገነባው ስርዓት በግል ያደረሰብህ በደል ይኖራል። በአገርም ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሊሰማህ ይችላል። ይሁን እንጂ ከላይ የተከተበው ሀረግ ካንተ የሚጠበቅ አይደለም። ይህን ማንም ቢጽፈው ቀጥተኛ መልስ አልሰጥበትም ነበር፣ ከአንተ፣ ወራሽን ካስነበብከንና የኢትዮጵያ ትቅደምን መንፈስ ያውቃል ከምንለው ደራሲ በፍጹም አይጠበቅም።

አባ ፈርዳ፣ የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ እኮ አሁን ደረስ ያለ ይመስለኛል። በጎጥ ያልተከፋፈልች አንድ ኢትዮጵያ የምናይበት ዘመን እኮ ሩቅ አይደለም። ከቀይ ባህር አስከ ተፈሪ በር ያለ ህዝብ በእንድ ብሄራዊ መዝሙር፣ በአንድ ባንዲራና በአንድ መንግስት በስላም፣ በፍቅርና በአንድነት የሚኖሩበት ዘመን እውን እስኪሆን በእውነት ይህ ትውልድ አያልፍም። ታዲያ ያ ክቡር የኢትዮጵያ ትቅደም መንፈስ በሂደት እየደከም መምጠቱን በአንተ ስመለከት ልቤ ይደማል።

ለመታረም ባለህ ድፍረት በመተማመን
ፓስ
ሰላም ሰላም ፓሱ ማለፊያ ቃል
እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ስምቼም አላውቅም ያልኩት እውነቴን ነው ...ይሄንን ቃሌን በምን መልኩ ተረድተህኝ ወደ ዘረኝነትና ጥላቻ እንደወሰድከው አልገባኝም ....አሁን አንድ ሰው ተነስቶ የኦሮሞ ቄስ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ብሎ ቢጽፍ ዘረኛ ሊባል ነው ????እስቲ መልሰህ እየው
ከሰላምታ ጋር ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሾተል » Thu Feb 26, 2009 10:52 am

በክብርነቴ ሆኜ ለተወሰነች ደቂቃ ጊዜ ሰጥቼ ስለትውልዳችን የመረረ ዘረኛነትና ስለተጠናወተው ጥላቻ አመጣጡን ሳስብ ወደ አንድ ቦታ ወሰደና አመራመረኝ::ዘረኝነትና ጥላቻ ያልኩት ይበልጥ በአሁኑ ሰአት እንደስድብ ተደርጎ የተቆጠረው የዘረኝነትና የጥላቻ ቃል........አንተ ሻኢቢያ ነህ....አንቴ ሻኢቢያ....አንተ ኤርትራዊ የሚሉት የዘረኝነትና የጥላቻ ስድብ::ታድያ ይሄ ነገር በእኛ ትውልድ ላይ እንዴት ሊሰነቀር ቻለ?መሰረቱ ምን ይሆን ስል መልስ አገኝ ዘንድ አንዳንድ እውነታዎችን እንድገምት አደረገኝ::ያ እውነታ ምን ይሆን?

በሉ ሰድቦ ለሰዳቢ ሰጠን አትበሉኝና እውነታዊ ግምቴን ላስፍር::ከዛ በፊት ግን ስለ ኤርትራዊ ያለኝን እምነት ማለት በእኔ ሞኙ እምነት ኤርትራዊ የኛ ኢትዮዽያዊ ወንድምና እህት እናትና አባት አክስትና አጎት አያትና ቅድመአያት እንደሆኑ አምናለሁ::ፖለቲካ ለያየን እንጂ ኤርትራ ኢትዮዽያ እንደሆነች አውቃለሁ::ይሄ የኔ ሞኙ እምነት ነው::በመቀጸል የጠፋው ወገኔ አንተ ኤርትራዊ ነህ እያለ ወይም ኤርትራዊ ሁሉ ሻኢቢያ እንደሆነ ሁሉ (ቢሆንም መብቱ መሰለኝ በርግጥ) አንተ ሻኢቢያ ነህ (ሻኢቢያ ማለት የድርጅት ስም ነው እንጂ ስድብ አይደለም በርግጥ ) እያለ ኤርትራዊነቱን ጠቅሶ ሲሳደብ ሳይ በውስጡ አንድ ነገር እያሰቃየው እንዳለ እረዳለሁ::እና እሱ ምንድነው?

መጣሁ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby password » Thu Feb 26, 2009 11:32 am

የጋሽ ለማልጅ wrote:

በሳቅ. ሀዴዱ አስተዋይ ታዛቢ ነህ ወንዳታ.!, እኔም አሁን ገና ተገለጠልኝ. ሰውየው እራሱን ሲያጃጅል በ 3ዳይሜንሽን ይጫወታልና. ባንዱእ ዘርጣጭ በሊዬላው ፊልምና መጣህፍ ሀያሲ በሶስተኛው አሽቃባጭ ሴት ሆኖ ብቻውን ድራማ ይሰራል. ጥንብ ሻቢያ

የለማ...
:lol: 1. password 2. ሾተል 3. early bird :lol:
አንድም ሶስትም ነን... እንዳመለካከትህ ነው... ህመምህ እየጠና ከሄድ በዛ ብለን ልንታይህ እንችላለን... ከሶስት በላይ ሆነን ከታየንህ ግን ሀኪም አማክር ....

ባለፈው ሻእቢያ ያልካኝ እኮ ደርሶኛል ... አሁን ወያኔ ወይ ሌላ ነገር አይሻልም... አሰልች ክሊሼ እንዳይሆን...

አንተ ግን በስንት ስም ነው የምትገባው? በዚህ ስምህ የታየከው feb 2009 ውስጥ ነው... ነባር ተሳዳቢ እንደሆንክ ታስታዋለህ.... በተረፈ በርታ
Last edited by password on Thu Feb 26, 2009 11:38 am, edited 1 time in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሾተል » Thu Feb 26, 2009 11:36 am

የደርግ ዘመን ልጅ ስለሆንኩና ኢሀዴግ ከመምጣቱ ከትንሽ አመት በፊትና እንደመጣ እድሜዬ ነገሮችን ማየት የሚችልበት የሙጭቅላ እድሜ ባለጸጋ ነበርኩና አይኔን ገልጬ የአገሬን የንግድ ባለሀብት እንዳየሁት የገራጁ የባለትላልቅ ሆቴሎች የባለስቴሽነሪ እንዲሁም መለዋወጫ እቃዎችና የባለጭነት መኪና ባለቤቶች ከኤርትራው ክልል የመጡ ኢትዮዽያዊ ዛሬ ኤርትራዊ እንበለው እና የነዛ ባለሀብቶች ነበሩ::የጎጆ ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች::

እና ከኤርትራ አካባቢ ተወልዶ ያደገ ቤተሰብ እንደምገምተውና እንደተነገረኝ ባህሉ ወደ አውሮፓው ባህል እንዲሁም ወደ ጣልያኑ ባህል ጠጋ ያለ ነው::እሱም እንደተባልኩት ጣልያን የኤርትራ ቅኝ ገዢ ስለነበረች ያንን ባህል ጥላው ሄዳ ነው::ለዛውም አስመራ ያሉ ብዙ ነገሮች በጣልያንኛ የስም አጠራር እንደሚጠሩ ተነግሮኛል::እንኩዋን ለብዙ አመታት በቅኝ የተገዙ አይደለም አርበኛ ኢትዮዽያዊ አባቶቻችንና እናቶቻችን በ 5 ቱ አመት ጣልያን ኢትዮድያ ውስጥ በቆየበት ጊዜ የነበረው ትውልድ ከአማርኛው ጣልያንኛ ይቀናው ነበር::አሁንም ድረስ የድሮ ሰዎች ሲናደዱ እንደጣልያኖች ነው ሲሳደቡ የጣልያንኛ ስድብ ነው::እንግዲህ 5 አመት ነች::ኤርትራ ውስጥ ደጎ ጣልያን በቅኝ ግዛት ኤርትራን ያስተዳደረችው የእትየለሌ አመታቶችን ነው::እና ነገሮችን ላገናኛቸውና ከኤርትራ ክልል የመጡ ኢትዮድያን የነበሩ ወገኖቻችን በመላው የኢትዮድያ ክልል ቀድመው ነቅተው ስለነበር ስራ ስለሚወዱ ንግድ ከፍተው ህዝቡን ሲያገለግሉ ነበር::እንደፖለቲከኞች አባባል ደግሞ የኢትዮዽያን ሀብት ሲመጠምጡ...እኔ ግን አልመጠመጡም እላለሁ....ስለዛ ወደፊት ያለኝን ማንም ሳይነግረኝ ያገናዘብኩትን እላለሁ::

እና እነዚህ ኤርትራዊ የጎጆ ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች በላባቸው ሀብት ስለነበራቸው ከአብዛኛው ኢትዮዽያዊ በተሻለ ይኖሩ ነበር::በሀብታቸው ይፈሩ ይከበሩ ነበር::ይህንን ስል ከውራጌ ክልል የመጣውንም ሰርቶ ባለሀብት የሆነውን ሳያወራ ሳይመቀኝ በላቡ የሚኖረውን ሳልረሳ ነው::ጨዋታዬ ወደ ኤርትራ ስለሆነ ነው::

እና ወደጨዋታየ ልመለስና የገራጁ የባለ ትላልቅ የጭነት መኪናና የባለ ትላልቅ ሆቴሎች ባለቤት ባለሀብቶች ኤርትራዊያኖች ስለነበሩ የሰፈር ስም እራሱ እነሱ ለንግዳቸው ባወጡለት ስም እስከመጠራት የተደረሰበት ጊዜ ነበር::ታድያ የአገሬ ህዝብ ዛሬ እሱ የሚያስበውን ያላሰበና የሚደግፈውን ያልደገፈ ሁሉ ኤርትራዊ ነው ሻኢቢያ ነው እያለ እንደስድብ ሲጠቀምበት የምናየው እንደእኔ እምነት ትላንት ኤርትራዊያኖች በላባቸው ሀብት ሲያገኙ ድሀው የነሱ ሰፈር ልጅ ዛሬ ሻኢቢያ ኤርትራዊ እያለ የሚሳደበው ደጎ እነሱ ሲበሉ ሲጠጡ ሲለብሱ ተመቻችተው ሲኖሩ በንዴት ሲበግን የነበረ ምድረ ዘረ መናጢ ቤተሰቦቹ ስራን በእስራት ሳይሆን በቅናት በምቀኝነት አድገው ያሳደጉት የሰነፍ ልጅ ሰነፍ ነው::ትላንት በደርግ ጊዜ እነዚህን ባለሀብቶች ይመቀኛቸው ነበር::በዛውም ልክ ኑሯቸውን ይመኘው ነበር::አልፎም ሌላ ሰፈር ሄዶ የሌላ ሰፈር ልጆች ቢተዋወቅ በነዚህ ሰዎች ስለሚኮራ የሰፈሩን ስም ለመንገር የነሱን የድርጅት ስም በመጥቀስ ወይም የድርጅቱን ባለቤት ስ በመጥቀስ ነበር...ሴት ሊጠብስ ሲል እንድታከብረውና እሺ እንድትለው ከነዛ ቤተሰቦች አንዱ እንደሆነ አድርጎ በመጎረር ነበር::ሲለውም ደግሞ ሰርቶ እንደነሱ እንደመሆን ሀብታቸውን እየቆጠረ በቅናት ድብን ብሎ ያድር ነበር::

ታድያ በዛን ዘመን ኤርትራዊ ቅብርጥሴ ብሎ እንዳይሳደብ ደርግ ሁሉንም አንድ አድርጎ ስለነበር የሚገዛውና ዘረኝነት ጠላቱ ስለነበር ይቅመው ነበር::ታድያ ዛሬ ዘረኛነት የመሆን ዲኦክራሲ ስለተሰጠ ያንን ቅናት ያንን ሰይተው ሳያገኙት ያደጉበት የሰው ሀብት ወይኔ በማለት የቁጭት ስሜት ወደጥላቻነት ቀይረነው በዘረኝነት ደዌ ሸብበነው ስሜታችንን ቅናታችንን ያ ልጅነታችን ተሰንቅሮ ያደገውን እልክ ዛሬ እናወጣው ጀመርን::

ያ የሰውን ሀብት እያዩ የመቅናት እድገታችን ዛሬ ወደ ጠዪነት ተቀየረብን::የጥላቻ ዲሞክራሲ በገፍ ስለተሰጠን ጥላቻችንን በማይገባበት ቦታ ሁሉ እናንጸባርቀው ጀመርን::ያ ነጸብራቅ ደግሞ ከመረረ ለዛውም መሰረት ከሌለው ዘረኝነት ውስጥ ከተተን::ያ ደግሞ ስድብ ን እንደሆነ ለይነት እስካናውቅ ድረስ ወተፈን::ያ መወተፍ ትንሽነታችንን አሳበቀብን::

እንግዲህ ያ ነው ስለድርሰት ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ስለ እምስና ቁላ ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ስለ አሜሪካ የፕሬዚዳንቶች ርጫ ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ወዘተ እያልን ደረጃና ዝርያ እንመድባለን::በዚህ አጋጣሚ እንደዚሁ ስለንም ያውራ ምን ስለምንም ይቃወም ስለምን ወያኔ ወይም ትግሬ ነው እያልን የምንሳደበውንም አልረሳሁም::ጨዋታው ስለ ኤርትራዊ ወይም ሻእቢያ ስለሆነ ነው እንጂ ስለምንም ተቃውሞ ያሰማ ወያኔ ያልተባለ ማን አል....በርግጥ አሁን ወያኔ ማለት የድርጅት ስም እንጂ ስድብ አይደለም::ስለዚህ ከእኔ ጨምሮ ይሄንን ስድብ አድርገን የተጠቀምን ምን ያህል ፉርሾች እንደሆንን ሳስብ በራሴ አፍራለሁ::ስንት መሳደብ ስችል ይሄ ወያኔ ይሄ ሻእቢያ እያልኩ የተሳደብኩ መስሎኝ የድርጅቱን ስም ከፍ ከፍ ሳደርግ......

እና ልል የፈለግኩት አብሮን ያደገ ቅናትና ምቀኝነት ነው ዛሬ ወደዘረኝነትና ቅናት እንዲሁም ጥላቻ የተቀየረብን ይበልጡን ከኤርትራዊ እህት ወንድ አባት እናቶቻችን ጋር ያለን ጥላቻ ጎልቶ የታየብን::አባቴ ለፍቶ ሰርቶ እነሱ የደረሱበትን የሀብት እርከን መድረስ አቅቶት ከሰፈር የእድሜ እኩዮቹ ጋር አረቄ እየተጋተ በወሬ ጊዜውን አጥፍቶ ግን ተሸክሞ ያገኛትንና ከወሬውና አረቄው የተረፈችውን ገንዘብ ለእናቴ ሰጥቶ ኤርትራዊ ሱቅ ሽሮ ገዝታ እኔን ስላሳደገችኝ ባለሀብቱ ነው ወይስ ወረኛውና ጠጪው አባቴ ነው መወቀስ ያለበት?ወይም መጠላት ያለበት?

ወገን ስለእውነት ብለን እናስብ::አንገመት::
በርግጥ ይሄ ብቻ ሳይሆን ሌላም ሪዝን አለ::እሱ ካስፈለገ ምን ያህል በሆኑ ድርጅቶች ብሬን ወሽድ እንደሆንንና እኛን ለፖለቲካ ጥቅማቸው ሲሉ እየተጫወቱብን እንዳሉ መጥቀስ ካስፈለገ ክብርነታችን ሊል ይችላል::

ለጊዜው መልክቴን ካስተላለፍኩ ተንፈስ ብዬ እውላለሁና ጨረስኩ::

ግን እሰብ ይላል ያገሬ ጎጃሜ::እውነቱን ነው እሰብ::ወይም የገባን ከየቱም የሌለነው እናስብልህ መብቱን ስጠን::

ሾተል........አንድ አለም
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 1 guest