ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ShyBoy » Sun Dec 28, 2008 2:30 am

አንች ሴትዮ ባገር አለሽ? ደህንነትሽን ስላወቅሁ ደስ ብሎኛል ግን በጣም አኩርፌያለሁ አላናግርሽም................ የት እንደጠፋሽ: ለንም እንደጠፋሽ ሪፖርት ካላቀረብሽ እንዲሁም ይቅርታ ካልጠየቅሽ በቃ መነጋገር የለም :cry: :cry: :cry:
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፍርሀት » Mon Dec 29, 2008 11:30 pm

ናፍቆት
ገዐ 15 ላይ እንዳየሁት ዖም እንደምዖሚ ነው::ግን የሆነ ቦታ ላይ`` ከሞት ቀጥሎ ህይወት አለ ምናምን የማይጥም ወሬ እንዳትሉኝ.........``ብለሽ ነበር::የምትዖሚው ዳይት ለማረግ ይሆን?ጥያቄ ነዉ::
God is allways with us! I knowe!!!!!!!!
ፍርሀት
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Mon Nov 03, 2008 9:58 pm

Postby ናፍቆት » Tue Feb 17, 2009 7:26 am

ፍርሀት - ወይ ጉድ - አረ እዚሁ አለም ላይ እያለሁ ጣጣዬን እንዳያበዛው ብዬ ነው:: ህ ... አንተ ታሾፋለህ - እዚህ የተሰጠኝን ህይወት በቅጡ የተወጣሁት አይመስለኝም አንተ ለሌላ ህይወት ትደራደርልኛለህ::

ትዝ ያለኝን ልበልህማ .... ያንድ ነገር 'መኖር' (existence እንደሚሉት) ... ስለሱ በፈላስፋዎች ሲወራ ነው የምልህ .... አንድ ነገር 'በራሱ' የለም:: አንተ ያ ነገር 'አለ' ብለህ ስታረጋግጥ ነው ነገሩ አለ የሚባለው ..... ለምሳሌ 'This computer' ስትል በቃ ኮምፕዩተሩ አለ ማለት ነው 'This' ብለህ ስትጀምር የኮምፕዩተሩን መኖር አረጋግጠሀል ማለት ነው:: ስለዚህ 'ላንተ' ኮምፕዩተሩ አለ (it exists) ማለት ነው .... እንጂ ኮምፕዩተሩ በራሱ 'የለም' .... ነው የሚሉት ሰዎቹ ..... በቃ የለም:: ...... እና እሱ ላይ ስናወራ አንዱ ቆንጆ ቺክ ያለችውን ልጅ ሌላኛው በምሳሌ ሲያስረዳው ... ለምሳሌ እንትናን (ልጅትዋን) ሌላ ወንድ ቢስማት ወይም ምናምን ነገር .... እና አንተ ምንም ባታውቅ ... ያ ሳሚው ሰውዬ 'ላንተ' የለም:: ..... በቃ አልተፈጠረም:: እና ምንህም አይደለም:: አንተ መኖሩን አውቀህ እስካላረጋገጥክ ድረስ ሰውየው በቃ የለም:: ... ምናምን ብሎ ዘበራረቀና ..... በመጨረሻው ምሳሌ ሰጪው ልጅ ከባለገርልፍሬንዱ ጋር ተጣልተው ዲስከሽኑ እንዳለቀ ነው የማወራህ.... አይ ወንዶች .... ታስቁኛላችሁ እኮ ግን ... ከምር

እኔ የምለው ግን ያፍሪካ መሪዎችን ስብሰባ ተከታተላችሁ ወይስ እንዲያው ዘጥ ዘጥ ነው ብላችሁ ተዋችሁት? ያ ከሶስት መቶ በላይ አሽከር አስከትሎ የመጣው ጋዳፊ እንደተመረጠ መቼም ሰምተሀል .... ጋዜጣ ላይ 'ያፍሪካ መሪዎችን አልወዳቸውም' እንዳለስ አልሰማህም? አይጥምም? እኔ ከሰውየው ይሄ ከላይ ደረብ የሚያደርገውን 'brown' ጎጃም-አዘነውን እወድለታለሁ:: በተረፈ ያዲሳባ ቆነጃጅትን መከሩ ተብሎ የተጻፈውን እስቲ አንብቤ አጫውትሀለሁ:: ....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Tue Feb 17, 2009 3:53 pm

ShyBoy - ውይ ስሞት .... እንዳታኮርፈኝ .... እስቲ አስበው ተራርቆ ኩርፊያ ምን ይመቻል በናትህ .... ከምር ..... አጠገቤ ብትሆን እንኳን መላ መላ አይጠፋም ነበር ለማባበል::

ኩርፊያ ግን እንዴት ነው ? በልጅነቴ አኩርፌ ብታምንም ባታምንም 2 ወይም 3 ቀን እህል በቅጡ አልበላም ነበር:: አሁን ግን እንደዛ አይደለም .... ወይ ብልጥ ሆኛለሁ ወይ ሞኝ ሆኛለሁ ... ብቻ .... ብዙም አላኮርፍ ....

ረስቼው
ፍርሀት - በናትህ ባልጠፋ ስም ይሄ ሲጽፉት ሁሉ ፍርሀት ፍርሀት የሚል ስም ለምንድነው ግን የያዝከው? ከምር?
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby እህምም » Tue Feb 17, 2009 4:05 pm

ናፍቆት wrote:
እኔ ከሰውየው ይሄ ከላይ ደረብ የሚያደርገውን 'brown' ጎጃም-አዘነውን እወድለታለሁ::


:lol:
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ሀሪከን2 » Tue Feb 17, 2009 4:24 pm

ናፍቆት
ShyBoy - ውይ ስሞት .... እንዳታኮርፈኝ .... እስቲ አስበው ተራርቆ ኩርፊያ ምን ይመቻል በናትህ .... ከምር ..... አጠገቤ ብትሆን እንኳን መላ መላ አይጠፋም ነበር ለማባበል

ቅቅቅ የምር ግን አጠገብሽ ቢኖር እንዴት አድርገሽ ነበር ልታባብይው ያሰብሽው :lol: :lol:
እኔ ሻይቦይን ብሆን እንዳኮረፍኩሽ ኢትዮጵያ እመጣ ነበር :lol: :lol:

እስኪ ናፍቆታችን በነካ እጅሽ ጋዳፊ ለኢትዮጵያ ቆነጃጅት የመከረውን ንገሪን
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ማርስ » Thu Feb 19, 2009 11:07 pm

ታድያስ ናፍቆትየ እንደምነሽ? ወይኔ እስካሁን እንዲህ ከረሜላ እንደሆንሽ ነሽ?! ወድድድድድድድ ነው የማደርግሽ የምትፅፊአቸው በሙሉ ይመቹኛል:: ለምን እንደሆነ አላውቅም በጣምምምም ያስቀኛል:: የሚገርመኝ ነገር አለ ካንቺ:::

እስኪ ለማንኛውም አትጥፊ
ቻው ናፍቆትየ
የዘወትር አክባሪሽ ማርስ!!
I dreamed of some one like you
you see too marvelous for it to be true.
-
-
Image
ማርስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Sat Jan 03, 2004 12:54 am

Postby ጅብገደል » Fri Feb 20, 2009 2:16 am

ናፍቆት ልጆችሽ አደጉ ወይ ?
ወንዱስ ሚኒስትሪ መቸ ነው የሚወስደው አዲስ አበባ ሁለቴም ላፕቶብ ይዥልሽ መጥቼ አጣሁሽ ድሮ ድሮ ነው ያወራሁሽ ስለ ስብሀት ግ/እ የጠየቁሽ ነኝ ትዝ ይበልሽ
ጅብገደል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1144
Joined: Wed Jan 14, 2009 3:23 am
Location: BULGA ENBUR GEBYAW GA

Postby ናፍቆት » Thu Mar 19, 2009 7:21 am

እዚህ አንድ ስለስፖርት እንነጋገር የሚል ኢቲቪ 2 ላይ የሚቀርብ የግማሽ ሰአይ ሾው አለ:: እና አቅራቢዎቹ ደስ የሚል አቀራረብ ሰለሆነ ያላቸው በተቻለኝ መጠን አያለሁ:: ስለአርሴናል ማንቸስተር ምናምን ቡድን ግን እንዳትጠይቀኝ ... ከነሱ ከምሰማው በስተቀር ብዙም እንትኑ የለኝም ... እና ዲስከሽኑ ጣጣ የሌለው ዘና ያለ አይነት ስለሆነ ተመችቶኛል ... ይሄ English እና አማርኛ ለምን ጉራማይሌ አርጋችሁ ትናገራላችሁ ምናምን ጣጣ የለበትም ... ድብልቅልቅ አርገው ነጻ ሆነው ያወራሉ ... ይጥማል ..... ሶስቱ ጋዜጠኞች በትንሽ ጠረጴዛ ዙሪያ ስኒከር ጅንስ ምናምን አድርገው .... ቀለል ጸዳ ብለው ... ማውራት ..... እና ምን ነበርማ ልነግርህ የነበረው .... አዎ ማክሰኞ ለት የቀረበው ዝግጅት ላይ ... እ... በዝግጅቱ መጨረሻ ላይ ሁሴን የሚባለው ጋዜጠኛ የሚያቀርባቸው አዝናኝ ፊልሞች አሉ .... ብዙ ጊዜ በሱ ማብራሪያ ታጅበው አንድ ወይም ሁለት ፊልሞች ..... እና ደስ ይለኛል..... ያሁኑ ማክሰኞ ምን ቀረበ አትለኝም? ይሄ ባላክ የሚባለው የጀርመኝ ተጫዋች አለ አይደል? ባለፈው በሰአት 136 km የሚበር በጣም ፈጣን ኳስ (ጎል) አስመዝግቧል አለና አንዱ ፊልም እሱን አሳየ .... ከዛ 'እንግዲህ ፍጥነቱን አስቡት የኳሱን' አለና ... ሌላኛው ፊልም ቀጠለ .... ባላክ በዚህ በኩል ቆሟል .... ትንሽ ራቅ ብሎ ደሞ አንድ ሰውዬ የሆነ ሰርክል ቀዳዳ ያለው ነገር ወደቀኝ በኩል ይዞለት ቆሟል .... እና ባላክ ኳስዋን ቀዳዳው ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል:: ምን ቢሆን ጥሩ ነው ..... ባላክ ተንደርድሮ ሲለጋ ሰርክሉን ስቶ ኳሱ የሰውየውን እንትን አላጎነውም? እየው ..... እኔ በሳቅ የለሁም ..... ደስ ያለኝ ደሞ የሁሴን ገለጻ ነው .... እራሱ በሳቅ እየፈረሰ ... እንግዲህ ተመልከት .... በዛ ፍጥነት የሚበር ኳስ .... 'አላስፈላጊ' ቦታ ላይ ቢመታህ ... ምናምን ሲል .... እየው ... እኔ በቃ ፈረስኩ .....

ወይ 'አላስፈላጊ' .... እስቲ አስበው እንደዚያ አይነት ኳስ እንትንህን መቶህ እንዴታባክ እንደምትሆነው ...... ለማንኛውም the scene was really fun for me. ከምር
Last edited by ናፍቆት on Wed Apr 08, 2009 2:39 pm, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri Mar 20, 2009 8:59 am

ዛሬ ጠዋት የገጠመኝ ..... እየነዳሁ የሆነ አካባቢ ላይ .... ጥቂት ሰዎች ሰብሰብ ብለው መጠነኝ ግርግር አይነት .... naturally ቀዝቀዝ አደረግሁና ሳልጠጋ ቆም አልኩ ..... አንድ በግምት ከ 22 እስከ 24 የሚደርስ ወንድ ወጣት ... ቀይ .... ጸጉሩ ሉጫ ግን ያልተበጠረ ... በቅርቡም አልተቆረጠም አይነት ..... ቀጠን ዘለግ ያለ ..... ፌድ ያረገ ጅንስ .... ነጣ ያለ ሸሚዝ .... ጃኬቱን በመንገዱ ዳር ጣል አድርጎታል ... በጁ ትልቅ ድንጋይ ይዟል .... እና ለመወርወርና ላለመወርወር ግራ የተጋባ አይነት ይመስላል .... ድንገት ስታየው የሚያሳዝን ነገር የሚሰማህ አይነት ..... ከሰፈሩ ወዳስፋልቱ ሲወጣ የተከተሉት ሰዎች ይመስሉኛል ሰብሰብ ያሉት .... ገና ጀማሪ እብድ ....

ድንገት ከኔ ጎን አካባቢ 'ይሄ የንትና ልጅ አይደል እንዴ? ' ... አሉ አንድ ሴት ወደ ቤ/ክ የሚሄዱ ወይም ከዛ የሚመለሱ የሚመስሉ .... ልጁን ማንም አልደፈረውም ነበር ... መኪናዎች ከሁአላዬ ቆም ቆም እያሉ መደርደር ጀምረዋል .... ሴትዮዋ በኮንፊደንስ ወደመሀል አስፋልቱ ገቡ .... መጀመሪያ ዞር ብሎ ሲያያቸው ድንብር ነገር አለ ወጣቱ ... በድንጋዩ እንደማስፈራራት አላቸው ... ሴትዮዋ ግን አልፈሩትም ... ቀጥ ብለው ሄደው ድንጋይ የያዘበትን እጁን ያዙ ...... ካስፋልቱ ወደዳር አወጡት ... ታዘዛቸው .... ወዲያው ቅዝዝ ነገር አለ ...... ዝምብሉ ተጎተተላቸው .... አይኖቹ ያሳዝናሉ ... .... ከዛ ሴትዮዋ ጃኬቱን አንስተው ሊያደርጉለት ሲታገሉ .. አንድ ሰውዬ ምንተፍረቱን ሊያግዛቸው ጠጋ አለ ......ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም ብዬ ቆሜ ልብ ብዬ እያየሁት ነበር ... በሀሳቤ ብዙ ነገሮች ተመላለሱብኝ ... ስለ ውጣትነት ... ስለእብደት .... ስለመኖር .... በአለም ላይ ከሁሉም ነገር ቀላሉ ማበድ ይመስለኛል:: በዚህ 'ኑሮ' በሚባለው ውጥንቅጥ ጉድ ውስጥ ላለማበድ መታገሉ ይመስለኛል ከባዱ ....

.......... ብንን ያደረገኝ ከሁአላዬ ቆመው የነበሩ ያንድ ጥቁር መላጣ ሽማግሌ የመንግስት መኪና ሾፌር ክላክስ ነበር .... To my own surprise, እንባዬ ከመነጽሬ ስር ይፈስ ነበር .... This is Friday. I should have started my day with something relaxing. But , no .....

Don't you sometimes wonder? ህይወት ግን ምንድናት?
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ENGEDA1967 » Fri Mar 20, 2009 9:50 pm

1000ኛ መሆን አማረኝ ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

Postby ShyBoy » Sat Mar 21, 2009 4:59 am

ሄይ ናፍቆት: እንዴት ነሽ ባያሌው? እኔ ከስደት ኑሮ ጋር አለሁልሽ: እግዚአብሄር ይመስገን!

በሄድሽበት እየቀረሽ ቤትሽ መምጣት ትቸ ነበር:: ሰሞኑን ደሞ ብቅ ብቅ ማለት መጀመርሽ በጣም ደስ ብሎኛል! ከምኔው ከኢትዮጵያ ወጠሽ እንደገና ሀገር ቤት እንደተመለስሽ ግን ገርሞኛል:: ሪፖርት አድርጊ ብትባይም እምቢ ብለሻል :lol: የሆነው ሁኖ..........ኑሮ: ስራ: ጤንነት እና የመሳሰሉ ተባዮች እንዴት እያደረጉሽ ነው? :lol:

በነገርሽ ላይ: እንዲህ ሆደ ቡቡ አትመስይኝም ነበር:: የልጁን ሁኔታ ስታስተውይ ቆይተሽ እምባሽ ከቁጥጥርሽ ውጭ መሆኑ ምን ያህል ሩህሩህ እንደሆንሽ ይናገራል! እስቲ ለዋርካና ዋርካዊያንም ራርተሽ ቢያንስ 10 ደቂቃ በቀን (በሁለት ቀን) አጫውችን............ካገሩ የወጣ ደሞ ያገር ቤት ወሬ በጣም ይናፍቀዋል::

መልካም የእረፍት ቀናት!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ናፍቆት » Wed Apr 08, 2009 2:22 pm

ሰሞኑን እዚህ አገር 'discover' ስለተደረገ ጠንቋይ ወይም አታላይ ወይም 'a very smart guy' ልትለውም ትችላለህ ... ብቻ ስለታምራት አልሰማሁም አትለኝም .... ከተማው ሳር ቅጠሉ ወሬው እሱ ነው ..... ስምም ወጥቶለታል 'እያንግዋለለ' ተብሎልሀል .... በምን ምክንያት እንደዛ እንደተባለ ግን እንዳትጠይቀኝ ..... ጋዜጣው ምኑ እሱኑ ነበር ... ግን እኔ ሰሞኑን ትንሽ ቢዚ የሚያረገኝ ነገር ነበርና እህ አላልኩትም .... አላነበብኩም ..... አሁን አረፍ ስል ነው .... አንድ መሀል ላይ ያጋጠመኝ ጽሁፍ ላይ ግን (ያው ጸጉር ቤት ያገኘሁት ጋዜጣ ላይ) ሰውየው የብዙ ታዋቂ ድምጻውያን - 'አርቲስቶች' - ባለስልጣኖች ... ምናምን አገልጋይ እንደነበር ምናምን ነገር ..... እና ብዙ ታዋቂ ሰዎች ምናምን ስማቸው እየተብጠለጠለ እንደሆነ ምናምን ነገር.....

ከዚህ ጋር በተያያዘ .... የመጀመሪያዎቹ ስማቸው የተነሱት ሰዎች ፍቅራዲስ ነቃጥበብና ማናልቦሽ ማነው ... ነበሩ ... እና ያሳቀኝ ነገር ፍቅራዲስ አስተባብላለሁ ብላ ዝም ብላ ያልቸገራትን ቀበጣጥራለች .... የማናልቦሽ ... እ .... ያ መጣልኝ ስሙ የማናልቦሽ ዲቦ ወንድም ግን ቀጥሎ ያለውን አትጠይቀኝም? 'ማናልቦች ታሜ ጋር ብትሄድ መብትዋ ነው' ብሎ የሚያስኬድ መልስ ሰጥቷል .. ለማንኛውም ልንገርህማ የፍቅራዲስን ድምጽ እወደዋለሁ ... የማናልቦሽ ግን ... ልጅትዋን የምጠላበት ምንም ምክንያት የለኝም ግን ዘፈኖችዋ አይመቹኝም .... የሆነ ከበድ የሚል ነገር አላቸው ...(ለኔ) ... አንድ በቲቪ ስቱዲዮ ውስጥ ያስቀረጸችው አሳ በለው እያለች የምትዘፍነውን ዘፈን መቼም ሳታውቀው አይቀርም .... እኔ ምናውቅልሀለሁ ያገርህ ልጅም ልትሆንልህ ትችላለች .... እና ... እዛ ዘፈን ላይ ስቱዲዮውን ትሽከረከር የለ? ያ መሽከርከርዋ እንዴት እንደሚያስጠላኝና እንደሚሰለችኝ እንደነበር አታውቅም ... ከምር .. ለም እንደሆነ አላውቅም ብቻ 'I am like why is she dancing like this? Doesn't she have something better to show? ' .... እስዋ ታድያ ልታቆም እንዳይመስልህ .... ትሽከረከረዋለ........ች - ተጀምሮ እስኪያልቅ ... እና ይሄ ሰውዬጋ ደንበኛ ነበረች ሲባል ..... I was like 'That must be it! ' ከምር .... እኔ ምናውቅልሀለሁ ተሽከርከሪ ብሎ አዟትስ እንደሆነ ..... እስዋ ዞሮባት እኛንም ልታዞርብን ....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby yammi » Wed Apr 08, 2009 3:52 pm

:lol: :lol: :lol: :lol:

ናፍቆት ሙች አላስተረፍሻትም:: ሳቄን ማቆም አልቻልኩም :lol: :lol: :lol: :lol:
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby እህምም » Thu Apr 09, 2009 7:39 am

ናፍቆት wrote:ዛሬ ጠዋት የገጠመኝ ..... እየነዳሁ የሆነ አካባቢ ላይ .... ጥቂት ሰዎች ሰብሰብ ብለው መጠነኝ ግርግር አይነት .... naturally ቀዝቀዝ አደረግሁና ሳልጠጋ ቆም አልኩ ..... አንድ በግምት ከ 22 እስከ 24 የሚደርስ ወንድ ወጣት ... ቀይ .... ጸጉሩ ሉጫ ግን ያልተበጠረ ... በቅርቡም አልተቆረጠም አይነት ..... ቀጠን ዘለግ ያለ ..... ፌድ ያረገ ጅንስ .... ነጣ ያለ ሸሚዝ .... ጃኬቱን በመንገዱ ዳር ጣል አድርጎታል ... በጁ ትልቅ ድንጋይ ይዟል .... እና ለመወርወርና ላለመወርወር ግራ የተጋባ አይነት ይመስላል .... ድንገት ስታየው የሚያሳዝን ነገር የሚሰማህ አይነት ..... ከሰፈሩ ወዳስፋልቱ ሲወጣ የተከተሉት ሰዎች ይመስሉኛል ሰብሰብ ያሉት .... ገና ጀማሪ እብድ ....

ድንገት ከኔ ጎን አካባቢ 'ይሄ የንትና ልጅ አይደል እንዴ? ' ... አሉ አንድ ሴት ወደ ቤ/ክ የሚሄዱ ወይም ከዛ የሚመለሱ የሚመስሉ .... ልጁን ማንም አልደፈረውም ነበር ... መኪናዎች ከሁአላዬ ቆም ቆም እያሉ መደርደር ጀምረዋል .... ሴትዮዋ በኮንፊደንስ ወደመሀል አስፋልቱ ገቡ .... መጀመሪያ ዞር ብሎ ሲያያቸው ድንብር ነገር አለ ወጣቱ ... በድንጋዩ እንደማስፈራራት አላቸው ... ሴትዮዋ ግን አልፈሩትም ... ቀጥ ብለው ሄደው ድንጋይ የያዘበትን እጁን ያዙ ...... ካስፋልቱ ወደዳር አወጡት ... ታዘዛቸው .... ወዲያው ቅዝዝ ነገር አለ ...... ዝምብሉ ተጎተተላቸው .... አይኖቹ ያሳዝናሉ ... .... ከዛ ሴትዮዋ ጃኬቱን አንስተው ሊያደርጉለት ሲታገሉ .. አንድ ሰውዬ ምንተፍረቱን ሊያግዛቸው ጠጋ አለ ......ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም ብዬ ቆሜ ልብ ብዬ እያየሁት ነበር ... በሀሳቤ ብዙ ነገሮች ተመላለሱብኝ ... ስለ ውጣትነት ... ስለእብደት .... ስለመኖር .... በአለም ላይ ከሁሉም ነገር ቀላሉ ማበድ ይመስለኛል:: በዚህ 'ኑሮ' በሚባለው ውጥንቅጥ ጉድ ውስጥ ላለማበድ መታገሉ ይመስለኛል ከባዱ ....

.......... ብንን ያደረገኝ ከሁአላዬ ቆመው የነበሩ ያንድ ጥቁር መላጣ ሽማግሌ የመንግስት መኪና ሾፌር ክላክስ ነበር .... To my own surprise, እንባዬ ከመነጽሬ ስር ይፈስ ነበር ....


My day at አማኑኤል was probably the most emotionally intense experience in my life.

i remember his face, he probably was from the gambela area, very tall, skinny, had scars on his face. he was wearing a white shirt...no pants. He stood in the middle of the compound in chains, staring at me-puzzled.

A mother fighting with her son urging him to stay in bed. He lets out random screams. She screams at him back to keep silent, but she was quitely crying herself.... it didn't help that we were there. She seemed ashamed. we were told he was addmited two night before....he used to be ሰቃይ at AAU.

"እኑዬ, ሞባይልሽን አንዴ ልጠቀመው? ማርስ ልደውል ነበር..." , a light skinned, very handsome guy-late twenties. He used to be a brilliant geography teacher...

It was hard to see kids my age going through their treatment. Some of them were very sloppy cuz of their meds. Some were a week or so away from being released but still had a look in their eyes as if something inside is still broken. I wish i knew how to talk to them, If i could be of an outlet...whithout feeling sorry for them....without lossing myself in their stories....

-i was mad at myself for walking out of the hospital bawling my eyes out.
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests