የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፋኖፋኖ » Tue May 18, 2010 7:39 pm

ስርርር wrote::lol: :lol: :lol: :lol: በጣም ያስቃል:: ለነገሩ የሚያስቅ ሆኖ አይደለም:: ግን ይህ ጥርስ ስንወለድ አብሮን አልተወለደም አይደል! እሱ ምን ቸገረው...በሚያስቀውም በማያስቀውም ይስቃል:: :? ከፅሁፍህ እንደምረዳው እንክዋን ለመተቸት ለማንበብ እንኩዋን ብቁ አትመስለኝም:: እንግዲህ የሚመችህ ከሆነ አንብብ...ያለዚያም ዝም ብለህ ተራ ፅሁፎችህን ፖስት ማድራግህን ቀጥል::- መብትህ ነው:: ለእልፍ አንባቢዎቼ የምመክረው ቢኖር...እየመረጣችሁ አንብቡ ነው....wierdo!


መሳቅህና ስድብ መጀመርህ ጥርጣሬዬ ትክክለኛ መሆኑን ይጠቁመኛል :: አሁንም የምታመጣቸው ጽሁፎች ያንተ አይደሉም ብየ አምናለሁ:: በለስ ቀንቶኝ የፒ.ዲ.ኤፍ ምንጭህን አግኝቼ ለማረጋጥ ያብቃኝ::
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

የስርርር መጣጥፎች 18

Postby ስርርር » Tue May 18, 2010 10:56 pm

ዳዊቴ

ለእማማም ለአባባም አንድ ነኝ:: እናቴ በልጅነቴ ብትሞትብኝም...አባቴ ግን እንደናትም እንደአባትም ሆኖ ነበር ያሳደገኝ:: ገና በህፃንነቴ እንኮኮ በጫንቃው ላይ አድርጎ ሀሁ እንድቆጥር ወደየኔታ ሲወስደኝ....ከፍ ስል ደግሞ ልብሴን ሽክ አድርጎ አለባብሶ አስክዋላ ሲያደርሰኝ....ደብተሬን ሲያነብልኝ....ሲቆጣጠረኝ.....አቤት! የእውነት ግን እንደሱ አይነት አባት በአለም ላይ አልተፈጠረም:: ለኔ ያለው ፍቅር ምንም ገደብ የለውም ነበር:: ሉሻ ፀጉሬን በፍቅር እየደባበሰ የሚመክረኝ ምክር ምንግዜም በልቦናዬ ፅላት ተፅፎ ይኖራል::

የዛሬ 15 አመት የአንደኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ አባባ አንዲት የሰፈራችን ውብ የምትባለዋን ፈት ሴት ወሸመ ሲባል ሰምቼ እብድ ሆንኩ:: ፍቅሩ የሚቀንስብኝ መሰለኝ:: የኔ ብቻ እንዲሆን ፈልጌ እንድሁ አላውቅም ግን ተናደድኩ...:: ይባስ ብሎ አገባት እና አስረገዛት:: "ደም አማታት" ተብሎ ልጁ ሳይወለድ ቀረ እንጂ እኔም የ15 አመት ጎረምሳ ወንድም ይኖረኝ ነበር:: አባባ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝ ስጦታ ቢኖር አንድ ከቅድመ-አያቱ የወረሰው ዳዊት ብቻ ነበር::- እንዴት ይሆናል ብዬ ጥዬለት ወጣሁ:: በዚሁ ምክንያት ተቀይሜው ለ13 አመታት አባባን ሳላገኘው እንዲሁ በሩቁ ወሬውን ስለደህንነቱ ስስማ ኖርኩ:: አሁን ሆኘ ሳስበው ቁጭት ይለኛል::

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ለሮዛ ዳኛምየለው የሚል በላዩ ላይ የተፃፈበት ቴሌግራም ይደርሰኛል:: እንዴት ተጣድፌ እንዳነበብኩት አትጠይቁኝ:: ልቅም ባለ የአማርኛ የጅ ፅሁፍ የተፃፈው መልክት እንዲህ ይል ነበር::
"ሮዛ...አባትሽ በፀና ታሟል እና በነፍስ ድረሺ!"
ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ብመኝም...ጉዋደኞቼ ቀደም ብለው አውቀው ነበርና ከስቱትጋርት ወደፍራንክፈርት(ጀርመን) ከዛም ወዳዲሳባ የበረራ ቲኬቴን አስጨበጡኝ::

አባባን በነፍሱ አልደረስኩበትም:: ቁጭቴ! እንደእግር እሳት የሚያንሰፈስፈኝ ናፍቆቴ! ከየት ላግኘው አባባን!?? ሁልግዜ ሊያዬኝ እንደተመኘ...በወዲያኛው አለም እንድንገናኝ ብሎ መሄዱን ነገሩኝ::

ያፈራውን ንብረት ሁሉ አንዲት ሰባራ ጣሳ እንኩዋን ሳትቀር ለውሽማው አውርሷታል:: ለኔ ግን የዚያን ግዜ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝን ስጦታ ብቻ...በአደራ መልክ አውርሶኛል:: ትንሽ ብናደድም የአባቴን ስጦታ ለሁለተኛ ግዜ እምቢ ማለት አልሆነልኝም:: ገለጥ ገለጥ አድርጌ አየሁት:: ዳዊቱ መሀል ላይ አንድ ካርታ እና የወረቀት ጥቅልል ደብዳቤ አለ:: ገርሞኝ ካርታውን አተኩሬ አየሁት:: ደብዳቤውንም አነበብኩትና ...እስቲወጣልኝ ድረስ አለቀስኩ:: ከዚያን ቀን ወዲህ መኖሪያየን ኢትዮጵያ አደረኩ:: ያውም ጭልጋ:: በካርታው እየተመራሁኝ ሄጄ ደብዳቤው ያመላከተኝን ቦታ በውድ ዋጋ ገዛሁና ቤት ሰራሁበት:: ከቤቴ ስር ታፍሶ ያማያልቅ የወርቅ ሳንቲሞች ክምችት ነበር::
በእያንዳንዱ ሳንቲም ላይ "ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ወልደ አንበሳ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ" ይላል::

ይህንን ሚስጥር በጣም የምወደው ባሌ ሳሙዔል እንክዋን አያውቀውም:: ልጄን ዳዊት ብየዋለሁ:: እንግዲህ እሱም ከኮሌጅ ሲመረቅ የምሰጠው ስጦታ ቢኖር ዳዊቴንና ሚስጥሩን ነው:: ዳዊቴ የኔ ልጅ!
_________________
ድህረ ታሪክ!
ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ከ1413 እስከ 1414 በኢትዮጵያ የነገሱ ሲሆን በዚህች በአንድ አመት የንግስና ወቅት በኢትዮጵያ ወርቃማ ዘመንን አምጥተው ነበር:: በእሳቸው ግዜ ምድር ሁሉ ሙሉ ነበረች, ሁሉም ሰው ሀብታም ነበር:: እሳቸው ከሞቱ በህዋላ ብዙ ሺህ በርሜል ወርቆችን ደምቢያና ጭልጋ አካባቢ እንደቀበሩ አፈ-ታሪክ ይነገራል::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ሾተል » Wed May 19, 2010 12:05 am

ከአቶ የዚኽ ቤት ባለቤት የፍቃድ አረንጉዋዴ መብራት ጠብቀን ነበር ነገር ግን ባለቤቱ ባተሌ ሆኖ ነው መሰል ምንም መልስ አልሰጠንም....ቢሆንም ጸሀፊነቱን ሊያሳድግ የሚችል ትንሽ ግምገማ ነገር እንቸረዋለንና ያንን አደረጋችሁ ብሎ ዘመቻ ሰርርርን እንደማያውጅብን ነው::በቀና መንገድ የሚያየን ከሆነ ይጠቅመዋል....በዛኛውም ካየን እንግዲኽ ምን ይደረጋል?


ጊዜ ገና ዛሬ ነው ትንሽ ያገኘነውና ባልነው ቀን ስላልተከሰትን ይቅርታ::

በነገራችን ላይ ስለጽሁፍ የማታውቁ ሰዎች ምናለ ደራሲዎችን ውዳሴ ከንቱ በማሻር ባታዘናጉዋቸው?ጸሀፊዎች በናንተ የተነሳ ኩፍ ብለው ሳለ በባዶ እንደሚሞካሹ ሲያውቁ እየጠፉ አስቸግረዋልና እባካችሁ ይኼ ውዳሴ ከንቱ ይቅር::አትፍሩ ድፈሩና ክቡር ደራሲ እዚኽ ጋር የሆነች ስህተት አለችብኽ እዚች ጋር ጠንካራ ነኽ...ይቺን እንዲህ ብታደርጋት የተዋጣለት ጽሁፍ ይሆናል...ይኸ ግን እንደዚኽ መሆን የለበትም ወዘተ ብትሏቸው ሊያድጉ ይችላሉ እንጂ ሾላ በድፍኑ አይነት ነገር አንተን የሚያክል ጸሀፊ የለም ....አቤት ጽሁፍ ከተባለ እንደዚኽ ነው....እጅኽን ያለምልመው....ወዘተ አይነት የፉገራ አድናቆታችሁን አትለግሱ::በርግጥ ሰው ያለውን ነው እዚኽ እየመጣ በነጻ የሚቸረው....ግን እነዚኽ ለጋስ ጸሀፊዎች ውዳሴ ከንቱ ሳይሆን ጥንካሬያቸውንና ድክመታቸውን አውቀው እራሳቸውን ማሻሻል ይፈልጋሉ::የአንድን ጽሁፍ ጠንካራም ሆነ ደካማ ጽሁፉን ለመተቸት የግድ ዩኒቨርስቲ መግባት የለብንም::ለምሳሌ እኔ በሚስቶቼ ነው ዩኒቨርስቲ አይደለም 8ንተኛ ክልፍ የጨረስኩት::በእኔ የአቦጊዳ አርበኛ ነኝ::ታድያ እውቀት ከነሱ አልጋባብኽ ብሎኝ እውቀት አልባ እንደሆንኩ ይኼው አለሁ::ታድያ ሚስቶቼ ባወቁት እኔ የሰውን ጥንካሬና ድክመትን ባላመላክት የማወቅ አምላክ አይከሰኝም?

ሰዎች እስኪረዱን ድረስ ሊጠሉን ሊያወግዙን ሊረግሙን ይችላሉ....ወዳንጎላቸው አንድ ቀን ሲመለሱ እግዜር ይስጥልን ይሉ ይሆናል::ያ እኛን አያሳስበንም....የሚያሳስበን የሰው ልጅ ማደግ ካለበትና ለሰው ልጅ ማደግ የምንችለው አስተዋጾ ካለን በምን መንገድ ያንን አስተዋጽኦ እንስጥ ነው::

እንደ ከብቱና ደደቡ የተማረ እንኩዋን ጨብጦ የማያውቀው ቻይና ገብረ የማርያም ጠላት ምኑንም ሳያውቅ እንደናቱ እንትን ክብርነታችንን ስለሚጠላ ወይም ስለሚፈራ ይኼ ቤት ተረበሸ ብሎ ጽፎዋል....ኑሮው ከህልሙ ጋር ተምታቶ እንደተረበሸ እንደረበሸው ይኑርና::---- ስለሆነ ሰው ቀና ቢያስብም ለእሱ እድገቱ ተረባብሾ ስላደገ የሚረበሽ መስሎት አንቋልጧል::እኔ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው ይኼንን ሩም ወይ አይቼው አላውቅም ነበር ወይም ሳልገባበት አይቼው አላነበብኩትም....ታድያ ዘው ብዬ ባለፈው ገብቼ ጽሁፉን ብጀምረው የሆነ ነገር ታየኝ....ከዛ ለምን ያ የታየኝን ለደራሲውና ለታዳሚዎቹ አላሳይም ብዬ በቅንነት ፍቃድ ጠየቅኩኝ....ለጥያቄዬ መልስ የለም....ግን ይኼ ዋርካ ሁሉንም የሚያሳትፍ ስለሆነ እኔም ዋርካ በተሰጠኝ መብት ልሳተፍ ስለፈለግኩ እነሆ ልሳተፍ ጀመርኩ::

በነገራችን ላይ ሩሙ ክርክርም ያለበት ሩም ስለሆነ ያ እኔን አያገባኝም ነገር ግን የሚያገባኝ የታየኝን ማለት ነውና የታየኝን ልበል....

መልካም ንባብ

ሾተል ነን..........ውዳሴ ከንቱ ቀርቶ ደራሲዎችን ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በማሳየት እናሳድጋቸው
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Wed May 19, 2010 12:18 am

የቅፅበት

በህሙማን መመርመርያ ክፍል ውስጥ ሆኘ የእለቱን የህክምና ስራዬን ለመጀመር እየተሰናዳሁ ነው :: ሲስተር ትርሲት የክፍሉን በር ከፍታ የተለመደውን ማኪያቶ አቅርባልኝ ወጣች :: ጃኬቴን ከመስቀያው ላይ አኖርኩና ገዋኔን ለብሸ ቁጭ አልኩ :: ከፊቴ ብዙ የህሙማን ፋይሎች ተደርድረዋል ::

በሽተኛ ላስገባ ? አለችኝ ሲስተር ትርሲት
አዎን አልኩ ::
አንድ ወጣት አይነርግብ የለበሰች ውርዚት ብቅ አለችና
"ሀይ ዶክ " አለችኝ :: ሀይ ፕሊስ ሀቭ ኤ ሲት ! አልኩ

እሺ ጀሚላ ...ምንድነው ችግሩ ? ምን ሆንሽ ?
ዶ /ክ እኔ ከዚ በፊት ወንድ አላውቅም :: ግን ፔሬዴ ከቀረ ቆይትዋል :: አንተ ደግሞ ፕሮፌሽናል ጋይኒስት ነህ ሲባል ሰምቼ ቼክ እንድታደርገኝ ነው ....አለች እንደማፈር እያለች ::

የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ጠየቅህዋትና ቃሬዛውን አስተካክየ በይ ነይ እስኪ ...ፊዚካል ቴስት ያስፈልግሻል አልክዋት ::
እያፈረች ቀሚስዋን ገልባ በጀርባዋ ጋደም አለች ::

two bud and a leaf ይሉታል በሳይንስ :: ሁለቱን የፊት እና አውራ ጣቴን ደርቤ ለአመል ያህል ወደብልትዋ ከተትኩት :: ዋው !!!!! እውነትም ውርዚት ! ድንግል ናት :: ወንድ አታውቅም :: በዚያ ላይ እስላም ናት :: ፔሬዷ ለምን ቀረ ????
ደምና ሽንት እንድትሰጥ ነግሬያትና ወጣች :: ከዚያ በህዋላ ...ቀኑን ሙሉ ያ ትኩስ ገላዋ በአይኔ ድቅን እያለብኝና ሙያዬን ሲፈታተነኝ ዋለ :: በምሳ ሰዓትም እንዲሁ ቁጭ ብየ ስለራሴ ሳስብ ...እስከመቼስ እንደማላገባ ? ልጅስ መቼ እንደምወልድ ....ስተክዝና ስቆዝም የሚያፅናናኝ የነበረው ረጅም ባትዋ , ዝብርቅርቅ ብሎ እዚህም እዚያም የበቀለው ጭገሯ , ብስል ቀይ ገላዋ ....ነበር :: እንደሳይንሱ ከሆነ የፔሬድ መቅረት ኖርማል ነው :: እስከ ሁለት ወር ድረስ ሊቀር ይችላል ::

የምርመራዋ ውጤት ኖርማል ከሆነ እንደማገባትና ሌላው ቢቀር ice breaker እንደምሆን ለራሴ ወስኜ ወደቢሮየ ገባሁ ::

የብዙ እንስቶችን የምርመራ ውጤት ሳስረዳ , መድሀኒቶችን ሳዝ , ኮንግራ ስል , አብሬ ሳዝን ...ምናምን ቆይቼ ተራዋ ደርሶ የወደፊትዋ ሙሽራዬ ....የዛሬዋ በሽተኛዬ ገባች :: ፈገግ ስትል ጉንጮችዋ ስርጉድ ! እያሉ ልቤን አዘለሉት :: ጭገርዋ ላንድ አፍታ በአይኔ መጣብኝ :: እንደምንም ራሤን ተቆጣጥሬ ውጤቱን ማንበብ ጀመርኩ ::

ሥሜቴ ሁሉ በአንድ ግዜ ኩምሽሽ አለ :: ላብ ላብ አለኝ ቀና ብየ ሳያት የጥዋቱ ትዝ ብሏት ይመስላል ፈገግ አለች :: ድንጋጤዬን እንዳታውቅብኝ በጣም ተጠንቅቄ ለአንዳንድ ተጨማሪ ምርመራዎች ስለምንፈልጋት ነገ ተመልሳ እንድትመጣ ነግሬያት ወጣች :: በሩ ላይ ስትደርስ ግን መለስ ብላ በሁለቱም አይኖችዋ ጥቅስ ! አደረገችኝ :::

ኖ ኖ ኖ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ???? የ 19 አመትዋ ወጣት ልጃገረድ የሁለት ወር እርጉዝ ናት :: የደም ምርመራ ውጤትዋን ሳዬው ...ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ ....

የቅፅበት ሙሽራየ ! ሳላስበው እንባየ በጉንጨ ክብልል አለ ...

የመጨረሻ ማሰተካከያ በስርርር እገሌ በማክሰ May 18, 2010 11:18 pm ተደረገ በጠቅላላ 10 ገዜ ተሰተካከሏል


በመጀመርያ ላየው የፈለኩት ጽሁፍ ይኼንን ነው::ይኼ ጽሁፍ አፕሪል 27 ተጽፎ ለ 10 ጊዜ እስከትላንትናዋ ሜይ 18 ድረስ ተስተካክሏል::ታድያ ለ 10 ጊዜ የተስተካከለውን ጽሁፍ ብመነጣጥረው ምን ይለኛል?

መጣን

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: የስርርር መጣጥፎች 18

Postby ትርዛ » Wed May 19, 2010 12:21 am

እግዚአብሄር ይስጥልኝ ወዳጀ ስርርር! :lol: ተመልሰህ እንደምትመጣ አውቅ ነበር:: :D :D :lol: በርታ በርታ :lol: እንዳትረታ!
ትርዛ ነኝ (የነፍሴ ደስታ)


ስርርር wrote:ዳዊቴ

ለእማማም ለአባባም አንድ ነኝ:: እናቴ በልጅነቴ ብትሞትብኝም...አባቴ ግን እንደናትም እንደአባትም ሆኖ ነበር ያሳደገኝ:: ገና በህፃንነቴ እንኮኮ በጫንቃው ላይ አድርጎ ሀሁ እንድቆጥር ወደየኔታ ሲወስደኝ....ከፍ ስል ደግሞ ልብሴን ሽክ አድርጎ አለባብሶ አስክዋላ ሲያደርሰኝ....ደብተሬን ሲያነብልኝ....ሲቆጣጠረኝ.....አቤት! የእውነት ግን እንደሱ አይነት አባት በአለም ላይ አልተፈጠረም:: ለኔ ያለው ፍቅር ምንም ገደብ የለውም ነበር:: ሉሻ ፀጉሬን በፍቅር እየደባበሰ የሚመክረኝ ምክር ምንግዜም በልቦናዬ ፅላት ተፅፎ ይኖራል::

የዛሬ 15 አመት የአንደኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ አባባ አንዲት የሰፈራችን ውብ የምትባለዋን ፈት ሴት ወሸመ ሲባል ሰምቼ እብድ ሆንኩ:: ፍቅሩ የሚቀንስብኝ መሰለኝ:: የኔ ብቻ እንዲሆን ፈልጌ እንድሁ አላውቅም ግን ተናደድኩ...:: ይባስ ብሎ አገባት እና አስረገዛት:: "ደም አማታት" ተብሎ ልጁ ሳይወለድ ቀረ እንጂ እኔም የ15 አመት ጎረምሳ ወንድም ይኖረኝ ነበር:: አባባ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝ ስጦታ ቢኖር አንድ ከቅድመ-አያቱ የወረሰው ዳዊት ብቻ ነበር::- እንዴት ይሆናል ብዬ ጥዬለት ወጣሁ:: በዚሁ ምክንያት ተቀይሜው ለ13 አመታት አባባን ሳላገኘው እንዲሁ በሩቁ ወሬውን ስለደህንነቱ ስስማ ኖርኩ:: አሁን ሆኘ ሳስበው ቁጭት ይለኛል::

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ለሮዛ ዳኛምየለው የሚል በላዩ ላይ የተፃፈበት ቴሌግራም ይደርሰኛል:: እንዴት ተጣድፌ እንዳነበብኩት አትጠይቁኝ:: ልቅም ባለ የአማርኛ የጅ ፅሁፍ የተፃፈው መልክት እንዲህ ይል ነበር::
"ሮዛ...አባትሽ በፀና ታሟል እና በነፍስ ድረሺ!"
ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ብመኝም...ጉዋደኞቼ ቀደም ብለው አውቀው ነበርና ከስቱትጋርት ወደፍራንክፈርት(ጀርመን) ከዛም ወዳዲሳባ የበረራ ቲኬቴን አስጨበጡኝ::

አባባን በነፍሱ አልደረስኩበትም:: ቁጭቴ! እንደእግር እሳት የሚያንሰፈስፈኝ ናፍቆቴ! ከየት ላግኘው አባባን!?? ሁልግዜ ሊያዬኝ እንደተመኘ...በወዲያኛው አለም እንድንገናኝ ብሎ መሄዱን ነገሩኝ::

ያፈራውን ንብረት ሁሉ አንዲት ሰባራ ጣሳ እንኩዋን ሳትቀር ለውሽማው አውርሷታል:: ለኔ ግን የዚያን ግዜ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝን ስጦታ ብቻ...በአደራ መልክ አውርሶኛል:: ትንሽ ብናደድም የአባቴን ስጦታ ለሁለተኛ ግዜ እምቢ ማለት አልሆነልኝም:: ገለጥ ገለጥ አድርጌ አየሁት:: ዳዊቱ መሀል ላይ አንድ ካርታ እና የወረቀት ጥቅልል ደብዳቤ አለ:: ገርሞኝ ካርታውን አተኩሬ አየሁት:: ደብዳቤውንም አነበብኩትና ...እስቲወጣልኝ ድረስ አለቀስኩ:: ከዚያን ቀን ወዲህ መኖሪያየን ኢትዮጵያ አደረኩ:: ያውም ጭልጋ:: በካርታው እየተመራሁኝ ሄጄ ደብዳቤው ያመላከተኝን ቦታ በውድ ዋጋ ገዛሁና ቤት ሰራሁበት:: ከቤቴ ስር ታፍሶ ያማያልቅ የወርቅ ሳንቲሞች ክምችት ነበር::
በእያንዳንዱ ሳንቲም ላይ "ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ወልደ አንበሳ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ" ይላል::

ይህንን ሚስጥር በጣም የምወደው ባሌ ሳሙዔል እንክዋን አያውቀውም:: ልጄን ዳዊት ብየዋለሁ:: እንግዲህ እሱም ከኮሌጅ ሲመረቅ የምሰጠው ስጦታ ቢኖር ዳዊቴንና ሚስጥሩን ነው:: ዳዊቴ የኔ ልጅ!
_________________
ድህረ ታሪክ!
ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ከ1413 እስከ 1414 በኢትዮጵያ የነገሱ ሲሆን በዚህች በአንድ አመት የንግስና ወቅት በኢትዮጵያ ወርቃማ ዘመንን አምጥተው ነበር:: በእሳቸው ግዜ ምድር ሁሉ ሙሉ ነበረች, ሁሉም ሰው ሀብታም ነበር:: እሳቸው ከሞቱ በህዋላ ብዙ ሺህ በርሜል ወርቆችን ደምቢያና ጭልጋ አካባቢ እንደቀበሩ አፈ-ታሪክ ይነገራል::
ትርዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 78
Joined: Fri Apr 09, 2010 10:10 pm

Postby ሾተል » Wed May 19, 2010 12:27 am

ይኽ ከላይ ያጣቀስኩት የደራሲ ሰርርር ጽሁፍ የተወሰኑ ልበለው ጥቂት ብቻ በቃ ድክመቶች ይታዩበታል::

-ሰእላዊ መግለጫ ከቶም አይታይበትም::ድርቅ ያለ ታሪክ እንጂ ልብ-ወለዳዊ ውበት ብዙም አላሸውም::
-የቃላትና የስርአተ ነጥብ ግድፈቶች ይታዩበታል:: (ያ ሁሉም ላይ አለ ችግር ቢሆንም አንዱ የሚያቀውን ላንዱ ቢያካፍል ሁላችንም ከዚኽ ድክምት በወጣን ነበር::የዋርካ ጸሀፊዎች መሀል የሚታይ ትልቅ ችግር ነው:: )

-ቃላቶች ሆኑ አረፍተ ነገሮች ያላግባቡ ገብተው ድርሰቱን አበላሽተውታል::

-ደራሲው ለድርሰቱ አወራረድና አወጣጥ ሳይሆን የተጨነቀው ለሁለት አረፍተ ነገሮች ነው::አንድ ግልጽ ጸሀፊ ለመባል ያልሆነ ቃል አስገብቶ ለዛ ቃል ወይም አረፍተ ነገር ማብራርያ ወይም መሰረተ ታሪክ አላበጀለትም.....ሌላው ደግሞ አሳዛኝና አስደንጋጭ ታሪክ ለማድረግ ለማሳዘን ወይም ለማስደንገጥ የተጠቀመበት የጽሁፉ መቋጫ ታሪክ ምንም የታሪክ ተከታታይነት የሌለው ዝም ብሎ ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ነገር ግን ተወርውሮ አጠገብ ላይ እንደተወረወረ ድንጋይ አድርጎታል::

ወዘተ ተረፈ.....ግድፈቶች ጽሁፉ ሲኖሩት እስቲ ከላይ ያልነውን አብራሩ ብንባል በሚቀጥለው ገጽ አብራርተን ከላይ ያልነውን ለማጠናከር ወደ ሚቀጥለው ገጽ ሄደናል::

መጣን

ሾተል ነን....የግምገማ ሙድ ላይ ነን ነው እኮ የምንላችሁ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ፋኖፋኖ » Wed May 19, 2010 7:42 am

አይ ሾተል
ለዚያውም እኮ ጽሁፉ የሱ ቢሆን ነው::
99 ጊዜ ኤዲት የሚደረገው ሽፋን ነው
ስም ይለወጣል
ቦታዎች ይለወጣሉ
አርስት ይለወጣል

እስኪ ከጀመርክ የንግሊዝኛውን ታሪክ ከሱ የእግሊዝኛ ፖስቶች ጋር እያነጣጠርክ ገምግመው
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

Postby ስርርር » Wed May 19, 2010 4:43 pm

"ልሳቅ ባይኔ...ጥርሴስ ልማዱ ነው" አለች አበሩ! ይህንን አብየ ሾተል ለአስተያየቶችህ በጣም አመሰግናለሁ:: ደረቅ ፅሁፍ ፃፍክ...ሰላዊነት አይታይበትም ላልከው....እኔ በበኩሌ አልቀበለውም:: ሐኪሙ ገዋኑን አውልቆ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ሲል ጠረጴዛው ላይ ያለው የፋይል ክምር...የጀሚላ ሁኔታ (አይነ-እርግቧ, ውርዚትነቷ, የባቷ ርዝመት, የጭገሯ አበቃቀል....).....ወዘተ...እኔ ከዚህ በላይ ስዕላዊነት ለብሎግ ፅሁፍ አይታየኝም:: አየህ...የብሎግ ፅሁፍ ስታነበው የሚጣፍጥ, የማይሰለች...ያልተንዛዛ, አጠር ብሎ ቁምነገርን ከጫወታ ጋር እያዋዛ ማቅረብ ነው ያለበት::

በተረፈ ግን ይህንን ፅሁፍ ለመጀመርያ ግዜ የፃፍኩት "ዋናው" የሚባል ፀሀፊ "አጫጭር ልቦለዶች" የሚለው ቤት ውስጥ በጥገኝነት እያለሁ ነው:: ይህንን ቤት ስከፍት ግን ወደዚህ አመጣሁት:: ኦሪጅናሉን እዛው እየውና አመሳክረው እስቲ::....እኔ ኤዲት የማደርገው አንዳንዶች እንደሚሉት ስለተኮረጀ ለማስተካከል አይደለም:: አዲስ ፅሁፍ ፖስት ሳደርግ ለአንባቢዎቼ ለማሳውቅ ርዕሱን እቀይረዋለሁ:: ይህ ደግሞ በኔ አልተጀመረም:: ለምሳሌ የትርንጎን ሙንጭርጭር የመጀመርያ ፖስት ብታየው ብዙ ግዜ ኤዲት ተደርጎአል::
ለገንቢ አስተያየትህ ግን አመሰግናለሁ::

There are in deed many writers in Warka, but am sure none have troden along the paths I am in. To most aptly describe the paths, they are burdens or rigors. At times of frailty like these, I am among those that feel to be devoid of the ardor and zeal in their possesion. BUT, I wont recoil and retreat. I will never be perplexed, and surely, wont let anyone step on my sunshine. I might be bewildered, yet 'am always eager to come back to Warka. I am exhausted of all the negativities, yet 'am determined to make a real difference in Warka. No matter what is being said, I remain intricately attached and intrinsically drawn to the overpowering love I have for warka.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤዶም* » Wed May 19, 2010 6:27 pm

ዳዊቴ ለእማማም ለአባባም አንድ ነኝ :: እናቴ በልጅነቴ ብትሞትብኝም ...አባቴ ግን እንደናትም እንደአባትም ሆኖ ነበር ያሳደገኝ :: ገና በህፃንነቴ እንኮኮ በጫንቃው ላይ አድርጎ ሀሁ እንድቆጥር ወደየኔታ ሲወስደኝ ....ከፍ ስል ደግሞ ልብሴን ሽክ አድርጎ አለባብሶ አስክዋላ ሲያደርሰኝ ....ደብተሬን ሲያነብልኝ ....ሲቆጣጠረኝ .....አቤት ! የእውነት ግን እንደሱ አይነት አባት በአለም ላይ አልተፈጠረም :: ለኔ ያለው ፍቅር ምንም ገደብ የለውም ነበር :: ሉሻ ፀጉሬን በፍቅር እየደባበሰ የሚመክረኝ ምክር ምንግዜም በልቦናዬ ፅላት ተፅፎ ይኖራል ::

የዛሬ 15 አመት የአንደኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ አባባ አንዲት የሰፈራችን ውብ የምትባለዋን ፈት ሴት ወሸመ ሲባል ሰምቼ እብድ ሆንኩ :: ፍቅሩ የሚቀንስብኝ መሰለኝ :: የኔ ብቻ እንዲሆን ፈልጌ እንድሁ አላውቅም ግን ተናደድኩ ...:: ይባስ ብሎ አገባት እና አስረገዛት :: "ደም አማታት " ተብሎ ልጁ ሳይወለድ ቀረ እንጂ እኔም የ 15 አመት ጎረምሳ ወንድም ይኖረኝ ነበር :: አባባ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝ ስጦታ ቢኖር አንድ ከቅድመ -አያቱ የወረሰው ዳዊት ብቻ ነበር ::- እንዴት ይሆናል ብዬ ጥዬለት ወጣሁ :: በዚሁ ምክንያት ተቀይሜው ለ 13 አመታት አባባን ሳላገኘው እንዲሁ በሩቁ ወሬውን ስለደህንነቱ ስስማ ኖርኩ :: አሁን ሆኘ ሳስበው ቁጭት ይለኛል ::

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ለሮዛ ዳኛምየለው የሚል በላዩ ላይ የተፃፈበት ቴሌግራም ይደርሰኛል :: እንዴት ተጣድፌ እንዳነበብኩት አትጠይቁኝ :: ልቅም ባለ የአማርኛ የጅ ፅሁፍ የተፃፈው መልክት እንዲህ ይል ነበር ::
"ሮዛ ...አባትሽ በፀና ታሟል እና በነፍስ ድረሺ !"
ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ብመኝም ...ጉዋደኞቼ ቀደም ብለው አውቀው ነበርና ከስቱትጋርት ወደፍራንክፈርት (ጀርመን ) ከዛም ወዳዲሳባ የበረራ ቲኬቴን አስጨበጡኝ ::

አባባን በነፍሱ አልደረስኩበትም :: ቁጭቴ ! እንደእግር እሳት የሚያንሰፈስፈኝ ናፍቆቴ ! ከየት ላግኘው አባባን !?? ሁልግዜ ሊያዬኝ እንደተመኘ ...በወዲያኛው አለም እንድንገናኝ ብሎ መሄዱን ነገሩኝ ::

ያፈራውን ንብረት ሁሉ አንዲት ሰባራ ጣሳ እንኩዋን ሳትቀር ለውሽማው አውርሷታል :: ለኔ ግን የዚያን ግዜ ከኮሌጅ ስመረቅ የሰጠኝን ስጦታ ብቻ ...በአደራ መልክ አውርሶኛል :: ትንሽ ብናደድም የአባቴን ስጦታ ለሁለተኛ ግዜ እምቢ ማለት አልሆነልኝም :: ገለጥ ገለጥ አድርጌ አየሁት :: ዳዊቱ መሀል ላይ አንድ ካርታ እና የወረቀት ጥቅልል ደብዳቤ አለ :: ገርሞኝ ካርታውን አተኩሬ አየሁት :: ደብዳቤውንም አነበብኩትና ...እስቲወጣልኝ ድረስ አለቀስኩ :: ከዚያን ቀን ወዲህ መኖሪያየን ኢትዮጵያ አደረኩ :: ያውም ጭልጋ :: በካርታው እየተመራሁኝ ሄጄ ደብዳቤው ያመላከተኝን ቦታ በውድ ዋጋ ገዛሁና ቤት ሰራሁበት :: ከቤቴ ስር ታፍሶ ያማያልቅ የወርቅ ሳንቲሞች ክምችት ነበር ::
በእያንዳንዱ ሳንቲም ላይ "ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ወልደ አንበሳ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ " ይላል ::

ይህንን ሚስጥር በጣም የምወደው ባሌ ሳሙዔል እንክዋን አያውቀውም :: ልጄን ዳዊት ብየዋለሁ :: እንግዲህ እሱም ከኮሌጅ ሲመረቅ የምሰጠው ስጦታ ቢኖር ዳዊቴንና ሚስጥሩን ነው :: ዳዊቴ የኔ ልጅ !

_________________

ሰላም ስርርር.......ይህንን አጭር ፅሁፍ ሳነብ ከዚህ ቀደም ምናልባትም ካንድ አመት በፊት ያነበብኩት ታሪክ ፊቴ ድቅን አለ! ፅሁፉ በፈረንጅኛ ነው.....(ዋርካ ጀነራል ውስጥ ' A Piece of Cake " የሚል ትሬድ ውስጥ አለለህ)

ፅሁፉ እንዲህ ይነበባል......የእንግሊዝኛው ድርሰት ደራሲም አንተ ካልሆንክ በቀር እንዲህ አይነት መመሳሰል የሚገርም ነው :? :? :?


young man was getting ready to graduate college. For
many months he had admired a beautiful sports car in a dealer's
showroom, and knowing his father could well afford it, he told
him that was all he wanted.

As Graduation Day approached, the young man awaited
signs that his father had purchased the car. Finally, on the
morning of his graduation his father called him into his private
study. His father told him how proud he was to have such a fine
son, and told him how much he loved him. He handed his son
a beautiful wrapped gift box.

Curious, but somewhat disappointed the young man
opened the box and found a lovely, leather-bound Bible. Angrily,
he raised his voice at his father and said, "With all your money you
give me a Bible?" and stormed out of the house, leaving the holy
book.

Many years passed and the young man was very successful in
business.
He had a beautiful home and wonderful family, but realized his
father was very old, and thought perhaps he should go to him. He
had not seen him since that graduation day. Before he could make
arrangements, he received a telegram telling him his father had
passed away, and willed all of his possessions to his son. He
needed to come home immediately and take care things.
When he arrived at his father's house, sudden sadness and
regret filled his heart.

He began to search his father's important papers and
saw the still new Bible, just as he had left it years ago. With
tears, he opened the Bible and began to turn the pages. As he
read those words, a car key dropped from an envelope
taped behind the Bible.
It had a tag with the dealer's name, the same dealer who had the
sports car he had desired. On the tag was the date of his graduation,
and the words...PAID IN FULL.
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ስርርር » Wed May 19, 2010 7:07 pm

:D ኤዶም እንዴት ነህ?
በእውነት በጣም ነው እኔንም የገረመኝ:: ታሪኩ በእርግጥ ይመሳሰላል:: ነገር ግን ጭብጡ ይለያያል:: የኔ ጭብጥ በድህረ ታሪኩ እንደገለጥኩት በሀገራችን ብዙም ስለማይታወቁት ስለ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ የአገዛዝ ዘመን መፃፍ ነበር:: በሳቸው ግዜ ሀገራችን ልዩ የሆነ ግዜን አሳልፋለች:: .....አንድ ትንቢትም አለ....
"የንግስናውን ስም "ቴዎድሮስ ሳልሳይ" ያደረገ (በተፀውዖ ስሙ ዳዊት የሚባል) አንድ ሰው ኢትዮጵያ ላይ ብልፅግናን ያሰፍርና ለ40 አመታት ያስተዳድራል, ከዚያ በህዋላ ድብልቅልቅ ይልና እስከምፃት ቀን ድረስ እልቂት ይሆናል...." የሚል ትንቢት!
የኔ ጭብጥ የሚያጠነጥነው በዚህ ታሪክ ዙርያ ነው:: የዚያኛው ታሪክ ጭብጥ ግን no matter what, any gift is a gift, don't turn it down! የሚል ጭብጥ ነው ያለው:: ከጭብጥ አንፃር ያለው መለያየት ይህ ነው:: መቼቱንም ብታየው እብዲሁ የተለያየ ነው:: ግን አንተ እንዳልከው, የታሪኩ ውቅር መመሳሰል ይገርማል::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Fri May 21, 2010 12:43 am

ፍካሬ

ንኡ ንትሀሰስ ....ንኡ ንትፈሳህ ባቲ
ስቡህኒ ስርርር መፅዐ...ዮም ዛቲ

ፍካሬ ይደሉ ....ባቲ ለስርርር
ፍስሀ ወሀሴት....ዋርካነ ትገብር

ስርርር ስርርር ..... ዘይግርም ስመ
በግብር ወክእሌከ.... ኹሉ ተደመ

ይደሉ ይባቤ ወይደሉ ሀዋዝ
ሀመ መዋ ኹሉ በስርርር ዝ

ደናግላን ሀቡ ከበሮ ወንፍዑ ቀርነ
ዋርካ ተፈስሀ.....በስርርር ወልድነ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby አቃቂ » Fri May 21, 2010 4:57 am

ስርርር! ስርርር The Redoubtable!!! የምን መቸነፍ ነው?! ጨለማ ከፅልመት ሌላ ምን ያውቅና?! በል ቀጥል ብርሃን ይሁን...
እናንተ ፋኖ : ሾተል ምናምን የምትባሉ ሌጌዎኖች! ዋ!!
አቃቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 25
Joined: Thu Sep 09, 2004 5:25 am
Location: Akaki Beseka, Ethiopia

Postby ስርርር » Fri May 21, 2010 5:42 pm

ሪያና
ማድሪድ- ስፔን:: በምኖርበት አፓርታማ ውስጥ ብዙ ደሀና እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የውጪ ዜጎች አሉ:: በተለይ እኔ የምኖርበት የአፓርትመንት ባለ 2 ክፍል ሲሆን ሁልት ፍናፍንት (ጌይ) የሆኑ ስፓኒሾች አንደኛው ከፍል ውስጥ ይኖራሉ:: አንደኛው ሖዜ ይባላል ሌላኛው ደግሞ ሎፔዝ:: ብዙ ግዜ ሎጵፔዝ እንደሴት ስለሚለብስ ሚስት እሱ ሳይሆን አይቀርም:: ለኔ አንዱን ክፍል በነፃነት ሰጥተውኛል:: በተሰባበረ የስፓኒሽ እንግሊዝኛ "አልማዝ....ኢት ኢዝ ኦል ዩርስ..." ያሉኝን አልረሳውም:: መጀመርያ አካባቢ ምንም ነፃነት አይሰማኝም ነበር...ህዋላ ግን ራሴን ነፃ አድርጌው እንደውም እነሱ ፊት ሁሉ ልብሴን አወልቅ ነበር::

የስፔን መንግስት ለስደተኛ በጣም ይመቻል:: ትምህርት ቤት እንድሄድ, ቅዋንቅዋ እንድማር, አድርገው የ600 ዩሮ የምግብ ካርድ አብረው የሰጡኛል:: ታድያ እንደልቤ ለደሀዋ እናቴ ስራ ሰርቼ ገንዘብ መላክ ባልችልም እኔ ደስተኛ ነኝ::

ይስፔን ህዝብ በአብዛኛው ተግባቢ ና ጥሩ ናቸው:: እኔም ይህንኑ መግባባታቸውን አይቼ ቅዋንቅዋቸውን ለመልመድ ብዙ ጥሬ ነበር:: አልሆነልኝም አንጂ...ምናልባትም ትልቅ ከሆንኩ በህዋላ ስለመጣሁ ይሆን? የሚገርመው እስካሁን ድረስ የማውቀው ውስን ቃላትን ብቻ ነው::
ቦነሲያስ.....እንደምን አደርሽ
ቦነታሬ.....እንደምን አደርሽ
ግራሲያስ....አመሰግናለሁ....
ሙይ ቢየን ኢቱ? እኔ በጣም ደህና ነኝ አንቺስ? እና የመሳሰሉትን የቀንተቀን መግባቢያዎችን ያኔ የመጣሁ ሰሞን ነበር ያወክዋቸው::

ነገር ሁሉ የሚሆነው ለበጎ ነው ብዬ አምናለሁ:: ከነዚህ ጌይ ሩምሜቶቼ ጋር ስኖር....አንድ ቀን ማታ ሎፔዝ በጣም ያመሻል:: ሆዜ በቅናት ሲቃጠል ያመሽና... ይወጣል:: ሲመለስ አንድ ካርቶን ቢራ ይዞ ይመጣና እኔ ክፍል እንዳስገባው ይነግረኛል:: ሰመር ስለነበር ማድሪድ ግለቷ ጨምሯል:: በዚሁ ምክንያት እኔም የለበስኩት ፓንት የምታክል ቁምጣና ጡቴን ብቻ የሸፈነች ብጣቂ ጨርቅ ነበር:: ቢራውን እኔ ክፍል ሳይሆን ፍሪጁ ውስጥ ከተትኩና መለስ ስል ከምንግዜው ልብሱን እንዳወላለቀ ሳላውቀው እርቃኑን ሶፋው ላይ ቆሞ አየሁት:: ስለሴክስ ብዙም እውቀት የለኝም:: አንድ በጣም የምወደው ቦይ ፍሬንድ ኢትዮጵያ ነበረኝ:: አልፎ አልፎ እንወጣ ነበር::

ሆዜ...ተንደርድሮ መጥቶ ብድግ አደረገኝ ወደላይ:: ዝም አልኩ...ሰውነቴም ሙሉ ለሙሉ ታዘዘ:: የስደት ጣጣ:: ከዛማ ባልተገረዘ ሸለፈቱ.... ኖርማል ብቻ ሳይሆን ከሎፔዝ ጋር እንደሚያደርጉት እንዳልሆነ እንዳልሆነ አደረገኝ::

ከዚያ በህዋላ ከኔ ጋር ሳምንትም ሳይኖሩ ተያይዘው ወደሰሜናዊቷ የስፔን ከተማ ሳን ሰባስቲያን አቀኑ::

9- የጭንቅ ወራትን ብቻየን አሳልፌ.... ፈረንጅ ከመሆነዋ በቀር ቁጭ እናቴን የምትመስል ልጅ የዛሬ 6 አመት ተገላገልኩ:: ሪያና እልክዋት ስሟን:: ንግስቴ! እንደማለት ነው .... ስፓኒሹን አቀላጥፋ ትናገረዋለች....አማርኛውንም ከማስተማር አልቦዘንኩም::

እንቆቅልሽ ሆኖ እረፍት የሚነሳኝ ግን ሆዜ ያውቅ ይሆን?? የሚለው ነው:: ማወቅስ አለበት?አባትሽ ሞትዋል ስላልክዋት ብዙም አትጠይቀኝም.... ግን አንድ ቀን...ትልቅ ስትሆንልኝ... ታሪኬን በደንብ እነግራታለሁ::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Sat May 22, 2010 6:14 pm

ቅቅቅቅቅቅቅ ጉድ! ዘረፍኸው::
እስኪ ቀጽለው!
ስርርር wrote:ፍካሬ

ንኡ ንትሀሰስ ....ንኡ ንትፈሳህ ባቲ
ስቡህኒ ስርርር መፅዐ...ዮም ዛቲ (ቅቅቅ)

ፍካሬ ይደሉ ....ባቲ ለስርርር
ፍስሀ ወሀሴት....ዋርካነ ትገብር አሜን ትገብር!

ስርርር ስርርር ..... ዘይግርም ስመአዎ! ዘ ይገርም! ቅቅ
በግብር ወክእሌከ.... ኹሉ ተደመ ግብሩን አናቅም! ቅቅቅ

ይደሉ ይባቤ ወይደሉ ሀዋዝ
ሀመ መዋ ኹሉ በስርርር ዝ

ደናግላን የትኞቹ? ቅቅ) ሀቡ ከበሮ ወንፍዑ ቀርነ
ዋርካ ተፈስሀ.....በስርርር ወልድነ

I Love it! ቅቅቅ

ዳሞት!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ቀብራራው ንጉሴ » Sat May 22, 2010 8:38 pm

ሾተል wrote:
- ቃላቶች ሆኑ አረፍተ ነገሮች ያላግባቡ ገብተው ድርሰቱን አበላሽተውታል::


ሰላም ሾተል በምትሰነዝራቸው ሀሳቦች ብዙ ጊዜ ባልስማማም ያለህን የስነ-ጽሁፍ ችሎታ እንዲሁም የሰዋሰው አገባብ ሳላደንቅ አላልፍም:: እናም ካንተ የማልጠብቀው ስህተት ካንቢነት ወደ ተሳታፊነት አሸጋገረኝ::

ቃላት ወይም ቃሎች በሚል ይታረም::
ቀብራራው ንጉሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:27 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests