Mo's coffee house ሁሉንም የዋርካ ታዳሚዎች ትልቅ ትንሽ ሳይል በደስታ ያስተናግዳል!
ይሄ ቤት በተለይ ይሄ ቤት ጥቅሙ ስዎች who wants to get away from hustle and bustle of their daily lives!!!
ኮፊ ሀውሳችን ቀልዶችን ምክርንና, ራስልምድ ላይ የደረሱ አስቂኝና አሳዛኝ ነገሮች, መወያየት የምንችልበት ባህላዊ ቤት ነውና......ladys and gents. please feel free!!!
Mo's coffee house is helping you to unwind and slacken since you can talk about anything and everything under the sun!!!!(as long as it is refrain from obscene, and racist remarks)
Mo's coffee house ምንም እንክዋን ለቡናችንና ለደስታችሁ ገንዘብ ባናስከፍልም...............አንድ ነገር የምትጠየቁት እዚህ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትገቡ አንድ የሚያስቅ ነገር የደረስባችሁን ወይም የምታውቁት ስው ላይ የደረስውን እንድታጫውቱን ስጠይቅ በደስታ ነው::
እስኪ እኔ የማውቀውን አንድ ልበል
***********
አዲሳበባ ለእረፍት ሄጄ....... አንድ ቅዳሜ ከስአት በህዋላ ለመውጣት ሽር ብትን ስል መልክት ይዤ የመጣሁለት ስው አጉል ስአት ደውሎ እቃውን ልወስድ ነበር ይለኛል..... እኔም እቤት ጥዬልህ እሄዳለሁ ስለው እዛው ቤታችሁ አካባቢ ነኝ ይለኝና ይዘሽው የምትሄጂው መልክትም ስላለኝ የሆነ ኬክ ቤት ይዘሽው ነይ ይለኛል ( literally I live 3 minutes walk from the place and I think it was a new hot spot)
እኔም በአለም ላይ እንደኔ ዘናጭ ያለ የለም የምል እመስላለሁ.....ትንሽ የዘመድ ልጅ ቢጤ አስከትዬ መሬት ለምን ነካኝ ብዬ ቀና ዘርጋ ስል ኬክ ቤቱ ከፊትለፊት ይታየኛል እና ቅዳሜ ስለሆነ መኪናውና ስው ሞልቶታል......እኔም የአገሩ ሁሉ አይንና አቴንሽን እኔ ላይ ነው ብዬ አስቤ በኩራት ስራመድ (የዛ ጊዜ መንገድ እየተስራ ነበር.....) ያው የአገራችን መንገድ ጉድጉዋድ ምናምን አያጣውም አይደል....አንድ ከርካሳ ታክሲ በአጠገቤ ሲያልፍ ትዝ ይለኛል ከዛ በህዋላ የሆነው እንደው ጭንቅላቴን እንደቴፕ slow motion አድርጌ ሳስበው.......ያ የተረገመ ታክሲ ነጂ ጎማው እዛ ditch ውስጥ ገብቶ ለካ የአለም የጭቃ ውሀ ከጸጉር እስከ እግሬ ድረስ አልብሶኛል!!አቤትትትትትትትት ቅሌትትትትትትትትት :evil: :evil: :evil: :evil: ምናለ መሬቱ ተስንጥቆ ቢውጠኝ አምላክ እንደዛ ከሚያዋርደኝ ነበር ያልኩት! እርግጠኛ ነኝ መቼም ስው ጥሩ ነገር ሲሆን አያይም ለመጥፎ ግን ማን ብሎን............. በልቤ የመስለኝ የመንገዱ ትራፊክ አንድ ፕሬዘዳንት እንክዋን ሲመጣ እንደዛ መኪናና ህዝብ አይበዛም( 3 መኪናም ቢሆን እንደዛ አይነት ጊዜ ላይ 30 ሆኖ ነው የሚታየው)!!! ስዉ አንዳንዱ አፍጥጦ ሲያየኝ ግማሹም ታክሲ ነጂውን ሲሳደብ ግማሹም ደህና ነሽ ሲል....... (እንዳላለቅስ አፍሬ ወደቤት ሩጫዬን) ከዛ በህዋላ እዚህ እስክመለስ ድረስ በእግሬ ከቤቴ በራፍ ፍንክች አልልም ነበር!!!
ይባስ ብሎ ያቀሽም ልጅ ሻወር እንክዋን መውስጃ ጊዜ ሳላገኝ እኔ መሆኔን አውቆ ከ2 ቆንጆ ጉዋደኞቹ ጋር እቤት ተከትሎኝ ከች :evil: :evil: :evil: በመጀመሪያ ደረጃ እቤትና ስለው እምቢ ያለው ልጅ አሁን በጭቃ ቦክቼ ሊስቅ ነው የመጣው? :evil: :evil: :evil: :evil: ዳሩ በአመቱ ስመለስ ያስታወስኝም ስው ያለ አይመስለኝም እዛ አካባቢ ካሉት ሊስትሮዎች በቀር.....ከድሮ ጀምሮ ስለማውቃችው :oops: :oops: :oops: መንገዱም ቆንጆ ሆኖ ተስርቷል!
በሉ ቡና ድገሙ እባካችሁ