by Acts 8:26-39 » Thu Dec 08, 2005 6:57 pm
ዲጎኔ
የመለስ ዜናዊን አገዛዝ ለመጣል የቆመ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ብሔራዊ እርቅን ይደግፋል:: ኢትዮጵያችንን ከመለስ ዜናዊ ቀንበር ነፃ ለማውጣት የሚደረገው ትግል ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያናችንንም ነፃ የሚያወጣ ነውና የእምነቱን ተከታዮች ይበልጥ ለትግል ያነሳሳናል:: ማንም እንደሚያውቀው ውጭ የሚገኙ አባቶች የእንቅስቃሴው ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች ናቸው:: በአገር ውስጥም ቢሆን እንደ ሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ያሉ አባቶች የወያኔን አገዛዝ ከመጀመርያው አንስተው ኮንነዋል ሕዝቡም እንዳይቀበለው አስተምረዋል:: በቅርቡ እንኳን እነ ተፈራ ዋልዋ "የነፍጠኞች ምሽግ" ብለው ባደባባይ ሲያውገዟት እነ ጁነዲ ሳዶና አባ ዱላ ገመዳ ምእመናኗን ሲያስጨፈጨፉባት ቤተክርስትያኗን ሲያቃጠሉባት ትንፍሽ ያላለው "አባ" ጳውሎስና የሚቆጣጠረው "ቤተ ክህነት" በሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል ከማድረስ ግን ወደኹዋላ አለማለቱ ወያኔው በቅድስት ቤትክርስትያናችን ላይ የጫናቸው መሆኑን ያረጋግጣል ::
ወደ ነጥባችን ለመመለስ ስለ ሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም በዋርካ general ላይ እንደአሁኑ ተገቢ ያልሆነ ዉረፋ ስንዝረህ መልስ እንደሰጠንህ ታስታውሳለህ:: አጋጣሚ ጠብቀህ በዚህ መድረክ ማንሳትህ ስላስገረመን ነው በድጋሚ መልስ የፃፍነው::
የምትለውን የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ስሙን ሰምተህ ሳይሆን ገጾቹን አገላብጠህ አንብበህ የምታውቀው ከሆነ በየትኛው ገጽ ላይ ግዝት መፃፉን ጠቅሰህ አሳየንና የምትናገረውን እውነትነት አረጋግጥ:: ከሺህ አመታት በላይ የቆየ የዶክትሪንና የሥርዓተ አምልኮት ልዩነትን በ"እርቅ" ስም ተው የምትል ከሆነ ግን ፈጽሞ ሊሆን የማይቻል ነገር ነው:: በነገራችን ላይ አንተ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነህ በኦርቶዶክስና ካቶሊክ መሀል በገላጋይነት ራስህን መሾምህም የሚያጠያይቅ ነው....