ሁሜይዲ
አገር ቤት በአመት አንዴማ ለአንድ ወር ተኩል አካባቢ እሄዳለው ያው አንዴ ስለሆነች ብርቅ ትሆንብኛለች እንጂ :lol: ያንተን አስበው በአመት 40 ጊዜ በየስምንት ቀኑ አንዴ ደረስ ብለህ ትመለሳለህ ማለት እኮ ነው እኔ ደግሞ እንኳን የግል ቦይንግ ልመኝ ምንም እንኳን እንደየኢትዮጵያ አይነት ጥሩ አየር መንገድ ብመርጥም ፈርስት ክላስ እንኳን ገብቼ አላውቅም ሁሌ በኢኮኖሚ ክላስ ነው የምሄደው ግን በዛም ደስተኛ ነኝ
ያ ያልከኝ መጽሀፍት ቤት ኩራዝ መጽሀፍት መደብር ይባል የነበረው ይሆን ? እኔ የካቴድራል ልደታ ወንዶች ትምህርት ቤት ተማሪ ነበርኩና ያን አካባቢ በደንብ አውቀዋለው ኤንሪኮ የተባለ ጥሩ ኬክ ቤት ፊት ለፊቱ እንደነበር ትዝ ይለኛል እንግዲህ መጽሀፉ እዛ ካለ አስገዛለው ካልተገኘ እንግዲህ አንተን አስቸግራለው እንጂ ምን አደርጋለው 50 ኮፒ ገዝተህ አንዱን ለኔ አትጨክንብኝም አይደል? :lol:
የሞኒካ ነገርማ ተወኝ የዋርካ ጭቅጭቅ ምር-------------ር ብሏት ወደ ፌስ ቡክ ሺፍት አደረገች መሰለኝ :: ቢሆንም እንዳልከኝ እስቲ በግልም "ሞኒክዬ ምነው ምነው ምነው ምን አጠፋን ..." የሚል አይነት መልእክት እልክላትና መልስ ከሰጠችኝ የጠፋችበትን ምክንያት አሳውቅሀለው :)
ደሀና ሁን