ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime. Image

ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

Postby ENH » Thu Dec 15, 2005 6:45 pm

ሪፖርተር - 11-12-2005

ከ1969 እስከ 1976 ዓ.ም የጎንደር ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ እና የአዝኮ (አብዮታዊ ዘመቻ አስተባባሪ ኮሚቴ) ሰብሳቢ እና በአምባገነኑ የመንግሥቱ ኃይለማርያም መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበረው ሻለቃ መላኩ ተፈራ በዘር ማጥፋት ወንጀል በተመሠረተበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሞት እንዲቀጣ ፍ/ቤት ወሰነ።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

Postby በማእረጉስ » Tue Dec 20, 2005 11:09 pm

መቸም የሰው ልጅ ነገን አስተውሎ ማየት ቢችል እንዲት መልካም በሆነ ነበር እናም መላኩም በዘመኑ ያን ሁሉ ግፍ ሰርቶ በሰላም ወደ መቃብር የሚሂድ መስሎት ይሆናል:: ሆኖም ግን እንዲህ ሆኖ አረፈው:: የዛሪ ፈራጆችም ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ ሳያውቁ ግፋቸውን እየሰፈሩ ነው:: አንዱ በተራው በሊላው ሲፈርድ ዘመናችንም አለቀ:: ያልታደለ ሕዝብና ያልታደለች ሀገር!!
በማእረጉስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun May 29, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

Postby አቡዬ » Sun Jan 01, 2006 10:40 am

ነገ የመለስም ዕጣ ከዚህ አያልፍም በኢትዮጵያ ንፁህ ሕዝብ ደም ተጨማልቋልና
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Postby ጎራዴው » Mon Jan 02, 2006 8:17 am

በሻለቃ መላኩ ተፈራም ሆነ በመለስ ዜናዊ የጠፋ ነፍስ ዋጋቸው እኩል እስከሆነ ድረስ ሁለቱም ፍርዳቸው ተመጣጣኝ መሆን አለበት::
Wounds from the knife are healed, but not those from the tongue.

በብረት ስለት የቆሰል ወዲያው ይድናል :: በምላስ ለቆሰለ ግን መዳኛ የለውም
ጎራዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 227
Joined: Fri Dec 31, 2004 4:51 am
Location: united states

Postby Monica**** » Mon Jan 02, 2006 1:17 pm

ሻለቃ ተፈራ ምን አይነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ይሆን የስራው???? እኔ የሚገርመኝ ነገር እኮ " አመድ በዱቄት ይስቃል እንደሚባለው " አሁን መለስና መስሎቹ ስውን ሲፈርዱ አያፍሩም????????
ከነሱ ወዲህ ኢትዮጵያን በዘር የከፋፈለ ፋሽሽት አልተፈጠረም ወደፊትም አይፈጠርም!!! ማፈሪያ ነገሮች
ደሞ የሞት ቅጣት???????
Vengeance is mine ብሏል አምላካችን!!! አሁን ስውዬውን ቢገድሉ ጥፋቱን አይክስም...........ግን ዳሩ ሻለቃ ተፈራ ይሄኔ አማራ ይሆናል........የአማራ ጥላቻችውን ለመወጣት ያደረጉት ተንኮል ነው!!! :evil: :evil: :evil:

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለወያኔ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ይሁኔ » Mon Jan 02, 2006 6:35 pm

ሰላም ሞኒካ እስካሁን ሰላምታ ተለዋውጠንም አናውቅ ግን ብዙ የምትያቸው ነገርችን አነባለሁ ጽሁፎችሽን እወዳቸዋለሁ እከታተላለሁም
አሁን ግን የተሳሳትሽ ይመስለኛል ለምን? ብትይኝ
1ኛ= መላኩን ያውቅሽው አይመስለኝም የብዙ ወጣቶችን ህይዎት ያለምንም ጥፋት የለምንም ፍርድ ባደባባይ ይረሽን የነበረ አረመኔ ነው ከሁሉ ከሁሉ የማይደሳኝ ወጣቶችን እየገደሉ ከተወለዱበት ቦታ ከመኖርያ ቤታቸው አጠገብ እንዲጣሉ ማድረጉ ሲሆን እናት ይህን ልጅዋን አይታ ብታለቅስ ትታሰር ነበር
2ኛው ደግሞ አንድ ሰው ላጠፋው ወንጀል ጊዜውን ጠብቆ ፍርድ ካላገኘ ያሁኖችስ ማንን ይፍሩ እህትየ እንደኔ እንደኔ የሞት ፍርድ አይገባውም ነበር እንደውሻ ምግብ እየወረወሩ እስኪሞት ድረስ ጨለማ ውስጥ መቅበር ነበር
ሰላም ሁኝ እህትየ
ቆንጆ ቆንጆ ሀሳቦችሽ አይለዩን
ይሁኔ
ይሁኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Sat Sep 17, 2005 5:45 pm
Location: india

Postby Monica**** » Mon Jan 02, 2006 7:20 pm

ይሁኔ
ስላም ያገር ልጅ
በመጀመሪያ ስለጨዋ አስተያየትሽ/ህ ሳላመስግን አላልፍም!!
በትክክል ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም ስማችውን ለመጀመሪያ ጊዜ ስስማው ነው!!!!
ይሄን ያህል ካጠፉና ስው ከገደሉ በርግጥ ፍርድ ይገባችዋል ግን ሞት?
በዚህ አይነት እኮ በእስር ላይ ያሉትም የቅንጅትን መሪዎች ይሄ ስውዬ ሊጨፈጭፍ ነው! ካለፈው መማር ሲገባን እንዴት ወደህዋላ እንሄዳለን?
በርግጥ ስውየው በዘር ከፋፍሎ ነው ስው የገደለው ወይስ በፖለቲካ አመለካከት?
እንደዛ ማለት ጥፋቱን ቀላል ወይም ከባድ ያደርገዋል ለማለት ሳይሆን የዘር ነገር በወያኔ ጊዜ ነው በሀይል የከፋው እንጂ ከዛ በፊት ብዙ መጥፎ ነው ብዬ አላስብም! ወይም ህዝቡ ደርግን ፈርቶ ዝም ብሎ እንደሆን አላውቅም!
ወያኔ ግን ይሄንን ስውዬ በዘር በመከፋፈል ብሎ ሲወነጅል በጣም ገርሞኝ ነው!
በዛ ላይ an eye for an eye የሚሉት ሁዋላ ቀር አስተሳስብ የት ሊያደርስን ነው??? ያጠፋን በቁም ስቅል ማሳየቱ ሳይሻል ይቀራል ከመግደል? እሱን ለአምላካችን መተው ይሻላል ብዬ ነው!!!
አክባሪሽ/ህ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ግሩም 4 » Mon Jan 02, 2006 10:11 pm

መላኩ ተፈራ የእግዘር ታናሽ ወንድም:
የዛረን ማርልኝ ሁለተኝ አልወልድም::

ተብሎ የተገጤመለት ቸካኝ ሰው ነበረ:: ይህ ቅታቱ ያንሰዋል ወይም ይበዛበታልአይደልም ጥያቀው:: እንደት ከኒልሰን ማንደላ ትምህእርት መውሰድ አንችልም!! ኢትዮጵያችን ችግር ውስጥ ነው ያለችው:: የወደፊቱን ማስተካከል ነው ያለብን:: ስንወቃቀስ እድመአችንን ልንቸርስ ነው:: ሰላም ለሁላችሁም!!!
ግሩም 4
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Mon Jan 02, 2006 8:50 pm
Location: europe

Postby አለም1 » Mon Jan 02, 2006 10:52 pm

"የሞት በቃ ፍርድ"ን በመቃወሙ ረገድ እጅግ አድርገን እንደግፍዎታለን::አንደኛ "አትግደል::"የሚለው የፈጣሪያችን ት'ዕዛዝ በመሆኑ::ሁለተኛ እኒህ የአፍሪካ ጀብደኞች በየምክንያቱ እየተነሱ ክቡሩንና መተኪያ የሌለውን የሰውን ህይወት እንዳይቀጥፉ ልጕም ይሆንባቸዋል ብለን ስለምናምን::
እዚህ የተጠቀሱትን ግለሰብ አስመልክቶ ምንም አለማወቅዎ ትንሽ ለማመን ቢያዳግተንም በአይናችን ባናይም በይሁኔ ከተገለጸው በከፋ አረመኔያዊ ተግባራቸው እጅግ የታወቁ ናቸው:: ከገደሏቸው ይልቅ በሕይወት ያሉና የርሳቸውን ስም ሲሰሙ የሚያንቀጠቅጣቸውን ማየቱ ይሰቀጥጣል::ያ ሳያበቃ የመለስ መቀጠሉ....!!!!
የዘር ማጥፋት የሚለው ጠባብ ትርጉም ያለው ይመስለናል::"ጄኖሳይድ" የሚለውን የውጭውን ቃል የሚተካ አይመስለንም::ይህንኑ ሁኔታ መለሳውያን እየተጠቀሙበት ናቸው::በጊዜው ነበርን::የአንድ ቤተ-ሰብ አባላት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በመግባት ተራኩተዋል!!!!
አንዲት ገጠመኝ ብቻ በማንሳት ይህንኑ ለማስረዳት እንሞክር::
ጎረቤታችን አንድ ቤተ-ሰብ ነበር::በዚህ ቤተሰብ ውስጥ አባት:ሁለት ወንድ ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ነበሩ::አባት "ተስፋለ-ዘውድ" ተብሎ የሚጠራው ኢዲዩ አባል: አንዱ ልጅ የመኢሶን አባል:ሌላው ልጅ የኢሕአፓ አባል ሆኑ::መኢሶኑ አባቱንና ወንድሙን "በጸረ-አብዮተኝነት" አሳሰረ::መኢሶን ሲፈረጥጥ እርሱም አባቱንና ወንድሙን ከርቸሌ ተቀላቀለ::እነርሱ ሲፈቱ እርሱ እዚያው...ከዚያ በኆላ ያለውን አናውቅም::ደም በጁ የለም::እንዲህ እንዲህ እያለ በቤተሰብ መካከል እንኩዋን ደም የፈሰሰበት ስለመኖሩ እርግጠኞች ነን::ዜር ማጥፋት የሚለው ሊነሳ ይችላልን?
መለሳውያን የጀኖሳይድን ትርጉም ለአላማቸው እያዋሉት ነው::የትግራይን ሕዝብ ከጎናቸው ለማሰለፍና ማለቂያ ወደ ሌለው የርስበርስ ጦርነት ለመግባት የሚያደርጉት ይመስለናል::ያ ጦርነት ደግሞ የትግራይ ትግሪንን መንግስት ለመመስረት ከነበራቸው የጠኆቱ አላማቸው የመነጨ ይመስለናል::መለሳውያንን ለማስወገድ ከተፈለገ እያንዳንዱ ቤቱን ማጽዳት ያሻዋል::በሰላማዊው ትግል::ክሎኒንግን መለሳውያን እየተጠቀሙበት ነውና ክሎኖቹን ለይቶ በማውጣት ወደ ሕዝቡ እንዲመለሱ ማድረግ ነው::ሆድ አደሮች ናቸው ትናንትም ሆነ ዛሬ ይበልጥ ያጠቁን::
"የቅንጅትን አባላትም በሞት ይቀጣል::" የሚል ፍራቻ ያሳደረብዎ የመላኩ መቀጣት መሆኑ ሳይገርመን አልቀረም::እንዲያውም ግብዝነቱን ነው ቁልጭ አድርጎ ያሳየው::ሕዝቡ የተደረግውንና የሚደረገውን ሁሉ በአርሞሞ ያየዋል እኮ!!!!"በማንም ላይ ለመፍረድ የሞራል ብቃቱ እንኮአን የለህም!እንኮአን የሕግ ድጋፍና መሰረት ይቅርና! አንተ የምት'ሰራው እርሱ ከፈጸመው በምን ይለያል?" እያለ እየጠየቀ ነው::መላኩን 'በሞት ቅጣት" መቅጣቱ ልዩ ምልክት ሊሆነን አይችልም::ምልክቱ የታየው ከዚያ በፊት ነው:_ሀገር ሲገድል::እነመላኩንም ያሳበደውና ለዚህ ያበቃውስ ማን ሆነና ነው? ካድሬዎቻቸው በመሀል ሀገር አልነበሩምን? ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል....
Monica**** wrote:ይሁኔ
ስላም ያገር ልጅ
በመጀመሪያ ስለጨዋ አስተያየትሽ/ህ ሳላመስግን አላልፍም!!
በትክክል ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም ስማችውን ለመጀመሪያ ጊዜ ስስማው ነው!!!!
ይሄን ያህል ካጠፉና ስው ከገደሉ በርግጥ ፍርድ ይገባችዋል ግን ሞት?
በዚህ አይነት እኮ በእስር ላይ ያሉትም የቅንጅትን መሪዎች ይሄ ስውዬ ሊጨፈጭፍ ነው! ካለፈው መማር ሲገባን እንዴት ወደህዋላ እንሄዳለን?
በርግጥ ስውየው በዘር ከፋፍሎ ነው ስው የገደለው ወይስ በፖለቲካ አመለካከት?
እንደዛ ማለት ጥፋቱን ቀላል ወይም ከባድ ያደርገዋል ለማለት ሳይሆን የዘር ነገር በወያኔ ጊዜ ነው በሀይል የከፋው እንጂ ከዛ በፊት ብዙ መጥፎ ነው ብዬ አላስብም! ወይም ህዝቡ ደርግን ፈርቶ ዝም ብሎ እንደሆን አላውቅም!
ወያኔ ግን ይሄንን ስውዬ በዘር በመከፋፈል ብሎ ሲወነጅል በጣም ገርሞኝ ነው!
በዛ ላይ an eye for an eye የሚሉት ሁዋላ ቀር አስተሳስብ የት ሊያደርስን ነው??? ያጠፋን በቁም ስቅል ማሳየቱ ሳይሻል ይቀራል ከመግደል? እሱን ለአምላካችን መተው ይሻላል ብዬ ነው!!!
አክባሪሽ/ህ
ሞኒካ
1. "Ignorance is the night of the mind, but a night without moon and star." -
-- Confucius
2. "Reading maketh a full man, conference a ready man, and writing an exact man." -
-- Sir Francis Bacon
አለም1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 73
Joined: Fri Jul 22, 2005 10:07 am
Location: ethiopia

Postby ይሁኔ » Tue Jan 03, 2006 7:45 pm

ሰላም ሞኒካ ደህና ነሽ ወይ ..
እኔና አንች የተግባባን ይመስለአል እኔም ይግደሉት አላልኩም ግን ጥያቄየ ሌላ ነው አንች ስታስቢው ስንት ህዝብ ያሰቃየ ግለሰብ ላጠፋው ጥፋት ተመጣጣኝ ቅጣት ካላገኘ አሁን ህዝብ የሚጨፈጭፉት እንዴት ፍርድ ማቅረብ ይቻላል ? ነው .. እህትየ እኔ የጎንደር ልጅ ነኝ እስካሁን የላንድሮቨር ድምጽ ስሰማ ትዝ የሚለኝ የመላኩ አሽከሮች ወጣት ሊለቅሙ በለሊት ሰፈራችን ሲገቡ ነው ;;ወይም ሊረሽኑ ሞኒካየ ቀን በቀን ወንዱ ወጣት ሴቱ [ነጻ እርንጃ] የሚባል ነገር መጥቶ ያለምንም ምክንያት እየታፈኑ ይወሰዱ ነበር ከ3 ቀን በኋላ ተረሽነው ይጣላሉ እቤታቸው በራፍ
ሞኒካየ ያኔ ልጅ ነበርኩ እማይረሳኝ ነገር ወደ መሰረት ት/ቤት ስንሄድ ነው መንገድ ዳር ወድቃ ያየኋት ልጅ አሁን ሳስበው 18 ዐመት ቢሆናት ነው ፊትዋን አላየሁም ረጂም ጸጉርዋ ተበትኖ በግምባርዋ ተደፍታ አስፓልቱ ላይ ትንሽ ደም ይታያል የሰውነትያ ማነስ ስታሳዝን አሁን ምን አደረገች ? ያች ህጻን ምን አደረገች?
ሞኒካ ይሄውልሽ እንግዲህ ትራውማ ሆናኝ ሴት የሚደባደብ ጎረምሳ ካየሁ ያው እኔን አልፎ ነው ባውቃትም ባላውቃትም
ይቅርታ ሞኒ ብዙ አወራሁ ያወራሁት ሁሉ ግን እውነት ነው ሰላም ሁኝ እህቴ
ይሁኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Sat Sep 17, 2005 5:45 pm
Location: india

Postby Monica**** » Tue Jan 03, 2006 9:27 pm

አለም 1
በቅድሚያ ለአስተያየትህ/ሽ አመስግናለሁ!!!
እኔ ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም የአገሬን ባለስልጣኖች ከመንግስቱ ህ/ማርያምና አንዳንድ ሌሎች በጣም ይታወቁ ከነበሩ አምባገነኖች በስተቀር.......የአገሬን ጸሀይ ሳልጠግብ ቶሎ ስለተስደድኩኝ እድሉን አላገኝሁም!! ያ ግን ኢትዮጵያዊነቴንና ለአገሬ ያለኝን ፍቅር በፍጹም ዝቅ አያደርገውም!!!
ስለዘር ማጥፋት ያደረግክልኝ ገለጻም በጣም ግሩም ነው! እኔ ዘር ማጥፋት ሲባል የመስለኝ አማራ ወይም ጉራጌ, ትግሬ ብሎ አንዱን የጠላውን ዘር መደምስስ እንጂ የአንድን ቤተስብ ዘር ማንዘር ማጥፋት አልመስለኝም!
ጥያቄ ያለኝ ግብዝነቱን ያሳያል ያልከው እኔን ነው ወይስ የመለስን ግብዝነት? እስኪ ያገር ልጅ አብራራልኝ
ከአክብሮት ጋር
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Tue Jan 03, 2006 9:35 pm

ይሁኔ
ስላም ያገር ልጅ ደህና ውለህልኛል?
ይሄ መላኩ ማለት ጭራቅ ነገር ነው! ከመንግስቱ ህ/ማርያም የባስ ነበር ማለት እኮ ነው! እኔ አዲሳበባ ውስጥ በኢሀፓ ጊዜ ብዙ ወጣት እየገደለ በጣም ያስችገረ ስው እንደነበር ሲወራ እስማለሁ ስሙን ባላስታውስውም!!
በግጥ የብዙ ስው ህይወት ያጠፋ ስው ለፍርድ መቅረቡ ትክክል ነው! የሞት ቅጣት ግን (Capital punishment) መቅረት ያለበት ዘግናኝ አስተሳስብ ነው ባይ ነኝ!!
አንተ ደሞ first-hand experience አለህ በነሱ እጅ የተገደለች ልጅ መንገድ ላይ ተጥላ! ምን ያህል እንደሚዘገንንና ከጭንቅላትህ ውስጥ እድሜ ልክ ተቀርጾ እንደሚቀር መገመት አያቅትም!!
ለማንኛውም ትሁኔ ያገር ልጅ ባለህበት መልካም ምሽት ይሁንልህ
ለኢትዮጲያችንም ስላምና ፍቅሩን ያውርድላት
አክባሪህ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby አተረማመሰው » Tue Jan 03, 2006 11:10 pm

ሻለቃ መላኩ ገፈኛ እንደነበር አንድና ሁለት የለውም:: አከራካሪው ነገር እሱ አይደለም:: የጎንደር እናቶች:-

ሻለቃ መላኩ የግዜር ታናሽ ወንድም
የዛሬን ይማሩኝ ከንግዲም አልወልድም!!!

ብለው ሲያዝኑ ነገሩ ሁሉ አብቅቶል::

የኔ ነጥብ የትግሬ ፍርድቤት ሻለቃ መላኩ ላይ ወሳኔ ለማሰተላለፍ የሞራል በቃት የለውም ነው::
££££
አተረማመሰው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Sat Apr 16, 2005 12:03 pm
Location: united kingdom

Postby ታጠቁ » Wed Jan 04, 2006 2:02 am

እንደዚህ ህዝብን ያስቃየን አረመኔን 7 ትውልዱን ፈልጎ ማቃጠል እንጂ እንዴት ወያነኤ ይህንን አደረገ ብሎ መተቸቱ የአስመሳዮችና የካሀዲዎች ልፍለፋ እንጂ ከአንድ ኢትዮጲያዊ የሚጠበቅ አይደለም:: አሁንም ባለንበት እስር የሚገኙትን የደርግ ባልስልጣኖች እንዲገደሉ መጠይቅ ይኖርብናል:: መንግስቱ ሀይለማርያምም ወደ ኢትዮጲያ ተመልሶ ይተሰጠውን የሞት ፍርድ እንዲቀበል ማድረግ ይኖርብናል::
ታጠቁ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Mon Nov 29, 2004 12:10 am
Location: united states

Postby aneresam » Wed Jan 04, 2006 2:16 am

አረመኔ አረመኔ ላይ ሲፈርድ::
aneresam
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Mar 05, 2004 2:47 am

Next

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest