ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ማይ ኔም » Thu Feb 12, 2009 6:09 pm

የደራሲው የወያኔን ሚስጥር ማዉጣት ተመችቶኛል….በተረፈ ግን
አብዛኛው የደራሲው ገለጻ አንድን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ሳይሆን ፣ በዘሩ እየከፋፈለ ነዉ ትረካዉን የሚቀጥለው፣ ኦሮሞ አማራ ..ትግሬው…ወደ ኤርትራ ስንመጣ ግን፣ ኤርትራዉያኑ ይለናል… ትዝ ከሚሉኝ
ጸረ-ኢትዮጵያ ስሜት ያላቸው ሃይለ ቃሎች ብዙ ቦታ ይታያሉ…
1)....ኦሮሞነቴን የማትቀበል ኢትዮጵያ አስር ቦታ ትከፋፈል::…
2)……አገራችሁን የማትወዱ እጃችሁን አዉጡ ሲባል..እኔ አላወጣሁም ነበር ይለናል
3)…ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ይልና፣..መች ዘረጋች..ዱሽ እጆችዋን ነው የምትዘረጋው?…ለነገሩ እጅ የትአላትና እያለ! ..ፌዙን ይቀጥላል
4) …የሻቢያ ተኩውዋሾች ..ሲፈልጉ የምትበላበት ቁርስ ሳህን ላይ ተኩሰው ሊያስቀምጡልህ ይችላሉ.. የሻቢያ ገድል መሆኑ ነው !
5)…..ይቀጥላል
ማይ ኔም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Thu Mar 17, 2005 6:16 pm
Location: united states

Postby የጋሽ ለማልጅ » Thu Feb 12, 2009 6:14 pm

ማይ ኔም wrote:የደራሲው የወያኔን ሚስጥር ማዉጣት ተመችቶኛል….በተረፈ ግን
አብዛኛው የደራሲው ገለጻ አንድን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ሳይሆን ፣ በዘሩ እየከፋፈለ ነዉ ትረካዉን የሚቀጥለው፣ ኦሮሞ አማራ ..ትግሬው…ወደ ኤርትራ ስንመጣ ግን፣ ኤርትራዉያኑ ይለናል… ትዝ ከሚሉኝ
ጸረ-ኢትዮጵያ ስሜት ያላቸው ሃይለ ቃሎች ብዙ ቦታ ይታያሉ…
1)....ኦሮሞነቴን የማትቀበል ኢትዮጵያ አስር ቦታ ትከፋፈል::…
2)……አገራችሁን የማትወዱ እጃችሁን አዉጡ ሲባል..እኔ አላወጣሁም ነበር ይለናል
3)…ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ይልና፣..መች ዘረጋች..ዱሽ እጆችዋን ነው የምትዘረጋው?…ለነገሩ እጅ የትአላትና እያለ! ..ፌዙን ይቀጥላል
4) …የሻቢያ ተኩውዋሾች ..ሲፈልጉ የምትበላበት ቁርስ ሳህን ላይ ተኩሰው ሊያስቀምጡልህ ይችላሉ.. የሻቢያ ገድል መሆኑ ነው !
5)…..ይቀጥላል


ምን አለበት ሌሎችም እንዳንተ ነቃ ብለው ቀላሉን ሀቅ ቢረዱት?
የጋሽ ለማልጅ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Sun Feb 08, 2009 8:05 am

Postby ሀሪከን2 » Fri Feb 13, 2009 11:37 am

ማይ ኔም
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ይልና፣ ..መች ዘረጋች ..ዱሽ እጆችዋን ነው የምትዘረጋው ?…ለነገሩ እጅ የትአላትና እያለ

ቅቅቅ መጀመሪያ አባባሉ በትክክል ኮት አላደርግከውም የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያ እጅ የላትም እግርም የላትም የሚያዝን አንጀትም የላትም :lol: :lol: መልካም የሰሩላትን ሁሉ ቅርጥፍ አድርጋ የምትበላ ሀገር እኮ ናት

ማን ነበር ???? ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የስራልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ብሎ ያለው
ለሚወዷት እና ለሚሰሩላት ሆና ለማታውቅ ሀገር ይህ ሲይንሳት ነው :lol: :lol:

የጋሽ ለማልጅ
ምን አለበት ሌሎችም እንዳንተ ነቃ ብለው ቀላሉን ሀቅ ቢረዱት ?

:lol: :lol: እንትን ለእንትን አብረህ አዝግም ይመስላል ነገሩ :lol: ሁለታችሁም መጽሀፉን ያነበባችሁት ሁሉ አይመስለኝም ማለቴ ትኩረታችሁ የመጽሀፉ ይዘት ላይ ሳይሆን እንደዚህ አይነት ቃላቶችን እና አረፍተ ነገሮችን ፍለጋ ላይ ብቻ የነበረ ይመስላል :lol: :lol:

ጥያቄ ለሁለታችሁም በመጽሀፉ ላይ ከተጋለጠው የወያኔ ባለስልጣኖች ጉድ እና እነዚህ ከመጽሀፉ ውስጥ በመብራት ፈልጋችሁ ካገኛችኌቸው አረፍተነገሮች ለእናንተ የትኛው ነው ሚዛን የሚደፋው?

በነገራችን ላይ ብዙ ወያኔወች በዚህ መጽሀፍ አማካኝነት በተገለጸው ጉዳቸው እያለቃቀሱ ይገኛሉ :lol: :lol: መጽሀፉ እንዳይነበብ ሁሉ የሚችሉትን እየቀሰቀሱ ነው :lol: :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ሙዝ1 » Fri Feb 13, 2009 12:35 pm

ሀሪከን2 wrote: በነገራችን ላይ ብዙ ወያኔወች በዚህ መጽሀፍ አማካኝነት በተገለጸው ጉዳቸው እያለቃቀሱ ይገኛሉ :lol: :lol: መጽሀፉ እንዳይነበብ ሁሉ የሚችሉትን እየቀሰቀሱ ነው :lol: :lol:


ቂቂቂ ... ሰልምሽ ከዚህ መጽሀፍ ጋ ፍቅር የወደቅሽ ትመስያለሽ? ...በሩጫ አነበብኩት .... ቂቂቂ .... ምንም ያልተሰማ አዲስ ነገር የለም .... ሁሉንም ታሪኮች ከሞላ ጎደል በወሬ እናዉቃቸዋለን .... ሚስጥር አወጣ የሚያስብለዉ አይመስለኝም .... ኤኒዌይ ይህ ቤት ስነጽሁፍ ስለሆነ የሚወራበት በናታችሁ ከበአሉ ጋ ለማወዳደር አትሞክሩ .... እንደ ደሀ ጋቢ በተለያየ ጨርቅ የተደራረተ የሚመስል ወጥነት የሌለዉን ድሪቶ ታሪክ መጽሀፍ አንብበህ ከነ በዐሉ ጋ ...ተዉ በናታችሁ ደስ አይልም :wink:

ስማ ሀሪክ ዘግሬት .... .... ይልቅ መጽሀፉ ላይ ያለዉን ኢብሳን አስታወስከዉ? ...ቂቂቂ .... ኢብሳ የመንግስትን ትኩረት ስቦ ታስሮ መገረፉ እዉነት ከሆነ የሚገርም ነዉ .... ያን ያክል እኮ ከአማራ ጥላቻ ባለፈ ጠንከር ያለ የፖለቲካ አቋምና እዉቀት የነበረዉ ልጅ አልነበረም .... ..... እሱን የማስታዉሰዉ ቲቪ ሩም ዉስጥ ዜና ልናይ ስንሄድ ...ልክ የኦሮምኛ ፕሮግራም ሲያልቅ ነዉ የምንደርሰዉና ... የሆነ ጠብ ያለሽ በዳቦ ለመለወጥ የሚታገል ምስኪን ተማሪ ነበር .... 92 በተከሰተዉ ደን ቃጠሎም .... ሌላዉ ተማሪ ለመዝመት ሲዘጋጅ ደስተኛ ካልነበሩት የኦሮሞ ተማሪዎች አንዱ ነዉ .... የኦሮሞ ተማሪዎች ብቻ ስራ አድርጎ ይቆጥር ነበር ደን የማትረፉን ስራ .... ቂቂቂ ... ምስኪን....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby password » Fri Feb 13, 2009 5:09 pm

:o

ተሰርዟል
Last edited by password on Sat Feb 14, 2009 12:44 am, edited 2 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Fri Feb 13, 2009 5:13 pm

አንድ ቀን ባህላቸውንና ወተታቸውን እየመገቡ ወዳሳደጉኝ የረርና ከረዩ ገበሬዎች እንደምመለስ መንፈሴ ዘወትር ሹክ ይለኛል። ወደ ሃገሬ ተመልሼ፣ በቢሾፍቱ ሃይቅ ዳርቻ ወይም በዝቁዋላ ተራራማዎቹ አካባቢ የራሴን ጎጆ እቀልሳለሁ። በጎችና ዶሮችም አረባለሁ። የምወዳቸውን ዘፎች በግቢዬ ውስጥ እተክላለሁ። መጻህፍትንም በብዛት እጽፋለሁ
ምን ጥያቄ አለሁ?
እኔ ንደሁ ትናንት ቢሾፍቱ ነበርኩ። ነገም ቢሆን ቢሾፍቱ ነኝ ከነግ ወዲያ ማናችንም በህይወት አንኖርም። በታሪክ በብጎ የመታወስ መብት ያለው ከቶ የለም


በማለት ነው ደራሲ ተስፋዬ የጋዜጠኛው ማስታወሻ በተሰኘው መጽሀፉ የጀመረውን እጅግ አስገራሚ ታሪክ የሚያጠናቅቀው።

ይህ ስራ የታሪክ አወቃቀሩ፣ የቁዋንቁዋው ጥራት፣ የአተራረክ ስልቱና ግልጽነቱ፣ መጽሀፉን ከዚህ በፊት ከታዩት እንደ አጥፍቶ መጥፋትና ኦሮማይ አይነት ማስታወሻ መሰል ስራዎች የተለየ ያደርገዋል። አጥፍቶ መጥፋት ከደርግ ውድቀት በሁዋላ ሰለተጻፈ ደራሲው ምንም አደጋ ባላጠላበት ሁኔታ የጻፈው ሲሆን ኦሮማይ ግን በስርአቱ ስር እያለ ደራሲው በተቻለ ህልውናውን አደጋ ላይ ባለመጣልና ማሰተላለፍ የፈለገውን እውነታንም ባለማዛበት መሀል ሚዛን ጠብቆ የጻፈው ነው ማለት ይቻላል። የጋዜጠኛው ማስታወሻ ለየት የሚለው ከአገር ውጭ በመጻፉ ሲሆን በትረካው የሚያጋልጣቸው ሰዎች እሁንም በስልጣን ላይ ያሉ ናቸው። ተስፈዬ ለበቀል እርምጃ ሰለ መጋለጡ የሚታውቅ ነገር የለም። ከህይወት እጣፈንታው አንዱ ይህን ታሪክ መተረክ ስለነበር በተለያየ አጋጣሚ፣ ከተለያየ አቅጣጫ በህልውናው ላይ የተሰነዘሩበትን ፈታኝ ጥቃቶች አምልጦ በኢትዮጵያ ስነጽሁፍ ታሪክ ውስጥ የራሱን የክብር ቦታ የሚይዝ ታሪክ ለመስራት በቅቶአል። አሁንም ይህን የቃላት ኣዳፍኔ ወርውሮ እዛው ከወረወረበት ጉዋሮ ቁጭ ብሎ ይጥብቃል ብዬ አልገምትም። ወርውሮ ዞር እንዳለ ነው የሚሰማኝ።

በአራት መቶ ገጻት ውስጥ ደራሲው ከልጅነት አስከ አሁኑ ጊዜ የገጠሙትን አበይት የሚላቸውን ክዋኔዎች ልቅም አድርጎ በጣፋጭ ቃላት ከሽኖ ሲያቀርብ የዘመንን ቅደም ተከተል chronological order አልተከተለም። ታሪኩን በአስራ ዘጠኝ ዐምት እድሜው ስራ ፍልጋ ሲወጣ ጀምሮ፣ መሀል ላይ ወደ ልጅነት ዘመኑ ይመልሰንና ህይወቱ አሁን ወዳለችበት አቅጣጫ እንድትታጣፍ ምክንያት ስለሆኑት ወላጆችና መምህራን ይነግረናል። ከመደምደሚያው የሚደርሰው እንደያስፈላጊነቱ ወደ ሁዋላና ወድፊት እየቃኘ ነው። ከአንድ መሳጭ ክፍለ ታሪክ ቀጥሎ ቀልድ ለበስ አስቂኝ ትረካ፣ ከአንድ አስገራሚ የፖለቲካ ሽፍጥ በሁዋላ አዝናኝ የፍቅር ታሪክ። ካስጨነቀን በሁዋላ እያዝናናን፣ ከሳቀን በሁዋላ እያሳዘነን።

ይህ የአጻጻፍ ዘዴ አንባቢና መጽሀፉ ሳይሰላቹ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ የሚያደርግ ዘመናዊ የአጻጻፍ ስልት ነው። አንባቢያን መጽሀፉን መጀምር ብቻ ነበር ችግራችን። ከዚያ በሁዋላ ያለው ስራ የመጽሃፉ እንደሆነ ነው የገባኝ። ከጀመሩት የማይለቅ መጽሀፍ።

የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሚደነቅበት ሌላው ገጽታ ቁዋንቁዋው ነው። አማርኛው። አማርኛ የመንግስት ቁዋንቁዋ ከሆነ ቢቆይም ባለፉት ሁለት መንግስታት ዘመን አቅሙ ከሚፈቅድለት በላይ አንዲያገለግል የተገደደበት ጊዜ ነበር። ደርግ ሶሸሊዝም የተሰኘውን ባእድ ርእዮተ ዓለም የሀገሪቱ መመሪያ እንዲሆን ካወጀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተገረሰሰበት ወቅት ድረስ አማርኛ ዲያሌቲክስን የመሰለን ረቂቅ ጽንሰ ሀሳብ እንዲገልጥ፣ ዳስከፒታልን ከሚያክል ውስብስብ ጥናት እንዲተረጉም ያልተሞከረበት ነገር አልነበረም። ገላጭ ቃል ፍለጋ ከግእዝ እስከ እንግሊዝኛ ያሉት ቁዋንቁዎች ተፈልቅቀው ተፈትሽዋል።
ርእዮተ ዓለም
ቀኝ መንገደኛ
ኢሳይንሳዊ ወዘተ
የሚባሉ ቃላት የተደመጡት በደርግ ጊዜ ነበር።

አሁን ያለው ስርአትም የፌዴራሊዝምን ፍትሀዊነት ለማብራራት፣ ብሄረሶችን የመገንጠል መብት ለመስበክ፣ ውሽቱን ውነት እውነቱን ወሽት ለማስምሰል ቁዋንቁው ላይ የማይሞከር ነገር የለም። አዲስ ሃሳብ ለመግለጥ አማርኛን ሲለጥጠውና ሲቆለምመው ይደመጣል።
አናሳ ብሄር
ሙስና፣
ገጠርን ያማከለ
የፈንጂ ወረዳ ወዘተ
መባል የተጀመረው በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ነው።

የደራሲ ተስድፋዬ መጽሀፍ ግን ያን አይነት ችግር አላየሁበትም። የተጠቀመው ቀላል የንግግር አመርኛ ሲሆን፣ የገለጸው ሀስብ ግን ጥልቅ ነው።

ምሳሌ
በእኛና በነሱ መሃል ውጊያ ከተጀመረ ያቺ ምድር በሀበሻ ደም ትጨቀያለች።


አምዴና እኔ እንግባባ ነበር። ያን ከተነጋገርን በሁዋላ (እጃቸውን ለወያኔ የመሰጠት ነገር ተነጋግረው ነበር።) እኔ እርምጃዬ ስቀንስ፣ እሱ ፍጥነቱን ጨመረ። በዚያ ተለያየን።


ተስፋዬን በጣም ተነባቢ ያደረገው አንዱ ይህ ጥልቅ ሀሳባትን በቀላል ቁዋንቁዋ የመግለጽ ችሎታው ይመስለኛል።

ሌላው መጽሀፉን ተነባቢና መሳጭ ያደረገው የልቦለድ አጻጸፍ ዘይቤ መከተሉ ነው። በእውነተኛ ዘገባ ወይም ማስታወሻዎች አጻጻፍ ያልተለመደ የአካባቢ ገለጣ፣ የባለታሪክን ባህሪያት መሳልና ቀጥተኛ ጭውውቶችን በተሳካ ሁኔታ ተጠቅሞባቸዋል። በተለይ ጭውውቱ ለትረካው ጣእመ ልቦለድ የሰጠው ዋና ከፍል ነበር ማለት ይቻላል። ደራሲው ከገለጣ ወደ ጭውውት፣ ከጭውውት እንደገና ወደ ገልጣ የሚያደርገውን ሽግግር ንባብን በማያደናቅፍ መልኩ ያመቻቸበት ዘዴም ሳይጠቀስ የሚያልፍ አይደለም።

በተረፍ ደራሲው በትረካው ውስጥ አልፎ አልፎ የግሉን አመለካከት በሰበካ መልክ መወተፉን አልወደድኩለትም። ሁለንተናዊ እውነታ ወይም ተፈጥሮወዊ ህግጋት ካልሆኑ በቀር ደረሲው የግሉን እምነት እንደማይገሰስ ቃለ መለኮት ሲያሰፍር ትረካው ግራዋ ግራዋ ሊል ይችላል።
ምሳሌ
ህወሀት ለስልጣኑ ህልውና መረጋገጥ ወሳኝ የሆኑ መስሪያ ቤቶችን መያዙ የሚጠበቅ ነው። ውጭ ጉዳይ፣ ደህንነት፣ ጠ/ሚንስትርና መከላከያን ከለቀቀ ህልውና አይኖረውምና ማንም ቢሆን ይህን ይገነዘባል። ህወሀት ህልውናውን ከማስጠበቅ ባሻገር ለሀገሪቱ እድገት ሲል እንኩዋ ከዚያ በመለስ ያሉ ሙያ ነክ የስልጣን ቦታዎችን ለባለሙያ መተው አለመቻሉ ነው ችግሩ።


ይህ የደራሲው ግለዊ አመለካከት ነው። አቀረረቡ እንደ ስበካ ነው። ህወሀት ያግበሰበሰው ስልጣን ለህልውናው የሚያስፈልገው ስለሆነ ይገባዋል፣ የሚል አንደምታ ያለው ሀሳብ ይመስላል። ደራሲው የግሌ አመልካከት ብሎ ቢያስቀምጠው ቅሬታ አይኖረኝም። እንደ ዐለምዐቀፋዊ እውነታ (UNIVERSAL TRUTH) ቁጭ ማድረጉ ላይ ነው፣ችግሩ።

በተረፈ እኔ በግሌ ... ይህን ስራ የማይው እዚህ ስራ ላይ ከሰፈርው ሀሰብና ሀሳብ ብቻ በመንሳት ነው። የደራሲው የቀድሞው ስራና እዚያ ላይ የሰፈረው ጉዳይ በጣም የረበሻቸው አንባቢያን ታዝቤአልሁ። ለዚያ ደራሲው የሚሰጠው መልስ ይኖር ይሆናል። ደራሲው ከኤርትራ ወደ መሃል ኢትዮጵያ ከመጡ ሰዎች መወለዱ ያቅለሸለሻቸው ጎጠኞች ለሰነዘሩበት ዘለፋ ግን ቅንጣት ታህል ትኩረት ይሰጠዋል ብዬ አልገምትም። ደራሲው ኢትዮጵያዊነቱን የሚሰጠው ሆነ የሚነጥቀው ምንም ሀይል እንደሌላ ራሱ ተናግሮአል።

በኔ እምነት ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ብቻ አይደለም። እውስጡ ከህልውናና ከማንነት ጋር የተያያዙ ብዙ እሴቶች አሉት። ኢትዮጵያዊነት አይሰጥም፣ አይነጠቅም፣ አይበላለጥምም። ባራክ ሁሴን ኦባማ የአሜሪካን ፕሬዝደንት በሆነበት በዚህ ዘመን ከጉልታዊነት በታች ዘቅጠው የዘር ጥያቄ የሚያነሱ እዛው በዘቀጡበት ተጉነፍንፈው እንዲቀሩ መተው እንጂ ከነሱ ጋር እስጥ አገባ አያስፈልግም።

ለማጠቃለል ያህል ለጋዜጠኛው ማስታውሻ ከ 5 ውስጥ 4.5 ዛፍ ስጥቼ
P P P P p

የሚከተለውን እላለሁ...

እዚህ መድርክ ላይ መሳተፍ ከጀመርኩ ጀምሮ ጎጠኝነት በእካል ይሁን በመንፈስ ሲንቀሳቀስ አይቼ አላውቅም። ይሁን እንጂ አራማጆቹ በየስርቻው መፈልፈላቸውን ስለማውቅ አንድ ቀን ዋርካ ስነጽሁፍ መድርከ ላይ ብቅ ይል ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ። ከጎጥኝነት በታች የዘቀጠ አጥንት ቆጣሪ ይነሳል ብዬ ግን በጭራሽ ጠብቄ አላውቅም።

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby የጋሽ ለማልጅ » Sat Feb 14, 2009 5:00 am

password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ
የጋሽ ለማልጅ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Sun Feb 08, 2009 8:05 am

Postby የጋሽ ለማልጅ » Sat Feb 14, 2009 5:16 am

ሀሪኬን እውነት እልሀለሁ መጻፉን እንክት አድርጌ ነው ያነበብኩት ግን እንዳንተ በጅል ልቦና አላነበኩትም:: ከባድ ጥንቃቄን እያረኩ እያስተነተንኩ ነው የማነበው ገባህ እንደዚ ሴንሲቲቭ ኢሹ ይዞ የተነሳን ጽሁፍ እንደ ማሞ ቂሎ መጻፍ ተረረም አድርገህ አታነብም:: በርግጥ ወንድሜ ሙዝ እንደጻፈው አቶ ተስፋዬ ገብረአብ በጭምጭምታ ስንሰማቸውን የነበሩ የፖለቲካ ትኩሳቶችን ነው ደግሞ የነገረን:: ያን ያህል አፈነዳው የሚባል ከባድ ነቅናቂ ሚስጥር ካለመኖሩም በላይ እራሱን እንደ ታዋቂው የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም 24 አክተር 'Jack Bauer' ነቄና ስለላ እርፍናዎችን ከኔ በላይ ላሳር ያለ ይመስላል:: ምናልባትም ለመጻሀፉ ማጣፈጫነት 24 ፊልምን ሳያቋርጥ ሁሉንም ሲዝኖች አይቶም ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ ቢያረገውም አይገርመኝም የ ደ.ዘ. ከተፎ ስለሆነ:: <<<<<((የአምቦውን አድባር አቶድ ደራራን ከላንድክሩዘር ውስጥ አፈሙዝ አሾልኮ የተገደለበት, ከባለሚስጥሩ ጀማል ጋር ወረቀት እንካ ሲለው በጥርጣሬ እምቢኝ ብሎ ቶሎ ሲለያዩ ጭለማ ውስጥ ተሸሽጎ አበይት አበይት ሚስጥሮቹን የቸከቸከው ምናልባትም bourne identitiy ዋና ገጸባህሪ 'ጄሰን ቡርን' እየተወነ አይነት ነገር የምታነብ ይመስልሀል:: ደሞ ምንድነው በታሪክ ውስጥ ያሉ ገጸባህርያቶች በሙሉ ሞቱ በሰበሱ ብለህ እርምህን ስታወጣ አለበለዛም በባሌም በቦሌም አይገናኙ በቃ ብለህ ከንፈርህን መጠህ ስታበቃ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከተስፍሽ ጋር ይገናኙና በሞቅታ ሰላምታ ሲለዋወጡ ታነባለህ:: የሉሳካዋ ክልስ, ኢብሳ, ላሊበላ ሬስቶራንት ያገኘው የጦርሜዳው ሰውዬ, ጆግራፊ አስተማሪዋ, የመስፍን ወልደማርያም ክላስሜት ሰውዬ, እስፖርት ዘጋቢነት ሊቀጠር የመጣው ተጋራፊ መምህር :lol:

ወቸው good
የጋሽ ለማልጅ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Sun Feb 08, 2009 8:05 am

Postby ሀሪከን2 » Sat Feb 14, 2009 6:19 am

የጋሽ ለማልጅ wrote:password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ

ቅቅቅ ነገሮችን እንደ አንተ አጣሞ ያላየ ሁሉ ሻቢያ ነው አይደል?
የምር ከልቤ አሳዝንከኝ :lol: በውስጥህ ያለው ችግርህ የዚህን ጹሁፍ መልካም ገጽታ እንዳታይ ስላደረገክ :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ሀሪከን2 » Sat Feb 14, 2009 6:28 am

ሙዝ1
ቂቂቂ ... ሰልምሽ ከዚህ መጽሀፍ ጋ ፍቅር የወደቅሽ ትመስያለሽ ? ...በሩጫ አነበብኩት .... ቂቂቂ .... ምንም ያልተሰማ አዲስ ነገር የለም

ምንም ያልተሰማ ባልከው እንኴን አልስማማም 8 ትልቁ ቁመነገር እኮ በወሬ ስንሰማው የነበረውን ሩመር በቦታው ተገኝቶ እንደሰማ እና እንዳየ መጻፉ ነው

በተረፈ ከፓለቲካው ወጣ ብየ ደግሞ ጽሁፉን እንደ ጸሀፊ ብቻ ሳየው ደግሞ በአጻጻፍ ውበቱ ከልቤ አስደንቆኛል ደራሲው ያለ ምንም ማጋነን he is the best ethiopian story teller [/quote]
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ሾተል » Sat Feb 14, 2009 11:01 am

የጋሽ ለማልጅ wrote:password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ


የሚያሳዝነኝ እንዳንተ ካለ መላጣ አንጎል ---- ባዶ ቅል ራስ ጋር አብሬ እዚች አለም መፈጠሬ ነው::በእውነት ነው የምልህ እንዳንተ ያለው ተራ ቆሻሻ ለራሱም ሆነ ለትውልድ ሸክም ጭንቅላት አልባ ተጠራርጎ ከሞተ በሁዋላ ነበር መፈጠር ያለብኝ::ወይም ከዛ በፊት::ፖለቲካ ሩም ውስጥ ያልሆነ ነገር ስትዘባርቅ በነጥብ በነጥብ ክብርነታችን ባዶነትህን አሳወቀኽ::እንደገና እዚህ መጥተህ ከፓስዎርድ የጥፍር ቆሻሻ ጋር የማትመደብ ሰው ፓስዎርድን የተናገርክ መስሎህ እራስህን ታስገምትልኛለህ::

እናትህ ትበዳና ጥቅምህ የተነካ የደርግ ሰው በላ የጥበቃ ጉዋደ ወይም 10 አለቃ ወታደር ነበርክ መሰል::ሻኢቢያ ሆነ ወያኔ ኢትዮዽያን ሲቆጣጠሩ አንተ የት ነበርክ?አገርን ያህል ነገር እናስተዳድራለን አንድነትዋን እንጠብቃለን ብላችሁ ያለእውቀታችሁ ስልጣን ያዛችሁ::ከዛ ጠላታችሁን ትታችሁ እንደ በአሉ ግርማ ያለን በቀላሉ ሊተካ የማይችል ደራሲ ስትገሉ የድሀን ልጅ በየመንገዱ ኢሀፓ ኢድዩ መኢሶን እያላችሁ ስትረፈርፉ ሻኢቢያና ወያኔ ቂጣችሁን ገልበው አገራችንን ይዘው ደስ ያላቸውን ገንጥለው ቁጭ አሉ::እና ሻኢቢያ ወያኔ እያልክ ከምታላዝን የዛን ጊዜ ቀበቶህን ጠበቅ አድርገኽ በተዋጋህ ነበር::ቅዘናም ሁላ::አገራችን ውድቀት ውስጥ ገብታ 100 አመት ወደሁዋላ እንድትሄድ ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ::እንደዚህ የወያነ መጫወቻ እንድትሆን::

አብዮት ብላችሁ 17 አመት ከምታላዝኑብን ስልጣን ለሚገባው ስልጣን ሰጥታችሁት ቢሆን ኖሮ ወያኔም ሻኢቢያም አይኖርም ነበር::እኛም አንሰደድም ነበር::የኢትዮዽያና የኤርትራ ችግር ደም በመፋሰስ ሳይሆን በሰላም ተፈትቶ ዛሬ ኤርትራዊ ነው ሻኢቢያ ነው የምትለው ስድብ አይሉት ምርቃት ነገር ባልኖረና እንደጠላት የሰውን ልጅ ባላየኽ ነበር::

ንፍሮ ጭንቅላት ብቻ::እነ እውነት ነው የምለው አስጠላችሁኝ::ምናለ እንደአንተ የሚያስቡትን ኤቦላ በጨረሳችሁ::

መጀመርያ መሪያችን ናቸው የምትሏቸው ዘመነኛ የቡድናችሁ መሪዎች ወንጀለኞች እንደሆኑና ቀን ሲመጣ ለፍርድ ከሚቀርበው ወያኔ ጎን እንደሚቆሙ ታውቅ ይሆን?ትላንት ወያኔ ጋር የመገንጠል ሆነ አገር የማውደም ፖሊሲ ሲያረቁና አገራችንን ጫካ ሆነው ሲወጉ የነበሩ ናቸው ዛሬ በቅይጥ ቅንጅት ብላ ብላ ስም መሪ ሆነው የተቀመጡት::ማስረጃ አለን::ከራሳቸው አንደበት የወጣ::

እና አንተ የጋሽ ለማ ልጅ ማገናዘብን ተማር::ክቡር ፓስዎርድ ከላይ የጻፈውን እስቲ ደጋግመህ አንብበው::-ትልቅ እውቀት ይሆንሀል::ምትጫወተው እራስህን ለማስገመት ያህል ነው::እንደዚህ ካለ ጭንቅላት ካለው ሰው ተማር::እስቲ አንብበው...የዘር ማንዘርህ አንጎል በቀዶ ጥገና ወጥቶ ትቲ ላይ ቢዘረገፍ የዚህን ክቡር ታላቅ ሰው ጭንቅላት አያክልምና አቅምህን እወቅ::----::ምፓስዎርድ ምን እንደጻፈ እንኩዋን አልተረዳህም ....እሱ ያለው ፖለቲካ አይደል....የጻፈው እኮ ስለድርሰቱ ውበት የአጻጻፍ ተሰጦ ማስታወሻ ጽሁፍን እንዴት በልብወለድ ያጻጻፍ ዘዴ መቼት አበጅቶለት ደራሲው እንደጻፈ ነው::ለጭውውቱ ወይም ዲያሎጉ ውበት እንደዘራበት....ልብ አንጠልጣይ ድርሰት መሆኑን ነው እንጂ እኔ እንደተረዳሁት ፓስዎርድ ስለምትግማሙበትና መቼም ስለማታሸንፉት የፖለቲካ ዲስኩራችሁ አይደለም::

እስቲ መለስ ዜናዊ ሆነ ኢሳያስ አፍወርቂ እንዲሁም መንግስቱ ሀይለማርያም መጽሀፍ ይጻፉ....የሚደነቅ ነገር ካለው መጽሀፉ እንክት አድርጌ በበኩሌ አደንቃለሁ::የግድ እንትናን ስለምጠላው ወይም ከጠላቶቼ ጎራ ስለመደብኩት የፈለገውን ጥሩ ይስራ መደነቅ የለበትም ነው?

ዲያስፖራዎች ከዚህ አስተሳሰብ ውጡና በነጻ አስቡ ወይም በነጻ የሚያስብን ሰው ለመገደብ አትሞክሩ::

እንደገባህ ወይም መሰሎችህ እንደገባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ወይም እውቀት ይግባባችሁ....አይምሯችሁ ካለማሰብ ወደማሰብ ይሸጋገር ወይም አትጠቅሙምና መኪና እላያችሁ ላይ ይውጣባችሁ::

ኢትዮዽያ ኤርትራ ወንድምና ወንድም እህትና እህት ናቸው::አንድ ቀን ደግሞ አንድ ሆነው እንደድሮው ተጋብተው ተፋቅረው ይኖራሉ::አምላክ ያንን ያድርግልን::

ሾተል ነን.......አለም አንድ በመሆንዋ የሚያምን....
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Feb 14, 2009 12:39 pm

የጋሽ ለማልጅ wrote:password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ


ማነህ አንተ የንግዴ ልጅ የጋሽ ለማልጅ....ከምንምና ከማንም በላይ የዘረኝነት ነቀርሳ እንደያዘኽ ፖለቲካ ሩም ጽፌልህ ነበር::ምን አልባት እረስተኸው ከሆነ ዳግም ታነበው ዘንድ ከታች ለጥፌልሀለሁ....ምን አልባት እንዳንተ ያሉ ጎጠኞች ይሄንን ካላነበቡት መልክቴ ለነሱም ይድረሳቸው::

ሾተል

ፖሰት የተደረገ: ሰኞ Feb 09, 2009 11:41 pmhttp://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... c&start=45

የአቶ ለማ ልጅ ....

ሳስብህ ሀይለኛ ዘረኛ ነገር ነህ ...አንተንም ሳስብህ ላንተ ኢትዮዽያ ማለት አማራ ብቻ ይመስለኛል ...እንዴው እንዳትገመት ትግሬን ወረፈ ኦሮሞን ነካካ አልክና ስለአማራው የጻፈው ላይ አጥብቀኽ አማረርክ .......ግን ሰውየው ምን ብሎ እንደጻፈ እንኩዋን አጥብቀኽ አላገናዘብክም ....ጎንደሬው መንግስትን በቅኔው ሰደበው ብሎ ጎንደሬ ምን ያህል የስነጽሁፍ አገርና የባለቅኔዎች አገር መሆኑን ከግጥማቸው ቀንጥቦ ሁሉ አሳይቶ ነግሮናል ....ግጥሙን ካነበብከው እንዴት ሀይለኛና የጠለቀ ነው :.....መንግስትን ለዛውም የመንግስት ባለስልጣኖችን ስም እየጠቀሰ ሙልጭ አድርጎ የሚሰድብ የጎንደሬ ቅኔ ...

ዘረኛ ነህ ያልኩህ ወንዳታው ጎጃሜን ተማረከ ይለዋል ያልከውን አይቼና ስለ አማራው አጥብቀህ መማረርህ ነው ""ምናለ በኢትዮዽያ አንድነት አምነህ ቢሆን ኖሮ ወንዳታው ኢትዮዽያን ባልክ ....የራሳችንን ሳናውቅ ሰውን ስንወነጅል ማለት ይሄ ነው ....ደራሲውስ ስለእራሱ እራሱ ስለነገረን ማን እንደሆነ ማወቅ ቀላል ነው ....ሲሰራለት የነበረው ድርጅት ማን እንደሆነም ስለምናውቅ መደጋገሙ አያስፈልግም ....ነገር ግን እንደአንተ ያለ ሳያውቀው ሌላውን የለየለት ዘረኛውን ሲሳደብ ይቆይና እራሱም ሆኖ መገኘቱ ነው ....

እና ሰለየለት ዘረኛ ደጋግመህ ከምታወራ አንተ ውስጥ የተሰነቀረውን ዘረኝነት መንቅረኽ አውጣና እንደክብርነታችን በአንድ ኢትዮዽያ እመን ""

ጎጃሜ ማን ነውና ነው የማይማረከው ?ጎጃሜ ከሌላው የደርግ ወታደር የተለየ ያደረገው ማነው ?በእኔ በእኔ ሁሉም ኢትዮዽያኖች ናቸው :....ስለዚህ የወለጋው በጦርነት ከተፈታ አንድ የመቶ ላይ ካሉ ጎጃሜውም መፈታቱ አይቀርም .....ወላይታው ከተገደለ ጎጃሜውም መገደሉ አይቀርም ....በእኔ ግን ሁሉም አንድ ኢትዮዽያዊ ናቸው ""...ጎጃሜም ተማርኮአል ....ትግሬም ተማርኮአል ወይም አደሬውም ተማርኮዋል .....ሌላውም ዘር እንደዚሁ ""

እና በውስጣችን ውስጥ የተደበቀ ዘረኝነታችንን ቀድመን እንፋቅ ......

ሾተል ነ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Feb 14, 2009 12:52 pm

የጋሽ ለማልጅ wrote:password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ


አንተ የጋሽ ለማ ልጅ አንተ ማወቅ የተሳነህ እንደዚህ ብዬ መክሬህ ነበር::ምክሬን እናትህ ---- ውስጥ ደብቀኸው ይሆን እንጃ አመከንክብኝ::በል ደግመው አንብበው::ምን አልባት ሻእቢያ የቂጥህን ድንግል ባንድ ጋንታ ወታደሮቹ አስወስዶብሀል መሰለኝ::ሻእቢያ ሻእቢያ እያልክ ልትሞት ነው::የሻእቢያ ምቀኛቸው ነህ እንዴ?እነሱ ሲመሰረቱ ...ተመስርተው ጦር ሲሆኑ...ጦር ሆነው ተዋጊ ሲሆኑ...ተዋግተው ኤርትራን ሲገነጥሉ የት ነበርክ?ለምን ስብሰባ ላይና ግምገማ ላይ እያሉ በአንድ ቦንብ አላዳፈንካቸውም ነበር?ይሄኔ አባትህ ኢትዮዽያን ከሸጡዋት አንዱ አያትህ የጣልያን ባንዳ ቅድመ አያትህ እንደዚሁ የቴዎድሮስ ወታደሮችን ምንሽር እየሰረቀ ለሽፍቶች የሚሸጥ ነበር::

ወዲ ሸርሙጣ ይላል ትግሬ ሲናደድ እና እኔም ያንንኑ ብዬኻለሁ::እስቲ ወደመከርኩህ ምክር


ሾተል
ማክሰ Feb 10, 2009 3:12 am ርዕስ ፖሰት ያድርጉ
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... c&start=45

ወንድሜ አንድ ነገር ልንገርህ ....ሁል ጊዜ ነገሮችን ሳይድ ይዘንና ከቁስላችን ጋር እያነጻጸርን እንዲሁም ጥላቻችንን እያነገስን ነገሮችን የምናይ ከሆነ መቼም ይሁን ለሚዛናዊ እይታና ፍርድ አንበቃም .....ምንም ደግ ነገር ተሰራ የተቃወምናቸው ሰዎች ከሆኑ ነገሩን የሰሩት የነሱ ጥሩ ስራ ሳይሆን የሚታየን ለነሱ ያለን ጥላቻ ,ትላንት የሰሩት መጥፎ ነገር ,ፈጥረው ያሰቃዩን ቁስል ወዘተ ነው .....እንደዛ ከሆነ ደግሞ መቼም ቢሆን በነጻ ማሰብ አንችልም ....ሁሌም ትላንትናው ይጎትተናል .......ስለዚህ ሁሉም ነገር ኔጌቲቭ ይሆንብናልና እኔ ሁላችንን የምመክረው ነገሮችን በነጻነት በምንም ነገር ሳንሸበብ የማየቱ ልምድ ይኑረን .....እንደዛ ካየን በሁዋላ አመዛዝነን እውነቱን ካወቅን በሁዋላ ወደ ድሮም አቁዋማችን መሄድ እንችላለን .....ግን አይምሯችንን ነጻ ሆኖ እንዲያውቅና እንዲያገናዝብ እንፍቀድለት ......

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby early_bird ! » Sat Feb 14, 2009 3:56 pm

ሾተል wrote:
የጋሽ ለማልጅ wrote:password ድብን ያልክ ሻቢያ ነህ


አንተ የጋሽ ለማ ልጅ አንተ ማወቅ የተሳነህ እንደዚህ ብዬ መክሬህ ነበር::ምክሬን እናትህ ---- ውስጥ ደብቀኸው ይሆን እንጃ አመከንክብኝ::በል ደግመው አንብበው::ምን አልባት ሻእቢያ የቂጥህን ድንግል ባንድ ጋንታ ወታደሮቹ አስወስዶብሀል መሰለኝ::ሻእቢያ ሻእቢያ እያልክ ልትሞት ነው::የሻእቢያ ምቀኛቸው ነህ እንዴ?እነሱ ሲመሰረቱ ...ተመስርተው ጦር ሲሆኑ...ጦር ሆነው ተዋጊ ሲሆኑ...ተዋግተው ኤርትራን ሲገነጥሉ የት ነበርክ?ለምን ስብሰባ ላይና ግምገማ ላይ እያሉ በአንድ ቦንብ አላዳፈንካቸውም ነበር?ይሄኔ አባትህ ኢትዮዽያን ከሸጡዋት አንዱ አያትህ የጣልያን ባንዳ ቅድመ አያትህ እንደዚሁ የቴዎድሮስ ወታደሮችን ምንሽር እየሰረቀ ለሽፍቶች የሚሸጥ ነበር::

ወዲ ሸርሙጣ ይላል ትግሬ ሲናደድ እና እኔም ያንንኑ ብዬኻለሁ::እስቲ ወደመከርኩህ ምክር


ሾተል
ማክሰ Feb 10, 2009 3:12 am ርዕስ ፖሰት ያድርጉ
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... c&start=45

ወንድሜ አንድ ነገር ልንገርህ ....ሁል ጊዜ ነገሮችን ሳይድ ይዘንና ከቁስላችን ጋር እያነጻጸርን እንዲሁም ጥላቻችንን እያነገስን ነገሮችን የምናይ ከሆነ መቼም ይሁን ለሚዛናዊ እይታና ፍርድ አንበቃም .....ምንም ደግ ነገር ተሰራ የተቃወምናቸው ሰዎች ከሆኑ ነገሩን የሰሩት የነሱ ጥሩ ስራ ሳይሆን የሚታየን ለነሱ ያለን ጥላቻ ,ትላንት የሰሩት መጥፎ ነገር ,ፈጥረው ያሰቃዩን ቁስል ወዘተ ነው .....እንደዛ ከሆነ ደግሞ መቼም ቢሆን በነጻ ማሰብ አንችልም ....ሁሌም ትላንትናው ይጎትተናል .......ስለዚህ ሁሉም ነገር ኔጌቲቭ ይሆንብናልና እኔ ሁላችንን የምመክረው ነገሮችን በነጻነት በምንም ነገር ሳንሸበብ የማየቱ ልምድ ይኑረን .....እንደዛ ካየን በሁዋላ አመዛዝነን እውነቱን ካወቅን በሁዋላ ወደ ድሮም አቁዋማችን መሄድ እንችላለን .....ግን አይምሯችንን ነጻ ሆኖ እንዲያውቅና እንዲያገናዝብ እንፍቀድለት ......

ሾተል


ሾተልዮ..... ለጋሽ ለማ ልጅ የሰጠህው ሌሰን አሪፍ ነው አፕላይ ካረገው ማለት ነው :D
:D
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby ሾተል » Sat Feb 14, 2009 4:04 pm

የጋዜጠኛው ማስታወሻ መጽሀፍ ደራሲ በመጽሀፉ ገጽ 56 ላይ ስለመቁሰሉና ቁስሉን ታክመው ስለነበረችው ማሚቴ ጠቅሶልናል::ታድያ ቁስሉን ስታክመው ሁልጊዜ አንድ የወያኔ የትግል ዘፈን ታንጎራጉር እንደነበረ አጫውቶናል::እሱም ውፈር ተበገስ ወይም ተነስ ዝመት የሚል ዘፈን ታንጎራጉር ነበር::ታድያ እንደምንም ፈልጌ ዩ ትዩብ ላይ ዘፈኑን አግኝቼዋለሁና ከ 4 አቅጣጫ ማየት የተሳናችሁ እንዲሁም የናንተን ብቻ ማንበብ ማዳመጥ መስማት ለምትፈልጉ ትምህርት ይሆናችሁ ዘንድ እኔ እንዳየሁት ዘፈኑን እዩት....አብራችሁ ዝፈኑ....ይሄ ታሪክ ስለሆነ ማወቁ ጥሩ ነው::

እስቲ ወደ ዘፈኑ

ውፈር ተበገስ

http://www.youtube.com/watch?v=QVeX-qZk ... re=related

ከዚህ በታች ደግሞ አንጋፋው ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ጦሩን ግንባር ድረስ ሄዶ ያበረታታና ያነሳሳ እንደነበር የሚያሳየውንም አብረን እንመልከት::ሁሉንም ብናውቅ ምንም አይለንም::ሁሉም የኛው ናቸውና::ፖለቲካ ለያየን እንጂ ከኛው እኛ ላይ ናቸው::ይሰመርበት::ከኛው እኛ ላይ::

http://www.youtube.com/watch?v=c1pL70X4 ... re=related

የወያኔው ተክላይ መስፍን
http://www.youtube.com/watch?v=mH3n7a2t ... re=related

የዶክተር ጥላሁን
http://www.youtube.com/watch?v=Jx3pDRMe ... re=related

አንድ አቅጣጫ ይዛችሁ በጥላቻ ተተብትባችሁ ጎጠኝነትና ጥላቻ በውስጣችሁ ለሚያሰቃያችሁ ባዶዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ ነውና ምርጫዬን እንደወደዳችሁት ነው::ወያኔ ጎጠኛ ነው እያልን ተቃዋሚዎቹ ከሱ በልጠን መገኘታችን የሚገርም ነው::

ሾተል ነን...ጥላቻ መቼም የማያሸንፈን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests