ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ብርሃኑ ዘርይሁን አልሞተም/ የጋዜጠኛው ማስታወሻ

Postby password » Thu Feb 26, 2009 2:52 pm

ፓን ሪዚኮ wrote: ፓሱ ማለፊያ ቃል
እኔ የትግሬ ደራሲ አይቼም ስምቼም አላውቅም ያልኩት እውነቴን ነው ...ይሄንን ቃሌን በምን መልኩ ተረድተህኝ ወደ ዘረኝነትና ጥላቻ እንደወሰድከው አልገባኝም ....አሁን አንድ ሰው ተነስቶ የኦሮሞ ቄስ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ብሎ ቢጽፍ ዘረኛ ሊባል ነው ????እስቲ መልሰህ እየው
ከሰላምታ ጋር ፓን


ወዳጀ ፓን ሪዚኮ
የጥበብ ሰዎችን የትግሬ ደረሲ፣ የአማራ ድምጻዊ፣ የኦሮሞ ሰዓሊ ብለን የምንፈልጋቸው ከሆነ እንዴት ልናውቃቸው እንችላለ? ምናልባት የተወለዱበትን ቀዬ መጥራት ይቻል እንድሆ እንጂ እነ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህ፣ እነበአሉ ግርማ፣ እነብርሃኑ ከኢትዮጵያዊነታቸው ሌላ የዘር ማንነታቸውን ብዙ ሰው አያውቅም። ያ መለያ አስፈላጊ አልነበርም። ጥለሁን ገሠሠ በትውልድ ከኦሮሞ ሊሆን ይችላል ግን ከኦሮሞነት በላይ የሚያንጽባርቅ አርቲስት ስለሆነ በዚያ መለያ እሱን ብታንሳው ስለማውቀው ጥላሁን ሳይሆን ስለሌላ የምታወራ ነው የሚመስለኝ። መሀሙድ ከጉረጌነት በላይ ነው። ሀዲስ አለማየሁን የአማራ ደራሲ ብትላቸው፣ አጽማቸው ይፋረድሃል። ደራሲያንን እንደ ዘመኑ ፖለቲከኞች በዘራቸው ፈልገህ አታገኛቸውም። ለዚህ ነው የትግሬ ደራሲ የማታውቀው። የትግሬ ደራሲ የሚባል ነገር ስለሌለ። የአማራም ደራሲ የለም። የኦሮሞም። አለሁ የሚል ከመጣ በበኩሌ ከደራሲ አልቆጥረውም።

እንደኔ ከሆነ እስከናካቴው አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ውራጌ ገለመሌ የሚባል ደራሲ ብቻ ሳይሆን ብሄርም የለም። የማውቀው አማርኛ የሚናገሩ፣ ትግረኛ የሚናገሩ፣ ኦሮምኛ የሚናገሩ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን ነው።

ኢትዮጵያ ትቅደም!
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby CUBBY » Thu Feb 26, 2009 4:29 pm

ሾተል ካላነበብካት እቺንም http://ethioforum.org/wp/archives/840#more-840አንባት ደስ ብላኛለች:: በተረፈ ኤርትራውያን ጥለውን ሄዱብን እንጂ እኛ እኮ የእኛ ናችው እያልን ነበር እስቲ በሰፊው እመጣለው:: ሩጫ ኑሮ ሆኖ ነው:: በተረፈ የፓስን አየኸው ፌብሩዋሪ 11 325ኛ ገጽ ላይ ነበር እኔ በ12 ነው አስተያየቴን የሰጠሁት አሁንም አምንበታለው (በጻፍኩት):: በተረፈ በፖለቲካ አምድ ላይ "እናንተ ፖለቲከኞች" ብለኽ ላልከው መልስ እሰጣለሁኝ መቀመጫ ሳገኝ:: ጽሁፍህ ግን ከአንድ ወገን ሆነብኝ ሾተል? በእነሱስ እስከዛሬ ሳይገነጠሉም ከጠገነጠሉም ያየኸው የለም? እኛ እኮ ኢትዮጵያ የጋራ ኤርትራ የግል የሚለው ይቅር ባይ ነን! ለማንኛውም ወይ ዊኬንድ ወይም አንዱን ቀን መለስ እላለው በደንብ ተዘጋጅቼ:: እስከዛው ሰላም ሁን::
ሾተል wrote:የደርግ ዘመን ልጅ ስለሆንኩና ኢሀዴግ ከመምጣቱ ከትንሽ አመት በፊትና እንደመጣ እድሜዬ ነገሮችን ማየት የሚችልበት የሙጭቅላ እድሜ ባለጸጋ ነበርኩና አይኔን ገልጬ የአገሬን የንግድ ባለሀብት እንዳየሁት የገራጁ የባለትላልቅ ሆቴሎች የባለስቴሽነሪ እንዲሁም መለዋወጫ እቃዎችና የባለጭነት መኪና ባለቤቶች ከኤርትራው ክልል የመጡ ኢትዮዽያዊ ዛሬ ኤርትራዊ እንበለው እና የነዛ ባለሀብቶች ነበሩ::የጎጆ ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች::

እና ከኤርትራ አካባቢ ተወልዶ ያደገ ቤተሰብ እንደምገምተውና እንደተነገረኝ ባህሉ ወደ አውሮፓው ባህል እንዲሁም ወደ ጣልያኑ ባህል ጠጋ ያለ ነው::እሱም እንደተባልኩት ጣልያን የኤርትራ ቅኝ ገዢ ስለነበረች ያንን ባህል ጥላው ሄዳ ነው::ለዛውም አስመራ ያሉ ብዙ ነገሮች በጣልያንኛ የስም አጠራር እንደሚጠሩ ተነግሮኛል::እንኩዋን ለብዙ አመታት በቅኝ የተገዙ አይደለም አርበኛ ኢትዮዽያዊ አባቶቻችንና እናቶቻችን በ 5 ቱ አመት ጣልያን ኢትዮድያ ውስጥ በቆየበት ጊዜ የነበረው ትውልድ ከአማርኛው ጣልያንኛ ይቀናው ነበር::አሁንም ድረስ የድሮ ሰዎች ሲናደዱ እንደጣልያኖች ነው ሲሳደቡ የጣልያንኛ ስድብ ነው::እንግዲህ 5 አመት ነች::ኤርትራ ውስጥ ደጎ ጣልያን በቅኝ ግዛት ኤርትራን ያስተዳደረችው የእትየለሌ አመታቶችን ነው::እና ነገሮችን ላገናኛቸውና ከኤርትራ ክልል የመጡ ኢትዮድያን የነበሩ ወገኖቻችን በመላው የኢትዮድያ ክልል ቀድመው ነቅተው ስለነበር ስራ ስለሚወዱ ንግድ ከፍተው ህዝቡን ሲያገለግሉ ነበር::እንደፖለቲከኞች አባባል ደግሞ የኢትዮዽያን ሀብት ሲመጠምጡ...እኔ ግን አልመጠመጡም እላለሁ....ስለዛ ወደፊት ያለኝን ማንም ሳይነግረኝ ያገናዘብኩትን እላለሁ::

እና እነዚህ ኤርትራዊ የጎጆ ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች በላባቸው ሀብት ስለነበራቸው ከአብዛኛው ኢትዮዽያዊ በተሻለ ይኖሩ ነበር::በሀብታቸው ይፈሩ ይከበሩ ነበር::ይህንን ስል ከውራጌ ክልል የመጣውንም ሰርቶ ባለሀብት የሆነውን ሳያወራ ሳይመቀኝ በላቡ የሚኖረውን ሳልረሳ ነው::ጨዋታዬ ወደ ኤርትራ ስለሆነ ነው::

እና ወደጨዋታየ ልመለስና የገራጁ የባለ ትላልቅ የጭነት መኪናና የባለ ትላልቅ ሆቴሎች ባለቤት ባለሀብቶች ኤርትራዊያኖች ስለነበሩ የሰፈር ስም እራሱ እነሱ ለንግዳቸው ባወጡለት ስም እስከመጠራት የተደረሰበት ጊዜ ነበር::ታድያ የአገሬ ህዝብ ዛሬ እሱ የሚያስበውን ያላሰበና የሚደግፈውን ያልደገፈ ሁሉ ኤርትራዊ ነው ሻኢቢያ ነው እያለ እንደስድብ ሲጠቀምበት የምናየው እንደእኔ እምነት ትላንት ኤርትራዊያኖች በላባቸው ሀብት ሲያገኙ ድሀው የነሱ ሰፈር ልጅ ዛሬ ሻኢቢያ ኤርትራዊ እያለ የሚሳደበው ደጎ እነሱ ሲበሉ ሲጠጡ ሲለብሱ ተመቻችተው ሲኖሩ በንዴት ሲበግን የነበረ ምድረ ዘረ መናጢ ቤተሰቦቹ ስራን በእስራት ሳይሆን በቅናት በምቀኝነት አድገው ያሳደጉት የሰነፍ ልጅ ሰነፍ ነው::ትላንት በደርግ ጊዜ እነዚህን ባለሀብቶች ይመቀኛቸው ነበር::በዛውም ልክ ኑሯቸውን ይመኘው ነበር::አልፎም ሌላ ሰፈር ሄዶ የሌላ ሰፈር ልጆች ቢተዋወቅ በነዚህ ሰዎች ስለሚኮራ የሰፈሩን ስም ለመንገር የነሱን የድርጅት ስም በመጥቀስ ወይም የድርጅቱን ባለቤት ስ በመጥቀስ ነበር...ሴት ሊጠብስ ሲል እንድታከብረውና እሺ እንድትለው ከነዛ ቤተሰቦች አንዱ እንደሆነ አድርጎ በመጎረር ነበር::ሲለውም ደግሞ ሰርቶ እንደነሱ እንደመሆን ሀብታቸውን እየቆጠረ በቅናት ድብን ብሎ ያድር ነበር::

ታድያ በዛን ዘመን ኤርትራዊ ቅብርጥሴ ብሎ እንዳይሳደብ ደርግ ሁሉንም አንድ አድርጎ ስለነበር የሚገዛውና ዘረኝነት ጠላቱ ስለነበር ይቅመው ነበር::ታድያ ዛሬ ዘረኛነት የመሆን ዲኦክራሲ ስለተሰጠ ያንን ቅናት ያንን ሰይተው ሳያገኙት ያደጉበት የሰው ሀብት ወይኔ በማለት የቁጭት ስሜት ወደጥላቻነት ቀይረነው በዘረኝነት ደዌ ሸብበነው ስሜታችንን ቅናታችንን ያ ልጅነታችን ተሰንቅሮ ያደገውን እልክ ዛሬ እናወጣው ጀመርን::

ያ የሰውን ሀብት እያዩ የመቅናት እድገታችን ዛሬ ወደ ጠዪነት ተቀየረብን::የጥላቻ ዲሞክራሲ በገፍ ስለተሰጠን ጥላቻችንን በማይገባበት ቦታ ሁሉ እናንጸባርቀው ጀመርን::ያ ነጸብራቅ ደግሞ ከመረረ ለዛውም መሰረት ከሌለው ዘረኝነት ውስጥ ከተተን::ያ ደግሞ ስድብ ን እንደሆነ ለይነት እስካናውቅ ድረስ ወተፈን::ያ መወተፍ ትንሽነታችንን አሳበቀብን::

እንግዲህ ያ ነው ስለድርሰት ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ስለ እምስና ቁላ ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ስለ አሜሪካ የፕሬዚዳንቶች ርጫ ያወራውን ኤርትራዊ ሻእቢያ ወዘተ እያልን ደረጃና ዝርያ እንመድባለን::በዚህ አጋጣሚ እንደዚሁ ስለንም ያውራ ምን ስለምንም ይቃወም ስለምን ወያኔ ወይም ትግሬ ነው እያልን የምንሳደበውንም አልረሳሁም::ጨዋታው ስለ ኤርትራዊ ወይም ሻእቢያ ስለሆነ ነው እንጂ ስለምንም ተቃውሞ ያሰማ ወያኔ ያልተባለ ማን አል....በርግጥ አሁን ወያኔ ማለት የድርጅት ስም እንጂ ስድብ አይደለም::ስለዚህ ከእኔ ጨምሮ ይሄንን ስድብ አድርገን የተጠቀምን ምን ያህል ፉርሾች እንደሆንን ሳስብ በራሴ አፍራለሁ::ስንት መሳደብ ስችል ይሄ ወያኔ ይሄ ሻእቢያ እያልኩ የተሳደብኩ መስሎኝ የድርጅቱን ስም ከፍ ከፍ ሳደርግ......

እና ልል የፈለግኩት አብሮን ያደገ ቅናትና ምቀኝነት ነው ዛሬ ወደዘረኝነትና ቅናት እንዲሁም ጥላቻ የተቀየረብን ይበልጡን ከኤርትራዊ እህት ወንድ አባት እናቶቻችን ጋር ያለን ጥላቻ ጎልቶ የታየብን::አባቴ ለፍቶ ሰርቶ እነሱ የደረሱበትን የሀብት እርከን መድረስ አቅቶት ከሰፈር የእድሜ እኩዮቹ ጋር አረቄ እየተጋተ በወሬ ጊዜውን አጥፍቶ ግን ተሸክሞ ያገኛትንና ከወሬውና አረቄው የተረፈችውን ገንዘብ ለእናቴ ሰጥቶ ኤርትራዊ ሱቅ ሽሮ ገዝታ እኔን ስላሳደገችኝ ባለሀብቱ ነው ወይስ ወረኛውና ጠጪው አባቴ ነው መወቀስ ያለበት?ወይም መጠላት ያለበት?

ወገን ስለእውነት ብለን እናስብ::አንገመት::
በርግጥ ይሄ ብቻ ሳይሆን ሌላም ሪዝን አለ::እሱ ካስፈለገ ምን ያህል በሆኑ ድርጅቶች ብሬን ወሽድ እንደሆንንና እኛን ለፖለቲካ ጥቅማቸው ሲሉ እየተጫወቱብን እንዳሉ መጥቀስ ካስፈለገ ክብርነታችን ሊል ይችላል::

ለጊዜው መልክቴን ካስተላለፍኩ ተንፈስ ብዬ እውላለሁና ጨረስኩ::

ግን እሰብ ይላል ያገሬ ጎጃሜ::እውነቱን ነው እሰብ::ወይም የገባን ከየቱም የሌለነው እናስብልህ መብቱን ስጠን::

ሾተል........አንድ አለም
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby password » Thu Feb 26, 2009 10:06 pm

CUBBY እንደጻፈው
በተረፈ የፓስን አየኸው ፌብሩዋሪ 11 325ኛ ገጽ ላይ ነበር እኔ በ 12 ነው አስተያየቴን የሰጠሁት አሁንም አምንበታለው (በጻፍኩት )::


CUBBY እንደጻፈው
PostPosted: Thu Feb 12, 2009 10:47 pm
ሾተል
ጸሀፊው ግን አራዳ ነው ከመሀከል የውሸት ዝብርቅርቅ እና መርዙን (እንደድሮው መጽሀፉ ) ካተተ በውሀላ የመስህእረሻው ፓርት ላይ እንደምክርም , ከተሰደደ በውሀላ በተለያየ ግዜ የሰማነውንም , (ከዕራፍ 29 በውሀላ ) እውነትነት ያለውን ነገር ጻፈና ያኔ አንባቢን ወደሱ ጎተተን ::

እስቲ እነፓስ ወርድ (ሳስባቸው የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ) እስኪ ገመግሙት ድረስ የተሰማኝ ይሄ ነው :: በተረፈ ይሄ ሰው ወያኔ ሊገባ ሀያ ቀን ሲቀረው የተቀላቀለው (ያውም እንደሱ ያለ ወታደር ሊሆን የሚፈልግ ሰው ይሆናል ተብሎ ባይታመንም ) ያው ለራዳራቸው (እንዳይሳቅብኝ እንጂ ) ጂቢየስ አስገብቶ ወታደርን ያስጨፈጨ አረመኔ ነው ::


CUBBY ከላይ በጻፍከው መጣጥፍ ምክንያት ትንሽ አለመግባበት ተከስቶ ነበር። ጽሁፍህ በመሰረቱ ፓስዎርድና ደራሲ ተስፋዬ ገ-አብ የቅርብ ዘመድ ናቸው የሚል አንድምታ ስለሰጠ... አጥንት ቆጣሪ ደሞ መጣ...ብዬ እኔ ከታች የሰፈረውን ሀሳብ ሰነዘርኩ።

እዚህ መድርክ ላይ መሳተፍ ከጀመርኩ ጀምሮ ጎጠኝነት በእካል ይሁን በመንፈስ ሲንቀሳቀስ አይቼ አላውቅም። ይሁን እንጂ አራማጆቹ በየስርቻው መፈልፈላቸውን ስለማውቅ አንድ ቀን ዋርካ ስነጽሁፍ መድርከ ላይ ብቅ ይል ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ። ከጎጥኝነት በታች የዘቀጠ አጥንት ቆጣሪ ይነሳል ብዬ ግን በጭራሽ ጠብቄ አላውቅም።ሾተልም በበኩሉ
የዋርካው ሀያሲ ፓስዎርድ በባዶ ስትካካቡበት የነበሩትን ፊልም ተብዬ ጋርቤጆችን ምንጥርጥር አድርጎ ስለገመገመና ላላወቅነው ስላሳወቀ ነው ወይስ ያንን የመከራ ዘመን በብእሩ ቁልጭ አድርጎ ለኛ ላልነበርነው ታሪክ ስለጻፈልን ነው አንዴ እናቱን በድቶ በቃር ይሙትና የጋሽ ለማ ልጅ የሚሉት ሌላ ሩም ውስጥ ፓስን ተናገረው አንተም ወስደህ ከምትጠላው ግን ምንም ካላደረገኽ ደራሲና ጋዜጠኛው ጋር ዘመድ ነው አልከው ::

ሲል የተሰማውን ገለጸ።

cubby እንደጻፈው
በመጀመሪያ ለተከሰተው የአጻጻፌ ስህተት አዝናለው የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ፓስ ዎርድን ያልኩት በጭራሽ ከተስፋዬ (ከደራሲው ) ጋር ሳይሆን :: ለእኔ የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ለማለት ነው ::

እሳቸውንም ዘመድ (ዴ ) ይሆናል ብየ የገመትኩት ከታች በፊርማቸው ላይ ያየሁትን ቪድዮ ስላየሁኝ ከነሱ አንዱ ናቸው ብዬ ስላሰብኩኝ ዘመድ የመሰሉኝ ::

ወደሌላ ስለተተረጎመብኝ ይቅርታ ::


የተከሰተውን የትርጉም ስህተትና ያስከተለውን አለመግባባት እዚህ ላይ የፈታነው ይመስለኛል። በዚህ አጋጣሚ ኩቢ የጠቀስከው ቪዲዬን የለጠፍኩት ባለታሪኩን በስራቸው የማደንቃቸው ሰው ስለሆኑ እንጂ የስጋ ዝምድና ስላለኝ እንዳልሆነ እገልጽልሃለው።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Thu Feb 26, 2009 10:10 pm

CUBBY እንደጻፈው
በተረፈ የፓስን አየኸው ፌብሩዋሪ 11 325ኛ ገጽ ላይ ነበር እኔ በ 12 ነው አስተያየቴን የሰጠሁት አሁንም አምንበታለው (በጻፍኩት )::


CUBBY እንደጻፈው
PostPosted: Thu Feb 12, 2009 10:47 pm
ሾተል
ጸሀፊው ግን አራዳ ነው ከመሀከል የውሸት ዝብርቅርቅ እና መርዙን (እንደድሮው መጽሀፉ ) ካተተ በውሀላ የመስህእረሻው ፓርት ላይ እንደምክርም , ከተሰደደ በውሀላ በተለያየ ግዜ የሰማነውንም , (ከዕራፍ 29 በውሀላ ) እውነትነት ያለውን ነገር ጻፈና ያኔ አንባቢን ወደሱ ጎተተን ::

እስቲ እነፓስ ወርድ (ሳስባቸው የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ) እስኪ ገመግሙት ድረስ የተሰማኝ ይሄ ነው :: በተረፈ ይሄ ሰው ወያኔ ሊገባ ሀያ ቀን ሲቀረው የተቀላቀለው (ያውም እንደሱ ያለ ወታደር ሊሆን የሚፈልግ ሰው ይሆናል ተብሎ ባይታመንም ) ያው ለራዳራቸው (እንዳይሳቅብኝ እንጂ ) ጂቢየስ አስገብቶ ወታደርን ያስጨፈጨ አረመኔ ነው ::


CUBBY ከላይ በጻፍከው መጣጥፍ ምክንያት ትንሽ አለመግባበት ተከስቶ ነበር። ጽሁፍህ በመሰረቱ ፓስዎርድና ደራሲ ተስፋዬ ገ-አብ የቅርብ ዘመድ ናቸው የሚል አንድምታ ስለሰጠ... አጥንት ቆጣሪ ደሞ መጣ...ብዬ እኔ ከታች የሰፈረውን ሀሳብ ሰነዘርኩ።

እዚህ መድርክ ላይ መሳተፍ ከጀመርኩ ጀምሮ ጎጠኝነት በእካል ይሁን በመንፈስ ሲንቀሳቀስ አይቼ አላውቅም። ይሁን እንጂ አራማጆቹ በየስርቻው መፈልፈላቸውን ስለማውቅ አንድ ቀን ዋርካ ስነጽሁፍ መድርከ ላይ ብቅ ይል ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ። ከጎጥኝነት በታች የዘቀጠ አጥንት ቆጣሪ ይነሳል ብዬ ግን በጭራሽ ጠብቄ አላውቅም።ሾተልም በበኩሉ
የዋርካው ሀያሲ ፓስዎርድ በባዶ ስትካካቡበት የነበሩትን ፊልም ተብዬ ጋርቤጆችን ምንጥርጥር አድርጎ ስለገመገመና ላላወቅነው ስላሳወቀ ነው ወይስ ያንን የመከራ ዘመን በብእሩ ቁልጭ አድርጎ ለኛ ላልነበርነው ታሪክ ስለጻፈልን ነው አንዴ እናቱን በድቶ በቃር ይሙትና የጋሽ ለማ ልጅ የሚሉት ሌላ ሩም ውስጥ ፓስን ተናገረው አንተም ወስደህ ከምትጠላው ግን ምንም ካላደረገኽ ደራሲና ጋዜጠኛው ጋር ዘመድ ነው አልከው ::

ሲል የተሰማውን ገለጸ።

cubby እንደጻፈው
በመጀመሪያ ለተከሰተው የአጻጻፌ ስህተት አዝናለው የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ፓስ ዎርድን ያልኩት በጭራሽ ከተስፋዬ (ከደራሲው ) ጋር ሳይሆን :: ለእኔ የቅርብ ዘመድ መሰሉኝ ለማለት ነው ::

እሳቸውንም ዘመድ (ዴ ) ይሆናል ብየ የገመትኩት ከታች በፊርማቸው ላይ ያየሁትን ቪድዮ ስላየሁኝ ከነሱ አንዱ ናቸው ብዬ ስላሰብኩኝ ዘመድ የመሰሉኝ ::

ወደሌላ ስለተተረጎመብኝ ይቅርታ ::


የተከሰተውን የትርጉም ስህተትና ያስከተለውን አለመግባባት እዚህ ላይ የፈታነው ይመስለኛል። በዚህ አጋጣሚ ኩቢ የጠቀስከው ቪዲዬን የለጠፍኩት ባለታሪኩን በስራቸው የማደንቃቸው ሰው ስለሆኑ እንጂ የስጋ ዝምድና ስላለኝ እንዳልሆነ እገልጽልሃለው።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:25 pm

ከዚህ በፊት ያገራችንን ፖለቲከኞችና ፖለቲካችንን ስለማላውቅና ስለማልከታተል ነው መሰለኝ ማንንምና ምኑንም አላውቅም ነበር ::በዚች ሁለት ወር ግን ፖለቲካውንና ፖለቲከኞችን መከታተል ስጀምር ተቆጥሮ የማያልቅ ብዙ ጉድፍ አየሁበት ::ለካስ ከፖለቲከኞችም የሰውን ልጅ አስተሳሰብ ማጥናት ይቻላል ?እስቲ ከትዝብቶቼ ውስጥ ዛሬ ደግሞ አንዱን ልበል ::

መቸም ጋዜጠኛው ተስፋዬ ሰሞኑን መጽሀፉን ካሳተመ በሁዋላ ስንት የምድር ጉዶች እራሳቸውን እያጋለጡ እንደሆነና ምን ያህል ዘረኝነትና ጥላቻ እንዳለባቸው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ እያወጡት እንዳሉ ዳር ሆነን የምንታዘብ ሰዎች ሳንገነዘብ አልቀረንም ::

ይበልጥ ጸሀፊው ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው የተናገራቸውና የጻፋቸው ተጠንቁለው እየወጡ ተራ የሆነ ሂስ ሲሰጥባቸው እያየን ነው ::ይበልጥ ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው ኤርትራን በተመለከተ እሰይ አሁን ጊዜው ነውና ዘረኝነቴንና ጥላቻዬን ልተንፍስ በሚል ::ታድያ ክብርነታችን ትላንት ከጻፍኩት ጋር የሚያያዝ የትላንትና የዛሬው አስተሳሰባችን ምን ያህል እንደተራራቀ እኛነታችንን አስታውሰው ዘንድ በሚቀጥለው ገጽ ልምጣ ::

መልካም ንባብ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:27 pm

ከዛሬ 18 አመት በፊት ለ 30 ምናምን አመታት ሻእቢያና ወያኔ ከደርግና ከሀይለስላሴ መንግስት ጋር ሲዋጉ እንደነበረና በመጨረሻ ድሉ ወደነሱ አዘንብሎ ኢትዮዽያን ለአላማቸው ማሳኪያ ሲሉ እንደተቆጣጠሩዋትና ኤርትራን ገንጥለው እንደወሰዱዋት ሁላችንም የምናውቀው ነው ::በአንድነት የሚያምነው ሁሉ በኤርትራ መገንጠል ጮኸ ::ልቡ ደማ ...ተቃጠለ ...አረረ .....ክብርነታችንም ጭምር ::
ያንን ተቃውሞ ያገሬ ተማሪ አደባባይ ወጣ ::ጥይትና ሞቱ አሸነፈው :ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ አገራችን በመጣ ሰአት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያደረጉትን ሰላማዊ ሰልፍና የከፈሉትን መስዋእትነት ያስታውሱ )...

ከዛ ኤርትራ ውስጥ ምርጫ ተካሄደ ::የይስሙላ ምርጫ ::ወደ ኢትዮዽያ ተቀላቅሎ መኖር ወይስ መገንጠል ...ግን እንዲህ በሚል መልክ ..."ነጻነት " ወይስ "ባርነት "...

ከዛ እንዳሁኑ የዘርና ጥላቻ ደዌ አልመረዘንም ነበርና እንዲሁም ኤርትራዊያኖችን እንደራሳችን አድርገን እንወዳቸው ነበርና እንዲሁም አንድ አካል አንድ አምሳል መሆናቸውን እናምን ነበርና ሁላችንም በተሰጣቸው "ነጻነት "ወይስ "ባርነት " የሚለውን እድል አይተን በጣም አዘንን ::በአምባገነኖቹ ሻእቢያና ወያኔ መሰሪነት ተቆጣን ::ተራገምን ::ጠላናቸው ::ለኤርትራ ህዝብም አዘንንለት ::ያለፍላጎታቸው ይገነጠሉ ዘንድ አስመረጧቸው አልንና ልባችንን አስለቀስነው ::ኤርትራ የኛ ነበረች ገነጠሉብን ቢሆንም በመገንጠሏ ስለማናምን የኢትዮዽያ ካርታ በግድ እስከገነጠሏት ኤርትራ ድረስ ነው ብለን ለብዙ አመታት የድሮዋን የኢትዮዽያ ካርታ ቤታችን ግርግዳ ላይ እንደሰቀልን በቲሸርታችን አትመን እንደለበስን በተለያዩ የድርጅታችን ሎጎ ላይ እንደተጠቀምን ለብዙ አመት ቆየን ::ኤርትራዊያን እህትና ወንድሞቻን እናትና አባቶቻችን በሻእቢያ የአምባገነን አስተዳደር ተገደው እንጂ በኢትዮዽያዊነታቸው ያምናሉ ብለን ተከራከርንላቸው ::

ታድያ እስከዚህ ድረስ እውነት አልነበረም እንዴ ሰነቻው ወገኔ

ከዛ በሁዋላስ ምን ተፈጠረ ?

መጣሁ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:29 pm

ከዛማ ይህ በእንዲህ እየተንገዋለለ እያለ የኤርትሮ ኢትዮዽያ ጦርነት ፈነዳ ::ከዛ አሁንም በአንድነት እናምን ነበርና ይህ ኢትዮድያንና ኤርትራን አይመለከትም ይሄ የወያኔና የሻእቢያ ይበልጥ የሀማሴንና የአጋሜ ወዘተ ጦርነት ነው ...ሁለቱ ከድሮ ጀምሮ ስለማይዋደዱና አንዱ አንዱን ስለሚንቅ ያንን ለመበቀል የከፈቱት ጦርነት ነው ....እንደገና ደግሞ ሻእቢያና ወያኔ አብረው የሰረቁዋትን ኢትዮዽያ ሊከፋፈሉ ሲሉ ስላልተስማሙ የጀመሩት ጦርነት ነው ወዘተ እየተባለ ለአንድነት ሶሊዳሪቲያችንን በያለንበት አሰማን ::እንደገና ደግሞ ድንበራችን ሸንበቆ ዛላምበሳ ወይም ባድሜ ሳይሆን ከመረብ ወዲያ ያለችው የኤርትራ ድንበር ነውና እኛ ስለዚህ ምንም አያገባንም አልንና ኤርትራዊ በሻእቢያ አገዛዝ ስር እየተረገጡ ያሉትን ምስኪኖች እንደራሳችን አድርገን በመውደድ ምንም ጦርነት ቢካሄድም የኛ ናቸው አልን ::

ይህ በእንደዚህ እንዳለ የመጀመርያው ጦርነት በመለስ ወገን ብዙ ዝግጅት ያልተደረገበት ስለነበር ብዙ ጦኑን ወይም ወገናችንን አጣን ::በዛ በሸቅን ::እንዴት ኤርትራን የሚያህል አገር ይበልጥ ወደባችንን አሰብንና ምጽዋን ሰጥቶብን ሳለ በባድሜ ዛላንበሳ ትንሽ መሬት ህዝባችንን ያስፈጃል ብለን የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነዛን ....ጸሀፊዎች ስለዛ ብተቃውመው ጻፉ ...የፖለቲካ ተንታኞች ነገርን እየመነዘሩ ተነተኑ ....ወያኔንና ሻኢቢያን ምን እንዳጣላቸው ዘርዝረው ሚስጥር ያሉትን ለኛ የሰውን እውቀት መጥጠን ለማንጠግበው ወለል አድርገው አሳወቁን ::እኛም እያንዳንዱዋ ነገር ተገለጸችልን ::

እስከዚህ ድረስ እውነት አይደለም እንዴ የተምታታብህ ወገኔ

መጣሁ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:31 pm

ከዛ የመለስ መንግስት ለመልሶ ማጥቃት ዘመጃ በከፍተኛ ህዝቡን ቀሰቀሰ ....የእምዬ ኢትዮድያ ምርጥ ልጆችን ከናታቸው ጉያ በፕሮፓጋንዳ በአስከር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን መለመለ ::በኢሳያስ ወገንም እንደዚሁ በግድ በውድ ወደ ሳዋ ወሰደና አስታጠቀ ::በመለስ ወገን ወጣቱ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ አጥቶ የበዪ ተመልካች ሆኖ የሴት ቂጥ እያየና የሀብታምን መኪና ሆነ ቤት እያዳነቀ እያወራና የሀብታሙን ሀብት በስማ በለው ይሄንን ያህል ብር አለው የሚነዳት መኪና በአለም ላይ 20 ብቻ ናቸው የተሰሩት ከአፍሪካ እሱ ብቻ ነው ያለው ....እንትና ጋር የተሰራው ፎቅ በአለም ሶስተኛ ሲሆን እሱም ኒውዮርክ ያለው እንትን ህንጻና ግብጽ ካይሮ ያለው ህንጻ ብቻ ነው የሚበልጠው ....ሸራተን በአለም አንደኛ ነው ...አላሙዲን እንትናን በድቶ ይሄንን ያህል ሚሊየን አጋጫት ወዘተ የሚሉትን የፈጠራ ወሬ እብጫት ሲያወራ የችግር ኑሮ በወጣትነቱ አሰልችቶት ስለነበር ክፍት የስራ ቦታ ወታደርነት መሆኑን አውቆና እራብ ጊዜ ስለማይሰጥ አንድ ቀንም እድሜ ስለሆነች በልቶ ለማደር እንዲሁም በተነዛለት የህውሀት ፕሮፓጋንዳ ተመርዞ አገሩ እስከባድሜና ዛላንበሳ ድረስ እንደሆነች ተሰብኮ ችግሩን ሊያላቅቅና ያገሩን ድንበር ሊያስከብር መስሎት ወደ እሳት ከባድሜ መልስ ወደመለስ ....እንደገና አስመራን ከያዝን በሁዋላ ስለ አሰብና ምጽዋ እንደራደራለን ብሎ በካቻማሌ ታጭቆ ለለብ ለብ ስልጠና ወደ ማሰልጠኛ ጣብያዎች የእምዬ ኢትዮዽያን ባንዲራ እያውለበለበ ጎረፈ ::

እስከዚህስ ድረስ እውነት አይደለም ማይገባህ ወገኔ

መጣሁ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:33 pm

ከዛማ ጦርነቱ በድጋሚ አንሰራራና ከዛኛው ወገን በግድ በገባና ወዶ ገብ ኗሪ ሻእቢያ ከዚህ ወገን ደግሞ ስራ ፈልጎ ወታደር የሆነና የናት አገር ፍቅር ናላውን ያነወዘው እንዲሁም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ህሊናውን እንዳያመዛዝን ያደረገው ጦርነት ገጠሙና ይሄኛው ወገን ወይም ያኛው ወገን አሸነፈ ገደለ ድል ተቀዳጀ ለማለት የሚያሳፍር አብሮ ተዋልዶ በደም ባህልና ሀይማኖት ተሳስሮ የቆየ ወንዳማች ተፋጅቶ አለም ሳቀበት ::ሁዋላ ቀርነቱን አረጋገጠለት ::አይ ካፍሪካ የሰለጠነ ነገር አይገኝም ተባለለት ::ለጥቂቶች አንዱ አንዱን በመግደሉ ድል ሲሆን ለአብላጫው በአንድነት ካልሆነም በጥሩ ጎረቤትነት እንደክብርነታችን ለሚያምነው ደግሞ በሁለቱም ወገን ባላስፈላጊ ጦርነት ለሞቱት ሰማእታት አለቀስን ...ፍቅራችን አካላችን ስለነበሩ ሲሞቱብን እህትና ወንድም እንደሞተብን መርዶ ተቀመጥን ::በአፍሪካዊነታችን አፈርን ::አንገታችንን ደፍተን መሄድ ጀመርን ::የፖለቲካ ፕላናቸውን ያሳኩ ደግሞ ባንዱ ወገን በተቀዳጀው ድል የደስታ ጮቤ አንድ ቀን ሳይደላው ለናት አገሩ የተዋጋ መስሎት በጥይት ሰራ አካላቱ ተነድሎ ተከፋፍሎ በሞተው ምርጥ ወጣት ደምም ላይ ቆሞ ደስታውን አሰማ ....በፈሰሰው ደሙ የአሸናፊነት እርካታውን ከጥሙ ረካ ::እናት በሁለቱም ወገን ልጅዋን ስስትዋን ስላጣች የደ እምባ አነባች ::አንዱ ሲሄድ የተሻለው መጥቶ ልጄን ከወታደርነት ለብሄራዊ ውትድርና ተመንጭቆ ከመሄድ ከስጋቴ ዳንኩ ብላ አረፍ ልትል ስትል የባሰ መጥቶ ድሮም በድሮዎቹ ልጆችዋን አጥታ ነበር አሁንም ይሄኛው ያጣሁትን ልጅ ይተካልኛል ብላ በጉጉት አሁን አደገልኝ አሁን ይጦረኛል ስትል ልጇን ወዳጅዋን ጧሪዋን ከሁለቱም ወገን አጣች ::

እስከዚህስ እውነት አይደለም እንዴ አንተ የማፍርብህ ወገኔ

መጣሁ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 27, 2009 2:35 pm

እንዴ ...14 ሰአት ሊሆን ነው ::ይሄ ሳንጠቀም ተጠቅማችሁዋልና ክፈሉ እያሉ የሚልኩልን ቢል ክብርነታችንን ሊያቀውሰው

እና ቢሮ ሳይዘጋ በየቢሮው ሄደን አንዴ አምሰን ቁም ስቅላቸውን አሳይተናቸው እንምጣ ::በቀላሉ መክፈልማ የለም ::አርብ ስለሆነ በጊዜ ይዘጋሉና ከመዝጋታቸው በፊት እንድረስና እንከራከር ::ከዛ ያው መልሳቸው ውይ ይቅርታ ስለሆነ ያላግባብ ሊሄዱ የታለመባቸውን ኦይሯችንን አስመልሰን ከች ነው ::ወይም እንደፈረደብን ከፍለን መምጣት ::የሚገርም እኮ ነው ..በዚህ ሰጥተው በዛ እጥፉን የሚቀበሉበት አገር ::ሲያታልሉ ሀይለኞች ናቸው ::ኦስትሪያ ብቻ ነው ወይስ ሌላም አገር እንደዚህ ነው ?የከፈልነውን ቢል መልሰው ይልኩትና በጊዜው ካልከፈልን ወይም ካልተከራከርን ዴድ ላይኑ ካለፈ እጥፍ ሆኖ ይመጣል ::ቡዋ አለ መለስ

እና የጀመርነውን ወደ በሁዋላ እንደሙዳችን እንጽፍላችሁዋለን ::

እስከዛው መልካም አርብ ይሁንላችሁ

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby Kaleb* » Fri Feb 27, 2009 4:50 pm

ሾተል wrote:
መቸም ጋዜጠኛው ተስፋዬ ሰሞኑን መጽሀፉን ካሳተመ በሁዋላ ስንት የምድር ጉዶች እራሳቸውን እያጋለጡ እንደሆነና ምን ያህል ዘረኝነትና ጥላቻ እንዳለባቸው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ እያወጡት እንዳሉ ዳር ሆነን የምንታዘብ ሰዎች ሳንገነዘብ አልቀረንም ::

ይበልጥ ጸሀፊው ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው የተናገራቸውና የጻፋቸው ተጠንቁለው እየወጡ ተራ የሆነ ሂስ ሲሰጥባቸው እያየን ነው ::ይበልጥ ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው ኤርትራን በተመለከተ እሰይ አሁን ጊዜው ነውና ዘረኝነቴንና ጥላቻዬን ልተንፍስ በሚል
ሾተል


ሾተል ስሞኑን የምትጽፋቸውን ነገር እይታህን በተለይ ደግሞ ሰለ ጋዜጠኛው ተስፋዬ እንዴት እንደወደደኩልህና ምን ያህል ንጹህ ከዘረኝነት የጸዳ ህሊና እንዳለህ ልገልጽልህ ነው አመጣጤ:
ከመጣው አይቀር እግረ መንገዴን ሰለ ጋዜጠኛው ተስፋዬ ትንሽ ምለው:- ተስፋዬ የአዲሱ ትውልድ ተምሳሌ ሊሆን የሚችል ከማንኛችንም የተሻለ ከዘረኝነት አአምሮው የጸዳ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው:: ምንም መሲሪ ተንኮል አለበት ብዬ አላምንም (ያህንን ስል ደሞ አውቃለው ስልጣን ቢኖራቹ ያህን በማለቴ ብቻ ኢትዮጵያዊነቴን ለመግፈፍ ምትሞክሩ ልትኖሩ እንደምትችሉ :( )
Kaleb*
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Tue Oct 25, 2005 2:42 pm
Location: ethiopia

Postby ሀሪከን2 » Sat Feb 28, 2009 1:06 am

Kaleb* wrote:
ሾተል wrote:
መቸም ጋዜጠኛው ተስፋዬ ሰሞኑን መጽሀፉን ካሳተመ በሁዋላ ስንት የምድር ጉዶች እራሳቸውን እያጋለጡ እንደሆነና ምን ያህል ዘረኝነትና ጥላቻ እንዳለባቸው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ እያወጡት እንዳሉ ዳር ሆነን የምንታዘብ ሰዎች ሳንገነዘብ አልቀረንም ::

ይበልጥ ጸሀፊው ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው የተናገራቸውና የጻፋቸው ተጠንቁለው እየወጡ ተራ የሆነ ሂስ ሲሰጥባቸው እያየን ነው ::ይበልጥ ኤርትራዊ ዝርያ ስላለው ኤርትራን በተመለከተ እሰይ አሁን ጊዜው ነውና ዘረኝነቴንና ጥላቻዬን ልተንፍስ በሚል
ሾተል


ሾተል ስሞኑን የምትጽፋቸውን ነገር እይታህን በተለይ ደግሞ ሰለ ጋዜጠኛው ተስፋዬ እንዴት እንደወደደኩልህና ምን ያህል ንጹህ ከዘረኝነት የጸዳ ህሊና እንዳለህ ልገልጽልህ ነው አመጣጤ:
ከመጣው አይቀር እግረ መንገዴን ሰለ ጋዜጠኛው ተስፋዬ ትንሽ ምለው:- ተስፋዬ የአዲሱ ትውልድ ተምሳሌ ሊሆን የሚችል ከማንኛችንም የተሻለ ከዘረኝነት አአምሮው የጸዳ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው:: ምንም መሲሪ ተንኮል አለበት ብዬ አላምንም (ያህንን ስል ደሞ አውቃለው ስልጣን ቢኖራቹ ያህን በማለቴ ብቻ ኢትዮጵያዊነቴን ለመግፈፍ ምትሞክሩ ልትኖሩ እንደምትችሉ :( )


እኔ ደግሜ እላለሁ ሀገራችን ኢትዮጵያን የሚያስፈልጔት እንደ ሾትል የሚያስቡ ፓለቲከኞች ናቸው

እንደ እነ መረዋ እና ጉግል አይነት ሀገርን ከፓለቲካ ድርጅት በላይ ማየት የማይችሉ የአምሮ ድኩማኖች እና ድሆች ከፓለቲካ ትግሉ ካልወጡ ወያኔ ቢወድቅም ከወያኔ የተሻለ ስርአት እንደማይመጣ ለመገመት ነብይ መሆን አያሻም :)

ሀገራችን መቸ ይሆን ከቶ ከበቀል ከጥላቻ እንዲሁም ከዘረኝነት የጸዳ አምሮ የታደሉ ፓለቲከኞች የሚመሯት :?
ምናልባት አሮጌው ትውልድ ሄዶ አዲሱ ትውልድ የፓለቲካ ትግሉን ሲረከብ ያኔ ከጥላቻ እና ከበቀል የጸዳ ሚዛናው አምሮ ያላቸው ሀገራችውን ከፓለቲካ ድርጅታቸው በላይ የሚወዱ እና የሚያዩ ራእይ ያላቸው ፓለቲከኞች እናይ ይሆናል
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby CUBBY » Sat Feb 28, 2009 6:35 pm

ሰላም ፓስ ወርድ አመሰግናለው:: አሁንም አንተን(እርስዎን) የገመትኩት የነበረው ከሞቱት ዝምድና ይኖርዎታል ሳይሆን በዛ ፊልም ላይ ኢንተርቪ ከተደረጉት ውስጥ አንዱ እርስዎ ስለመሰለኝ ነው: ያየመሰሉኝ ሰው ደግሞ ለእኔ ለኔ ዝምድና ስላላቸው ነበር:: ለማንኛውም እዚሁ ላይ ይቁም ስለተረዱት አመሰግናለው::
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Re: ተስፋዬ ገ/አብ

Postby CUBBY » Sat Feb 28, 2009 6:39 pm

yekolo wrote:I've read his book, የቡርቃ ዝምታ, and I can tell you that it was pure garbage. Not only interms of content but also literary style.

ለሎቹንም መጣጥፎቹን አንበቤያለሁ... ከብርሀኑ ዘሪሁን ጋር ማወዳደር is a huge exaggeration if not a crime.


ትክክል እኔም እንዳንተ ነው የምለው::

እስቲ አንዴ ከበዓሉ ግርማ ልብ ጋር ከመቃብር ቃለመጠየቅ ያረኩትን ላቅርብ::

ቃለ መጠየቅ ከበዓሉ ግርማ ልብ ጋር ከመቃብር::
እኔ:- ሰላም ጤና ይስጥልኝ አቶ በዓሉ ግርማ ጥሪዬን አክብረው ስለተገኙልኝ ከልብ አመሰግናለው::

በዓሉ ግርማ:-እኔም ከልብ አመሰግናለው

እኔ:- በመጀመሪያ በዓሉ ግርማ ማነው?

በዓሉ ግርማ:- በዓሉ ግርማ ማለት እኔ ነኝ, እኔ ማለት በዓሉ ነኝ::

እኔ:- ቅቅቅ አይ ያንማ እኔ አውቃለው: እንዴው የት ተወለዱ ስለቤተሰብዎ አመጣት ማለቴ ነው ለአንባቢም ለማያቅዎት እንዲያውቅዎት ለማረግ ነው::

በዓሉ ግርማ:- ወደ እዛ ዘር ቆጠራችው የምትወስደኝ ከሆነ ከአሁኑ ብናቆም እመርጣለው: ምክንያቱም እኔ በኖርኩበት ዘመን ኢትዮጵያዊነቴን እንጂ ዘሬን የሚባልመት ዘመን ስለነበርረባክህ አደራ እዛ ውስጥ እንዳታርመጠምጠኝ::

እኔ:- ዋው ኧረ ቤናትዎት እኔ በዛ ወስጄው አይደለም ግድ የለዎትም ብዙ ሰው ያቅዎታል ያን እንዳይባሉ እጥራለው:: አሁን ይንገሩኝ በዓሉ ግርማ ማለት ማነው?

በዓሉ ግርማ:- የተወለድኩት ከእናቴ ከው/ሮ ያዳኒ ዳባ አቦ ሚያዚያ 16 ቀን 1928 ዓ.ም ሱጴ ነገዎ ቦሮ የገጠር ከተማ ውስጥ ተወለድኩኝ::...

እኔ:- እምም በኦሮሚያ መጽሃፍ የተነሳ ብዙ ሰው ትውልድዎ ከኤርትራ ይመስለው ነበር:...

በዓሉ ግርማ:- አታቁዋርጠኝ ያም ቢሆን እኮ አገሬ ነው! ወይም ነበር! ...

እኔ:- እሺ እሺ ይቅርታ ያርጉልኝ ስለ አባትዎ አልነገሩኝም::

በዓሉ ግርማ:- አዎን ያው እናዳልኩህ ከናቴ ከላይ እንደተጠቀሰውና ከአባቴ ከህንዳዊው ነጋዴ ሚስተር ባቡና ነበር የተወለድኩት:: ሱጴ የምትገኘው በቀድሞው ኢሊባቡር ጠቅላይ ግዛት መቱ አውራጃ ከመቱ ከተማ ደቡባዊ ምስራቅ በግምት 35 ኪ.ሜ ርቃ የምትገኝ የገጠር ከተማ ናት::

እኔ:- አሃ! አቶ ግርማ አባትዎት አይደሉም ማለት ነዋ ታዲያ?

በዓሉ ግርማ:- አዎን ወላጅ አባቴ አይደሉም የስጋ ዝምድናም የለኝም ያሳደጉኝ ናቸው:: እኔ ለትምህርት ስደርስ በትውልድ መንደሬ በሱጴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1 እስከ 4 ከተማርኩኝ በውሃላ አሳዳጊ አባቴ አቶ ግርማ እኔ በትምህርት አቀባበሌ በጣም ጠንካራ ሆኜ ስለተገኘሁኝ ወደ አዲስ አበባ በማምጣት በቀድሞው ዘነበ ወርቅ ት/ቤት በአዳሪ እንድማር አደረጉ:: ከ5 እስከ 8ኛም በአጥጋቢ ውጤት አጠናቀቅሁኝ:: ከዚያም ጎበዝ ተማሪዎችን ብቻ ወደ ሚቀበለው ጄነራል ዊንጌት ግብቼ ከ9 እስከ 12 ትምህርቴን በአጥጋቢ ሁኔታ በሚገባ አጠናቀኩኝ ከዛም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲት ተቀበሉኝ እዛም በአርት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ቀጥሎም ወደ አሜሪካን በመሄድ በጋዜጠኛነት የማስተሬት ዲግሬዬን አግኝቻለው::

እኔ:- ከዛስ ወደ ትውልድዎ ወዲያው ነው የተመለሱት? ስራዎትስ?

በዓሉ ግርማ:- አዎን ወደትውልድ አገሬ ተመልሼ በቀድሞው ማስታወቂያና መርሃ ብሔር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተመድቤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ, የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ, ቤንግሊዘኛ ቋንቋ ይዘጋጅ የነበረውን ሐዲስ የተሰኘች መጽሄት ዋና አዘጋጅ በመሆንለጋዜጠና መጽሄት ብዙ ስራ ሰርቻለው::

እኔ:- (ለአንባቢ:- በአሉ ግርማ ቁመናና የግርማ ሞገስ ያላቸው ነበር ከላይ ነግረውኝ ያላሰፈርኩት ወይም የረሳሁት ነገር ቢኖር: አቶ ላዓሉ ግርማ ወላጅ አባታቸውን አያቁም ነበር:: ገና በልጅነታቸው ሕንዳዊው አባቱ ወደ ሀገሩ ህንድ(ቦንቤ) ተመልሱዋ)::

እኔ:- ሌላስ የሰሩት ? መቼስ ነው የድርሰት ስራ የጀመሩት?

በዓሉ ግርማ:- መጀመሪያ ድርሰቱን ላስቀድም:: ድርሰት የጀመርኩት በ1960ዎቹ ዓ.ም ነበር:: ከአድማስ ባሻገር, የህሊና ደወል, ሐዲስ, የቀይ ኮከብ ጥሪ, በመጨረሻም ኦሮማይ የተሰኘ መጽሃፎች ለአንባቢ አበርክቻለው ወይም ጽፌያለው::
እኔ:- (ለአንባቢ:- ከአቶ በዓሉ ግርማ ጋር ያለኝን ቃለ መጠየቅ እቀጥላለው:: ከጥያቄዎቹም ላቀርብላቸው የተዘጋጀሁት የአሁኑን የኢትዮጵያን ፖለቲካም ሆነ የወደፊት እጣ ፈንታዋ ምንድን እንደሚሆን ግመታቸውን, የአለም ለውጥ በአፍሪካ ላይ እያመጣ ስላለው, የዘር ልዩነት, ስለኤርትራና እና ስለኤርትራ ኢትዮጵያዊነት, እንዲሁም ከደርግ ጋር ብዙ በቅርበት ያገለገሉ (በተለይ ለመንግስቱ ሃይለማሪያም የቅርብ ታማኝ በነበሩበት ግዜ ያዩትንና የገጠማቸውን:: እንዲሁም በተለይ ሰሞኑን ስሙ እየተነሳ ስላለው ስለተስፋዬ ገብረዓብ ያላቸው አስተያየት ከሳቸው ጋር መመሳሰል እና አለመመሳሰል, ሌላም ሌላም እንደተመቼኝ ከልባቸው ጋር ከመቃብር ያቀረብኩላቸውን አቀርባለው, ስለወደፊቱ ምርጫ ማን እንደሚያሸንፍ የመሳሰሉትን አቀርባለው ከግዜ ጋር::) ደህና ቆዩኝ
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby CUBBY » Sat Feb 28, 2009 10:55 pm

ድጋሚ መጣው፦

ኤኔ፦ ለአንባቢዎች [ አቶ በዓሉ ግርማ በ1966 ዓ.ም በተነሳው አብዮት በሙሉ ድምጽ ደጋፊ ነበሩ። ከዛም የጦር ሀይሎች ደርግ አቁዋቁመው ቀዳሚው ሀይለ ስላሴን ከስልጣን አስወግደው ሥልጣን በያዙበት የደርጉ አንደኛ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት ኮለኔል መንግስቱ (በወቅቱ ሻለቃ) ከፍተኛ ቀረቤታ የነበረው በዓሉ፣ ልርሳቸው ከፍተኛ አማካሪና ፖለቲካዊ መግለጫዎችን የሚያዘጋጁላቸው ነበር። እና አንባቢዎች በዓሉ ግርማ በጋዜጠኝነትም ብቻ ሳይሆን ፖለቲካ ውስጥም ተሳትፉዋቸው ብዙ ነው። በኢማልህድም ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ለመንግስቱ ያደረጉ ሰውም ናቸው። ላለማሰልቸት ቀጥታ ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ብቻ ላነጋግራቸው ፍቀዱልኝ ግን እያስታከኩኝም ስለ ድሮውም እጠይቅ ይሆናል። አሁን ወደ እሳቸው]

እኔ፦ በድጋሚ ሰላምታ አቀርባለው።
በዓሉ ግርማ፦ ሰላም ብያለው ልጄ

እስቲ ወደ ለላው ከመግባቴ በፊት ቀደም ብሎ ያልተመለሰልኝ ያልጠየኩትም ነገር። ስንት ልጆች አልዎት?

በዓሉ ግርማ፦ ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ልጅ አሉኝ።

እኔ፦ እስቲ በአጠቃላይ አጠር ባለ ሁኔታ ስለእርስዎ ተግባራዊነት ወይም ስራዎትን አጠቃለው ይዝጉልኝና ወደ ሌላ ወቅታዊ ጉዳይ እንመለስ?

በዓሉ ግርማ፦ ያው በብዛት ከላይ ገልጬዋለው ከ፩፱፮፱ (1969) ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስተር ማዕረግ የማስታወቂያ መርሐ ብሔር ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ያቅሜን ሰርቻለው፤ ለሚኒስቴሩም መስሪያ ቤትም መሻሻል አብይ ሚና ተጫውቻለው ብየ አምናለው። በወቅቱም በሚኒስተሩ መስሪያ ቤት ሰራተኞችም በፍቅር ተወዳጅ በመሆን እንደጸባያቸው በመቻቻል ስርቻለው።

የኤርትራ የቀይ ኮከብ ሁለገብ ዘመቻ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሀደ ግዜ ከጥር ወር እስከ ሰኔ ወር ፩፱፯፬ ከመንግሥቱ ጋር በመሆን እኔ እና አቶ ሽመልስ ማዘንጊያ ከተባሉ ጋር አብረን በመሆን በሻቢያ ላይ ይሰራ የነበረውን ፕሮፖጋንዳም ከፍተኛ ስራ ሰርተናል።

ያው እንደምታውቀው ሌእኔ መቅሰፍት የሆነውን ኦሮማይ ትርጉሙም በጣሊያኒኛ ቋንቋ አለቀ፣አበቃ ማለት ነው። ያ ጽሁፍ ያው በኤርትራ ክፍለ ሀገር የቀይ ኮከብ ዘመቻ ውስጣዊና ውጫዊ ወይም ፖለቲካዊና ወታደራዊ ዘመቻውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ገጸ ባህሪን በተመረኮዘና እያንዳንዱ የዘመቻው ባለስልጣኖችን የግል ባህሪ ያለምንም ትጽኖ ያሳየ ጽሁፍ ጽፊያለው። በወቅቱ ይህ መጽሃፍ ኩራዝ አሳታሚ ነበር ያሳተመው። የታተመውም ቀን ነሃሴ ወር ፩፱፯፭ ዓ.ም ነበር። ይህ መጽሃፍ በታተመ 10ኛ ቀን ከምጽሃፍ መደብርና ከሰዎች እጅ እየተለቀመ ተሰበሰበ። እኔም በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ ከስራ ታገድኩኝ፣ በግድ የቤትም ቁራኛ ሆንኩኝ፤ በመጨረሻምካቲት ፯ ቀን ፩፱፯፮ ዓ.ም ደብዛዬ ጠፋ። እንግዲህ ይሄው ነው በአጭሩ። አይበቃም?

እኔ፦ ኧረ በጣም በቂ ነው አመሰግናለው።

እኔ፦ እስቲ በመጀመሪያ ከየት እንደምጀምር እንጃልኝ። ከአለም ፖለቲካ ጋር በዘንድሮ የኢኮኖሚ ቀውስ የአፍሪካ እጣ ፋንታን ወይስ ስለአገራችን የግዜው ሁኔታ ምርጫ፣ መንግስት፣ ተቃራኒ ቡድኖች፣ የኤርትራን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉና በ ኤርትራ ኢትዮጵያኖች? ከየቱ ይሻላል?

በዓሉ ግርማ፦ ከፈልከው ጀምር ግን እንድታውቅልኝ የምፈልገው እኔ ወይም አንተ የእኔ ልብ እንዴት ያስባል ብለህ የምታስበው እንጂ በተአምር ትክክል ነው ብሎ ህዝቡ ማሰብ የለበትም እዚህ ላይ በደንብ አስረግጠህ ለአንባቢህ አሳውቅልኝ በተረፈ ቀጥል።

እኔ፦ በጣም አመሰግናለው ገላገሉኝ ሰዉም ማንን እንደምጠይቅ እንዲረዳኝ ብዙ ሳብጠለጥል ነበር ቁልጭ ባለ አገላለጽ ነግረውልኛል። አሁን ወደ ጥያቄዬ ልሂድ።

በዓሉ ግርማ፦ በል ቀጥል!

እነ፦ በ2010 ማን ያሸንፋል?

በዓሉ ግርማ፦ ቅቅቅቅ አይ አጠያየቅ እስቲ አሁን ከዚህ ይጀመራል? ቀስ አርገህ እያያዝክ ወደዝህ ጥያቄ እንደመምጣት ዘለህ ወደዚህ መጣህ። እስቲ መጀመሪያ አንተ ፖለቲከኛ ነህ?ድጋፍህስ ለማን ነው? ወደ እዛ በውሃላ እንመለሳለን? አንተ ባዘጋጀሃው ጥያቄ እና መልስ እኔ ልጠይቅህ?

እኔ፦ ቅቅቅ ከምር ልክ ነዎት ልምዱም ስለሌለኝ ይሆናል ምን ላድርግ ብለው ነው። ፖለቲካ የምደግፈው ወይም ሙሉ ድጋፌን የሰጠሁት ፓርቲ እስካሁን የለም፤ ድጋፌ ለህዝብ ነው። እኔ ኮንሰርንድ ሲቲዝን ነኝ እንጂ ሙሉ ፖለቲከኛ ነኝ አልልም። ወይም እኔ ፖለቲከኛ ለመባል ቤንግሊዘኛ ኦቨርት እን ኮቨርት የሚባለውን ሁለቱን አንድ ላይ የማረግ ከሆነ አዎን ፖለቲከኛ ነኝ ያስብለኛል። ነገር ግን እኔን የማስበው በትክክለኛም የምሰራውም ባለሁበት አካባቢ ኦቨርትሊ ነው እንጂ ኮቨርት የሆነ ስራ አልሰራም።

በዓሉ ግርማ፦ ገለጽለጽ አርገው።

እኔ፦ አሃሃሃ ማለቴ ያው ኦቨርት ስል በግልጽ ምንም የተደበቀ ነገር የሌው ሲሆን ኮቨርት ደግሞ ያው የምደግፈው ፓርቲ ድጋፍ እንዲያገኝ በድብቅ የሚደረግ ስራ እና ብዙ በህቡዕ የሚሰራ እንደማለት ነው። ያ ማለት እኔን አይመለከተኝም። ስለዚህ እንዲሁ በደፈናው ዝም ብለው "ኮንሰርንድ ሲቲዝን" ቢሉኝስ! እሱ ሳይሻለኝ አይቀርም።

በዓሉ ግርማ፦ እንግዲህ አሁን ለማንም እንዳልሆንክ ካወኩኝ ማንንም ብናገር ከመንግስታችሁም ሆነ ከተቃራኒዎች አትቀየምም ማለት ነው።

እኔ፦ በጭራሽ!

በዓሉ ግርማ፦ በል እንግዲህ አሁን እንቀጥል ከፈለከው እንጀምር ወይስ ቅድም በጠየከው እንቀጥል?

እኔ፦ ቆይ አንዴ ጋሽ ግርማ የሆነች ቦታ ደርሼ ልምጣ! እና እንቀጥላለን።

ይቀጥላል
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests