ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime. Image

Postby አለም1 » Wed Jan 04, 2006 6:09 am

ይህቺን የዘመኑን ተክኖሎጂ አጠቃቀም በቅጡ ባለማወቃችን ተሳስተን አሳስተንዎት ወይንም አስቀይመንዎት ከሆነ ከፍተኛ ይቅርታ እንጠይቃለን::
ወደ አነሷቸው ነጥቦች ስንመለስ የርስዎ ሻለቃውን አለማወቅ የርስዎን ማንነት የሚገልጽ ስለመሆኑ ያነሳነው ነገር የለም::ቢያንስ ቢያንስ በዚህ የውይይት መድረክ የሚካፈል ሊያውቃቸው ይችላል ከሚል ግምት ብቻ ነው ያንን ያልነውና በዚሁ ቢያልፉት ደስ ይለናል::የርስዎንም ኢትዮጵያዊነት ለማሳነስ ያደረግነው ሙከራ የለም::ኢትዮጵያዊነትን ማንም ለማን የሚሰጠው ወይንም የሚነሳው አለመሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን::...
ስለዘር ማጥፋት የሰጠነው ትርጉም አልነበረም::የተፈለገው ጄኖሳይድን የዘር ማጥፋት በሚል የአማሪኛ ሐረግ ልንተካው የምንችል አልመስላች'ሁ እንዳለን ለመግለጽ ነበር::ስለዘር ማጥፋት እርስዎ "እኔ ዘር ማጥፋት ሲባል የመስለኝ አማራ ወይም ጉራጌ, ትግሬ ብሎ አንዱን የጠላውን ዘር መደምስስ..." ካሉት የተለየ ትርጉም የሰጠን መስሎት ከሆነ ላለመግባባታችን ምክንያቱ እንደምሳሌ የተጠቀምንበት የአንድ ቤተሰብ ታሪክ መሰለኝ::የዚያን ቤተሰብ ታሪክ ያቀረብነው እነሻለቃ ያጨፋጨፉት ቤተሰብን በቤተሰብ ጭምር እስከሆነ ድረስ ያ የዘር ማጥፋት ሊባል ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄያዊ አስተያየት ነበር ያቀረብነው::የፖለቲካቸው ተቀናቃኝ የሆኑትን ሁሉ ይደመስሱ ነበር እንጂ ያንድን ዘር ተወላጅ/ ተወላጆች አነጣጥረው ያጠቁበት ጊዜ ያለ አልመስላች'ሁ እንዳለን ነው የገለጽነው::
"..የአንድን ቤተስብ ዘር ማንዘር ማጥፋት አልመስለኝም!" ያሉት ሌላ ጥያቄ ቀስቅሶብናል::በመጀመሪያ የአንድ ቤተሰብ ዘር ማንዘሩ እንዲጠፋ ለምን ተፈለገ?ማነውስ ፈላጊው?መልሱን ለባለ ሙያ እንተወዋለን::
ስለግብዝነት ያነሳነውም ቢሆን እርስዎን የሚመለከት አይደለም::ለማለት የተፈለገው መለሳውያንን ብንሆን የትናንት ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረቡ ላይ ትንሽ የዳተኝነት እርምጃ እናሳይ ነበር:: በጃችን ደም አለና!!! አንድ የመድረኩ ተሳታፊ "አረመኔ በአረመኔ ላይ ሲፈርድ::" ሲሉ የኛን አባባል እጥር ምጥን ባለ አገላለጽ ረድተውናል::አሁን የተግባባን ይመስለናል::
Monica**** wrote:አለም 1
በቅድሚያ ለአስተያየትህ/ሽ አመስግናለሁ!!!
እኔ ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም የአገሬን ባለስልጣኖች ከመንግስቱ ህ/ማርያምና አንዳንድ ሌሎች በጣም ይታወቁ ከነበሩ አምባገነኖች በስተቀር.......የአገሬን ጸሀይ ሳልጠግብ ቶሎ ስለተስደድኩኝ እድሉን አላገኝሁም!! ያ ግን ኢትዮጵያዊነቴንና ለአገሬ ያለኝን ፍቅር በፍጹም ዝቅ አያደርገውም!!!
ስለዘር ማጥፋት ያደረግክልኝ ገለጻም በጣም ግሩም ነው! እኔ ዘር ማጥፋት ሲባል የመስለኝ አማራ ወይም ጉራጌ, ትግሬ ብሎ አንዱን የጠላውን ዘር መደምስስ እንጂ የአንድን ቤተስብ ዘር ማንዘር ማጥፋት አልመስለኝም!
ጥያቄ ያለኝ ግብዝነቱን ያሳያል ያልከው እኔን ነው ወይስ የመለስን ግብዝነት? እስኪ ያገር ልጅ አብራራልኝ
ከአክብሮት ጋር
ሞኒካ
1. "Ignorance is the night of the mind, but a night without moon and star." -
-- Confucius
2. "Reading maketh a full man, conference a ready man, and writing an exact man." -
-- Sir Francis Bacon
አለም1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Jul 22, 2005 10:07 am
Location: ethiopia

Postby ታጠቁ » Fri Jan 06, 2006 1:20 am

እርግጥ የማንም ስውን ህይወት ማጥፋት ያሳዝናል:: ብበለጠ የሚያሳዝነው ግና ያላጠፉ ሲገደሉና ለገደለው የሚያዝኑ ሲኖሩ ነው:: እንድዚህ አይነቶቹ ሁሉ ከገዳዩ የበለጠ በስነ-ምግባር (ሞራል) ተጠያቂዎች ናቸው:: ስለሆነም የመንግስትን ስልጣን መከታ በማደረግ ንጹሃንን ዜጎች የገደሉ ሁሉ ለፍርድ ቀረበው ድርግታቸው ከተረጋገጠ በፍርዱ መሰረት የጸጣቸው ቅጣት እንዲፈፀምባቸው መደረግ አለበት:: ይህ አሁን በሰልጣን ላይ ለሚገኙት ሆነ ለወድፊቱም ስልጣን ለሚወስዱት ይመለከተአል::

"የወያኔ" መንግስት በደርግ ባለስልጣኖች ላይ የመፍረድ ግዴታ አለበት:: ወይኔ የስነ-ሓስኣብ ችግር እንጂ የኢትዮጲያውነት ችግር የለውም:: እንዲያውም በደርግ ባለስልጣኖች ላይ የተስጠው ፍርድ በቶሎ እንዲፈፀም መደርግ አለበት:: ህበረተሰባችን በፍትህና በመተሰሳሰብ የተመሰረተ እንዲሆን ወንጆሎኞችንን ከመሃላችን ፈልግን ለፍርድ ማቅረብ አለብን::
ታጠቁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Mon Nov 29, 2004 12:10 am
Location: united states

ኣመድ በዱቄት

Postby ጎርጎሪ » Fri Jan 06, 2006 7:52 am

ውድ ወገኖቼ ለተጠቃ በማዘን : በዳይም በበደሉ ተጸጽቶ የንጹሀን ደም አንደ ውሻ ደም ፈሶ አንዳይቀር የምሰጡት ሀሳብ ሁሉ መልካም ነው ነገር ግን አንዱ ሌላውን አየገደለ ያውም ከውሻው የባሰ ጅቡ አያጠቃ መቼ ይሆን በዚያች ሐገር በሰላም ወጥቶ የመግባት በሰላም ሐሳብን የመግለጽ :የመቃወም አድል የሚገኘው?ባልሳሳት ከዛሬ 10 ኣመት በፊት አሁን የዘነጋሁት ዘፋኝ "" ያለፈ አለፈ ይቅር ብቀላ አንደ........ሰው አንደ ማንዴላ . . ."" ያለውን አስታውሳለሁ ይህ የተጠናወተን በፍርድ ስም በሕግ ስም በቅጣት ስም ደም ማፍሰሱ ዛሬ ካልቆመ ነገም ይቀጥላል ነገር ግን አንድ ታሪክ ሰሪ ያስፈልገናል አኔ ልበደል አኔ ልጎዳ ብሎ ራሱን መስዋአት በማድረግ የደምን በደም ክፍያ ለማስቆም ታጥቆ የሚነሳ :: ኣስቲ በኛ ዘመን አንኳን አስቡት የስንቱ ምሁራን ደም በአደባባይ ፈሶ ቀረ የስንቱ ሕጻን ይስንቱ አዛውንት. . . በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከዚያኛው ወገን ባለመሆናቸው ስንቶቹ ታሰሩ: ተጋዙ:ተገደሉ . . . ቤት ይቁጠረው ሰው በላው አእረመኔው በፍርድ ስም ዛሬ ሞት ሲፈርድ ነገ አርሱንስ ምን አንደሚጠብቀው ያውቅ ይሆን ኣመድ በዱቄት ሲስቅ በነፋስ ልቡ ውልቅ ...አንዳለው አንዳይሆን አንጠንቀቅ
ልብ ያለው ልብ ይበል ቸር አንሰንብት
ጎርጎሪ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Dec 11, 2003 5:01 pm

Postby በማእረጉስ » Wed Jan 11, 2006 7:48 pm

ታጠቁ ማለት ወያኒ ማለት ይሆን? ፍርደ ገምድልና የአረመኒነት ባህሪ ታየብህኮ! የናዚ የጦር ወንጀለኞች በጊዚው ጉዳያቸው በፍርድ ታይቶ ነው የተወሰነው:: መች ነው የወደቀውን በለው በለው! የተነሳውን ደግሞ አይዞህ እያሉ በስሚት ብቻ መደጋገፍ የሚቀረው:: ሽለቃው በጊዚው ብዙ በደል መስራቱ ይታወቃል:: አሁን ፈራጅ ሆኖ የተቀመጠው ግን ማንዲቱ አለው ወይ? ነው ጥያቂው:: ራሱስ ከተመሳሳይ ወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ነው ወይ! አንዱ በሊላው በፈረደ ማግስት የባሰ ወንጀል ውስጥ ተነክሮ ቀኑ እስኪደርስ መቆየቱና መቀባበሉ የሚቀረው መች ነው?
በማእረጉስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun May 29, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

Postby ታጠቁ » Wed Jan 11, 2006 10:40 pm

ፍትሕ! ያለ ፍትሕ ሰላምና መተዛዘን የለም:: መንግስቱ ሃይለማርያምና ግብረ-አበሮቹ ንፁህ ኢትዮጲያውያንን ያለፍርድ እንደእንስሳ ሲያርዱአቸው ነበር:: እነዚህ ወንጀለኞች አሁንም እንዲገደሉ መደረግ አለበት:: ወያኔ የደርግ ባለስልጣናትን ያለፍርድ የመግደል መብትና ታሪካዊ ግዴታ አለበት::

የናዚ ወንጀሎኞች አንድ አመት ባልወሰደ መንገድ ጉዳያቸው ተጣርቶ ፍርዳቸውን አግኝተዋል:. ፋሽስቱ ሞሶሎኒ ደግሞ በጣልያን ህዝብ ያልፍርድ ታንቆ እንዲሞት ተደርጎአል:: የደርግ ባለስልጣናትና ጭፍሮቻቸውም የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው መደርግ አለበት::
ታጠቁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Mon Nov 29, 2004 12:10 am
Location: united states

አሁን ያስቸገረንን እንድንወያይበት ከማድረግ ፋንታ?

Postby ቃኘው » Wed Jan 11, 2006 11:06 pm

አሁን ያለብን ፋሽስት ወያኔ ሕወኃት ይባላል:: ለታጠቁ ስሙ ጠፍቶብህ እንደሆነ::

አሁን እውን ሕግና ፍትህ ታለ ወያኔስ በዚያን ሰዓት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የገደላቸውና አካለስ ጎዶሎ ያደረጋቸው ስንት ይመስሉኃል::

ለምን ታዛቢ ይታዘበኛል ብለህ አትጽፍም:: ነገም እነመለሰ እድል ታላቸው ተፈርዶባቸው ጽዋቸውን ይጎነጫሉ:: እድለኛም ታልሆኑ በሕብ እግር ተረጋግጦ ይሞታሉ:: አትፍረድ ይፈረድብኃል የሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስና የቅዱስ ቁርዓንን ትምህርት አትርሳው::

ያንተን አካሄድ ሁሉ ኢትዮጵያዊያን የሠፊው ሕዝብ ልጆች ያዩኃል ይታዘቡኃልም:: ይህን የመሰለን ጉዳዮች ሳታሰላስል ብትጽፍና ሌላውን ብትወነጅል አንተንስ ነገ ማን እንደሚወነጅልህ ታውቀዋለህን?

ለመለሰ ዜናዊ የተነገረ ስንኝ!!!

"አርግልኝ ያልኩህን አረግህልኝ ወይ::
ዕራሱን ወደታች ዕግሩን ወደላይ::

ለማንኛውም የኢትዮጵያ አምላክ ይቅር ይበልህ::

ታክብሮት ጋር

ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)


ታጠቁ wrote:ፍትሕ! ያለ ፍትሕ ሰላምና መተዛዘን የለም:: መንግስቱ ሃይለማርያምና ግብረ-አበሮቹ ንፁህ ኢትዮጲያውያንን ያለፍርድ እንደእንስሳ ሲያርዱአቸው ነበር:: እነዚህ ወንጀለኞች አሁንም እንዲገደሉ መደረግ አለበት:: ወያኔ የደርግ ባለስልጣናትን ያለፍርድ የመግደል መብትና ታሪካዊ ግዴታ አለበት::

የናዚ ወንጀሎኞች አንድ አመት ባልወሰደ መንገድ ጉዳያቸው ተጣርቶ ፍርዳቸውን አግኝተዋል:. ፋሽስቱ ሞሶሎኒ ደግሞ በጣልያን ህዝብ ያልፍርድ ታንቆ እንዲሞት ተደርጎአል:: የደርግ ባለስልጣናትና ጭፍሮቻቸውም የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው መደርግ አለበት::
tank you
ቃኘው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Thu Oct 23, 2003 11:35 pm
Location: Man

Postby ታጠቁ » Wed Jan 11, 2006 11:53 pm

መፅሐፍ ቅዱስ ይሁን ቅዱስ ቁራን ለገደሉ እዘኑ አላለም:: የኢትዮጲያ ህዝብ: አፄውና አቡኑ እንዲሁም ሚኒስተሮችና ሌሎችም ያለፍርድ በጅምላ በመንግስቱና ግብረ-አበሮቹ ተገደለዋል:: ይህ አይነቱ ወንጀል ላካሄዱት ሁሉ የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው መደርግ አለበት:: አለዝያ ህበረተሰቡ ለወድፊቱም ተመሳሳይ ችግር ይግጥመዋል:: ታሪክስ ምን ይለናል?

ወያኔ ለሰራቸው ወንጀሎችም ተመሳስይ ቅጣት እንዲፈጸምባቸው ይደረጋል:: ለወድፍትም የሚመጡ ባለስልጣናት ተመሳስይ ፍርድ እንደሚገጥማቸው ስለሚያውቁ የአስተዳደር በደል ይሁን የመግደል ወንጀል ከማካሄድ ይቆጠባሉ::

በነገራችን እኔ የወያኔ ደጋፊ ወይንም አባል አይደለሁም:: በመንግስቱ ሀይለማርያምና በግብረ አበሮቹ እንደ አንድ ሰው የደረሰብኝ ግፍ ወይንም በደል የለም:: በአጠቃልይ ሁኔታውን ሳየው የሚያሳፍር ክስተት ነው እነ መንግስቱ እንዲፈጠር ያደረጉት:: መንግስቱ እንደ አንድ ሰው እንዲጠየቅ መሆን የለበትም:: እነ መንግስቱ እዚህ ሁኔታ እንዲደርስ ያደረጉት እነ ነገደ ጎበዜ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን እነ ነገደ ጎበዜም ለፍርድ እንዲቀርቡ መደርግ አለበት!
ታጠቁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Mon Nov 29, 2004 12:10 am
Location: united states

Postby እንድሪያስ » Thu Jan 12, 2006 11:50 pm

አንተ የወያኔ ስውር የዘር ማጥፋት ዘመቻ ግቡን እንደሚመታ እርግጠኛ ትመስላለህ ::
ሁሌም "መደረግ አለበት"......."ይደረጋል" አይነት አነጋገር ይቀናሀል ::
"ወያኔ የደርግ ባለስልጣናትን ያለፍርድ የመግደል መብትና ታሪካዊ ግዴታ አለበት "....... ስትል : ትግሬዎች ኢትዮጵያዊያንን የመግደል መብት አላቸው .... ታሪካዊ ግዴታም አለባቸው ነው የምትለው ? መብታቸውንማ በትክክል እየተጠቀሙበት ነው :: ያውም ከሚገባው በላይ !!
ታሪካዊ ግዴታ የምትለው ደግሞ በደረግ ሰበብ የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻውን ነው ?


ታጠቁ wrote:ፍትሕ! ያለ ፍትሕ ሰላምና መተዛዘን የለም:: መንግስቱ ሃይለማርያምና ግብረ-አበሮቹ ንፁህ ኢትዮጲያውያንን ያለፍርድ እንደእንስሳ ሲያርዱአቸው ነበር:: እነዚህ ወንጀለኞች አሁንም እንዲገደሉ መደረግ አለበት:: ወያኔ የደርግ ባለስልጣናትን ያለፍርድ የመግደል መብትና ታሪካዊ ግዴታ አለበት::

የናዚ ወንጀሎኞች አንድ አመት ባልወሰደ መንገድ ጉዳያቸው ተጣርቶ ፍርዳቸውን አግኝተዋል:. ፋሽስቱ ሞሶሎኒ ደግሞ በጣልያን ህዝብ ያልፍርድ ታንቆ እንዲሞት ተደርጎአል:: የደርግ ባለስልጣናትና ጭፍሮቻቸውም የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው መደርግ አለበት::
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1826
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Postby ታጠቁ » Mon Jan 16, 2006 5:37 pm

እኔ እንደማየው የደርግ ባለስልጣናት በኢትዮጲያ ህዝብ ወንጀል ፈጽመዋል:: ብዙ ኢትዮጲያውያን በእነ መንግስቱ ተገድለዋል:: የገደለ መገደል አለበት:: ስለሆነም የወያኔ መንግስት አሁንም የደርግ ባለስልጣኖች እንዲገደሉ ማድረግ አለበት:: መንግስቱም ባለበት እንዲገደል መደረግ አለበት:: የወያኔ መንግስት የአገራችንን ስልጣን ስለተቆጣጠረ የደርግ አባላትንና ጭፍሮቻቸውን አሁንም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የተሰጠውን ፍርድ የመፈፀም ግዴታ በወያኔ ጫንቃ ተንጠልጥሏል::

የወያኔ መንግስት የወድፊት እጣ በነ መንግስቱና ግበረ-አበሮቹ መገደል ወይንም አለመገደል አይወስንም:: እንዲያውም የደርግ ባለስልጣኖች በወያኔዎች ቢገደሉ ህዝብ ድጋፉን ይሰጣል::
ታጠቁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Mon Nov 29, 2004 12:10 am
Location: united states

Postby ዘለቀ ጫፉ » Tue Jan 17, 2006 3:16 pm

ሰላም ልሁላችሁ

"መላኩ ተፈራ የሞት ታናሽ ውንድም
የዛሬን ማርልኝ ከእንግዲህ አልወልድም ::"

የተባለለት መላኩ ተፈራ ቢሞት ምኑ ያሳዝናል?? ለዛሬዎቹም ምሪዎቻችን ትልቅ ትምህርት ይሆናቸዋል እላልሁ::

ቸር ይግጠመን
ዘለቀ ጫፉ ነኝ
ዘለቀ ጫፉ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Thu Feb 03, 2005 3:07 pm
Location: netherlands

ሞት እኮ ሁለት ፊደል ነው::

Postby ARERU » Fri Jan 20, 2006 6:42 pm

[ሞት} እኮ ሁለት ፊደል ነው
[የህሊና ጸጸት
] ግን ስድስት ፊደል ነው::
ሰላም ወዳጆቸ ሻለቃ መላኩ ቢሞትም ባይሞትም ለሱ እሚተቅመውና እሚጎዳው ነገር የለም ምክኒያቱም ሞቶም በግዜር ቤት እሚያስቀጣው እያለም በህሊናው የሚቀጣ ሰው ነው ምክኒያቱም ምን አልባት በትክክል ቢጠየቅ በዛን ስአት ሲያደርገው የነበርውን ነገር እሱም እሚያውቀው አይመስለኝም ስል አንደኛ በቂ ትምህርት ያለው ሰው አይደለም ሁለተኛ የተፈጥሮ ጉረኝነት የተጠናወተው ሰው ነው ሶስተኛ ስለነገ እሚያውቀው ነገር የለለው ጭፍን ሰው ነው በርግጥ ሞት ፍርድ ለሰው ልጅ እሚሰጥ ነገር መስሎ አይታየኝም ምክኒያቱም ማንስ ነው እሱ ንጹህ ሆኖ በሌላው ላይ መፍረድ እሚችለው ግን ሻለቃ መላኩ በንጹህ ፈራጆች ፊት ቢቀርብ ምን አልባት አምስት ጊዜ ሞት ቢፈረድበት ያንሰዋል እላልሁ ከዛ በፊት ግን አሁንም ከመሞቱ በፊት ንስሀ ካልገባ እዛ የሚጠብቀው ፍርድ እሱነቱን ይነግረዋላና ባንከራከርበት መልካም ነው አሁን በሱ ላይ የሚፈርዱትም ሰውች ግም ለግም አብረህ አዝግም ነውና ቀናቸውን መጠበቅ እንጅ ባንድ እርምጃ አብረው እንዳሉ ሊያውቁ ይገባል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby በማእረጉስ » Wed Jan 25, 2006 12:34 am

ታጠቁ! ምን አዚም ነካህ? እስከ መቺ ነው እንዲህ አይነቱ አውሪነት የማይቆመው? የምታሳዝን ጨካኝ ሰው ነህ! ዛሪ ማንን ደግፈህ በስሚት እንዳልክና እንደፈረድክ ነገ ደግሞ ተራው ያንተና የዘመዶችህ እንዳይሆን አፍህን አስተካክለህ ዳቦ ብላበት!
በማእረጉስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun May 29, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

Postby ETYO » Wed Jan 25, 2006 5:49 pm

ይድረስ ልውድ ወገኖቸ ለዋርካ ተሳታፊወች እንደምን አላችሁ አዎ ምን ለማለት ፈልጌ ነው በሻለቃ መላኩ ተፈራ ላይ የተበየነውን የሞት ፍርድ በተመልከተነው ይህ ማለቴ በአሁኑ ሰአት ምን እንደሚደረግ ሁላችንም እንደምናውቅ ግልጽነው ማለቴ ይሀዴግ ምን እያደረገነው ከሻልቃ በምን ይለያል እስከዛሬስ ከምን ቆይቶ ዛሬ ሊፈርድ ተነሳሳ ከመውደቄ በፊት ገድየው ልለያይ ብሎነው እሱም ነገ ይህ እጣ እንደሚደርሰው ከሂሳብ አስቀምጦት ይቆይ መጀመሪያ አሁን ምን እንደሚሰራ ያጢን ከዛ የሰወችን ሀጢያት ይቁጠር ወይም ደግሞ እንደሚሞት ስላወቀ ብቻየን ሲኦል ከምወርድ ...ብሎ አስቦነው እንዲያው በከንቱ በሰው መፍረድ እንደኔ ሀሳብ ሻለቃ መሞት የለባቸውም ምክንያቱም ሁላችንም በዚህ አለም ሀጢያት እንደምንሰራ የታወቀነው እና ""አትፍረድ ይፈረድብሀል""ብላል አምላካችን መልካም ነገር ይግጠመን!!!!!!!!!!!!!!!!!
ETYO
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Thu Jul 28, 2005 10:08 am
Location: ethiopia

Postby ENGEDA1967 » Wed Jan 25, 2006 6:29 pm

አቤት አቤት አውርተህ ሞተሀል እስኪ መጀመርያ ልጠይቅህ አንድ ግለሰብ ይምጣና ወንድምህን ቢገድል እና ገዳይ አንድ ጊዜ ገልዋልና ምህረት ይደረግለት ቢባል ምን ትላነህ
ጉድ እኮነው ያን ያህል ህዝብ እንደ ድመት እራስ ራሱን እያለ ሲጥል ስልጣኑን ተመክቶ ነው ዛሬ ከርቸሌ ሲገባ እንዲያውም ሰላማዊ ሰልፍ ያስፈልግ ነበር የደስታ ሰልፍ
እንደኔ እንደኔ እሱን መግደል አያስፈልግም መጀመርያ ሚስቱን መግደል ከፊቱ ላይ /ከአክሊሉ ስዩም በጉልበት የቀማትን ሚስቱን/ በኋላ ጠቅላላ ልጆቹን በኋላ አባትና እናቱን በዱላ ቀጥቅጦ መግደል እሱን በማሳደጋቸው በመጨረሻ እሱን መጀመርያ አለሎ ብረት 5 ኪሎ ባፉ ትቀረቅራለህ አፉ አላስገባ ካለ 32 ጥርሶቹን በጉጤት ትመዛቸዋለህ ካዛ በኋላ በጉልነት ትገፋዋለህ አገጩ እስኪፈርስ ድረስ ከዛ እግሩን ትገለብጥና ወደላይ ታስራለህ ከዛማ ያው እሱ ሲያደርግ እንደነበረው 220V መለብለብ ደም እስከሚተፋ
ይህ ከመሆኑ በፊትማ መገደል የለበትም
ብትፈልጉ አረመኔ በሉኝ እሱ ይህን ሲያደርግ የነበረ የጁ ነው ይገባዋል ባይ ነኝ
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

Postby እንድሪያስ » Fri Jan 27, 2006 6:54 pm

አረመኔ ሳትሆን ደንቆሮ ነህ !!
የመላኩ ተፈራ ወላጆችና ልጆች የሀማዝ አጥፍቶ ጠፊ ሰራዊት አባላት መሰሉህ እንዴ ? የሆንክ ግማታም !!
እንደአንተ አይነቱ ፎከታም እረኛ መብት ሲያገኝ በአፉ ቀርቶ በቂጡ መጸዳዳቱ የማይቀር ነው :: በክት!!

ENGEDA1967 wrote:
እንደኔ እንደኔ እሱን መግደል አያስፈልግም መጀመርያ ሚስቱን መግደል ከፊቱ ላይ /ከአክሊሉ ስዩም በጉልበት የቀማትን ሚስቱን/ በኋላ ጠቅላላ ልጆቹን በኋላ አባትና እናቱን በዱላ ቀጥቅጦ መግደል እሱን በማሳደጋቸው............
.........ብትፈልጉ አረመኔ በሉኝ
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1826
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

PreviousNext

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest