by ወሮበላው » Wed Nov 15, 2006 12:26 pm
ሰላም ማንቼዎች ብድናቺን መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሎዋል
ከጨዋታዎች ሁሉ ፈርቼው የነበረው የበቀደሙ የ ብላክበርን
ጨዋታ ነበር ..ይህ ቡድን ባለፈው አመት 4 ጎል ያገባብን መሆኑን አለዘነጋውትም አምና ዘንድሮ አይደለም እና አልፈናቸዋል ...
ከፊታቺን የሼፍልድ ዩናይትድ እና የቼልሲ ጨዋታ ይጠብቀናል
በሁሉም ዘንድ የሚጠበቀው የቸልሲ ጨዋታ ነው
በአሁኑ ሰአት ሁለቱም ክለቦች ጥሩ አቁዋም ላይ ናቸው ያሉት
ማንቼስተር በሜዳው ላይ እንደመጫወቱና መሪነቱንም አሳልፎ ላለመስጠት የሚያደርገው ተጋድሎ ቀላል ይሆናል ብዬ አልገምትም ...ማንቼስተር እንደ እኔ አመለካከት በተለይ በተከላካይ ቦታ ላይ ትልቅ የአካል ብቃት ፈተና ይሚጠብቀው ይመሰለኛል ..ድሮግባም ሆነ ሰለሞን ካሉ እንደ ፈርዲናን ያለ ጠንካራ ተከላካይ ያስፈልጋቸዋል
ለምሳሌ ቀኝ ተከላካይ ላይ የምትጫወተው ፈረንሳዊው ፓትሪክ ኤቭራ ቦታውን ለ አርጀንቲናዊው ጋብሪኤል ሄንዝ ቢለቅ መልካም ይመስለኛል ሌላው ቪዲክ እና ኔቭልም አሪፍ ናቸው..........ይቀጥላል