የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ስርርር » Tue May 04, 2010 10:55 pm

አይጥ አይጥን ቢያሸት

ላሞች ባልዋሉበት ኩበትን ለቀማ
ሖምጣጤን ቢያቀርቡ ውሀ ለተጠማ

በዚህ በዘመኑ....ሌባ በበዛበት
ምን ያስገርመናል .... አይጥ አይጥን ቢያሸት

ከቶ ለምንድነው ..... እንዲህ መገረሜ
ፍቅርን ስዘራለት ......ቢጠላኝ ወንድሜ

አይኖቼ ቢጠቡ.....ማየቱ ቢሳነኝ
ባምሮ ህሊናዬ....ማየት መነው አቃተኝ ???

አይጥ አይጥን ቢያሸት...አይጥ በሌለበት
ብን...እልም...ይላል ደመት ሲመጣበት
Last edited by ስርርር on Wed May 05, 2010 10:52 pm, edited 2 times in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Tue May 04, 2010 11:08 pm

አፍንጫን ሲመቱት

ቻይናዎች አይናቸው ጠቦ አስቸገረ
ሲስቁ እልም ይላል....እንዳልተፈጠረ

አፍንጫን ሲመቱት ..... ይባል ነበር ድሮ
አይን ስለሚያለቅስ ...... ለጎረቤቱ አዝኖ

እንዲህ ሆነላችሁ ....... ዛሬና ዘንድሮ
አይን ሲጠብ ተሰማ ...... ያፍንጫ ሮሮ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ቻይና ገ/ማርያ » Wed May 05, 2010 12:37 am

ለመልስህ በጣም አመሰግናለው!!!
"አይጥ ሸተተኝ" በሚለውን ግን የተገናኘን አልመሰለኝም!
ፈሊጡን አታውቀውም እንዳልል ሰውየው ስርርርርርርርርርርር....
ያልተረዳህ መሰለህ...
ግን (ለምሳሌ ያህል) ይህ ያንተ ነው????? የስ ኦር ኖ!

"ባዶ የቮድካ ጠርሙስ .....የሲጋራ ቁርጥራጮችና እዝህም እዚያም የወደቁ ያልታጠቡ ካልሲዎች የቤቱን ወለል ሞልተውታል ::
"

ቆንጆ ብ እ ር!
ከ ስርርርርርርርርርርርርርር
>>>>>....
ቻይና ገ/ማርያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 05, 2009 6:05 pm

Postby yodit » Wed May 05, 2010 6:32 am

ቻይና ገ/ማርያ�� wrote:ስርርርርርርርርርርርር......
በጣም አሪፍ ነው ግን አንዳንዶቹን አረፍተነገር, ህረግ ሳብላላቸው "አይጥ ሸተተኝ"

እውነት ሁሉም የስርርርርርርርርርርር...ስራነው???
ወይስ ከሌላ አምጥተህ ልታካፍለን??

ይመችህ

ስርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር

ስላም ቻይና ከሌላ አምጥቶ እዚህ ከለጠፈ ከሌላ እንዳመጣው ያመጣበትን መለጠፍ አለበት ባይ ነኝ:: እንዴት ነው ኮፒ ራይት የሚባል በገር አለ አደል እንዴ::
yodit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Sat Oct 25, 2003 9:43 pm

Postby ቻይና ገ/ማርያ » Wed May 05, 2010 3:31 pm

yodit wrote:
ቻይና ገ/ማርያ�� wrote:ስርርርርርርርርርርርር......
በጣም አሪፍ ነው ግን አንዳንዶቹን አረፍተነገር, ህረግ ሳብላላቸው "አይጥ ሸተተኝ"

እውነት ሁሉም የስርርርርርርርርርርር...ስራነው???
ወይስ ከሌላ አምጥተህ ልታካፍለን??

ይመችህ

ስርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር

ስላም ቻይና ከሌላ አምጥቶ እዚህ ከለጠፈ ከሌላ እንዳመጣው ያመጣበትን መለጠፍ አለበት ባይ ነኝ:: እንዴት ነው ኮፒ ራይት የሚባል በገር አለ አደል እንዴ::

ሰላም ዮዲት!

ማካፈል መልካም ነው! ስራወቹ ይመቻሉ:: ግን ... ኮፒ ራይት....!?1?!
>>>>>....
ቻይና ገ/ማርያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 05, 2009 6:05 pm

Postby ስርርር » Wed May 05, 2010 4:55 pm

ህምምም!

አርምሞ ... ድምምታ
ፀጥ ረጭ.... ግርምታ
ዝም ዝም .... ዝምታ
የሰላም .... መኝታ

ብድግ .... እንደገና
ድብልቅልቅ ....ይልና
እሪታና ጩኸት... ይበረክትና

ውስጤ ... ተተራምሶ
አምሮዬ ... ታምሶ

ሁካታው ... ሲጋጋል
መንፈሴ ... ሲማልል

ውስጤ አምጦ አምጦ...በሲቃ ስወልደው
የመንፈሴን ጉልበት....ጭንቀቴ ሲያደክመው

በምጥ ተገድጄ....ልጅን ብወልድ እኔ
ያንቺ አይደለም ካለኝ....አዋላጅ ወገኔ

ምን እላለሁ ሌላ .... ዝምታ ዝምታ
ህምምም ህምም.....ግርምታ ድምምታ
....................... ድምምታ ህምምምታ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

የስርርር መጣጥፎች 11

Postby ስርርር » Wed May 05, 2010 7:44 pm

ህዳሤ

የግንቦት ፀሀይ ጉልበትዋን የምታሳይ ይመስል በሙሉ ሀይሏ ወጥታለች:: የሞተር ጀልባዎችና አሳን ፍለጋ የሚዋኙ ዳክየዎች የሚያሰሙት ድምፅ ልዩ ሐሴትን ይሰጣል:: ማእባሉም ብድግ እያለ ሲፈርጥ.....እንደገና ተነስቶ በአራትና ባምስት ረድፍ ሆኖ ወደ ሀይቁ ዳርቻ ሲገሰግስ....ደግሞ አሸዋውን ወደዳር ሲገፋ.... የሚፈጥረው ትእይንት እውነተኛ የአይን ምግብ ነው:: የሀይቁ ውሀ በእጅ ጨለፍ አድርገው ቢያዩት ጥርት ያለ ሲሆን:- እንዲሁ ሲታይ ግን ወርቃማ ነው:: ላንጋኖ! ከሐይቁ ዳርቻ ላይ እዚህም እዚያም የሚዋኙ.... የሚንቦጫረቁ.... ሰዎች አሉ::

"በወርቃማ ውሀ...ይንቦጫረቃል....እሱ ፍቅር እንጂ መዋኘት ይት ያውቃል" .. ብላ ነው ያዜመችው ድምፃዊቷ???

ብዙ ጥንዶችም በሀይቁ ዳር ሆነው የፍቅር ወሬ ይሰልቃሉ:: ይስቃሉ.. ይዘምራሉ...የፍቅር ዜማ! ደግሞ ይሳሳማሉ...ይላላሳሉ.....::

ከወላጆቻቸው ጋር የመጡ ህፃናትም ውሀ እየተራጩ ይጫወታሉ::

ትዝታ በሀይቁ ዳርቻ ቆማለች:: ቀደም ብላ ዋኝታ ስለነበር በውሀ ርሶ የነበረውን ረጅም ፀጉሯን የፀሀይዋ ጉልበት ኩችር አድርጎ ፍሪዝ አስመስሎታል:: ሰማያዊ የጡት ማስያዣዋ ዳሌዋ ላይ እንደነገሩ ካሸረጠችው ብጣቂ ጨርቅ ጋር ተስማምቷል:: አይኗን የሸፈነው ጥቁር መነፅር ቀይ ፊቷን ቢያጎላውም ለፀሀይ መከላከያ የተቀባችው ቅባት ነጭ አስመስሏታል::

በፍፁም ዝምታ ሀይቁን አሻግራ ትመለከታለች:: ዛሬን ብቻዋን እዚህ ብትሆንም ከዛሬ 3 ዓመታት በፊት ወደህዋላ በግዜ ፈረስ ተጉዛ እዚሁ ቦታ ላይ ቆማለች::

የአሸዋው ግለት ረመጥ ላይ እንደቆመች ሁሉ በእግሮችዋ ጣቶች መሀል ተሰምቷታል:: ነገርግን ውስጧን ሰቅዞ የያዛት የሀዘን እንጉርጉሮ, ብቸኝነት, የሶስት አመት ከንቱ ትዳርዋ..... ከአሸዋው ግለት የበለጠ ነበር::

"Damn you Kasa!" .. አለች ባሏን እያሰበች:: እዚች ቦታ የዛሬ ሶስት አመት ለጫጉላ ሽርሽር (ሀኒ ሙን) መጥተው ነበር:: እዚሁ ቦታ ቆመው... ላይለያት! ላትለየው የተገባቡት ቃል ትዝ እያላት ውስጥ ውስጧን አብሰለሰላት:: ሶስት አመት የገነባችው ትዳር ፍሬ አልባ መሆኑ ሲታሰባት...ተቆጨች:: የሱ እናት....."በቅሎ" እያሉ የሚሰድቧትን ባስታወሰች ቁጥር በእልህ ሆድ ባስ ይላታል::

ዛሬ ግን ወርቃማውን ውሀ እያየች ወደውስጧ አነባች:: በሀይቁ ዳር በጋለ አሸዋ ላይ ቆማ.... ቆዘመች:: ተከዘች....ትዝታ! በትዝታ ፈረስ እስኪበቃት ጋለበች::

"ይበለኝ.....የጄን ነው ያገኘሁት...." የሚለው የጥበቡ ወርቅዬ ዘፈን ባምሮዋ ተመላለሰ". ... .. አሁን ወደውስጥ ማንባቷ ቀርቶ አይኖችዋ መረጣጠብ ጀመሩ:: በሆድዋ ውስጥ ያለው ትንሹ ካሳም ገልበጥ እንደማለት አለ ::.... እናቱን ለማባበል ይመስል::

"አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው..." የሚለው የመዝሙረ-ዳዊት ጥቅስ ትዝ አላትና ሆድዋን ደበስበስ አደረገች...አንተነህ እንደማለት!

"ከእንግዲህማ ጎብዝ መሆን አለብኝ:: ልጄን ብቻዬን አሳድገዋለሁ.... ካሳ በቃሀኝ...." ትላለች እየደጋገመች::

ላንጋኖ ዋቢሸበሌ ሆቴል ከበረንዳው ላይ ሆኖ ትልቅ መፅሀፍ ያነብ የነበረ ሰውየ ድንገት መግነጢሳዊ የውበት ሀይል በሀይቁ ዳር ያየ ይመስል ተስፈንጥሮ ተነሳ:: አያት አተዋላት:: ጎመጃት!! "አይ ውበት!" እያለ ሲያስተውላት ቆይቶ የአሸዋው ግለት እያቃጠለው ወደሀይቁ ዳር ሄደ:: በቀረባት ቁጥር ስሜቱ እየነቃ "ውጣባት!" የሚል ስሜት ተፈታተነው:: 6 ሜትር ያህል ርቀት ሲቀረው ቆሞ ማድነቅን መረጠና እዚያው ባለበት ቆመ:: የሷ መቆዘም የተጋባበት ይመስል.... እሱም እዛው ፈዞ ቀረ::

ለብቻችን ትልቅ ግዛት ይገባናል የሚሉ የሚመስሉት ክብ መቀመጫዎችዋ, በለሙያ አናጢ የሰራው የአልጋ ሸንኮር የሚመስለው ባትዋ, ዳሌዋ.... ቁመትዋ.... በየተራ ውበቷን አደነቀ::

መለስ ብሎ የራሱን ፍቅር አሰባት:: ሚስቱን አሰባት.... በችኮላ የወሰነው ውሳኔ አሳፈረው...አሳዘነው:: አይኖቹ ሞጨሞጩ::

ትዝታ ድንገት ከገባችበት ትካዜ ነቃ አለች:: አንድ ሰው በእርግጥ ከህዋላዋ አለ:: ቀስ ብላ መነፅሯን አውልቃ ዞር ስትል ከሰውየው ጋር ተጋጩ....በአይናቸው:: ይህ ግጭት ትልቅ ብልጭታን ፈጠረ:: የዛሬ 3 ዓመት ባልዋን ስታገባ የነበራት ሙቀት ተመልሶ ውስጧ የገባ ይመስል ልቧ ጮቤ ረገጠች::

ውስጧ ""ተስፋ አለኝ....ወደፊት ተስፋ አለኝ.... ምናልባት ከዚህ ሰውዬ ጋር.... የተሰበረን ልብ የሚጠግን ፈጣሪ እሱ ያውቃል...." እያለ ብዙ ለፈለፈ::.

ሰውየው እንተዋወቅ በሚል አይነት እጆቹን ለሰላምታ ዘረጋ:: የተዘረጋውን እጅ በደስታ ጨበጠችው:: ምንም ቃላት ሳይለዋወጡ ተያይዘውም ወደሆቴሉ በረንዳ ተግዋዙ::

በዚያ ሆነው ..... ለባልዋ የነበራትን ፍቅር, የዛሬ ሶስት አመት እዚህ ቦታ ምን እንደተፈጠረ.... አሁን የ3 ወር እርጉዝ መሆንዋንና.... ባልዋ ደግሞ ልጅ እንደማይፈልግ::- በዚህም ምክንያት ከቤት እንዳስወጣት....ነገረችው:: ይህንን ሁሉ ስትነግረው ድምፅዋ በሲቃና በእልህ ይቆራረጥ ነበር:: አይኖችዋም ያነቡ ነበር::......ዛሬም ግን ባልዋን በጣም እንደምትወደው መናገሯን ቀጠለች....

"ሽሽሽሽሽሽ" በቃሽ አታልቅሺ..... አሁን ሁሉም አልፏል አላት:: ሊያቅፋት ወደሷ እየተጠጋ:: የድምፁ ቅላፄ... ሊያለቅስ የተዘጋጀ ህፃን ይመስላል:: ደነገጠችና ቀና ብላ አየችው:: ጉንጮቹ በእንባ ርሰዋል:: ይህንን ስታይ እሷም የባሰ ተነፋረቀች:: የህዋላ ዘመን ክፉ ገጠመኞቻቸውን በእንባ ያጥቡት ይመስል አንገት ላንገት ተቃቅፈው ተላቀሱ::
በይ ተነሽ ትዙ....ወደኔ ክፍል እንሂድ:: አላት ካሳ....

"ይቺን ቀን ህዳሴ ብያታለሁ..." አለች...በሚነፋነፍ ድምፅዋ::

"አ አ.... ህዳሴማ የልጀ ስም ነው:: ይልቅ ተነሽ ብዙ ስራ አለብኝ...." አለና አፈፍ አድርጎ ተሸከማት... ወደ አልጋው!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ትገብር

Postby ስርርር » Thu May 06, 2010 12:25 am

ዋርካኒ ትገብር

ባቲ እምርት እለት.... በአል ወተዝካር
ዮም መምር መፃ .....ፍስሀ ንግበር

ንቁም ወናፅምእ....ቃል እም መምርነ
ክሌሁ መምር.... ሀሴት ይሀበነ

ወዳሴ ወሀሴት .... ይደሉ ለከ
መምር ይሄይስ ..... እምኩሉ ቃልከ
ሀብ ጥበብ ወፍቅር......ንስርርር ገብርከ

ትገብር ዋርካኒ ...ፋሲካ ትገብር
ዮም ፍሰሀ ኮነ...በዝ ጥበብ ስርርር

ሰናይ እብለክሙ .... ናሁ ሰናይ ኮነ
ዮም ፋሲካ ገብራ---ዋርካኒ እምነ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby yodit » Thu May 06, 2010 2:49 am

ቻይና ገ/ማርያ�� wrote:
yodit wrote:
ቻይና ገ/ማርያ�� wrote:ስርርርርርርርርርርርር......
በጣም አሪፍ ነው ግን አንዳንዶቹን አረፍተነገር, ህረግ ሳብላላቸው "አይጥ ሸተተኝ"

እውነት ሁሉም የስርርርርርርርርርርር...ስራነው???
ወይስ ከሌላ አምጥተህ ልታካፍለን??

ይመችህ

ስርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር

ስላም ቻይና ከሌላ አምጥቶ እዚህ ከለጠፈ ከሌላ እንዳመጣው ያመጣበትን መለጠፍ አለበት ባይ ነኝ:: እንዴት ነው ኮፒ ራይት የሚባል በገር አለ አደል እንዴ::

ሰላም ዮዲት!

ማካፈል መልካም ነው! ስራወቹ ይመቻሉ:: ግን ... ኮፒ ራይት....!?1?!

ስላም ቻይና
እኔም ያለኩት እኮ ኮፒ ራይቱን ነው :lol: ይመቸው ምን አገባን እኛ እናንብብ::
yodit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Sat Oct 25, 2003 9:43 pm

Postby saron*** » Thu May 06, 2010 7:25 am

አይ ትዝታ ለምን ቶሎ አመነቹ እንደ መጀመርያው እንዳይፈነግላት ምስኪን .
saron***
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 168
Joined: Thu Apr 29, 2010 7:50 am

Re: የስርርር መጣጥፎች 11

Postby sleepless girl » Thu May 06, 2010 2:26 pm

ስርርር wrote:ህዳሤ

የግንቦት ፀሀይ ጉልበትዋን የምታሳይ ይመስል በሙሉ ሀይሏ ወጥታለች:: የሞተር ጀልባዎችና አሳን ፍለጋ የሚዋኙ ዳክየዎች የሚያሰሙት ድምፅ ልዩ ሐሴትን ይሰጣል:: ማእባሉም ብድግ እያለ ሲፈርጥ.....እንደገና ተነስቶ በአራትና ባምስት ረድፍ ሆኖ ወደ ሀይቁ ዳርቻ ሲገሰግስ....ደግሞ አሸዋውን ወደዳር ሲገፋ.... የሚፈጥረው ትእይንት እውነተኛ የአይን ምግብ ነው:: የሀይቁ ውሀ በእጅ ጨለፍ አድርገው ቢያዩት ጥርት ያለ ሲሆን:- እንዲሁ ሲታይ ግን ወርቃማ ነው:: ላንጋኖ! ከሐይቁ ዳርቻ ላይ እዚህም እዚያም የሚዋኙ.... የሚንቦጫረቁ.... ሰዎች አሉ::

"በወርቃማ ውሀ...ይንቦጫረቃል....እሱ ፍቅር እንጂ መዋኘት ይት ያውቃል" .. ብላ ነው ያዜመችው ድምፃዊቷ???

ብዙ ጥንዶችም በሀይቁ ዳር ሆነው የፍቅር ወሬ ይሰልቃሉ:: ይስቃሉ.. ይዘምራሉ...የፍቅር ዜማ! ደግሞ ይሳሳማሉ...ይላላሳሉ.....::

ከወላጆቻቸው ጋር የመጡ ህፃናትም ውሀ እየተራጩ ይጫወታሉ::

ትዝታ በሀይቁ ዳርቻ ቆማለች:: ቀደም ብላ ዋኝታ ስለነበር በውሀ ርሶ የነበረውን ረጅም ፀጉሯን የፀሀይዋ ጉልበት ኩችር አድርጎ ፍሪዝ አስመስሎታል:: ሰማያዊ የጡት ማስያዣዋ ዳሌዋ ላይ እንደነገሩ ካሸረጠችው ብጣቂ ጨርቅ ጋር ተስማምቷል:: አይኗን የሸፈነው ጥቁር መነፅር ቀይ ፊቷን ቢያጎላውም ለፀሀይ መከላከያ የተቀባችው ቅባት ነጭ አስመስሏታል::

በፍፁም ዝምታ ሀይቁን አሻግራ ትመለከታለች:: ዛሬን ብቻዋን እዚህ ብትሆንም ከዛሬ 3 ዓመታት በፊት ወደህዋላ በግዜ ፈረስ ተጉዛ እዚሁ ቦታ ላይ ቆማለች::

የአሸዋው ግለት ረመጥ ላይ እንደቆመች ሁሉ በእግሮችዋ ጣቶች መሀል ተሰምቷታል:: ነገርግን ውስጧን ሰቅዞ የያዛት የሀዘን እንጉርጉሮ, ብቸኝነት, የሶስት አመት ከንቱ ትዳርዋ..... ከአሸዋው ግለት የበለጠ ነበር::

"Damn you Kasa!" .. አለች ባሏን እያሰበች:: እዚች ቦታ የዛሬ ሶስት አመት ለጫጉላ ሽርሽር (ሀኒ ሙን) መጥተው ነበር:: እዚሁ ቦታ ቆመው... ላይለያት! ላትለየው የተገባቡት ቃል ትዝ እያላት ውስጥ ውስጧን አብሰለሰላት:: ሶስት አመት የገነባችው ትዳር ፍሬ አልባ መሆኑ ሲታሰባት...ተቆጨች:: የሱ እናት....."በቅሎ" እያሉ የሚሰድቧትን ባስታወሰች ቁጥር በእልህ ሆድ ባስ ይላታል::

ዛሬ ግን ወርቃማውን ውሀ እያየች ወደውስጧ አነባች:: በሀይቁ ዳር በጋለ አሸዋ ላይ ቆማ.... ቆዘመች:: ተከዘች....ትዝታ! በትዝታ ፈረስ እስኪበቃት ጋለበች::

"ይበለኝ.....የጄን ነው ያገኘሁት...." የሚለው የጥበቡ ወርቅዬ ዘፈን ባምሮዋ ተመላለሰ". ... .. አሁን ወደውስጥ ማንባቷ ቀርቶ አይኖችዋ መረጣጠብ ጀመሩ:: በሆድዋ ውስጥ ያለው ትንሹ ካሳም ገልበጥ እንደማለት አለ ::.... እናቱን ለማባበል ይመስል::

"አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው..." የሚለው የመዝሙረ-ዳዊት ጥቅስ ትዝ አላትና ሆድዋን ደበስበስ አደረገች...አንተነህ እንደማለት!

"ከእንግዲህማ ጎብዝ መሆን አለብኝ:: ልጄን ብቻዬን አሳድገዋለሁ.... ካሳ በቃሀኝ...." ትላለች እየደጋገመች::

ላንጋኖ ዋቢሸበሌ ሆቴል ከበረንዳው ላይ ሆኖ ትልቅ መፅሀፍ ያነብ የነበረ ሰውየ ድንገት መግነጢሳዊ የውበት ሀይል በሀይቁ ዳር ያየ ይመስል ተስፈንጥሮ ተነሳ:: አያት አተዋላት:: ጎመጃት!! "አይ ውበት!" እያለ ሲያስተውላት ቆይቶ የአሸዋው ግለት እያቃጠለው ወደሀይቁ ዳር ሄደ:: በቀረባት ቁጥር ስሜቱ እየነቃ "ውጣባት!" የሚል ስሜት ተፈታተነው:: 6 ሜትር ያህል ርቀት ሲቀረው ቆሞ ማድነቅን መረጠና እዚያው ባለበት ቆመ:: የሷ መቆዘም የተጋባበት ይመስል.... እሱም እዛው ፈዞ ቀረ::

ለብቻችን ትልቅ ግዛት ይገባናል የሚሉ የሚመስሉት ክብ መቀመጫዎችዋ, በለሙያ አናጢ የሰራው የአልጋ ሸንኮር የሚመስለው ባትዋ, ዳሌዋ.... ቁመትዋ.... በየተራ ውበቷን አደነቀ::

መለስ ብሎ የራሱን ፍቅር አሰባት:: ሚስቱን አሰባት.... በችኮላ የወሰነው ውሳኔ አሳፈረው...አሳዘነው:: አይኖቹ ሞጨሞጩ::

ትዝታ ድንገት ከገባችበት ትካዜ ነቃ አለች:: አንድ ሰው በእርግጥ ከህዋላዋ አለ:: ቀስ ብላ መነፅሯን አውልቃ ዞር ስትል ከሰውየው ጋር ተጋጩ....በአይናቸው:: ይህ ግጭት ትልቅ ብልጭታን ፈጠረ:: የዛሬ 3 ዓመት ባልዋን ስታገባ የነበራት ሙቀት ተመልሶ ውስጧ የገባ ይመስል ልቧ ጮቤ ረገጠች::

ውስጧ ""ተስፋ አለኝ....ወደፊት ተስፋ አለኝ.... ምናልባት ከዚህ ሰውዬ ጋር.... የተሰበረን ልብ የሚጠግን ፈጣሪ እሱ ያውቃል...." እያለ ብዙ ለፈለፈ::.

ሰውየው እንተዋወቅ በሚል አይነት እጆቹን ለሰላምታ ዘረጋ:: የተዘረጋውን እጅ በደስታ ጨበጠችው:: ምንም ቃላት ሳይለዋወጡ ተያይዘውም ወደሆቴሉ በረንዳ ተግዋዙ::

በዚያ ሆነው ..... ለባልዋ የነበራትን ፍቅር, የዛሬ ሶስት አመት እዚህ ቦታ ምን እንደተፈጠረ.... አሁን የ3 ወር እርጉዝ መሆንዋንና.... ባልዋ ደግሞ ልጅ እንደማይፈልግ::- በዚህም ምክንያት ከቤት እንዳስወጣት....ነገረችው:: ይህንን ሁሉ ስትነግረው ድምፅዋ በሲቃና በእልህ ይቆራረጥ ነበር:: አይኖችዋም ያነቡ ነበር::......ዛሬም ግን ባልዋን በጣም እንደምትወደው መናገሯን ቀጠለች....

"ሽሽሽሽሽሽ" በቃሽ አታልቅሺ..... አሁን ሁሉም አልፏል አላት:: ሊያቅፋት ወደሷ እየተጠጋ:: የድምፁ ቅላፄ... ሊያለቅስ የተዘጋጀ ህፃን ይመስላል:: ደነገጠችና ቀና ብላ አየችው:: ጉንጮቹ በእንባ ርሰዋል:: ይህንን ስታይ እሷም የባሰ ተነፋረቀች:: የህዋላ ዘመን ክፉ ገጠመኞቻቸውን በእንባ ያጥቡት ይመስል አንገት ላንገት ተቃቅፈው ተላቀሱ::
በይ ተነሽ ትዙ....ወደኔ ክፍል እንሂድ:: አላት ካሳ....

"ይቺን ቀን ህዳሴ ብያታለሁ..." አለች...በሚነፋነፍ ድምፅዋ::

"አ አ.... ህዳሴማ የልጀ ስም ነው:: ይልቅ ተነሽ ብዙ ስራ አለብኝ...." አለና አፈፍ አድርጎ ተሸከማት... ወደ አልጋው!

ዋ......ው!! እጥር ምጥን ያለች ጽሁፍ............ትመቻለች!!!!!! :!:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Re: ትገብር

Postby ስርርር » Thu May 06, 2010 4:17 pm

ሳሮን...ስምህ/ሽ በጣም ትርጉም ያለው ስም ነው:: የምድረበዳ አበባ (ተክል/ፅጌረዳ)! :: የዋርካ ዛፍ ስለተከልሽ/ክ እንክዋን ደስ ያልን!.... እስኪ አትጥፋ/ፊ::

ስሊፕና ሳሮን....ለአስተያየታችሁ በጣም አመሰግናለሁ:: ዮዲትና ቻይናም ጥርጥራችሁ ቢወገድ ብየ...ህምምም የሚል ግጥም ከዚህ በላይ ለጥፌ ነበር:: እንግዲህ እኔ ዝምታን መርጫለሁ:: ለማንኛውም ስጋታችሁን ተረድቻለሁ::

ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንሁ ከላይ የለጠፍኩትን የግእዝ ግጥም ጋብዣለሁ:: Dedicated to my spectators
ዋርካኒ ትገብር

ባቲ እምርት እለት.... በአል ወተዝካር
ዮም መምር መፃ .....ፍስሀ ንግበር

ንቁም ወናፅምእ....ቃል እም መምርነ
ክሌሁ መምር.... ሀሴት ይሀበነ

ወዳሴ ወሀሴት .... ይደሉ ለከ
መምር ይሄይስ ..... እምኩሉ ቃልከ
ሀብ ጥበብ ወፍቅር......ንስርርር ገብርከ

ትገብር ዋርካኒ ...ፋሲካ ትገብር
ዮም ፍሰሀ ኮነ...በዝ ጥበብ ስርርር

ሰናይ እብለክሙ .... ናሁ ሰናይ ኮነ
ዮም ፋሲካ ገብራ---ዋርካኒ እምነ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Re: ትገብር

Postby ቻይና ገ/ማርያ » Thu May 06, 2010 6:21 pm

[quote=" ዮዲትና ቻይናም ጥርጥራችሁ ቢወገድ ብየ...ህምምም የሚል ግጥም ከዚህ በላይ ለጥፌ ነበር:: እንግዲህ እኔ ዝምታን መርጫለሁ:: ለማንኛውም ስጋታችሁን ተረድቻለሁ::
""
እኔም በጣም አመሰግናለው!
ግን ከቻልክ ቶሎቶሎ ድፋብን :D
>>>>>....
ቻይና ገ/ማርያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 05, 2009 6:05 pm

ጋቢ

Postby ስርርር » Fri May 07, 2010 12:25 am

Gabi
I was born to an African American family, downtown Carlsbad in California. I have always been proud of my skin color, black. This pride gives me such a unique nature that inspires my soul to self love, as one would call it selfish, or racist for worse. Most of all, I dont like to be referred to as African American.

Hell no! I have never been to any other state for that matter, leave alone Africa. So, I like to be referred to as Black American. That is who I am. So, when anyone refers to me as African American, I get pissed off!

I had a boy friend. I loved him so dearly, and I still do. His name is Gabremeskal. He told me the meaning of his name, but I forgot it. It has something to do with the cross of Jesus.

You can imagine how f...ken boring it is to say all the name. But I call him Gabi for short. I love his smile, his eyes, his skin, I love everything about him. He told me that he is from a country in the f...ken Dark continent Africa, called Utopia. He said he is a city boy (from Addisbaba), but nothing of him looks like a city boy.

I tought him everything from the scratch. He was shy at first. I remember the day I dated him for the first time. I intentionally talked about pussy, dick and jiggle. It was much easy for me, and I really enjoyed every bit of his reactions.

Once, it was spring brake, and I wanted to introduce him to my parents. So I called him. Our conversation went on good. for a while. He said his mom has come all the way from Utopia, and he wants to spend time with her.

“oh really…congrats….Gabi aint you gonna introduce me to her?” I aksd him

He said….”that is not my culture …I will see you….” And hang up.

“Mother-f...r!” I cursed, and run to ma bed room to get changed and drive to his ass.

A good lookin colored women was sittin in the sofa. I said “Hello….”
The woman looked confused…and said something in her language, possibly Amharic.
Gabi told me the meaning of some words in Amharic.
To mention few, he told me the meaning of Pussy…..Kintir
Mother-f...r …..Enatu Yiveda
Lets do sex….Libdash… (but I think he cheated on this one because he told me that sh always connotes women)
Anyway, I caught two words….Tikur….Barya” from the womens talk to Gabi.
I got pissed of. Gabi once told me that HabeeChas refer to us as Barya, which means Negro. I got pissed off! I yelled at her (whom I was told that she was his mom) and dragged her on the floor. He came running from inside and pushed me real hard away!

It was quite a scene. I wanted to file a racial profiling, but…he is black too…. HABECHA!

It has been a while since we broke up. I miss my Gabi! I would give ma life for him to take me back! Enatu Yividal,…..hahaha I mean mother f....r
Last edited by ስርርር on Fri May 07, 2010 5:50 pm, edited 2 times in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤልሳ* » Fri May 07, 2010 12:40 am

:lol: ሞትኩ
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 4 guests