የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ስርርር » Thu Apr 29, 2010 8:30 pm

.......ቢላዋን

ከሙኒክ ወደሀኖቨር ጉዞ ለማድረግ ፈፅሞ አስቦት ስለማያውቅ ትንሽ ስጋት ወረር አድርጎታል:: ሀኖቨር ለስደተኛ አትመችም ሲባል ሰምትዋል:: ያውም ደግሞ እንደሱ ያለ ህገ-ወጥ ስደተኛ::

"አየ...እዚያው ሙኒክ ብቆይ ይሻለኝ ነበር...ምነው እግሬን በሰበረው..... " አለ ደምሌ....

ባቡሩ ውስጥ ፊትለፊቱ የተቀመጠው ሰውዬ በግልምጫና በጥላቻ አስተያየት እየደጋገመ ያየዋል:: ሰውየው እድሜው በ 30ዎቹ መጀመርያ ቢሆንም የጭንቅላቱን ጸጉር ሙልጭ አድርጎ ስለተላጨው እድሜው ጠና ያለ አስመስሎታል:: ይኮሳተራል!...ፊቱን ያጨማድዳል, ...ደምሌ በማያውቀው ጀርመንኛ ይሳደባል.....

ባቡሩ ጉዞውን ቀጠለ:: ሀኖቨር ከተማ ሜትሮ ስቴሽን ሊደርስ ብዙም አይቀረውም:: ደምሌ አጠገብ ተቀምጦ የነበረው አረብ ነገር ከፊታቸው የተቀመጠውን ጀርመናዊ ወጠምሻ የፈራ ይመስል ሹክክ ብሎ ተነሳና ወደ ህዋላ ወንበሮች ሄደ::

ደምሌ ፍርሀት ቆነጠጠው:: ይህንን ያስተዋለው ጀርመናዊ ወጠምሻ ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ከደምል ጎን ቁጭ አለ::
"ወይኔ ...አለቀልኝ ዛሬ" የኢትዮጵያ አምላክ አንተ እንዴት ታደርገኛለህ????" ደምል በውስጡ ፍርሀት እንደብርድ አንቀጠቀጠው::

ጀርመናዊው ወጠምሻ ጢቅ አድርጎ ወደደምል ተፋ::
ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ዝም አለ ደምሌ.....
"ወይ ወንድነቴ! ወይ ስደቴ!!".......በውስጡ ተቆጨ.....

ወጠምሻው ..... ይባስ ብሎ ጎራዴ የሚያህል ጩቤውን የደምል ጎን ላይ አሽት አሸት ማድረግ ጀመረ::

በጀርመንኛ ሐኖቨር ሜትሮ ስቴሽን እንደተደረሰ የባቡሩ አስተናጋጅ አሳወቀች::

በፍጥነት እርምጃ ከባቡሩ ወርዶ በሩጫ ወደአሳንሰሩ ገባ:: አሳንሰሩን መልሶ ዘግቶ ጉዞውን ወደላይ ቀጠለ:: እንደደረሰ አሳንሰሩ ተከፈተ:: የሀኖቨር ከተማ በምሽት መብራቶች ደመቅመቅ ብላለች:: ወጠምሻው እንደጅብራ የተከፈተው አሳንሰር ፊት ቆሞ ፈገግ አለ:: "አገኘሁሽ!" በሚል አይነት አስተያየት::

ደምሌም ከሌሎች ጋር ሹክክ ብሎ ወርዶ ከሩጫ ባልተናነሰ ሁኔታ መንገዱን ተያያዘው:: ሀኖቨርን ስለማያውቃት ወዴት እንደሚሄድ እንክዋን አያውቀውም:: ብቻ ማምለጥ::

ገልመጥ እያለ ሲያይ ከ 5 ሜትር በማይበልጥ ርቀት ወጠምሻው እየተከተለው ነው:: ሳያስበው መሮጥ ጀመረ:: ብዙ ፀጉራቸውን ሙልጭ አድርገው የተላጩ ነጫጭ ወጠምሾች ከበቡት:: ሁሉም ጎራዴ የሚያካክል ጩቤ ይዘዋል:: አንድ ግዜ ሁሉም ወደሱ ሮጡበት:: ተስፋ ቆርጦ አይኑን በሁለት እጆቹ ይዞ ቁጭ አለ:: ሁሉም ይጮሀሉ:: ሞቅ ያለ ላብ በላዩ ሲወርድ ተሰማውና....."ገና ሳይወጉኝ እንዴት ደማሁ..." በሚል እሳቤ አካባቢውን በእጁ መዳሰስ ጀመረ::

ደምሌ ዛሬ ቀጠሮ አለበት:: ጀርመርን ኢሚግሬሽን:: የ7 አመቱ የስደት ኑሮ ሊያበቃ ነው:: ዛሬ ዜጋ ሊሆን ነው::

"ተነስ እንጂ....ረፍድዋል:: ምን ትደባብሰኛለህ? አደርንበት አይደል እንዴ....? በል ተነስ የሀብሻ ቀጠሮ አንዳይሆንብን::" አለች አለች ህብስቴ! አጠገቡ ተኝታ ስታንኮራፋ የነበረችው::....
ባዶ የቮድካ ጠርሙስ.....የሲጋራ ቁርጥራጮችና እዝህም እዚያም የወደቁ ያልታጠቡ ካልሲዎች የቤቱን ወለል ሞልተውታል::
"ምን ሆነህ ደግሞ ይህ ሁሉ ላብ የኔ ጌታ.....?".....አለች በስስት እያየችው::
ተይኝ እባክሽ...." አለና .እየተነጫነጨ ተነሳ.....
"ዶሮ ብታልም ቢላዋን" ነው ተረቱ የሚለው?" አላት::
ፍንድቅድቅ ብላ በረጅሙ ሳቀች::
ምን ያስቅሻል......
... :lol: :lol: ጥሬዋን ነው የሚባለው....ወይ አንተ.... ሳቅዋ ቀጠለ
Last edited by ስርርር on Thu Apr 29, 2010 10:11 pm, edited 2 times in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ትርዛ » Thu Apr 29, 2010 9:52 pm

ስርርርዬ! ለካ ባለሙያ ኖርሀል? አይ ችሎታ! ምናል ታዲያ ለኔም ውዳሴ ብትፅፍልይ?

ስርርር wrote:ም ስ ጋ ና
ለማመስገን ብዬ ....
ወጉ እንዳይቀርብኝ ... እኔም ከሰው አይቼ
ብእሬን አሾልኩኝ....
ብራናየን ፍቄ ቀለም በጠበጥኩኝ

ፊደሉን ሳረባ ስቆጥር አያነሰኝ
ቃላቶቼ ሁሉ ስድብ እየሆኑብኝ
ኧረ እኔስ አዘንኩ...ሰዎች ድረሱልኝ????

ዶዮ ዘካዛንቺስ ቆንጂት ከስራኤል
እንዴት ላመስግንሽ አጣሁልሽ ቃል

ጣራ ጣራውን ሳይ ቃላትን ፍለጋ
ስሊፕለስ ሆኘ ሌቱ እንዲሁ ነጋ

ኧረ እንዴት ላመስግን እናንተን አሴመር
ከንቱ ሆነ ሁሉም. ቃል ጠፋ በሀገር

የሳሮን አበባ ላበርክት ስጦታ
የምድረ በዳ ተክል ለናንተ ወሮታ

ፍቀዱልኝና ልሳደብ ባካችሁ
እልቃሻ አንቢዎች አንዴ ልበላችሁ

ሰንዝሩ አስተያየት ተናገሩ ግዋዶች
ልሳደብ ፍቀዱ እናንት ያለም አሮች
ወይም ልበላችሁ እነኛ ለምጣሞች
ትርዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 78
Joined: Fri Apr 09, 2010 10:10 pm

Postby ስርርር » Fri Apr 30, 2010 5:26 pm

የልጅ አባት ለሆነው ወንድሜ ይችን ግጥም እንካ ልበለው

አንደኛውን ባልጋ ላይ ..... እየተጫወትኩኝ
ሁለተኛው ደግሞ ..........ሚስቴን እያየሁኝ
ሁለት ግዜ አምጨ........ አይኔን ባይኔ አዬሁኝ

ሁላችሁም አደራ እንክዋን ደስ ያለህ በሉልኝ::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Fri Apr 30, 2010 5:57 pm

ወንድሜን እንክዋን ደስ ያለህ በሉልኛ! I am happy for you bro. I am happy that I am an uncle
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ቆንጂት08 » Fri Apr 30, 2010 7:46 pm

ሰላም ስርርር....እንዴት ያልክ የአርት ሰው ነህ ጨዋታ ታቃለህ
ድርሰት ማለቴ ነው ....እንኩዋን ደስ ያለው ለወንድምህ መቸም ስሙ እንዳንተ ከሌላ ፕላኔት የመጣ ሳይሆን እንድማይቀር ነው እስኪ ሹክ በል ስሙ ማንይባላል?
ለማወቅ ጉዋጉዋሁ.....
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby ኤስመር » Sat May 01, 2010 12:49 pm

"..ፍሬው ያማረ ዘር.......እንዲሆንለት:
አባት ደስ ይለዋል ልጅ ሲወለድለት::"
??
የዘፈኑን ግጥም ረስቸዋለሁ.... አጎት ሆንክ ማለት ነው :lol: :roll:
ልጁ አድጎ ተመንድጎ .... አገሩን አስጠሪ እንዲሆን በመመኘት...
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

Postby ብሌን » Sat May 01, 2010 11:48 pm

ስላም ስርርር እንደዚህ ታመጣው አይ በል ቀልድ አያምርብህም በዚሁ ቀጥል በጣም ደስ የሚሉ ጽሁፎች ናቸው የት ደብቀሀቸው ነበር በል? እንግዲህ ትርንጎን የሚተካ አገኘን ልበል? ቅቅቅቅ
ብሌን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 328
Joined: Sun Jan 04, 2004 1:13 am

Postby saron*** » Sun May 02, 2010 7:08 am

ወንድምህ እንካን ደስ አለው አንተም እንክዋን ደስ አለህ.
saron***
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 168
Joined: Thu Apr 29, 2010 7:50 am

Postby ያባቱልጅ » Sun May 02, 2010 2:33 pm

ስርርር wrote:ወንድሜን እንክዋን ደስ ያለህ በሉልኛ! I am happy for you bro. I am happy that I am an uncle


እንኩዋን ደስ አለህ.....የወንድምህ ልጅ ፍቅር ከወንድምህ አልፎ ላንተም ይተርፋል...ልጅ ማለት ውስጡ ንጹህ የሆነ ፍቅር ነው.....

ሳምልኝ
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ስርርር » Mon May 03, 2010 5:27 pm

በጣም አመስግኗል! ...ወንድሜ:: የሚገርመው እሱም ዋርካ ውስጥ አካውንት አለው:: ስሙ የትኛው እንደሆነ ግን አላወኩትም:: እሱ ግን እኔ አካውንት እንዳለኝ በፍፁም አያውቅም::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

የስርርር መጣጥፎች 8

Postby ስርርር » Mon May 03, 2010 8:04 pm

182ኛ ትውልድ

ደጁ ሁሉ በሚያዝያ ወር ጭጋግ ተሸፍኗል:: ሚያዝያ 3/1969:: ሉሲ መኝታ ቤትዋ ውስጥ ሆና የልደት ፓርቲዋን ፎቶዎች ታያለች:: ፈገግ ትልና...ትኮሳተራለች....ደግሞ ፈገግ ትላለች:: ዛሬ የልደቷ ማግስት ነው::

የምዕራብ ዮክሻየር ተወላጅ ናት... ግን ደግሞ አሳ የመሰለች ጠይም:: በእንግሊዝ ሀገር ውስጥ ከነጭ ቤተሰብ ተወልዳ ጠይም መሆኗ የሁልግዜ እንቆቅልሿ ነው::

"ይህ ትልቅ የቤተሰብ ሚስጥር ነው ልጄ".....አለቻት ሚስ ሱዛን አላም:: በአልጋዋ ፊትለፊት ተቀምጣ:: በአረንግዋዴ ቢጫና ቀይ ጨርቅ የተጠቀለለ ትንሽዬ ሙዳይ በጇ ይዛለች::
"የዚህ ቤተሰብ ትውልድ ሁሉ እድሜው 18 ሲሞላ ይህንን ታላቅ የቤተሰብ ስጦታ ያገኛል" አለችና የተጠቀለለውን ሙዳይ ሰጠቻት::
"በነገርሽ ላይ "ሉሲ አላም" የመባልሽ ዋናው ሚስጢር ዛሬ ይገለጥልሻል::"........ ሁልግዜም አላም ነን::"
"በድጋሜ እንክዋን ለ18ኛው አመት የልደት በአልሽ አደረሰሽ የኔ ጠይም ወርቅ" አለቻትና ግምባሯን ስማት..."ጥያቄዎች ካሉሽ ጠይቂኝ" ብላ ወጣች::

ሉሲ በማታውቀው እንግዳ ስሜት እጆችዋ እየተንቀጠቀጡ የሙዳዪን ጥቅል ፈታችውና ሙዳዩን ከፈተችው:: ሙዳዩ ውስጥ ልክ እሷን የሚመስል... ግን ቁንጮ ያለው ህፃን ልጅ ፎቶ አለ:: በአንገት የሚጠለቅ ትልቅ ዶቃ እና ትንሽዬ መስቀልም በዚያው ነበር:: አይኗን የሳበው ግን የብራና ጥቅልሉ ነው::

ጥቅልሉ በማህተም የታተመ ሲሆን በላዩ ላይ ሱዛን አላም 181ኛ ትውልድ ይላል:: ማህተሙን....እየተቻኮለች ፈታችው::
.
ብራናው ላይ የተፃፈው ፅሁፍ በጥንት እንግሊዝኛ ቢሆንም ማንበብ ጀመረች:: ከላይ ብዙው ፅሁፍ ከግዜ ብዛት ተፋፍቆ ጠፍቷል:: ቀሪው እንዲህ ይላል....

"ለምን ሞተ ብለው እንዳስወሩብኝ አላውቅም:: እናቴንና አባቴን በጣም በልጅነቴ ባጣቸውም ዛሬም ቢሆን ገፃቸው በፊቴ ነው:: እነኚህ ሰዎች ለምን ወደዚህ ምድር እንዳግዋዙኝ አላውቅም:: እናቴ ክፉኛ ያስላት ነበር:: ትዝ የሚለኝ በትልቅ መርከብ ባህር ላይ ነበርን:: እናቴን የሚረዳት አጥታ እዚያው ባህር ላይ ሞተችብኝ:: ከዛማ...አዲስ ቅዋንቅዋ አዲስ ባህል ለምጀ በህንድና በዚህ በሀምፕሻየር የእንግሊዝ ግዛት ኖሪያለሁ:: እማማ ቪክቶርያን በጣም እወዳታለሁ::

ባለፈው የፀደይ ወራት ት/ቤት ሲዘጋ ለእረፍት ወደለንደን ሄጄ ነበር:: በዚያ እንደእህቴ የማያት ልእልት ኤልሳቤት ጋር በፈፀምነው ፍቅር ምክንያት እነሆ የ 7 ወር እርጉዝ ናት:: እኔንም ለመቅጣት በዱብሊን በረሀ በግዞት አስቀምጠውኛል:: ይህንን ደብዳቤ በእናትህ/በእናትሽ (በኤልሳ) በኩል ይደርስሃል/ሻል:: የኔ እጣ ፈንታ አሁን ይለያል:: ሊገድሉኝም ይችላሉ:: ትውልዴንና ፍቅሬን ግን አይገድሉትም:: ሀበሻነቴንም አይፍቁትም::"
ልኡል አለማዬሁ ቴዎድሮስ (ብቸኛው የቴዎድሮስ ልጅ)::"
ይላል ብራናው....

...ሚስጥሩ ተገለጠ:: እኔ ያቢሲኒያ ፈርጥ ነኝ:: እኔ ያለማየሁ ነኝ:: የቤተሰብ ስሜ አላም የሆነው ለዚህ ነው:: እኔ ሀበሻ ነኝ...." አለች አልጋዋ ላይ እየዘለለች:: ደስታዋ ጣራ ነካ!
ጥቅልሉን መልሳ እንደነበረ ጠቀለለችውና በስሟ አተመችው:: ልእልት ሉሲ አላማዮ 182ኛ ትውልድ::

ማህተሙን አተመችና ፈገግ አለች:: የእውነት ፈገግታ:: የታላቁ የሐበሻ ንጉስ የአፄ ቴዎድሮስ ዘር መሆንዋ በደስታ አቀለጣት::
Last edited by ስርርር on Wed May 05, 2010 6:49 pm, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ብሌን » Mon May 03, 2010 11:46 pm

ስላም ስርርር ወይ ጉድ አንተ ሰው አሁንስ ትርንጎ ትሆን እንዴ ብዬም ጠረጠርኩ :lol: በል የጀመርከው የሚጥም ታሪክ ቶሎ ቶሎ አጣድፈው አታሳጥረው ለቀቅ ለቀቅ አድረገው ቅቅቅ:: በነገራችን ላይ ትርንጎ መታለች ካላየሀት ሀ ሀ ሀ
ብሌን
ብሌን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 328
Joined: Sun Jan 04, 2004 1:13 am

Postby ዱዲ » Tue May 04, 2010 12:34 am

ስርርርር የአንባቢዎችን ቀልብ ክፉኝ እየሳብከው ነው:: በርታ!
ዱዲ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 316
Joined: Fri Mar 05, 2004 8:41 am
Location: united states

የስርርር መጣጥፎች 9

Postby ስርርር » Tue May 04, 2010 6:51 pm

ሰንሰለት

ግራ መጋባቴን ......... ካንቺ በመለየት
ማለሜን ማሰቤን ........ የፈፀምሽውን ክህደት

አየችና እንስቴ ....... እዚህ ነኝ አለችኝ
የግራ ጎኔ አጥንት..... እቅፍ ጋበዝችኝ

እኔ አንቺን ስወድ .... አንች ወደሽ ሌላ
አብልጣ የምትወደኝ ..... መጣችልኝ ህዋላ

መንፈሴ አንቺን ሲል.....ልቤ ሲያመነታ
ክህደትሽን ሲያስብ....ሲቅዋጥር ሲፈታ
ለበቀል ሲጣደፍ....ሌት ቀን ያለፋታ

አብልጣ የምትወደኝ ..... መጣችልኝ እንስቴ
ቦታዋን ፍለጋ ..... ከጎኔ ካጥንቴ

እኔ አንችን ሳደርግ ..... የልቤ ላይ ንግስት
ውስጥ ውስጤን በርብራ ...... እሷ ገባችበት

ሆነና ነገሩ..... የፍቅር ሰንሰለት
በልቤ ዙፋን ላይ....እሷ ሆነችበት

ግራ ገባኝ እኮ.....ፍቅሬ መላ በይኝ
ዛሬም እወድሻለሁ...እንቺ ስትጠይኝ

ነፍሷ እስክትወጣ.....እሷም ትወደኛለች
የሌላም አይደለህ..... የግሌ እያለች

መላ መላ መላ!!!!!!!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ቻይና ገ/ማርያ » Tue May 04, 2010 10:18 pm

ስርርርርርርርርርርርር......
በጣም አሪፍ ነው ግን አንዳንዶቹን አረፍተነገር, ህረግ ሳብላላቸው "አይጥ ሸተተኝ"

እውነት ሁሉም የስርርርርርርርርርርር...ስራነው???
ወይስ ከሌላ አምጥተህ ልታካፍለን??


ይመችህ

ስርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
>>>>>....
ቻይና ገ/ማርያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 05, 2009 6:05 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests