ታዋቂው የቲያትርና የቴሌቪዥን ድራማ ተዋናይ ጀምበሬ በላይ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በ፸፱ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ሥርዓተ ቀብሩም በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል። በ፲፱፻፵፱ በአገር ፍቅር ቴያትር የጀመረው ጀምበሬ ለረጅም ጊዜ የሠራው ግን በብሔራዊ ቴያትር ነበር።ከታወቀባቸው ቴያትሮች መካከል እናት ዓለም ጠኑ፥ሀሁ በስድስት ወር እና የአዛውንቶች ክበብ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው።ከቴሌቭዥን ድራማዎች ደግሞ ያልተከፈል ዕዳና ሞት ፍለጋ ሄደች የሚጠቀሱ ናቸው ።
https://www.facebook.com/fanabroadcasti ... 16/?type=3
https://www.facebook.com/ethiopianewsag ... 68/?type=3