ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby password » Sun Apr 19, 2009 5:20 pm

ሰላም አዋሽ

የሰንዘርከውን ሀሳብ በጥሞና አንብቤዋለሁ። ከጽሁፍ ውስጥ ምላሽ ልሰጥባቸው የፈለግሁዋቸውን አውጥቼ በጥቅስ ውስጥ ቀንፌአቸዋለሁ።

እነሆ

በተለይም የቡርቃ ዝምታ በተስፋዬ እንዳልተጻፈ ለማሳመን እየሞከርክ ነው ::


ለማሳመን ሳይሆን ለጥርጣሬዬ መሰረት የሆኑትን ነጥቦች ለማሳየት፣ አዎ ሞክሬአልሁ። አንባቢ የቀረቡትን መረጃዎች አይቶ የራሱን ግምት ይሰጣል ብዬ አምናልሁ። የማሳመን አልማሳመን ጉዳይ ሳይሆን እንደ አንድ የመወያያ ርእስ መነሳት የሚችል ይመስለኛል።


እንደምገምተው የቡርቃ ዝምታን ከማንበብህ በፊት የጋዜጠኛው ማስታወሻን ስላነበብክ የአጻጻፍ ዘይቤውን በጣም ስለወደድከው ይመስለኛል ::


የሰጠሁት አስተያይት በመውደድና በመጥላት ላይ እንዳልተመሰረተ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ይመስለኛል። ከመጽሀፉ የጠቀስኩዋቸው አረፍተ ነገሮች ውስጥ ሰዋስዋዊ ቅርጻቸው፣ የቃላት አጥቃቀምና ማንም አማርኛ ተናጋሪ የማይስታቸውን ብሂሎች ተዛብተው ይገኛሉ። ከዚህ በመነሳት ነው፣ ድርሰቱ የሌላ ሰው ብእር ነክቶታል የምለው፣ እንጂ የጋዜጠኛው ማስታወሻን ስለወደድኩልት ብቻ አይደለም።

የብርሀኑ ዘርይሁንን ቀደምት ስራዎች ብታነብ እውን እሱ ነው እንዲህ ደርቶ ደርቶ የጻፈው ብለህ ትገረማለህ ::


ሁለቱን መድብሎች አንብቤአቸዋለሁ።


በኔ ግምት ተስፋዬን ምልኡ በኩልሄ ያደረግከው ይመስለኛል ::
v

ግምትህ የተሳሳተ ነው። የጋዜጠኛው ማስታዋሻ እንደ ቡርቃ በፓስወርድ መነጽር ስር ቢውል ብዙ እንከን ይገኝበት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። የማስታወሻ ጽሁፍ ውስጥ ንግግሮች፣ በመቀርጸ ድምጽ ካልተቀዱ በቀር፣ እንዲህ ቃል በቃል የመጻፋቸው ጉዳይ የሚያሰነሳው ጥያቄ አለ ብዬ ከሚያምኑት ወገን ነኝ።


ተስፋዬ ያንን መጽሀፍ በመጻፉ ምን ያህል እንደሚኮራና ለስደት ካበቁትም ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል ገጽ 225


ተስፋዬ በቡርቃ ስራ ላይ የፈጽመውን ስህተት አሁንም የተረዳው አይመስልም፣ ስለዚህ መኩራራቱን ሊቀጥል ይችላል። ራስህን ማየት በጣም ከባድ ነው። ፊትህን የምታይበት አንድ ጥሩ መስታወትና መስታወት የሚይዝልህ ደህና ወዳጅ ያስፈልግሀል። በዚህ መጽሀፍ ማን ምን እንደሚጠቀም ሊያስረዳ የሚችል አይመስለኝም። የባድሜው ግጭት የተፈጠረ ሰሞን ወያኔ ብአጠቃላይ የኢትዮፕያን በተለይ ደግሞ የትግራይን ህዝብ ለማነሳሳት የተጠቀመበት የቅስቀሳ ስልት ሁላችንንም ያስደመመ ነበር። የአቶ ገብሩን ንግግር ያስታውሱዋል። ኤርትራዊያን 'ለአንድ ሺ ዝንብ አንድ ፍሊት ይበቃዋል።" ይላሉ....

በሚሊዮን የሚቆጠር ኤርትራዊያንና በትውልደ ኤርትራዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደርስባቸው የበቀል እርምጃ ግድ ያልነበርው ስድ ንግግር ነበር።
ይህን ሲስማ ተስፋዬ ምን ተሰምቶት ይሆን? በዚያን ስሞን በመንግስት መገናኛ ሚዲያ ይተላለፍ የነበርው ለጆሮ የሚቀፍ ቅስቃሳ አይዘነጋም።
ኤርትረዊያን የአማራ፣ የኦሮሞ ለተለይም የትግራይ ህዝብ ላይ ንቀት አላቸው የሚል ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ይዘከዘክ ነበር። አላማው በወቅቱ የህዝብን የጥላቻና የበቀል ስሜት ለመቀስቀስ ነበር። ያንን ተስፋዬ እንዴት ያየው ይሆን? የሱስ ቡርቃ ከዚያ በምን ይለያል? ቡርቃ ሰዎችን ለበቀል የሚያነሳሳ ይዘት የለውም? አንዳንዴ እንኩዋን ህዝባችን ፊደል አልቆጠረ ያሰኛል። ፊደል ቆጥሮ የትኛውን የረባ ነገር ሊያነብ!

ክንፈ ሰበብ ፈጥሮ እኔን ከሀገር እንዲያባርር መታዘዙን ጠረጠርኩ :: የቡርቃ ዝምታም አልተመቻቸውም ::


አቶም ቦንብን የፈጠሩ ሳይንቲስቶች ቦንቡ የሚያስከትለውን ጥፋት ካስተዋሉ በሁዋላ መልሰው ሊያጠፉት መጣራቸውን ታውቃለህ ብዬ እገምታለሁ። አነ ክንፈ የብሄርስቦችን መቃቃር የሚፈልጉት በተወሰነ መጠን ይመስለኛል። ለአገዛዛቸው በሚመች መጠ። አንሱ በሚገዝዋት ኢትዮጵያ ሁዋላ ሊያቆሙት የማይቻላቸው የጎሳ ጦርነት እንዲቀጣጠል አይፈልጉም። የሚፈልጉት በልክ ነው። የተስፋዬ "ዶስ" የበዛባቸው ይመስለኛል እና አልወደዱትም።

አንተ ደሞ ሽንጥህን ገትረህ የምትከራከረው ይሄ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ በሌሎች ሰዎች ተስፋዬ ላይ እንደተጫነ እንጂ የተስፋዬ አማርኛ እንዳልሆነ ነው ::


በእንድ አማርኛ ተናጋሪ ሊባል የማይችል ሀረግ ሳነብ ምን ልበል? እስኪ ይሄን እይ።
ጂብሪል፣ ምንም እንኩዋ የስራተኛው ፓርቲ አባል ቢሆንም ብዙውን ጊዜ የታዘዘውን እንደ ጥሩንባ ከማስተጋባት የተቆጠበ ....


እግዜር ያሳይህ አንተስ ብትሆን እንዲህ አይንት አረፍተ ነገር ስታነብ አማርኛ ተናጋሪ አልጻፈውም ብለህ አትጠራጠርም። አንድ ቦታ አንቱ ያለውን ገጸባህሪ ሌላ ቦታ አንተ የሚለው ከሆነ ምናልባት ደራሲያኑ ከሁለት በላይ ይሆናሉ አትልም? ለምሳሌ፣ አንቱ ሲባል የነበረውን ፕ/ መንግስቱ ገጽ 252 ላይ አንተ ብሎታል።

ይህ የተስፋዬን ማንነት በደንብ ካለመረዳት ወይም you are overwhelmingly charmed by his recent book.


ከማንነቱ ጉዳይ የለኝም። And I have enormous respect for his resent book both as a literary work and source of vital information.

አንተ ስታስበው እንዲህ አይነት ተራ ፕሮፓጋንዳ መጻፍ ባይችል ኖሮ , ከትምህርት ትምህርት ሳይኖረው , ከልምድ የታጋይነት ልምድ ሳይኖረው (ወያኔን የተቀላቀለው በሰማኒያዎቹ መጀመሪያ እንደሆነ ተናግሩዋል ) ባንዴ የኢትዮ ፕሬስ ዋና ስ /አስኪያጅ ሊሆን እንዴት ይችላል ብለህ ታስባለህ ?


የኢህአዴግ ሹመት አስጣጥ መስፈርት ቅድሚያ የሚሰጠው ታማኝነትን እንደሆነ አባላቱ አይደብቁም። የፕሬስ መምሪያን ለመቆጣጠር ተራ ፕሮፓጋንዳ መጻፍ የሚችል ሰው ሳይሆን አንድ እሺ ባይ ነው የሚያስፈልግህ። አቶ ታምራት ተስፋዬን ሲሾሙት እሺ ባይነቱን እንጂ ለትምህርቱ ግድ አልነበራቸውም። እሳቸውም ቢሆኑ እንኩዋን አገር አንድ አውራጃ ለማስተዳደር የሚያበቃ ትምህርት የነበራቸው አይመስለኝም።


so, I'm afraid you are misleading your readers when it comes to who was behind this 'crap'.


I was simply entertaining my right to share my opinion with warka mates. Readers are entitled to freely form theirs opinion as well. "Misleading" is not the right word here.

It was written by Tesfaye and only by Tesfaye with his consent to fulfill Afeworki's 100-years homework for Ethiopia.


This is a serious allegation. If you really meant you words, you will be required to come up with a convincing evidence. I 'm sure your allegation is not based on the simple fact that Tesfaye is born to Eritrean parents.


ብርሀነ ትንሳኤው ለሁላችንም ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Fri Apr 24, 2009 11:41 pm

ተስፋየ ገ-አብ ከአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ጋር
http://www.addisdimts.com/
(19-4-09)
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ዛዙ » Sat Oct 02, 2010 12:59 pm

ያላነበበ ሁሉ እንዲያነበው አዋራውን ጠርጌ ከመዝገብ ቤት አወጣሁት:: መቼም ድንቅ ያፓስ ትንተና ድንቅ ነበር:: እግዜር ይስጥህ ፓስ ......የት ጠፋህ ግን?
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby password » Tue Oct 12, 2010 11:36 pm

እንዴት ነው? ዛዙ/ ምን ተፈጥሮ ነበርና ነው ይህን ገጽ አውጥተህ የጠበቅኽኝ። ተስፋዬ አሁንም አነጋጋሪ ሆኖአል እንዴ፣ በሁለተኛው መጽሃፉ ምክንያት ይሆን። ኣላነበብኩትም።

ሰላም ሰላም

ዋርካዎች እንዴት ከረማችሁ? ደህና ናችሁ ሁላችሁም?

ሶስት ወር አገር ቤት ከርሜ መምጣቴ ነው። በዚህ አመት ብቻ ሶስቴ ሄጃለሁ። ለዚህ ነው ዋርካዋ ስር ያልታየሁት።

እንደመጣሁ እዛም እዛ ሳልል እዚህ ባህልና ስነጽሁፍ ነው የገባሁት ፣ እና የፓስወርድ መነጥርን ሳይ ገርሞኝ እንደ አዲስ አነበብኩት፣ ውይይት ምልልሱ/ ተረቡ/ ትንተናው/ ስድቡ

እኔማ ተስፋዬ ራሱ የሰጠው መልስ ይኖራል ብዬ ተጣድፌ ነበር። ሳጣ /ለምን መልስ አይሰጥበትም? ብዙ ቦታ ስለሚጠይቅ ሰልችቶት ይሆን? አልኩ።
ግን እኮ እዚህ የተተቸው ስነጽሁፋዊ ጉድለቱ ነው። በተለይ ገጸባህሪ አሳሳሉ ላይ ያለው ድክመት፣

አንድ ሰው ልቦለድ እስከጻፈ ድረስ የፈለገውን መከተብ ይችላል። አንባቢውን ማሰምን ብቻ ነው፣ የሚጠበቅበት። የልቦለድ ድርሰት ዋናው አቀበት ደግሞ ያ ነው፣ አንባቢን ማሳመን። ማሳመን እስከቻልክ ድርስ ገጸባህሪህን የመስታውት አይን አስገብተህለት አንገቱን ሳያዞር በእንድ ጊዜ ሁዋላና ፊት ማየት እንድሚችል ልታደርገው ትችላለህ።
የተስፋዬ ድክመት፣ አንባቢ ከገጸባህሪያቱ አፍ የሚወጣውን ቃል እንዲያምን የሚያስችል ባለመሆኑ ምክንያት፣ የሁሉም ባህሪያት ንግግር የደራሲው የራሱ መስሎ መነበቡ ላይ ነው።
ያን ነበር ለመጥቀስ የሞከርኩት። ለማንኛውም ተስፋዬ ራሱ መለስ ቢስጥበት ብዙ የምናነሳው ነገር ይኖር ነበር።

ዛዙ ስላስታወስከኝ አመስግናልሁ።

ሰላም ለሁላችሁም።

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሙዝ1 » Wed Oct 13, 2010 3:47 pm

ተስፋዬ ድሪቶዉን መደረት እንጂ መች ወጥ መጽሀፍ ጻፈ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby password » Fri Oct 15, 2010 12:17 am

ያ የምናውቀው ሙዝ ነው ወይስ በሱ ስም የሚጠቀም ሌላ? አያስብልም? :lol:

የምናውቀው ሙዝ ክሆነ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጠኛል ብዬ እጠብቃልሁ።

፩ ዲሪቶ መደረት ስትል በስነጽሁፍ ዘርፍ ምን ማለት ነው።

፪ ወጥ ስትልስ እንዴት ማለት ነው?

፫ ሃሰቡን ሳይሆን ሰውዬውን ራሱን እገለው ነበር ብለህ ስለነበር፣ ተስፈዬን በተመለከተ የምትሰነዝረውን ሀሰብ በስሜታዊነት ስለሚሆን/ አንበቢዎችህ ይቀበሉታል ብለህ ትጠብቃለህ?

አክበሪህ

ፓስ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሙዝ1 » Sat Oct 16, 2010 4:21 pm

ሰላም ነህ ፓስ ወገኔ? እንደዉ ወደ አዲስ አበባ ጎራ ስትል አንድ እሳት ይሁን ንፋስ አልያትም የሆነ ነፍሳት ነገር አለ ልጠይቀዉ አይባልም? እስኪ ይሁን ...

እንደዉ ቀኗ ባለፈች ቁጥር የምትዉጠዉ ምራቅ ወፈር እያለ ሲሄድ ደጋግመህ ዋጥ ዋጥ ስታደርገዉ እንደቀድሞዉ ዘዉ ዘዉ ... አወኩ አወኩ ለማለት ድፍረት እያሳጣኝ ተቸግሬ እንጂ ቢያንስ ከወር 2 ቀን ዋርካን ሳልጎበኛት አልቀርም ....

እስኪ ወደጥያቄዎችህ ልግባ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Sat Oct 16, 2010 4:33 pm

በመጀመሪያ ደረጃ ስነጽሁፍን በቁሙ አላዉቀዉም እንደዉ ጋደም አድርጌም ለማወቅ የረዳኝ ያኔ የዛሬ 15 አመት አካባቢ ጊዜዉ እንዴት ይነጉዳል ጃል .... የዛሬ 15 አመት አካባቢ ለኑሮ ይጠቅመኝ ይሆን ብዬ ስማር 11ኛ ክፍል እያለሁ የስነጽሁፍ አላባዉያን ሲባል የሰማሁትን መምህሩ ድንገት ፈተና ላይ ቢያመጣዉ መስማቴን ለማረጋገጥ እመልስለት ዘንድ ዳሰስ ዳሰስ ከማድረግ ባለፈ ለትንታኔ የሚሆን ቴክኒኮችን አላዋሀድኳቸዉም .... አሁንም ድረስ ...

የሆነዉ ሁኖ የስነጽሁፍን ትሩፋቶች ግን አጣጥሚያለሁ ወደፊትም አጣጥማለሁ ...

ድሪቶ ስል ... ወጥ አለመሆንን ለመግለጽ ነዉ ... ወጥ ደግሞ እናንተ የሙያዉ ባለቤቶች እንደምትሉት ትርጉም ያልሆነ ለማለት ሳይሆን ... ከጫፍ ጫፍ በአንድ ፍሰት የማይሄድ ለማለት ነዉ ... ድሪቶ ቃሉ መደረትን ለመግለጽ ነዉ እባክህ ደ ን ጠበቅ አድርገህ አንብብልኝ ... መደረት ደግሞ ካለ ቅርጽ አንዱ ባንዱ ላይ ሲነባበር ማለቴ ነዉ ... ሰዉየዉም በሁለቱ መጽሀፍቶች ያሳየኝ ያንን ነዉ ... መዝሙረ ዋልዋ ... ሁለቱ ዝሆኖች ... ምናምን ...

እንዳልኩህ ስነጽሁፍን ባላዉቅም ...መጽሀፍትን ግን አነባለሁ .... ፍቅር እስከ መቃብር ከገጽ 1 ... ወይዘሮ ዉድነሽ በጣሙን ጨምሮ .... የነ ወይዘሮ ጥሩ አይነት .... ከዚያም እነ እቡኝ ኑሬ ... እንዴ እንዴት ወደታሪኩ ፍሰት እየተቀላቀሉ ታላቁን ፍቅር እስከመቃብር ታላቅ ያደረጉበትን ከገጽ 1 እስከ 420 ድረስ ... አንድ ገጽ በተጨመረ ቁጥር መጠኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩም እየዳበረ .... ፍልስፍናዎች እንደ ጥቅምት እሸት እያፈሩ .... በስስትና በምኞት እያባበሉ ... ጭዉዉዉ ... ታዲያ እንዴት ብዬ በየትኛዉ ልቤ ታላቋንና ጥልቋን ስነጽሁፍ ለጻፈ ሁሉ ማዕረግ ስትሆን ልቤ ይቻልና ከስሜት ልንጻ ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሙዝ1 » Sun Oct 17, 2010 1:33 pm

password wrote:፫ ሃሰቡን ሳይሆን ሰውዬውን ራሱን እገለው ነበር ብለህ ስለነበር፣ ተስፈዬን በተመለከተ የምትሰነዝረውን ሀሰብ በስሜታዊነት ስለሚሆን/ አንበቢዎችህ ይቀበሉታል ብለህ ትጠብቃለህ?

አክበሪህ

ፓስ።

እሽ ፓስ! ትናንት ለዚህችኛዋም ጥያቄ መልስ የሰጠሁ መስሎኝ ነበር .... ዘልያታለሁ ወይንም በዋርካ ሰላቢ ተሰልቢያለሁ ....

የሆነዉ ሁኖ .... ዋርካ ላይም ይሁን በዋናዉ ህይወቴ ሰዎች ይቀበሉኝ ይሆን የሚል ጥያቄ ለራሴ አላቀርብም ... የኔ ድርሻ መተንፈስ .... አተነፋፈሱን በልኬ ወይንም በልካቸዉ ልኬን መፈለግ የፈላጊዉ ድርሻ ነዉ .... ምን አደከመኝ ብለኽ ነዉ?

ተስፍሽ በቡርቃ ዝምታ ላይ በነበረዉ እይታ ትልቅ ቂም ቋጥሬበት ነበር ---ሰዉ መስሎኝ:: አሁን ግን ተከታታይ መጽሀፍቱን ሳነብ ልቤ በሀዘን ነዉ ሚያስበዉ:: በዉነቱ ሊታዘንለት የሚገባ ሰዉ ነዉ:: በህይወት ዘመንህ ምንም አይነት አቋም ሳይኖርህ መኖር ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ስለሚገባኝ አዝንለታለሁ:: በህይወት ዘመንህ የምትኖርለት የኑሮ አላማ ሳይኖርህ እንደ እስስት በሚቀያየር ማንንነት መኖር አሳዛኝ ነዉ ... በአመለካከት:: እናም ቆየሁ ካነሳሁት ጥላቻዬን ....

እርግጥ ነዉ እኔም ከጥላቻ እየራኩ ነዉ .... ለተፈጥሮ ቅርብ በሆንክ ቁጥር ለፍቅር እጅህን ጸጣለህ .... ከተፈጥሮ ጋ ህይወትህ ወግ ሲጀምር ..... ከፍቅር ዉጭ ምንም ገዥ ሀይል እንደሌለ ስትረዳ ሰዎችን ትወዳለሁ .... የሚጠሉትም ከሚጠሉት በላይ ሊታዘንላቸዉ ይገባል::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ዲማሚት » Sun Oct 17, 2010 1:59 pm

ወዳጄ ፓስወርድ እንደምን አለህልኝ ጽሑፍህን መከታተል የጀመርኩት ገና ሰማያዊ ፈረስን ስትገመግም ነበር ከዚያ ወድህ ዋርካ በገባው ቁጥር አንዴ ከጥበብ ማዕድህ ሳልቋደስ አልፌ አላውቅም
ከአንተ አንድ የተማርኩትን ልንገርህ ባለሙያ በለይ የጥበብ ባለሙያ ገምጋሚ እያወቀ ካላለፈ በስተቀር ከምንም ውስጥ እንከን ማውጣት ይችላል ብዬ ደመደምኩ ተስፋዬ ገ/አብ ድሮ የጻፋቸውንም ሆነ አሁን እይጻፋቸው ያሉትን መጻሕፍት የምታይበት መነጽርገርሞኝ ነው ተስፋዬ ተልዕኮው ከገባኝ በሀላ ቂም ይዠበታለሁ መሰሪ የወያኔ-ሻቢያ ቅጥረኛ ለመሆኑ አልጠራጠርም ግን እስቲ በዚህ ግምገማ ውስጥ ጹሑፎጭን ገምግም በተለይ ስለ ተስፋዬ የምትናገራቸውን አድናቂህ ነኝ ቀድመህ የቡርቃ ዝምታን አንብበህ ቢሆን ኖሮ የጋዜጤኛው ማስታወሻንም እንደ ባለሞያ ትገመግም ነበር በአጠቃላይ ግምገማህ ፌር አይደለምና አስብበት አንድን ሰው ከወደድከው ቢሳሳትም ጥሩ ነው ከጠላሄው ደግሞ ጥሩ ቢሰራም መንጽሬ አያልፈውም የምትል መሰለኝ:: ለችሎታህ ለዚህ ታላቅ ሙያ አክብሮቴ ግን እንደተጠበቀ ነው የፖለቲካ ወገንተኝነትን ትተህ ሙያው ላይ ብታተኩር ከዚህ የተሻለ ታስተምረን ነበር
ተስፋዬ ግን አሁንም መወገዝ እንዳለበት አስምሬበት ልጨርስ
ዲማሚት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 165
Joined: Fri Mar 05, 2010 11:06 pm

Postby password » Sun Oct 17, 2010 2:17 pm

ሰላም ሙዝ

ጥቃቄዎቼ በሙሉ በብቃት ተመለስውልኛል። አመሰግናለሁ። እውነት ለመናገር ወጥ የሚለው ቃል ከልቦለዶች ጋር ተያይዞ ሲንሳ ብዙ ጊዜ ያጋጥመኛል። ትክክልኛ ትርጉሙን፣ ወይም ምንን ለማመልከት እንደሚጠቅም ግን በደንብ አላውቀውም ነበር። ቃሉ በአረፍተ ነገር ውስጥ ገብቶ ሳነበው ጸሀፊው ምን ለማለት እንደፈለገ እገነዘባለሁ። እንዳልከው አንዳንዴ /ትርጉም/ ያልሆነ ስራን ወጥ ብለው ሲጠሩት፣ ሌለ ጊዜ ደግሞ የአጫጭር ልቦለዶች መድብል አለመሆኑን ለመግለጽ ሲጠቀሙበት አይቻለሁና ነው የጠየቅኩህ።

ድሪቶ የሚለው ቃል ግልጽ ነው። የተስፋዬን /የጋዜጠኛው ማስታወሻ/ ዲሪቶ ነው ማለት ያስቸግራል። ቡርቃን ማለትህ ከሆነ ግን እስማማለሁ። ቡርቃ ስነጽሁፍ ስላልሆነ የፈለከውን ስም ብትሰጠው ግድ የለኝም።

ሶስተኛውን ጥያቄ በተመለከተ የስጠኸውን መለስ ሳነበው በጭንቅለቴ ያቁዋረጠው ሃሰብ፣ ይሄ ሰው ከባድ አንበቢ ነው፣ ደራሲስ ይሆን? የሚል ነበር። ይህን ያስባለኝ በቃላት የፈለከውን ስሜት መገልጽ መቻልህ ነው።

/ሃሳቡን ሳይሆን ሰውየውን ራሱን እገለው ነበር/ የሚለው ሃረግ ሰውየውን ሳይሆን ሃሳቡን፣ በአንድ መስመር አረፍተ ነገር ለመግደል የተጠቀምክበት ረቂቅ አባባል ነበር። የሰራም ይመስለኛል። ተስፋዬ ዋርካ አካበቢ ዝር የማይለው አንዱም በዚህ ምክንያት ሳይሆን ይቀራል።

መልካም ሰንበት።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Sun Mar 18, 2012 8:23 am

የደራሲው ማስታወሻ ላይ የተጻፈ አስተያየት ... ሂስ ... ወዘተ ያየ?

ተስፋዬ..... ከደራሲው ማስታወሻ በሁዋላ የጻፈው መጽሀፍ አለ?

የምታውቁ እባካችሁ .....
Last edited by password on Sat Jan 04, 2014 10:49 am, edited 1 time in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ዲጎኔ » Sun Mar 18, 2012 6:55 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወደዚህ አምድ እንድገባ ያበቃኝ ስለተስፋዬ ቀጣፊነት በይሉል በከፈተው አምድ የተስፋዬን ቀጣፊነት ሳስረዳ ስለቅን ጸሀፊ ስገልጽ ያነሳሁዋቸው ዘመን የቀደሙ ጸሀፊ ዶ/ር አዲስ አለማየሁ ታላቅ ስራ መጠቀሱ ነው::ጸሀፊ ለምን ይጽፋል?ለሚያምንበት ወይም ለበላበት::ዶ/ር አዲስ የሚያምኑት ፊውዳል ኢትዮጲያ እንድትለወጥ የኢትዮጲያን ህዝቦች አብዮት ፋና ወጊ መጽሀፍ አቀረቡ::እኝህን የዘመን እንቁ ከዚህ ወራዳ ተስፋዬ ጋር ማነጻጸር ነውር ነው::
ስነጽሁፍ የህብረተሰቡ ነጸብራቅ ሲሆን ተገቢ ስነጽሁፍ ደግሞ ፍትህ እኩልነት ሰላም እንዲሰፍን ይዘግባል::በዚህ ትንታኔ ያላመነ መብቱ ነው::
ዲጎኔ ሞረቴው ለስውዘር ፍትህ ከጻፉ ዮፍትሄ ንጉሴ አዲስ አለማየሁ አቤ ጉበኛ ወዘተ አምባ ከተስፋዬና መሰሎቹ ሩቅ ማዶ

ሙዝ1 wrote:በመጀመሪያ ደረጃ ስነጽሁፍን በቁሙ አላዉቀዉም እንደዉ ጋደም አድርጌም ለማወቅ የረዳኝ ያኔ የዛሬ 15 አመት አካባቢ ጊዜዉ እንዴት ይነጉዳል ጃል .... የዛሬ 15 አመት አካባቢ ለኑሮ ይጠቅመኝ ይሆን ብዬ ስማር 11ኛ ክፍል እያለሁ የስነጽሁፍ አላባዉያን ሲባል የሰማሁትን መምህሩ ድንገት ፈተና ላይ ቢያመጣዉ መስማቴን ለማረጋገጥ እመልስለት ዘንድ ዳሰስ ዳሰስ ከማድረግ ባለፈ ለትንታኔ የሚሆን ቴክኒኮችን አላዋሀድኳቸዉም .... አሁንም ድረስ ...

የሆነዉ ሁኖ የስነጽሁፍን ትሩፋቶች ግን አጣጥሚያለሁ ወደፊትም አጣጥማለሁ ...

ድሪቶ ስል ... ወጥ አለመሆንን ለመግለጽ ነዉ ... ወጥ ደግሞ እናንተ የሙያዉ ባለቤቶች እንደምትሉት ትርጉም ያልሆነ ለማለት ሳይሆን ... ከጫፍ ጫፍ በአንድ ፍሰት የማይሄድ ለማለት ነዉ ... ድሪቶ ቃሉ መደረትን ለመግለጽ ነዉ እባክህ ደ ን ጠበቅ አድርገህ አንብብልኝ ... መደረት ደግሞ ካለ ቅርጽ አንዱ ባንዱ ላይ ሲነባበር ማለቴ ነዉ ... ሰዉየዉም በሁለቱ መጽሀፍቶች ያሳየኝ ያንን ነዉ ... መዝሙረ ዋልዋ ... ሁለቱ ዝሆኖች ... ምናምን ...

እንዳልኩህ ስነጽሁፍን ባላዉቅም ...መጽሀፍትን ግን አነባለሁ .... ፍቅር እስከ መቃብር ከገጽ 1 ... ወይዘሮ ዉድነሽ በጣሙን ጨምሮ .... የነ ወይዘሮ ጥሩ አይነት .... ከዚያም እነ እቡኝ ኑሬ ... እንዴ እንዴት ወደታሪኩ ፍሰት እየተቀላቀሉ ታላቁን ፍቅር እስከመቃብር ታላቅ ያደረጉበትን ከገጽ 1 እስከ 420 ድረስ ... አንድ ገጽ በተጨመረ ቁጥር መጠኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩም እየዳበረ .... ፍልስፍናዎች እንደ ጥቅምት እሸት እያፈሩ .... በስስትና በምኞት እያባበሉ ... ጭዉዉዉ ... ታዲያ እንዴት ብዬ በየትኛዉ ልቤ ታላቋንና ጥልቋን ስነጽሁፍ ለጻፈ ሁሉ ማዕረግ ስትሆን ልቤ ይቻልና ከስሜት ልንጻ ...
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby password » Sat Jan 04, 2014 11:05 am

የፓልቶኩ Genocide room ዘንድ ተጋብዞ ተስፋዬ ገ/አብ ቃለምልልስ ማድረጉን ሰምቼ ነበር..

ምን ምን አለ? አስኪ አውጉን.....

በተረፈ ያላገባችሁና በእድሜ ከ30 አመት በታች የሆናችሁ... እንዲሁም ነፍሰጡሮች እዚህ ሩም ዳጃፍ እንዳትደርሱ በዚህ አጋጣሚ እመክራለሁ...
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Postby ቢተወደድ » Thu Jan 30, 2014 6:09 pm

ሰሞኑን በተስፋዬ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች: ትክክለኛ ማንነቱን እያወጡት ይገኛሉ:: ጽሁፎቹን አንብበሀቸው ከሆነ; አስተያየትህን ልታካፍለን ትወዳለህን?

password wrote:በተስፋዬ ገ/አብ የተደረሰው ''የጋዜጠኛው ማስታወሻ'' የተሰኘው መጽሀፍ


ተስፋዬ ... ብርሀኑ ያበረታታኝ ነበር ... ይላል ...

ገጽ 75 ላይ ደርሼአለሁ ... ብርሀኑ ላካ ተኪውን አዘጋጅቶልን ኖሯል ...

ጉርም ትረካ .... አስደናቂ ዘገባዎች ... ውብ ስነጽሁፍ

እያነበብኩት ነው ... ስጨርስ እመለሳለሁ ....

PDF የተሰራጨውን የምታነቡ የዚህን ደራሲ ድካም አትዘንጉ

በርድ መጽሀፉን አግኝተሻል ?.
እንደ ልቦለድ ልብ የሚሰቅል ..
እንደ ትሩዝ ግጥሞች ቀልብ የሚስብ ... አንብቢው

ፓስ
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests