የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 4:58 pm

የቅፅበት

በህሙማን መመርመርያ ክፍል ውስጥ ሆኘ የእለቱን የህክምና ስራዬን ለመጀመር እየተሰናዳሁ ነው :: ሲስተር ትርሲት የክፍሉን በር ከፍታ የተለመደውን ማኪያቶ አቅርባልኝ ወጣች :: ጃኬቴን ከመስቀያው ላይ አኖርኩና ገዋኔን ለብሸ ቁጭ አልኩ :: ከፊቴ ብዙ የህሙማን ፋይሎች ተደርድረዋል ::

በሽተኛ ላስገባ ? አለችኝ ሲስተር ትርሲት
አዎን አልኩ ::
አንድ ወጣት አይነርግብ የለበሰች ውርዚት ብቅ አለችና
"ሀይ ዶክ " አለችኝ :: ሀይ ፕሊስ ሀቭ ኤ ሲት ! አልኩ

እሺ ጀሚላ ...ምንድነው ችግሩ ? ምን ሆንሽ ?
ዶ /ክ እኔ ከዚ በፊት ወንድ አላውቅም :: ግን ፔሬዴ ከቀረ ቆይትዋል :: አንተ ደግሞ ፕሮፌሽናል ጋይኒስት ነህ ሲባል ሰምቼ ቼክ እንድታደርገኝ ነው ....አለች እንደማፈር እያለች ::

የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ጠየቅህዋትና ቃሬዛውን አስተካክየ በይ ነይ እስኪ ...ፊዚካል ቴስት ያስፈልግሻል አልክዋት ::
እያፈረች ቀሚስዋን ገልባ በጀርባዋ ጋደም አለች ::

two bud and a leaf ይሉታል በሳይንስ :: ሁለቱን የፊት እና አውራ ጣቴን ደርቤ ለአመል ያህል ወደብልትዋ ከተትኩት :: ዋው !!!!! እውነትም ውርዚት ! ድንግል ናት :: ወንድ አታውቅም :: በዚያ ላይ እስላም ናት :: ፔሬዷ ለምን ቀረ ????
ደምና ሽንት እንድትሰጥ ነግሬያትና ወጣች :: ከዚያ በህዋላ ...ቀኑን ሙሉ ያ ትኩስ ገላዋ በአይኔ ድቅን እያለብኝና ሙያዬን ሲፈታተነኝ ዋለ :: በምሳ ሰዓትም እንዲሁ ቁጭ ብየ ስለራሴ ሳስብ ...እስከመቼስ እንደማላገባ ? ልጅስ መቼ እንደምወልድ ....ስተክዝና ስቆዝም የሚያፅናናኝ የነበረው ረጅም ባትዋ , ዝብርቅርቅ ብሎ እዚህም እዚያም የበቀለው ጭገሯ , ብስል ቀይ ገላዋ ....ነበር :: እንደሳይንሱ ከሆነ የፔሬድ መቅረት ኖርማል ነው :: እስከ ሁለት ወር ድረስ ሊቀር ይችላል ::

የምርመራዋ ውጤት ኖርማል ከሆነ እንደማገባትና ሌላው ቢቀር ice breaker እንደምሆን ለራሴ ወስኜ ወደቢሮየ ገባሁ ::

የብዙ እንስቶችን የምርመራ ውጤት ሳስረዳ , መድሀኒቶችን ሳዝ , ኮንግራ ስል , አብሬ ሳዝን ...ምናምን ቆይቼ ተራዋ ደርሶ የወደፊትዋ ሙሽራዬ ....የዛሬዋ በሽተኛዬ ገባች :: ፈገግ ስትል ጉንጮችዋ ስርጉድ ! እያሉ ልቤን አዘለሉት :: ጭገርዋ ላንድ አፍታ በአይኔ መጣብኝ :: እንደምንም ራሤን ተቆጣጥሬ ውጤቱን ማንበብ ጀመርኩ ::

ሥሜቴ ሁሉ በአንድ ግዜ ኩምሽሽ አለ :: ላብ ላብ አለኝ ቀና ብየ ሳያት የጥዋቱ ትዝ ብሏት ይመስላል ፈገግ አለች :: ድንጋጤዬን እንዳታውቅብኝ በጣም ተጠንቅቄ ለአንዳንድ ተጨማሪ ምርመራዎች ስለምንፈልጋት ነገ ተመልሳ እንድትመጣ ነግሬያት ወጣች :: በሩ ላይ ስትደርስ ግን መለስ ብላ በሁለቱም አይኖችዋ ጥቅስ ! አደረገችኝ :::

ኖ ኖ ኖ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ???? የ 19 አመትዋ ወጣት ልጃገረድ የሁለት ወር እርጉዝ ናት :: የደም ምርመራ ውጤትዋን ሳዬው ...ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ ....

የቅፅበት ሙሽራየ ! ሳላስበው እንባየ በጉንጨ ክብልል አለ ...
Last edited by ስርርር on Mon Aug 22, 2011 8:14 pm, edited 28 times in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

የስርርር መጣጥፍ 2

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 5:00 pm

አክንባሎ ሰባሪዬ

የመስሪያ ቤቴ ዋና ማናጀር ሆኘ ከተሾምኩኝ እነሆ ሶስት ዓመት ሆነኝ :: በብቃት በቅቼ አልነበረም :: ግን ህይወት ራሷ እየመራች ያደረሰችኝ ቦታ ነው ::

የዛሬ 5 አመት አካባቢ እዚሁ መስርያ ቤት በዋና ፀሀፊነት ሳገለግል ሳለ አሁን የያዝኩትን ቦታ ይዞ የነበረው ኦኬሎ የሚባል የጋምቤላ አካባቢ ምሁር ነበር :: በስራው ህፀፅ የሌለበት ሊቅ ነበር :: አንድ ፋይል የሱ ጠረጴዛ ላይ አታድርም :: አምሽቶም ቢሆን ፈርሞበት , አፅድቆ , የውሳኔ ሀሳብ ሰጥቶ , ወስኖ , የመስሪያቤቱን መሪ እቅድ ብቻውን አውጥቶ .....ብቻ ምን አለፋችሁ ድንቅና ውጤታማ አስተዳዳሪ ነበር :: በፀሀፊነቴ (የሱ ፀሀፊ ሆኘ ) ከሱ ብዙ ነገሮችን ተምሬያልሁ :: እንዲያው በደፈናው ብዙ ነገሮችን :: ያን ግዜ እልልታ (ልጄ ) ተወልዳ የ 8 ወር አካባቢ ነበረች :: ባለቤቴ ብዙ ግዜ በስራ ምክንያት ወደተለያዩ ክፍላተሀገራት ስለሚሄድ የብቸኝነት ኑሮ ያነጫንጨኝ ነበር :: አንድም ቀን ታድያ የኦኬሎን ትዛዛት ከመፈፀም ወደህዋላ ብዬ አላውቅም :: ምሁር ነዋ :: እሱም ያዝንልኛል :: ፍቃድ ብጠይቀውም እምቢ አይለኝም ::

ቀኑ አርብ ነበር :: ከቀኑ 10 ስዓት :: ሚያዝያ 18 ቀን :: ኦኬሎ በውስጥ ስልክ ደውሎ ብዙ ስራ ስላለ ማምሸት እንዳለብኝ እና ከኔ ሌላ ማንም ሊያግዘው የሚችል እንደሌለ ነገረኝ ::

ወይኔ ልጅት ! እልልታ አሳዘነችኝ :: አባቷ እንድተለመደው ክ /ሀገር ነው :: አለቃየን ደሞ እምቢ ማለት አልችልም :: ለማንኛውም ለሰራተኛዬ ደውዬ ነገሬያት ስራዬን ቀጠልኩ :: ያለወትሮየ ልቤ ፈራ ፈራ ይል ነበር :: ከባለቤቴ ውጭ ለማንም ወንድ ወጥቼ አላውቅም ::

ኦኬሎ ብዙ ፋይሎችን ከምሮ ወደኮምፒተር ያስገባል :: ከእኩል በላይ የሚሆነውን ወስጀ እኔም ወደኮምፒተር እያስገባሁ ነበር :: ከምሽቱ 2:17 ሲል ሁሉን ነገር ጨርሼ በ MS Office Outlook ኢሜል አረኩለት :: ከጥቂት ደቂቃዎች በህዋላ በስልክ ጠራኝ :: እየተነጫነጭኩና የልጅ እናት መሆኔን ....ወደቤት መሄድ እንዳለብኝ እንደምነግረው እያሰብኩኝ ወደቢሮው ገባሁ ::

"ስራችንን ጨርሰናል !" አለኝ ፈገግ እያለ :: ከጥቁር ፊቱ ውስጥ ብልጭ የሚሉት ነጭ ጥርሶቹ ልብ ያማልላሉ ::
ብድግ ብሎ መጥቶ ግምባሬን ሳመኝ :: እኔም ተሳምኩኝ :: ዝቅ ብሎ ጉንጨን , ከንፈሬን ....መጠመጠኝ ::
ህሊናየ አልፎ አልፎ "ተይ " ቢለኝም አካሌ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ነበር :: It has been a long time. ምን ማለታችሁ ነው :: እልልታ ከተወለደች ግዜ ጀምሮ ባለቤቴ አድርጎኝ አያውቅም :: አክንባሎውም አልተሰበረም ::

ልብሴና አንድ ባንድ ከላየ አወላልቆ የሱን ማውለቅ ሲጀምር ስሜቴ ጣርያ ነካ :: ሳላስበው ትርጉሙን በማላውቀው ንግግር እለፈልፍ ነበር :: የተለበለበ ግንድ የሚመስለው አካሉ , ወንዳወንድ ግርማው , ቁመቱ , የደረቱ ስፋት .....ኡኡኡኡ ! ከዚያማ ...የፖሊስ ቆመጥ በሚያህለውን እንትኑ ልቤ እስኪጠፋ አደረገኝ :: አክንባሎዬንም ሰበረው !!! ሲጨርስ ያለኝን እስካሁን አልረሳውም
"ጭገርሽን በጣም ነው የወደድኩት !"

በማግስቱ ድንግልናዋ እንደተወሰደባት ልጃገረድ መራመድ ሲያቅተኝ , ደውዬለት አልመጣም አልኩት :: በሶስተኛው ቀን ቢሮዬ ስገባ ..... በቦታዬ ሌላ ፀሀፊ ተቀምጣለች ::

ከወደግራዬ በኩል አይኔን ወርወር ሳደርግ ....የመስሪያ ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆኘ መሾሜን የሚገልጥ ፅሁፍ አየሁ :: ዋጋዬ !!!

ኦኬሎ መ /ቤቱን እስኪለቅ ድረስ ሳላናግረው ወደሌላ መ /ቤት ተዛወረ :: እኔም አክንባሎዬ የተሰበረበትን ቢሮ ይዥ ይህው አለሁ :: ዛሬ ታድያ ዝክር ነው :: ሚያዝያ 18:: ለሱ መታሰቢያ ሁልግዜ ለአንድ ወር ያህል ጭገሬን አሳድግና ሚያዝያ 18 እላጨዋለሁ ::

አክንባሎ ሰባሪዬ የት እንዳለ አላውቅም !
Last edited by ስርርር on Wed Apr 28, 2010 11:46 pm, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ዶዮ ወ ካዛንች » Tue Apr 27, 2010 5:35 pm

"ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ
በዋለበት ሜዳ አይቀርም ማኩራቱ"

ማን ነበር ያለው?
አየህ ወንድሜ ስርርርር በፊልድህ ስትወል ሲያምርብህ ! በቃ ያንተን ኦዲየንስ ፈጥረህ እንደዚህ የጽሁፍ ችሎታህን አሳይ! አለቀ ደቀቀ::
ቁምነገር ክፍል ገብተህ እንደኔ ሁኑ አትበል::
አይ ጣፊ ይጥፋል ነው የሚባል ስርርርርርር ብዕርህን አደነቅኩ!
በርታ ወንድም ዓለም !!!
ዶዮ ወ ካዛንች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Mon Jan 18, 2010 5:27 pm

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 6:24 pm

ዶይዬ! አንቺ ግን በጣም አንባቢዬ ነሽ አይደል? በጣም ነው የማመሰግንህ! You are the man!
እንደው ለእርምት ያክል!
"ሰው ከተሰማራ...እንደየስሜቱ...
ከዋለበት ሜዳ አይቀርም ማፍራቱ....

ትንሽ ቅር ያልኝ እንደው ይህ ቁምነገር ቦታ ምናምን የምትይው ነው::
Last edited by ስርርር on Wed Apr 28, 2010 11:46 pm, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

የስርርር መጣጥፎች 3

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 10:34 pm

ስርርር
እኔስ ስርርር ነኝ ....በሬ ጠምዶ አዳሪ
ያለረፍት የማርስ ...ገበሬ ታታሪ .

ልዝረፍልህ ቅኔ ላፍስስልህ ቀለም
ስርርር የወንዳጥር ባል እንዳንተ የለም

ብላ ዘፍና ነበር የአለም ኮረዳ
ብር አምባር ሰባሪ ሳልሆን እዳበዳ

ሳያረጅ ያረጀ ...የማያውቅ ዳዴ
ባለ ሶስት እግሩ ሰው ....ስርርር አይደል እንዴ ?

የት ነው ያለው ብለው ቢጠይቅዋችሁ
ዋርካዋ ጥላ ስር ያውና በሏቸው
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Tue Apr 27, 2010 10:40 pm

ስ ር ያ

በጉንጭሽ ስርጉዳት .... ተለመኝልኛ
በይና ስደቢኝ ..... ከልብ ዳተኛ

ታውቂዋለሽ አንቺም ...... ወደየት እንደዋልኩኝ
ስራስር ነቀላ ..... ቆላ እንደወረድኩኝ

ከልብ ዳተኛ ..... መሆኔን አታውሪ
ይልቅ ጥሪኝ ብለሽ ....ስር ነቃይ ታታሪ

ሳታረግዝ ያምራታል የኔ ቅብጥ ያለች
ደግሞ ብላ ብላ እብድ አማረኝ አለች


ምላሽ መለስኩላት ቅኔ በሐገርኛ
የሧን ተጠቅሜ የእብድ አማርኛ


የቅኔ ድርድራት ምን ያደርግልኛል
ጨዋ መሃል ሆኘ ....ይደናገረኛል
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤስመር » Wed Apr 28, 2010 12:06 am

ቤት ለንቦሳ ብለናል ..ስርርር!!
ቅኔዎቹን ዘረፍካቸው ነው የሚባለው :!: :lol:
ደሞ ሸቤ እንዳትገባ በመዝረፍ ወንጀል ተከሰህ . :lol: :lol:
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

Postby ቆንጂት08 » Wed Apr 28, 2010 6:23 am

አቶ ስርርር.... ከመጀመሪያው አወቄአለሁ ጥሩ ጽሀፊ እንደሆንክ አሁን ችሎትህን ከቦታው አዋልከው እንግዲ አንተን ስከተል መክረሜ ነው. ዋርካ ስነጽሁፍ አንዲህ አዲስ ደራሲ ሲፈጠር አግባብ ካለው ቦታ ያስደስታል የማቀነባበር ስነጽሁፍን ችሎታ አለህ.......
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby ስርርር » Wed Apr 28, 2010 7:36 pm

አቢሻግ

የ5 ዓመታት የትዳር ህይወትዋን መለስ ብላ ስታየው የተቀላቀለ ስሜት, የማይወለድ የትረገዘ, የደስታ አይሉት የሐዘን ሲቃ ያስምጣታል:: ሆድዋን ሆድ ይብሳትና እንባ እንባ ሲላት, ለምትወደው ሽማግሌ ባልዋ ፍቅር የምትከፍለው መስዋእትነት ትዝ ይላትና ካንጀቷ ፈገግ ትላለች::-ትስቃለች:: ትፍነከነካለች:: አያ በሪሁንን በጣም ትወደዋለች....በፍቅር:: ከባሏ ብዙ ቁምነገሮችን ተምራለች...ስለሀይማኖት, ስለሀገር ፍቅር, ስለታሪክ, ስለፍልስፍና....ስለህይወት....ስለፈጣሪ....ስለአለም......ብዙ ብዙ ነገር:: አያ በሪሁኔ!! ትለዋልች ታድያ... በስስት::

ገና በልጅነቷ ነበር ለአያ በሪሁን የተዳረችው:: የአባትዋን አጥንት ቆጥሮ...በሀብቱ ተመክቶ ነበር ያገባት:: የግንባር ነገር ሆኖ እንጂ ለአያ በሪሁን በየትኛውም መስፈርት ቢሆን ትበዛበታለች:: አያቷ ሊሆን የሚችል ሰው ነውና:: ያኔ ገና የ 15 ዓመት ልጅ ሳለች ነበር:: ታድያ አያ በሪሁንን ከምትወዳቸው ቤተሰቦቿ ስለለያይ ትጠላው ነበር:: በህዋላ ግን ውድድድድድድ አደረገችው::

ሁል ግዜ ብክን እንዳለች ቀኑ መሽቶ እንደገና ይነጋል:: የኑሮን ጣጣ በልጅነት ተሸክማ በእንጉርጉሮ ብቻዋን ትተክዛለች:: ትንገዳገዳለች:: የብቸኝነት ትዳር...ብቻ!...ብቸኛ::-ግን ደግሞ የማይለማ ባል....አጋር!:: ብቸኛ... ግን ጥርስ ያበቀለ የ4-ዓመት ህፃን::እንዲህ የመቆዘሟ...የመባከንዋ,....የብቸኝነቷ ሁሉ መንስዔ የባሏ መቀዝቀዝ...የጉልበቱ መድከም ...ነው:: እነሆ እንዲህ ከሆነ 4 ዓመት ሆነ አይደል....ልክ የክንዴ እድሜ!

"አያ.......ሮማኔን የበላው መቼ ነበር...?" ትላለች ወጣትነት ሲፈታተናት:: ስጋዋ አሁን አሁን ሲላት:: ሽማግሌው ባሏ...ሴት ያደረጋትን ቀን በሀሳብ እያሰበች.....በስሜት ትጋልባለች:: ስጋዋ ረጠብጠብ እስኪል ታስታውሰዋለች:: መለስ ትልና ደግሞ ስሜቷን ትገታለች:: ታማትብና....
"ሆሆይ ምናይነት ፈተና ነው ባካቹ....." ትላለች::
እንደግና የተዳፈነው ስሜት ....ብድግ ይላል:: እንዲሁ ሲወድቅ ሲነሳ ቀኑ ይመሻል::

ሲመሽ ታድያ አያ በሪሁኔን እቅፍ አድርጋው ትተኛና በሀሳቧ ወደ አቢሻግ ትሄዳለች:: በሀሳብ ፈረስ ተሳፍራ ያቺን መሰሏን እንስት ትፈልጋታለች:: አያሌ አመታትን ወደህዋላ ተጉዛ ወደነቢዩና መዝሙረኛው ዳዊት ዘመን ትግዋዛለች:: እንስት አምሳያዋን ፍለጋ በሐሳብ ትባክናለች::

"አቢሻጌ! እስቲ እንዴት ቻልሽው የዳዊትን የቀዘቀዘ ገላ አቅፎ መተኛት!......" በረዶና እሳት እንዴት አስማማሽ.....?" ብዙ ጥያቄዎችን ትጠይቃለች::

ደግሞ መለስ ትልና በራቁት አካሏ ቅዝቅዝ ያለውን ግማሽ አካሏን (ባሏን) ታሞቃለች:: እቅፍ ታደርገዋለች:: ፍቅር! ታድርገዋለች......."የኔ ዳዊት!" ትለዋለች:: ኮራ ኮራ ትላለች:: አይኖችዋም ለእንቅልፍ ይከደናሉ:: ደግሞ ይነጋል::

ዛሬ የለት ውሎዋን ከምንጩ ለመጀመር በዚያው ናት:: ሳርና ጉድፉን በሽክናዋ ቂጥ ገፈፍ እያረገች ጥሩውን ውሀ ወደ እንስራዋ ትሞላለች:: ትርጉሙን እሷም የማታውቀውን, ግን ደግሞ አንጀት የሚበላውን እንጉርጉሮዋን የሚረብሸው የጥዋቱ ንፋስ ሽውታና ውሀውን ወደ እንስራው ስትጨምረው የሚሰማው ድምፅ ነው::- ጩርርርር........>>

ቁንጮውን በወጉ ያሳደገችለት ክንዴ ካጠገቧ ሆኖ እናቱን ሲያስተውል ቆየና በኮልታፋ አፉ
"ማማዬ!...በታም ወድሻለው" አላት::
በፍቅር እንባ የተሞሉ አይኖችዋ ቃኘት አደረጉት....::
"ስምን መላክ ያወጣዋል የኔ ጌታ:: አንተ ክንዴ ነህ" ብላ ለራሷ አጉረመረመች.........አቢሻግ!

------------------------------
ለማታውቁት ...አቢሻግ ማለት የነቢዩ ዳዊት የመጨረሻ ሚስት ናት
Last edited by ስርርር on Wed Apr 28, 2010 11:41 pm, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ዶዮ ወ ካዛንች » Wed Apr 28, 2010 8:13 pm

ኪስ አውላቂው ጭፈራ ቤት ገብቶ የኪ-ቦርድ ተጫዋቹን ጣቶች አለንጋነት ተመልክቶ " አሁን ይህን የመሰለ ጣት ለማይረባ ነገር ይጠቀምበት" አለ አሉ::
ወንድሜ ስርርርርም ይሔን የመሰለ ብዕር ከጓሮ አስቀምጠህ ነው እዛ ሁሉ ጦርነት ውስጥ የከተትከን? ይገርማል!
ስርርርርር እንደ ተራ ሰው ስለፈረጅኩህ ይቅር በለኝ ወንድሜ::

ጫረው እኛም በጫጫርከው እንርካ!

የጠከራራው ዶዮ::
ዶዮ ወ ካዛንች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Mon Jan 18, 2010 5:27 pm

Postby ቆንጂት08 » Wed Apr 28, 2010 8:20 pm

ስርርርነት ደግሞ አቢሻንግ ማለት የዳዊት ሚስት ናት በል ዲክሽነሪም አይስፈልገኝ አንተው ከተሮገምክልን መለካም ጅምር ........
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

የስርርር መጣጥፍ 6

Postby ስርርር » Wed Apr 28, 2010 11:22 pm

ኢያረምም ስርርር

ወኢያረምም ንሱ ይገብር ቃለ-ግስ
ሊተ ቅኔ ስርርር እምኩሉ ይሄይስ

ይቀትል በቅኔ ወበነቢብ ይንግር
በእዝል ባራራይ በሀልዮ ያአምር
ንሱ ውእቱ ዝንቱ ስርርር

ተደምመ ሰማይ ወተደም ምድር
ዘገብረ አምላክነ ለስርርር (2)

ሊቀ-ሊቃውንት ሀዳሴ መምር
ውስተ አለም እለ ይነብር
እስመ ውእቱ ኢያረምም ስርርር (2)
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby saron*** » Thu Apr 29, 2010 8:36 am

ዋው ስርርርር በታም ኮንጆ ንው
saron***
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 168
Joined: Thu Apr 29, 2010 7:50 am

Postby sleepless girl » Thu Apr 29, 2010 4:17 pm

ኽረ.ረረረ.......ስርርርርር አንዴ? ይህ ሁሉ ችሎታህን የት ደብቀህ ነበር እስከዛሬ?? እሚገርም ነው. :shock: :shock: :shock: :shock:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby ስርርር » Thu Apr 29, 2010 7:42 pm

ም ስ ጋ ና
ለማመስገን ብዬ ....
ወጉ እንዳይቀርብኝ ... እኔም ከሰው አይቼ
ብእሬን አሾልኩኝ....
ብራናየን ፍቄ ቀለም በጠበጥኩኝ

ፊደሉን ሳረባ ስቆጥር አያነሰኝ
ቃላቶቼ ሁሉ ስድብ እየሆኑብኝ
ኧረ እኔስ አዘንኩ...ሰዎች ድረሱልኝ????

ዶዮ ዘካዛንቺስ ቆንጂት ከስራኤል
እንዴት ላመስግንሽ አጣሁልሽ ቃል

ጣራ ጣራውን ሳይ ቃላትን ፍለጋ
ስሊፕለስ ሆኘ ሌቱ እንዲሁ ነጋ

ኧረ እንዴት ላመስግን እናንተን አሴመር
ከንቱ ሆነ ሁሉም. ቃል ጠፋ በሀገር

የሳሮን አበባ ላበርክት ስጦታ
የምድረ በዳ ተክል ለናንተ ወሮታ

ፍቀዱልኝና ልሳደብ ባካችሁ
እልቃሻ አንቢዎች አንዴ ልበላችሁ

ሰንዝሩ አስተያየት ተናገሩ ግዋዶች
ልሳደብ ፍቀዱ እናንት ያለም አሮች
ወይም ልበላችሁ እነኛ ለምጣሞች
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests