የ CYBER ጉዶች!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

እስካይሽ!!!

Postby እድል » Wed Aug 17, 2005 8:45 am

ላይመለስ ትላንት ሄዶ
ቀን ሲለወጥ ጎህን ቀዶ:
ፍንትው! ፏ! - ብላ ጸሃይ
ሞቆ ሲደምቅ - ምድር ሰማይ:
እኔ ገና’አንጎላጃለሁ
በእንቅልፍ ልብ’ናውዛለሁ
ሳልነቃ - እወዘወዛለሁ
በግብዳው አዛጋለሁ::

የተጨናበሱ አይኖቼን
እያሻሸሁ በእጆቼ
እወጣለሁ ተጎትቼ
ከአልጋዬ ተነስቼ::
ከዚያም ተደናብሬ
እያሸሁ ጸጉሬን - ተንጨብርሬ
እየተማታ እግሬ ከግሬ:
ጠጋ ነዋ ከመስኮቱ
ደጅ ደጁን ለመመልከቱ::

ስምገው በረዥሙ
የጥዋት አየር አይ መጣሙ
ንጽህናው ማስገረሙ::
ከዛፍ ላዩ ጎጆ መድረክ
ጣፋጭ መዝሙር ሲፈበረክ:
የወፎቹን ኦርኬስትራ
ያለዳንስ ያለዳንኪራ:
ያለጭብጨባ ያለ እስክስታ
ሳጣጥመው በዝምታ:
ጀመረች ልቤ ልትጨፍር
ደስታን ልትረጭ በደሜ ስር
መላ አካሌን ልታነዝር::

የጽጌረዳ መአዛ
አፍንጫዬን እያዋዛ:
ሆነኝ የጥዋት ፍስሃ ደስታ
ቀን አዋይ ስንቅ - ጣፋጭ ስጦታ::

ሰማዩን ብዬ ቀና
ሳይ ጥራቱን አንደንቅና:
መደመሜ ሳያልቅ ገና
ሃሳቤ ይዋልልና
ዱካሽን ይከተልና
ይፈልጋል ያንቺን ፋና
የወሰደሽን ያን ጎዳና::

ሲጥለቀለቅ አዕምሮዬ
ባንቺ ሃሳብ ህሊናዬ:
እኔነቴን እረሳና
ውበትሽን አልምና:
ድው ድው ትላለች ልቤ
ትረግጣለች አንዳች ጮቤ
ትመታለች የደስታ ድቤ::

ከዚያ ታዲያ ምናለፋሽ
መቁነጥነጥ ነዋ መረባበሽ
መጥተሽ እዚህ ባይን እስካይሽ
ከች እስክትይ አቆራርጠሽ
ጠረፍ ድንበሩን አሳብረሽ
በሰማይ ባቡር አየር ቀዝፈሽ::

ውርስ ትርጉም በእድል
(Source: ለጊዜው ያልታወቀ)
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Postby Debzi » Wed Aug 17, 2005 10:09 am

ወይ መታደል? እኛም እድለኞች ነን አንተ ዋርካ ላይ በመሳተፍህ አንተም እድለኛ ነህ የዚህ አይነት ታለንት ስላለህ:: እድል ውነትም እድል ልበል እንጂ ሌላ ምን እላለሁ!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

....

Postby እድል » Fri Aug 19, 2005 9:33 am

......
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

ለ Profanity ሊቆች!!

Postby እድል » Wed Sep 07, 2005 12:08 pm

ለዛ ባለው ጠምዛዛ አሽሙር
አውቆ እውነቱን በማሳከር
ጎሸምሸም - ሸንቆጥ በነገር:

ተረብ ጥሎ መፎጋገሩ
ተሞጋግሶ መደራደሩ
ተዘራጥጦ መነጋገሩ
በስላቅ ቧልት መጠጋገሩ:
ማን አለ እኮ ከፋ
ጨዋታነቱ እስካልጠፋ::

በአዝናኝ humor በተሞላ
ጭውውት ቁም ነገር ሲብላላ:
Sarcasmሙን እየተረተሩ
ሲዋዛ ቀደዳው - chatteሩ
አቤት ወጋችን ማማሩ!!!

ክርክሩ በውስጠ-ወይራ
ቅኔ ነክ ቃላት ውርወራ
ተጋግሎ ሲያንሰራራ
ተውቦ ወሬው ሲደራ:
መንፈሳችን በተሃድሶ
ከድካም ጭንቀቱ ተፈውሶ
ዘና ይላል ተመልሶ::

ግና ሁሌም አይሞላማ
ጥልቅ ይላል አንዱ ጠማማ:
ባፈጠጠ ስድብ ዜማ
ወጋችንን እያግማማ
አጨማልቆ ሊያገለማ::
አድፍጦ እያደባ
አለአግባብ እየገባ
ጨዋታን ሊያደፈርስ
አቆርፍዶ ሊያፋርስ::

ሞያው የሱ ነው መራቀቅ
በ profanity መመጻደቅ
በራቁት ብልግና መሞሻለቅ:
'ዝቅ" ባለ ጸያፍ ወሬ
መበርገድ እንደ አቦሬ::

ሸፈንፈን አርጎ በለበጣ
ለመባለግ 'ሳያስጠጣ'
መች ያውቃል ቃላት መረጣ
ማቀርሸት እንጂ እንደመጣ::
የሚያውቀው እሱ ከፍጥረቱ
መለጠፍ ብቻ እንደንፍጡ
መቅዘን ነው Vulgar በጠጡን::

እድል
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Postby 4get.this » Thu Sep 08, 2005 12:20 pm

8) perfect
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

ለእድል...

Postby Ellenie » Thu Sep 08, 2005 8:46 pm

አቶ እድል ግጥሞችህን በጣም በጣም ወድጃቼዋለሁ!! በጣም! ፓ! አሰኝተውኛል የመጨረሻውን ግን አላነበብኩትም ቅቅቅቅ

ያንተው ጫሪ ኢሌኒ :wink:
Smile
Ellenie
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1000
Joined: Wed Jul 27, 2005 4:36 am
Location: ethiopia

Postby SUAVE » Fri Sep 09, 2005 7:43 am

CONSPICUOUS CRITICS OF PROFANITY :wink:
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby ኦፕን » Fri Sep 09, 2005 8:13 am

ተጫወት ጨዋታህን
የሰጠህ <B>እድል</B> ፈንታህን
ሰውን ምን አስመለከተህ
የሱ ግብር ላንተ ላይሆን
መቅዘን ካሰኘው ይቅዘን
ጥረግ ያለህ የለ አንተን
ጨዋነኝ ብለሀል ራስክን
እንዳፍህ ያድርግልህ
እንዲህ ሁኑ
እንዲያ ሁኑ ምን አስባለህ
ዋርካ እንደው የግል አይደል
አባትህ የገዛልህ
ያንተ ቁም ነገር ላንተው ነው
ሰንፍጦት ይሆናል ለሌላው
አናም አታስገድደው
በግድ ልጋትህ አትበለው
ይልቅ አንተ ዝም ብለህ
ተጫወት ጨዋታህን
የሰጠህ<B>እድል</B> ፈንታህን
ኦፕን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 148
Joined: Wed Mar 09, 2005 11:13 am
Location: guinea

Thanks

Postby እድል » Fri Sep 09, 2005 10:21 am

4getthis - Thanks!!

Elleni - Thanks!! (የመጨረሻውን ግጥም አላነበብኩትም ነው ያልሽኝ? ..... ግን እኮ እሱን ገና አልጻፍኩትም :lol: .... )

Suave - Thanks!!

ኦፕን - Thanks!! ግን ም-ነ-ው .... ጎዳሁሽ እንዴ?
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Re: Thanks

Postby ኦፕን » Fri Sep 09, 2005 10:33 am

እድል wrote:ኦፕን - Thanks!! ግን ም-ነ-ው .... ጎዳሁሽ እንዴ?


አየኸው ጨዋነትህን?! ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል የነበረው ከዚችው ለማታለፈው ነው? ይልቅስ ዝም ብለህ ከ <B>ግን ም-ነ-ው</B> ጎራ ተቀላቀል::
ኦፕን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 148
Joined: Wed Mar 09, 2005 11:13 am
Location: guinea

Re: Thanks

Postby እድል » Fri Sep 09, 2005 11:17 am

ኦፕን wrote:
እድል wrote:ኦፕን - Thanks!! ግን ም-ነ-ው .... ጎዳሁሽ እንዴ?


አየኸው ጨዋነትህን?! ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል የነበረው ከዚችው ለማታለፈው ነው? ይልቅስ ዝም ብለህ ከ <B>ግን ም-ነ-ው</B> ጎራ ተቀላቀል::


ኦፕን! ኦፕን!

ም ነ ው!
ከተጻፈው ውጪ ብዙ ለመረዳት የሞከርክ መሰለኝ:: ወይስ ይሄ 'reading between the lines' የሚሉት ነገር ይሆን? እንደኔ እንደኔ ግን አንተ ካልከው ውስጥ አንዳንዱ ነገር 'between the lines' አይደለም ከመጽሀፉ በስተጀርባ መኖሩን እርግጠኛ አይደለሁም ..... ም ነ ው ያስባለኝም ይኸው ነው ሌላ አይደለም ...... ያዙኝ ልቀቁኝ?! ... አረ በናትህ!!::

ባይ ዘ ዌይ የነ 'ምነው' ጎራ የቱ ይሆን?

እድል
To handle yourself, use your head. To handle others, use your heart.
እድል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Thu Feb 17, 2005 11:51 am
Location: ethiopia

Re: ለቲቴክስ

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 10:23 am

የኔ ነገር jul ተጽፎ sep ነው የማየው ወይ ጉድ! የነጋብሽ እንደማትለኝ ነው መቼም! እረ አይገባም እኔኮ ያንን ያህል አላዘንኩብህም ደሞ ለዛውም ባንተ? እንዴት መጨከን እችላለሁ? አይዞህ እድልዮ ስቀልድ ነው እሺ:: የግጥምህ ነገር ግን በማይችል አንደበቴ እንዴት ላድንቅህ እንጂ ብዙ እል ነበር::

አክባሪህ

እድል wrote:አዝኛለሁ ግን በሌላ ሳይሆን ያ የዘባረቅኩት ነገር ያንቺን ምቾት በመቀነሱ ብቻ እንጂ! የሞከርኩት ዋርካ ውስጥ በታዘብኩት ነገር ላይ ተመርኩዤ ትንሽ ፈጠራ ነገርም ኖሮት የተሰማኝን ለማሳየት ነበር... ድንገት የሚያዝናና ሊሆንም ይችላል ብዬ ማለት ነው ... የናንተን ስም የጠቀስኩትም እንደቃለ ጉባኤ የተናገራችሁትን verbatim ለማስቀመጥ ሳይሆን ..በቃ ብዙ ጊዜ በተለያየ አርዕስት ላይ ምክራችሁ ሲጠየቅ ስላየሁ ብቻ ነው ....አሊያማ የሌላም ሰው ስም ላነሳ ሁሉ እችል ነበር (ማለቴ ማንም ሊሆን ይችላል ዋርካን የሚያዘወትር እስከሆነ)... እናም ደግሞ በዚያ አይነት አርዕስት ላይ እጅሽን እንደማታስገቢ አውቃለሁ ... በደንብ ካየሽው እንዲያው ስለጥያቄው መነሳት እንጂ ስለናንተ አስተያየት መስጠት እኮ ምንም አላልኩም...

ቲቴክስ ይህ ሁሉ ላያስፈልግ ይችል ይሆናል ግን I just want to convey to you that hampering your comfort was not at all my intention.

በተረፈ ግን በዋርካ ላይ የማየውን መልካም ባህሪሽን እና ፖዘቲቭ አመለካከትሽን ማድነቅ መብቴ እንደሆን በዚህ አጋጣሚ ብነግርሽስ?

ሰላም ቆይልን.
እድል ነኝ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Re: የዋርካ ጉዶች!

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 10:26 am

ውይ ደብዚዮ አፈር በበላሁ ነው የምትይው ስትደነግጪ እኔ ልብላልሽና! አይዞሽ እኔኮ ያንን ይህል አላዘንኩም! እኔ እህትች ደሞ የሰው ምክር እሰማለሁ! ሰው ለመቀየም የሚጨክን ሆድ የለኝም ስለዚህ አንጣላብሽ እኔና እድልዮ አይዞሸ!

አክባሪሽ!

Debzi wrote:
እድል wrote:
ሚስቴ ሆዴ የኔ ገላ
ባታውቅም እኔን በድላ
ልተዋት ነው ይለናላ:
ምን ላርግ ታዲያ....እቃዋ ቦርቅቋላ
ሞኒካ ወይ ትትና በሉኛ እስቲ መላ
መፍትሄ አምጡ blah blah blah blah

በነ ት(ህ)ትና ትንተና
ባለጉዳይ ሲል ዘና
የሞኒካን ወግ ጥረቃ
ሲከታተል ብሎ ነቃ

እንዲያ ቢሆን ደሞ እንደዚ
ስትለው ማድሞዜል? ደብዚ
ይላታል thank you! now I see!
Oh now I really really see!

እድል


ትትናዬ ወይስ አንቺ እንደምትይው ትትናዮ ልበልሽ?
እንድትስቂ ብዬ ነው.....(እነኛን Emoticons አልወድ አይደል?)
የሆኖ ሆኖ...እድልን ሚስአንደርስታንድ ያረግሽው ስለመሰለኝና አንቺንም እሱንም ስለምወድ ለማስታረቅ ገባሁ!
አንቺን ሞኒካንና እኔንኮ መካሪዎች አድርጎ ነው ያቀረበን ግጥሙ ላይ:: ቅር አይበልሽ እንጂ ትትናዮ!

በተረፈ:- እኔንና ዳሞትን ባንድ መስመር ጻፍሽን?? ተዪዪ ኧረንደው አይሆንም! ዳሞትና እድል ብትዪ እሺ...ደብዚ?? ሰው እንዳታስቂብኝ ነው እሚባለው? ለማንኛውም Thank you for your vote of confidence!

ትላለች እህትሽ ዲብዚ......ይቅርታ ደብዚ ለማለት ነው:: እድልና ጊታ (ይቅርታ ጌታ) ናቸው የራሴን ስምም የሚያስረሱኝ!! (It's an inside joke between ጌታ እድል and myself!


Where is 4get.this by the way????
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Re: ለእድልና ለደብዚ

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 10:29 am

ሞኒዮ ወዳጄ! የምወድሽ ልጅ! ሰሞኑን ጥፍት ብለሽ በጣም ናፍቀሽኛል በነገራችን ላይ!!! እንዳው ደብዚ እንዳለችው ይሆን እንዴ? እኔ እህትሽ ለሚዜነት አለሁ አንቺ ብቻ አትጥፊ!!!

አክባሪች

Monica**** wrote:እኔ እምለው አልታይም እንዴ ይሄን ያህል :?: :?: :?: :?: :?: :lol: :lol:
ሁለታችሁም ለትህትና ምስጋናውን ስታዥጎደጉዱላት ሞኒካና ለና አመስግናለሁ ለድጋፍሽም አይባልም ወይስ የኔና የለና ጽሁፍ እናንተ ስክሪን ላይ አይወጣም :lol: :lol: :lol:
ትትናዬ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ላንቺ ተመቅኝቼ አይደለም እንደው ቀንቼ ነው :oops: :cry: :oops: :cry:
እንደፈለጋችሁ ዝጉኝ እንጂ እኔ ለናንተ ያለኝን አድናቆት አይቀንስውም!!!
ስላም ሁኑልኝ
አድናቂያችሁ
ሞኒካ
Monica**** wrote:እድል ያገር ልጅ
በጣም ቆንጆ አጻጻፍ ነው በርታልን
አንተና Debzi በጣም ትስማማላችሁ በአጻጻፍ እስኪ ደብዚዬ እንደድሮው አዝናኝን የኔ ቆንጆ!

አክባሪህ
ሞኒካ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

እድልዮ

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 10:30 am

በጣም ይቅርታ የኔ ነገር ሁሌ አርስት ቀየርሽ እየተባልኩ መወቀስ ነው ስራዮ:: ለማንኛውም ያንተ ግጥም ይቀጥል እኔም ጨርሻለሁ ካሁን በኃላ አረብሽም እንዳው ወዳጆቼን ስላየሁ ነው::

አክባሪህ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests