ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Mon Feb 16, 2009 9:52 am

ኮሮጆ ኢትዮጵያ wrote:ከምትወያዩበት ርእስ ጋር ሳይስማማ አይቀርምና ተመልከቱት

http://www.ecadforum.com/content/094.html


ሰላም ታላቅ ሰው ኮሮጆ...እንዴት አለኽልኝ::ሰሞኑን ከረንት አፌርስ ላይ እያደረክ ያለኸውን ነገር ወድጄዋለሁ::አንተ እንደሁሌውም ለእኔ ታላቅ ሰው ነህ::ለጥበብ የምታደርገው አስተዋጽኦ የሽልማቶች ሁሉ ሽልማት የሚያሰጥህ ነው::
ስለ ፕለቲካው ስለማይገባኝ ከፖለቲካው ውጭ ባለው የጥበብና የታሪክ ዙሪያ ነው ታድያ....

ምድረ ሰነቻው ያለፈ ታሪኩን ያውቅ ዘንድ ሰሞኑን የምታነብላቸው እንዲሁም እንደክብርነታችን ላለው ታሪኩን ለማወቅ ለሚማስን ጊዜህን ሰውተህ በዛ በምወደው የአነባበብ ዘይቤው የምታነበው ነገር ይቀጥል እላለሁ::ሰነቻው ስለማይገባው ቢጮኽ አትስማው::በግድ እውነትን አግተው::

ስለነ ጀነራል ጽጌ ዱቤ,መንግስቱ ነዋይና በ 53ስቱ መፈንቅለ መንግስት ጊዜ የተሳተፉትና ያሳተፉትን የመጨረሻዋን የፍርድና የምስክር ቃል ያላወቅኩትን ስላሳወቅከኝ ምስጋናዬ ይድረስህ::

ጀነራል ጽጌ ዱቤ በስማቸው መንገድ ወይም ሀውልት የሚያስፈልጋቸው የብዙ ነገር ጀማሪ የገባቸው አባት ነበሩ::እንደዚህ ያለ ጀግና ለስሙ ማስታወሻ ይሆን ዘንድና አዳዲስ ትውልድ ስሙን ይጠራለት ዘንድ አንድ ማስታወሻ ማቆም ሲገባን ባለማድረጋችን ምን ያህል እንደማዝን አልጠየቅ::

ኮሮጆ ወንድሜ እንደሁልጊዜው በርታ::እግዚአብሄር ያሰብከውን ያሳካልኽ::መጽሀፎች እንደጉድ ወዳንተ ይጉረፉልህ::ያላወቀውን ታሳውቅ ዘንድ ሁሌም በውስጥህ መገፋፋትንና ትእግስትን እንዲሁም ቸርነትን በውስጥህ ያቆይልህ

ሁሌም አድናቂህ ነኝ

ሾተል........
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby እንሰት » Mon Feb 16, 2009 10:10 am

ሾተል wrote:[
ስለ ፕለቲካው ስለማይገባኝ ከፖለቲካው ውጭ ባለው የጥበብና የታሪክ ዙሪያ ነው ታድያ....
ስለነ ጀነራል ጽጌ ዱቤ,....
ጀነራል ጽጌ ዱቤ...
ሾተል........

ዱቤ ወይስ ዲቡ?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሾተል » Mon Feb 16, 2009 10:13 am

እንሰት wrote:
ሾተል wrote:[
ስለ ፕለቲካው ስለማይገባኝ ከፖለቲካው ውጭ ባለው የጥበብና የታሪክ ዙሪያ ነው ታድያ....
ስለነ ጀነራል ጽጌ ዱቤ,....
ጀነራል ጽጌ ዱቤ...
ሾተል........

ዱቤ ወይስ ዲቡ?


ሰላም እንሰት::ሰው ስህተት ሰርቶ ሲታረም እንዴት ደስ ይላል?ጀነራል ጽጌ ዲቡ ልል ነው....ሰሞኑን ስም በመጥራት የመሳሳት ውሽንፍር ውስጥ ተዱዬልሀለሁና ስለእርማቱ ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ::

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby እንሰት » Mon Feb 16, 2009 10:22 am

ሾተል wrote:
እንሰት wrote:
ሾተል wrote:[
ስለ ፕለቲካው ስለማይገባኝ ከፖለቲካው ውጭ ባለው የጥበብና የታሪክ ዙሪያ ነው ታድያ....
ስለነ ጀነራል ጽጌ ዱቤ,....
ጀነራል ጽጌ ዱቤ...
ሾተል........

ዱቤ ወይስ ዲቡ?

ሰላም እንሰት::ሰው ስህተት ሰርቶ ሲታረም እንዴት ደስ ይላል?ጀነራል ጽጌ ዲቡ ልል ነው....ሰሞኑን ስም በመጥራት የመሳሳት ውሽንፍር ውስጥ ተዱዬልሀለሁና ስለእርማቱ ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ::
ሾተል

ምንም አይደል!
ልጆቻቸው ስለአባታቸው ሊጽፉ ያስቡ ነበር ይሳካ አይሳካ አላወቅሁም:: እድሉ ያለህ ይመስላልና ፓልቶኮች የሚያወቁት ካለ ብታሳውቀን
ከምስጋና ጋር
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሾተል » Mon Feb 16, 2009 11:48 am

እንሰት::

ከትላንት ወድያ ባጋጣኢ ፓልቶክ ገብቼ ነበር::እና ከረንት አፌርስ ሩም ጎራ ስል ኮሮጆ ስለ 53ስቱ መፈንቅለ መንግስት የተለያዩ መረጃዎችን ያነብ ነበር::ይበልጥ እስከዛሬ ሰምቼው የማላውቀውን በቦታው የነበሩት የምስክርነት ቃል ለፍርድ ቤቱ ሲሰጡ....እንዲሁም እነ ጀነራል መንግስቱ ነዋይ የሰጡትን ቃል::ዘግይቼ ስለነበር የገባሁት ምንጩ ሲነገር አልሰማሁም::ከኔ ይበልጥ ወንድማችን ኮሮጆን ብታናግረው ምንጩን ይነግርህ ይሆናል::

በመቀጠል ዛሬ ከረንት አፌርስ ካልተሳሳትኩ በ53ስቱ መፈንቅለ መንግስት ጊዜ ከተሳተፉት ሰዎች አንዱን ሳይጠይቁት አይቀሩ....እንዲሁም እነ ኮሮጆ ቃል በገቡት መሰረት እነዚህን ባእህይወት ያሉ ባለታሪክ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ እያፈላለጉ እንደሚያደርጉዋቸው ነውና መቼ እንደሆነ ፕሮግራሙን ጠይቃችሁ አዳምጡ::እነ እድሉን ካገኘሁ ነው::የትያትር ስራ እንደ ሸሌ ማታ ማታ ነው::ስለዚህ ሰሞኑን የመድረክ የማታ ማታ ስራ አለኝ::

እንሰት ሰሞኑን አንድ ታላቅ አባት በኢትዮዽያ ቴሌቪዥን ኔት ወርክ ተጠይቀው ኢትዮትዩቦች ኢትዮትዩብ ላይ ለጥፈው እዚህም ለጥፈውልን ነበር ተመለከትከው?ስለመፈንቅለ መንግስቱና ስለ ጀነራል ጽጌ ዲቡ ያሉት ነገር አለ::

ጀነራል ጽጌ ልጆች አሉዋቸው?ታሪካቸውን እየጻፉ ነው?እንደዛ ካደረጉ በጣም ጥሩ ነው::ካወቅካቸው በርቱ በላቸው

መልካም ቀን

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby Ahmed-1 » Mon Feb 16, 2009 1:54 pm

ሙዝ1 wrote:
password wrote:
Ahmed-1 wrote: .........ደራሲው ኢትዮጵያውያኖችን እርስ በርስ የሚያባላ አንጀት ቢኖረው እንደዚህ ብዕሩ ባልተገራ!!!

አህመድ


ተባረክ ወዳጄ አህመድ, በአንድ አረፍተ ነገር ሁሉንም መለስክው አይደል!!!


ፓስና አህመድ ...
እሳቢያችሁን አከብራለሁ .... የናንተ ችግር ግን በማህበረሰባዊ የሞራል እሴትና በፖለቲካ ..... ከፖለቲካ ዉስጥ ደግሞ አንዱና ዋነኛዉ የህዝብን እምነት ማግኛ መንገድ የሆነዉን ፕሮፖጋንዳ አደበላልቃችሁ እያያችሁት መሆኑ ነዉ ... ......... ለያዩዋቸዉ ........ አበጥሯቸዉ .......... ከዛ አስተዉሏቸዉ ..... ..........


ሙዜ የከበረ ሠላምታዬ ካለህበት ይድረስህ!!
የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሚለውን አንብቤ የሥነ ጽሁፍ ውበቱን አደነኩ:: አዝናናኝ:: የደራሲው የድርሰት ችሎታ መሰጦኛል:: ከዚያ ባሻገር ዘርማንዘሩን አልፈትሽም .....መችም ያንጎላ ልጅ አይደለም!! ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ አቋም አለው ብዬ በጭራሽ አላምንም!! ከዚህ ውጭ ኦሮሞን ደግፎ አማራን አጠቃ ወይም ተገላቢጦሹ በደራሲው ላይ ጥርስ አያስነክስም.....በኔ ግምት!
የየትኛውም ፓርቲ ደጋፊ ወይም ተቃውሚ አይደለሁም... እናም የደራሲውን ብዕር እንጂ የፓለቲካ አቋም ከምንም ውስጥ አላስገባሁትምና እለፈኝ::

ባለፈው የርብቃ ዝምታ በሚለው መጽሀፉ ስለ አማራ የጻፈው እንዳበሳጨህ አነበብኩ:: በዚያ ዙርያ አስተያየቴን ለመስጠት አስቤ ይበልጥ ያስቆጣህ ይሆናል ብዬ በማሰብ ተውኩት:: አሁን ግን በግል ልጽፍልህ ወስኛለሁ!! ካስከፋህ እክሳለሁ :) ::

ፓስ
የምታቀርባቸው የስነ-ጽሁፍ ግምገማዎች እንደ ድርሰት ይጥማሉ!! አንድ ቀን ጉደኛ የሆነች ድርሰት እንደምትጽፍ ተስፋ አለኝ!! ለተላከኝ ስጦታ በድጋሚ ምስጋና አቀርባለሁ::
Ahmed-1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 174
Joined: Mon Mar 19, 2007 3:17 pm

Postby ሾዞተዘልዝ » Mon Feb 16, 2009 3:14 pm

dubie wrote:Hi Shotel:

Do not exaggerate minor things. As you know in any ethiopian cities there are persons from Tigray and Eritrea. They are the ones solely responsible for menged memirat. Some friend told me there were no war between Derg and Woyane/Shabia in Gojjam. the Derg soldiers simply left Gojjam and confront woyane in Abay Bereha between Wollega and Gojjam border. That is the area where there is no any civilian. the derg abandons birr sheleko and left for the berha west of it. And I admire the concern of Derg military leaders for the civilians. And they control debremarkos coming from North Shewa in the last days. There may be very minor incidents of such acts by Gojam farmers but in most cases people feed and give money to soldiers in return the soldiers give their uniforms and amunitions for the purpose of melting to the civillian popoulation. please do not exagerate heararsies.

አባ ምናለበት ማስተርጎምያ ሳቢ አብረሽ ብገጪው ከአስተያየትሽ ጋር? :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ሾዞተዘልዝ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Tue Jan 06, 2009 3:04 pm

Postby ሾዞተዘልዝ » Mon Feb 16, 2009 3:19 pm

ሾተል wrote:
dubie
Hi Shotel:


ዱቢ ስለጎጃም እየተጫወትን ሳለ ምነው በእንግሊዘኛ ጻፍክ?ጎጃም ውስጥ የስራ ቋንቋ እንግሊዘኛ ሆነ እንዴ?ያገሬ ገበሬ እንግሊዘኛ ቻለልኝ?ተመስጌን ነው::ጎጃም ውስጥ አማርኛ መሰለኝ የሚወራው::ምን አልባት ዋሸራ የቅኔ ትምህርት ቤት ቅኔ በእንግሊዘኛ ከጀመረ እኔ እንግሊዘኛ እንደ ቁምጣ ያጥረኛልና ሄጄ እማራለሁና ንሳና ንገረኝ::

ሌላው በአማርኛ እያጫወትኩት በባእድ ቋንቋ የሚያናግረኝ ጠላቴ ስለሆነ መልስ አልመልስምና በምንግባባበት ቋንቋ ናና እመልስልሀለሁ::

በኦሮምኛ,በትግርኛ,በአማርኛ,በሺናሻኛ,በገለብኛ በንዌርኛ በዲንካኛ ወዘተ ብትጽፍ በአገሬ ቋንቋ ይሁን እንጂ ምን ገዶኝ ግን በንግሊዘኛ በነጭኛ...አልስማማም

ሾተል....ሀ ሁ....አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞ


:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ማዘርፋዘር ነገር ነው አይደል ሾተል ይሄ ዱቤ የሚሉት?? :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: እንዴት አባቱ ክብርነታችንን ሰምተነው አንበነው በማናውቀው የባእድ ቋንቋ ሊያናግረን ይሞክራል?? :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ሾዞተዘልዝ ነን---- ኤ ቢ ሲ ዲ እምቢ :lol: :lol: :lol:
ሾዞተዘልዝ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Tue Jan 06, 2009 3:04 pm

Postby ሙዝ1 » Tue Feb 17, 2009 2:06 pm

Ahmed-1 wrote:ሙዜ የከበረ ሠላምታዬ ካለህበት ይድረስህ!!
የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሚለውን አንብቤ የሥነ ጽሁፍ ውበቱን አደነኩ:: አዝናናኝ:: የደራሲው የድርሰት ችሎታ መሰጦኛል:: ከዚያ ባሻገር ዘርማንዘሩን አልፈትሽም .....መችም ያንጎላ ልጅ አይደለም!!

ሰላም አህመድ .....የስነጽሁፍ ዉበቱ አዝናኝነቱ ምናምን ላይ ጥያቄ የለኝም .... እነዚህ ነገሮች በሰዎች የመዝናኛ ፍላጎትና አይነት ላይ የተመረኮዙ ናቸዉ .... እኔም ብዙም አላስደሰተኝም አልልህም .... ተክሉ ተክላይን እያፈላለኩት ነዉ ብልህ ምን ትለኝ ይሆን? ቂቂቂቂ .... ከምሬ ሲያስቀኝ የነበረ ገጸባህሪ(ግለሰብ) ነዉ ... ... ዘርማንዘሩጋም ምንም ጉዳይ የለኝም .... የወደፊት ባለቤቴም የሱዉ ዘር ናት ብልህ ምን ትለኝ ይሆን? ቆንጅዬ ኤርትራዊ .... ይህም እዉነት ነዉ ....
ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ አቋም አለው ብዬ በጭራሽ አላምንም!! ከዚህ ውጭ ኦሮሞን ደግፎ አማራን አጠቃ ወይም ተገላቢጦሹ በደራሲው ላይ ጥርስ አያስነክስም.....በኔ ግምት!

እዚህ ጋ ነዉ ልዩነቱ .... ኢትዮጵያዊ አቋም በቁጥር አላስቀምጠዉም በስሜትና በፍላጎት እንጂ .... .... ለዛም ነዉ ...ከላይ በፕሮፖጋንዳና በማህበራዊ የሞራል እሴት መካከል እየዋዠክ ነዉ ያልኩት ... ሁለቱ እጅግ ..እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ ....
የየትኛውም ፓርቲ ደጋፊ ወይም ተቃውሚ አይደለሁም... እናም የደራሲውን ብዕር እንጂ የፓለቲካ አቋም ከምንም ውስጥ አላስገባሁትምና እለፈኝ::

ቂቂቂቂ ... እንዴታለ ነገር ነዉ .... አስተያየትክን ሰጥተህ ጨርሰሀል እኮ :wink:
ባለፈው የርብቃ ዝምታ በሚለው መጽሀፉ ስለ አማራ የጻፈው እንዳበሳጨህ አነበብኩ:: በዚያ ዙርያ አስተያየቴን ለመስጠት አስቤ ይበልጥ ያስቆጣህ ይሆናል ብዬ በማሰብ ተውኩት:: አሁን ግን በግል ልጽፍልህ ወስኛለሁ!! ካስከፋህ እክሳለሁ :) ::

የቡርቃ ዝምታ ማለትህ ነዉ መሰለኝ ... ስለሱ መጽሀፍ አስተያየትህን ብትሰጠኝ አልከፋም .... ችግር የለብኝም .... ቂቂቂ .... በተደጋጋሚ ለማለት እንደ ሞከርኩት .... መጽሀፉን ትምህርት ቤት እያለሁ ነዉ ያነበብኩት .... መጽሀፉን በተመለከተም ... ከብዙ የኦሮሞ ...የትግራይ ...የደቡብ ልጆች ጋ ተወያይቸበታለሁ .... በጊዜዉም ብዙ ብዙ ስድብ ወቀሳ ... ደርሶብኛል .... ያንተዉም ከዛ በላይ አያስከፋኝም ... እኔን ያስከፋኝ በቡርቃ ዝምታ ዉስጥ ያለዉ .... ከብላክ ኤንድ ኆይቱ ጀርባ የጸሀፊዉ መርዛማ እቅድ ነዉ .... .......... እንዳመታደል ሆኖ ባርቆበታል:: ለ1 ሳምንት ኢንተርኔት አካባቢ ስለሌለሁ ... ከሳምንት በሗላ በግልም ይሁን ፊት ለፊት ....እስከፈለከዉ ድረስ ለመወያየት ፍቃደኛ ነኝ ...

ቂቂቂ ... በነገራችን ላይ ሁላችሁም ይህ መጽሀፍ የተጻፈዉ ለናንተ አይደለም ብላችሁ ምን ልትሉኝ ይሆን? ...ቂቂቂቂ ይህ የደራሲዉ ማስታወሻ የተጻፈዉ ለኪነ ጥበብ ፍጆታ አይደለም .... ታርጌት ኦዲየንሱም አብዛኞቻችሁ አይደላችሁም ....ቂቂቂ .... ፕሊስ በድጋሚ .... 1+1= 2 ነዉ ብላችሁ አታስቡ .... ይህ በሂሳብ እንጂ በፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ አይደለም ... 1+1= 3 ሊሆን ይችላል ...1 ሊሆን ይችላል ... ::

ኤኒዌይ ... ስላዝናናችሁ አመሰግነዋለሁ ...ምንስ ቢሆን ወገኖች አይደለን? :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሀሪከን2 » Tue Feb 17, 2009 2:51 pm

ሙዝ
ለዛም ነዉ ...ከላይ በፕሮፖጋንዳና በማህበራዊ የሞራል እሴት መካከል እየዋዠክ ነዉ ያልኩት ... ሁለቱ እጅግ ..እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ ....

እኔ ምልሽ ሙዝ እግር ይች በተደጋጋሚ የምትጠቀሚያት እሴት የምትባል አማርኛ ትርጉሟ ምን ይሆን :lol:

ቂቂቂ ... በነገራችን ላይ ሁላችሁም ይህ መጽሀፍ የተጻፈዉ ለናንተ አይደለም ብላችሁ ምን ልትሉኝ ይሆን ? ...ቂቂቂቂ ይህ የደራሲዉ ማስታወሻ የተጻፈዉ ለኪነ ጥበብ ፍጆታ አይደለም .... ታርጌት ኦዲየንሱም አብዛኞቻችሁ አይደላችሁም ....ቂቂቂ ..

ቂቂቂ ልበል እንጅ እንደ አንች :lol: እኔ እኮ በአማርኛ የተጻፈው ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን አንባቢወች መስሎኝ ነበር :lol: እኔ ምልሽ ታድያ ደራሲው ታርጌት ያደረገው እኛን ካልሆነ ምናልባት ደቡብ አፍሪካዊያን ይሆን? :shock: :shock: :shock: አይ ሙዝነት አንዳንድ ጊዜ እኮ ያለ አቅምሽ ስትፈላሰፊ ታስቂኛለሽ :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ሙዝ1 » Tue Feb 17, 2009 3:43 pm

ቂቂቂቂ ሰልምሽ ... እሴት ..ትርጉሙን አላዉቀዉም ዝም ብዬ ነዉ ምቀባዥረዉ ቂቂቂቅ.,.... .......

እኔ ምልሽ ታድያ ደራሲው ታርጌት ያደረገው እኛን ካልሆነ ምናልባት ደቡብ አፍሪካዊያን ይሆን ?


ይህንን ነገር ለቀልድ ያክል የጻፍሽዉ ይመስለኛል ... መቸም በአማረኛ ተጽፎ ... ለደቡብ አፍሪካዊ አይደለም ...ቂቂቂቂ ... ያልኩት አሁንም ልንገርህ በድጋሚ ...ለኔና ለአንተ አይደለም ...ቂቂቂ .... ምስኪን .... ይህንን'ኮ ነዉ ምልህ .... እያንዳንድሽ ብዙ ይቀርሻል .... ገና ነጭና ጥቁር እያነበብሽ ነዉ ያለሽዉ ...ቂቂቂቂ ....

አይ ሙዝነት አንዳንድ ጊዜ እኮ ያለ አቅምሽ ስትፈላሰፊ ታስቂኛለሽ


ልክ ነህ ... ሀቅሜን ማየት አትችልም አልልህም ... እንደዉም የአንድ ሰዉ አዋቂነት የሚለካዉም የሌላዉን አለማወቅ በማየት ነዉ .... ነገር ግን በዚህችኛዋ አባባልህ ... ......... ስለሳክ ደስ ብሎኛል ... ሳቅ የደስታ ምንጭ ነዉ .... ቂቂቂቂ ልበል እስኪ እንደበረከት ስምዖን .... ቂቂቂ ... ነገር ግን ... አዝኛለሁ .... ጫፉን ብቻ በመያዝሽ .... ብዙ አታንብቡ ...ትንሽ አንብባችሁ ብዙ አገናዝቡ :P :P የሳምንት ሰዉ ይበለን ለዚህ ቤት ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሀሪከን2 » Tue Feb 17, 2009 4:16 pm

ሙዝ
ቂቂቂ ሰልምሽ ... እሴት ..ትርጉሙን አላዉቀዉም ዝም ብዬ ነዉ ምቀባዥረዉ ቂቂቂቅ .,.... .......

አቦ ቀልዱን ተውና ትርጉሟን ንገረኝ የመጨረሻ እኮ የከበደችን አማርኛ ነች :lol:

. መቸም በአማረኛ ተጽፎ ... ለደቡብ አፍሪካዊ አይደለም ...ቂቂቂቂ ... ያልኩት አሁንም ልንገርህ በድጋሚ ...ለኔና ለአንተ አይደለም ...ቂቂቂ .... ምስኪን .... ይህንን 'ኮ ነዉ ምልህ .... እያንዳንድሽ ብዙ ይቀርሻል

ቂቂቅ አይ አንች :lol: ቆይ አንች ግን ይህ በአማርኛ የተጻፈ መጽሀፍ ለእናንተ አይደለም ካልሽ :lol: ለምን ለእነማን እንደ ተጻፈ ነግረሽን አትገላግይንም :lol: ሚስጥሩን ይዘሽ ለምን ታስጭንቂናለሽ :lol:


ልክ ነህ ... ሀቅሜን ማየት አትችልም አልልህም ... እንደዉም የአንድ ሰዉ አዋቂነት የሚለካዉም የሌላዉን አለማወቅ በማየት ነዉ

እንደ እውነቱ ከሆነ የአንችን ሀቅም አውቃለሁ ማለቴ ትክክል አለነበረም
የሰወች አዋቂነት የሚለካው ሌሎችን እንደ አዋቂ ባለመቁጥር ከሆነማ የዋርካ ታላቁ ታላቁ አዋቂ ሾጥል ወይም አባጨው ደጀኔ ነው ማለት እኮ ነው :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ግዮን » Tue Feb 17, 2009 4:21 pm

ሙዝ1 wrote:ቂቂቂቂ ሰልምሽ ... እሴት ..ትርጉሙን አላዉቀዉም ዝም ብዬ ነዉ ምቀባዥረዉ ቂቂቂቅ.,.... .......

እኔ ምልሽ ታድያ ደራሲው ታርጌት ያደረገው እኛን ካልሆነ ምናልባት ደቡብ አፍሪካዊያን ይሆን ?


ይህንን ነገር ለቀልድ ያክል የጻፍሽዉ ይመስለኛል ... መቸም በአማረኛ ተጽፎ ... ለደቡብ አፍሪካዊ አይደለም ...ቂቂቂቂ ... ያልኩት አሁንም ልንገርህ በድጋሚ ...ለኔና ለአንተ አይደለም ...ቂቂቂ .... ምስኪን .... ይህንን'ኮ ነዉ ምልህ .... እያንዳንድሽ ብዙ ይቀርሻል .... ገና ነጭና ጥቁር እያነበብሽ ነዉ ያለሽዉ ...ቂቂቂቂ ....

አይ ሙዝነት አንዳንድ ጊዜ እኮ ያለ አቅምሽ ስትፈላሰፊ ታስቂኛለሽ


ልክ ነህ ... ሀቅሜን ማየት አትችልም አልልህም ... እንደዉም የአንድ ሰዉ አዋቂነት የሚለካዉም የሌላዉን አለማወቅ በማየት ነዉ .... ነገር ግን በዚህችኛዋ አባባልህ ... ......... ስለሳክ ደስ ብሎኛል ... ሳቅ የደስታ ምንጭ ነዉ .... ቂቂቂቂ ልበል እስኪ እንደበረከት ስምዖን .... ቂቂቂ ... ነገር ግን ... አዝኛለሁ .... ጫፉን ብቻ በመያዝሽ .... ብዙ አታንብቡ ...ትንሽ አንብባችሁ ብዙ አገናዝቡ :P :P የሳምንት ሰዉ ይበለን ለዚህ ቤት ....

ንዴት ሙቀትን ይጨምራል ሙዝ ደግሞ አንድ ሳምንት ያህል ሙቀት ውስጥ ሲቆይ ምን እንደሚሆን መገመት አያዳግትም ስለዚህ ሰከን ብትል ጥሩ ነው::
እንዳባባልህ ደግሞ የወደፊት ባለቤትህ ኤሪትራዊት ናት እና አምባሻ በሽ በሽ ነው እንግዲህ: መልካም ዕድል ......
ግዮን
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Tue Jan 13, 2004 12:47 pm

Postby sarandem » Thu Feb 19, 2009 4:26 pm

አንድ ጋዜጠኛ እለታዊ ገጠመኞቹን አጠራቅሞ ክሽን አድርጎ አንድ መጽሀፍ ጻፈልን:: ይህ ጋዜጠኛ በሀያ አንድ አመቱ አማራጭ እና ሥራ በማጣቱ ወታደርነት ተቀጠረ አማራጭ ቢኖረው ኖሮ ግን የጋዜጣ ሪፓርተር መሆን ይፈልግ ነበር:: ሆኖም እድል ወታደር ቤት ላይ ጣለችው:: ምኞትና ፍላጎቱ ከጦር ሜዳ ካድሬነት ጀመረ:: ይህ ሰው ለአስር አመታት የህወሀት አባል እና ካድሬ ነበር:: ራሱን ከመካብ ይልቅ ብዙ ቦታ ላይ ሲያዋርድ አንብቤዋለሁ:: ራሱን ከልጅነቱ ጅምሮ ቁጥር አንድ ቂል ነበርኩኝ ብሎ ይገልጻል::
ቂልነኝ ይበለን እንጂ ከልጅነቱ ጅምሮ ያነሳቸው የነበሩት ፍልስፍናዎች ቀላል መስለው ውስብስብ ነበሩ:: ይህ ሰው በወቅቱ ማያቃትን ሀገሩን ስለማላውቃት አልወዳትም ስላለ አስተማሪው ገረፈው እኛም ዋርካ ላይ ጮክንበት::
ያ ሰው ደግሞ ተስፋዬ ገብረአብ ነው::

መጀመርያው ክፍል ላይ ምንም ነገር ሳይሰንቅ ሥራን ፍለጋ ብሎ ይጀምራል:: ያኔ የነበረው ሰርተፍኬት ወይም ዲፕሎማ አልነበረም:: ብርሀኑ ዘሪሁን እና ከበደ አኒሳ ብቻ :!: እነዚህ የታወቁ ስመ ጥር ጸሀፍት ስለተስፋዬ ችሎታ ጥሩ አመለካክት ስላላቸው ብቻ ሥራ ሊያገኝ አለመቻሉን በደርግ የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ በነበረው ሙሉጌታ ሎሌ ሪፖርተሮችን ይቀጥር የነበረው በዘር ቆጠራ /Kinship & Nepotism/ ነው በሚል ምክንያት ሀገሩ ላይ ቁርሻ መያዙን እና ከዚያ ግቢ መውጣቱ ገልጾልናል::

ይህ የተስፋዬ ችግር የእኛም ችግር ነው:: ለምንፈልገው ሥራ ሚያስፈልገውን መሰረታዊ እውቀት ወይም ብቃት /Qulification /ሳይኖረን ራሳችንን መካብ እና ያንን ቦታ ስለፈለግን ብቻ ማግኘት እንዳለብን /ይገባኛል/ ብሎ መጠበቅ:: ትሁቱን ተስፋዬ አዚህ ጋር አጣሁት ሀገሬ በሚላት ኢትዮጵያ ላይ አላግባብ ቂም ይዞባት ነበር:: በወቅቱ ለቦታው ብቁ ሚያደርግውን በትምህርት የታገዘ ሙያ ወይም ቢያንስ በት/ቤት ደረጃ በሚኒ ሚድያ ሲሳተፍ ወይም የስነ ጽሁፍ ላይ አዘንብሎ ሪፖርተር የመሆን ፍላጎቱን እና ተስጦውን አላሳየንም :: ከመስፍን ሀ/ማርያም ጋር አብሮ አደግ በመሆናቸው ሚመፃደቁት መምህሩ አንዴ ስለ አባቶች የጻፍውን አይተው የገሰጹትን ጨረፍ አርጎ እንደዋዛ አልፏታል:: እንድያውም የ 11ኛ ክፍል መምህርቱ <<ተማሪ ሆነህ ሳውቅህ ሰነፍ ተማሪ ነበርክ አሁን የፕሬስ ሀላፊ እንዴት ልትሆን በቃህ :?: >>ብላ ስትሞግተው እንመለከታለን እና በዚያ ዘመን አዚያ ቦታ ላይ እንዴት በሪፖርተርነት መቀጠር ነበረብኝ ብሎ አሰበ?
አስቦም አላበቃም እንደ በቀል ወሰደው?
ገጽ 14 ላይ ተገቢውን ቦታ/ሪፖርተርነት/ በመከልከሌ ውጤቱ ከአራት አመታት በኃላ ይህ ሆነ ይላል::

ተስፍሽ የጻፍካት አጨቃጫቂ መጽሀፍ ፓለቲካን ከገጠመኞችህ ጋር እንደ ዋዛ እያዋዛክ ስልጻፍከው አንብቦ ለመጨረስ ሁለት ቀን ብቻ ነው የወሰደብኝ::

ለሪፖርተርነት ሚሆን ብቃት ሳይኖርህ የፕሬስ መምርያ ያህል ግዙፍ የአገሪቱን ሚድያ ከፍተኛ ኃላፊነት ስትወስድ ይሰማህ የነበረውን መሰቅጠጥ እኔም ተጋርቻለሁ:: ምክንያቱም እንዲህ ያለ ችሎታ በፓለቲካ ታማኝነት እና በዘር ግንድ ቆጠራ ሥራዎችን መቆናጠጥ አይነት ነገር በፈረደባት ኢትዮጵያ የአዳባባይ ሚስጢር ነው :shock:
አንተም ገጽ 17 ላይ እንደገለጽከው ይህንን መስሪያ ቤት እየተንገዳገድክ ለሁለት አመታት መርተከዋል:: ከእንዲህ አይነት መምርያ ከኒውዮርክ የመጣ እንግዳ የተቀበለ ታምራት ላይኔ ወደ ኒውዮርክ እንደሄደ ቢጻፍልን እይገርመንም ምክንያቱም ለእኛ የሁለቱ ዜና መቀያየር ለውጥ አያመጣም::

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ተወዳጅ እና ብዙ አንባቢ የነበረውን የአድማስ አምድ አዘጋጁን ክፍሌ ሙላት ጨምሮ ሌሎች ጋዜጦችን በወቅቱ ማባረርህ ለጊዜው የጎዳካቸው ቢመስልህም የግል ጋዜጣ ለመመስረት ምክንያት ስለሆንካቸው ሊያመስግኑህ ይገባል:: :wink:

ግልጽነትህ ታሪኩን እንደወረደ ልክ ለጋደኛ እንደምትተርክ አርገህ እያዋዛክ ስለጻፍከው አድናቆቴን ሳልገልጽልህ አላልፍም::

ማን ያልወረድክበት አለ ተፈራ ዋልዋ የጦጣና ቆንጥር ፊሎሶፈሩ :roll: :lol:

እንደ ሸዋዚንገር ተገለባብጦ መተኮስ አያቀትውም የተባለለት :lol: በረከት :P ኤርትራዊ ሆኖ ስለ ኤርትራ መገንጠል ራሱን ቃለምልልስ አድርጎ በካሳ ደሜ ኢንዲታተም ያደረጋት ነገር መሪዎቻችን ምን አይነት ተራና ተልካሻ እንደሆኑ ይበልጥ ስላሳየክን እናመሰግንሀለን::

መለስም ሆነ በረከት ምን ያህል በቂም በበቀል በእጅ አዙር ሰዎችን እንደሚተናኮሉ እና ጠላልፈው እንደሚጥሉ በድንብ ገልጸካቸዋል::

የመለስ ሚስት ህገወጥ ነጋዴነት እና የእርሧ ተባባሪ የጫት ጄኔራል ተብዬ ታሪክ የዘመናችን አሳዛኝ ታሪክ ነው :: ወይ መከራችን

የአብዱል መጂድ ቁጣም ቢሆን አሪፍ ወግ ነው ከ 6 ማዞርያ ቴክኖሎጂ 4ቱ ለምን ለትግራይ ክልሎች ተተክሉ ብሎ ያነሳው ቁጣ ለምን እንደ ናዝሬት ወይም ድሬዳዋ ላሉት ትላልቅ ከተሞች አልሆነም ሳይሆን ለምን ለራሴ ክልል ጅጅጋ አልሆነም ማለቱ ያው የተለመደ ፍርደ ገምድልነት ነው::

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳም ቢሆን አላስተረፍካቸውም ታሪክ ለማጥናት ወደ ጀርመን ሲሄዱ ወጣት ሌንጮ አንተ ሄደህ ታሪክ ተማር እኛ ታሪክ ሰርተን እንጠብቃለን ያላቸው ነገር ፈገግ ታደርጋለች::<< ዛሬ ላይ ቆሜ ስታዘብ የተከበሩት ነጋሶ ታሪክ ቢማሩም የታሪክ ስህተቶችን ደጋግመው ሲሰሩ ስመለከት የተማሩትን ታሪክ እንጠራጠረዋልን>> ገጽ 151 ይችን ድንቅ አባባልህን በቀይ እንዳሰመርኩባት አልደብቅህም::

በቅርጽ እና በይዘታቸው አንድ የሆኑትን የወያኔ ተለጣፊ ዘውግ ተኮር የሆኑ የፓለቲካ ፓሪቲዎችንም ቢሆን አላስተረፍካቸውም:: ውነትም እንደ ኮካ ኮላ እርስ በርሳቸው አንድ ናቸው:: የኮካ ኮላ አባላት በህውሀት አንድ ጊዜ ተጠፍጥፈው ከተሰሩ በኃላ ህውሀትንም እንዳይከዱ በሙስና እና በወንጀል እንዲዘፈቁ ተደርገው አፈነግጣለው ካሉ ግን ያቺ ቀይ ካርድ ቀኗን ጠብቃ እንደምትመዘዝባቸው ጥሩ አድርገህ ጽፈከዋል::

ቤተመንግስት ባሉ የታሰሩ አናብስት ከመሰልካቸው መካከል ቢዘገይም ራሥህን ነጻ በማውጣትህ ልትደነቅ ይገባሀል::

መጨረሻ ላይ ልለው ምችለው ነገር ቢኖር ቆንጆ መጽሀፍ ነው:: ወደ ፊትም ሌላ ጥሩ መጽሀፍ እንደምትወልድ እንጠብቃለን::
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ShyBoy » Sun Feb 22, 2009 4:24 am

ሰላም ሰዎች!

እኔ እንኳን አንባቢ ሰው አይደለሁም ሆኖም ግን ይሄ መጽሀፍ ካነበብኋቸው በጣት የሚቆጠሩ መጽሀፍት አልዱ ለመሆን በቅቷል:: መጀመሪያ ላይ ስጀምረው ለመጨረስ አልነበረም:: እዚህ ዋርካ ላይ ብዙ ሲወራለት ሳይ ምን አይነት መጽሀፍ ቢሆን ነው ብዬ ገረፍ ገረፍ ለማድረግ ነበር አጀማምሬ:: ግን መጽሀፉ ማግኔት ሁኖ ነው ያገኘሁት:: በጭራሽ አይለቅም! እጅግ በጣም የሚስብ ሁኖ ነው ያገኘሁት!!! ብራቮ ተስፋዬ ብያለሁ!!!

ወደ ይዘቱ ከተመጣ ብዙ ነገር ሊባልለት የሚችል መጽሀፍ ነው:: እኔ ግን ያን ያህል አንድን መጽሀፍ comprehend አድርጎ ትችት ለመስጠት ልምዱም ሆነ ብቃቱ ስለሌለኝ ዝርዝር ግምገማውን ለሚያውቁት ልተወውና በጥቅሉ ግን መጽሀፉን በማንበቤ ከልቤ ረክቻለሁ!!! ብዙ ትምህር ይሰጣል: ለማመን የሚያጠራጥሩ ነገሮችም አይጠፉትም:: በጣም ያዝናናል: ብሎም ያስተክዛል/ያሳዝናል:: በጣም ከማልረሳቸው እና ከልቤ ካሳቁኝ ሰዎች አንዱ ተክላይ ተክሉ......ነው ወይስ ተክሉ ተክላይ (ጸሀፊው ራሱ ትክክለኛው የቱ እንደሆነ ግራ እንደሚያጋባው ስለገለጸ ነው) ፍርፍር እስክል ነው የሳቅሁት:: የሲያትሉ ገጠመኞቹም በጣም አስቂኝ.......ሲሉም አሳዛኞች ናቸው: የኬንያውም አይረሳም:: የቁንድዶ ፈረሶች ታሪክ ደሞ የሚገርም ነው:: እኔ ስለዚህ ነገር ጭራሽ ሰምቸ አላውቅም ነበር:: ፖለቲካ ነኩ እና የውትድርናው ጊዜማ ምኑ ይወራል?

መጽሀፉን አንብቤ ከጨረስሁ በኋላ ስለ አቶ ተስፋዬ የተሰማኝ ነገር ቢኖር ግልጽነት እና ተንኮል የማያስብ አይነት ሰው ሁኖ ነው የተሰማኝ:: ድሮ ሳይወድ በግድ ያደረገቻውን ስህተቶች ሁሉ የተናዘዘ ሲሆን ላወጣቸው የተሳሳቱ መረጃዎች ሳይቀር እርማት ሰጧል (ለምሳሌ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ስለሚለው መጽሀፍ የተናዘዘው ነገር...እኔ መጽሀፉን አላነበብሁም)::

የቡርቃ ዝምታ የሚል መጽሀፍ መኖሩንም ያወቅሁት አሁን ዋርካ ላይ ሲወራ እና እዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነው:: ባላነበብሁት መጽሀፍ ላይ አስተያየት መስጠት ባልችልም እነ ሙዝ እና ሀሪከን መጥፎ መጽሀፍ (ኦሮሞን ከአማራ የሚያቃቅር) እንደሆነ ገልጸዋል:: ዛሬ ወሬ ስቃርም EMF ላይ የሆነ ነገር ተለጥፎ አየሁና ቀልቤን ስቦት ከፍቸ አዳመጥሁት:: ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር የተካሄደ ቃለመጠይቅ ነበር:: የቡርቃ ዝምታ ምንም አይነት ተንኮል ከጀርባው እንደሌለ ሰውየው ይገልጻል:: የልቁንም ያለውን እውነታ በማጋለጥ በፍትሄ እንዲፈለግለት ለማድረግ አስቦ እንደጻፈው አይነት ነገር ይገልጻል:: ቃለመጠይቁን እዚህ ጋ በመሄድ በግራ በኩል ካሉት "ቃለ-ምልልስ ከተስፋዬ ገ.አብ ጋር" የሚለውን ተጭናችሁ ማዳመጥ ትችላላችሁ http://www.ethioforum.org/wp/ (የዚህን ቃለ ምልልስ ብቻ ለይታችሁ ሊንክ ማቅረብ የምትችሉ ብትተባበሩ ጥሩ ነው የዌብሳይቱ ይዘት በየጊዜው ሊቀያየር ስለሚችል የቃለምልልሱ ማስታወቂያ ሊጠፋ ይችላልና)::

በሉ ሰላም ሁኑ!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests