ቡርቃና የጋዜጠኛው ማስታወሻ - በፓስወርድ መነጽር ሥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby CUBBY » Sat Feb 28, 2009 11:21 pm

እስከምመለስ የሚከተሉትን ትምህርታዊ ፊልሞች እጋብዛለው:-
ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

ክፍል ሶስት

ክፍል አራት

ክፍል አምስት

ክፍል ስድስት
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby CUBBY » Thu Mar 12, 2009 3:06 pm

እኔ:- ሰላም በጣም ይቅርታ ትንሽ የግዜ ሁኔታ ሆኖ ዘገየሁኝ።

በዓሉ:-ኧረ ምንም አይደል ልጄ የት እንዳልሄድ ነው: አንተ ኑር እንጂ:: እንኩዋን ደህና መጣህ?

እኔ:- እንኩዋን ደህና ቆዩኝ:: ወደ ጥያቄዬ ዘልዬ ልግባ ይፍቀዱልኝ?

በዓሉ:- በሚገባ ቀጥል

እኔ:- ከሰሜናዊ በኩል ክልል ወይም ዛሬ ስለተለየችን አገር ልጀምር። እስቲ ስሌርትራና ስለመገንጠልዋ አጠር ባለ ሁኔታ ቢነግሩኝ?

በዓሉ፦ ያው የኤርትራ መገንጠል ከጣሊያን ወረራ ጀምሮ ነው። ከአጼሚኒሊክ ግዜ መሆኑ ነው። በጠቅላላው የኢትዮጵያ ክፍል ነጻ ሲሆን የኤርትራ መሬት ክልል ብቻ በጣሊያን ቀረች (ከ40 አመት በላይ ተገዛች)። በዛን ግዜ ለምን ኤርትራ ብቻ ነጻ ሳትወጣ ቀረች? ለምን ትግሉ እዛ ላይ ቀመ? ለሚለው ብዙ የተሰጡ ምክንያቶች አሉ፡ ለእኔ ግን (ምን አልባት አንባቢዎችህን ላስቀይም እችላለው)፡ በእኔ ሃሳብ ወይም እምነት ወይም እውነት ሆኖ የሚታየኝ ያው አጼ ሚኒሊክን ከዛ ክልል ስልጣናቸውን የሚፈታተን ስለነበር ልስልጣን መጠበቅ ወይም ማትረፍ ነው ብዬ ነው የምለው። ይሄ ምግብ እጥረት፣ ኮሌራ፣ ቅብርጥሴ ለኔ አይገባኝም... በአጭሩ ስልጣንን ከተቀናቃኝ ለማትረፍ ነው። በዚህ አጋጣሚ ኤርትራ ከዛ በፊት የኢትዮጵያ አካል ናት ወይ ብለው ለሚጠይቁ ግን በአጼ ቴድሮስ ግዜ ደጋውን የኤርትራን ክፍል ያስተዳድሩም ግብርም ያስገብሩም እንደነበር ታሪክ ይመዘግባል። ከሃማሴን 37 ቀበሌዎች፣ ከሰራይ 40 ቀበሌዎች እንዲሁም ከአካለጉዛይ 28 ቀበሌዎችን ጎንደር ቤተ መንግስት ድረስ ቤግራቸው በጋማ ከብት በመታገዝ ለንጉሳቸው ይገብሩ እንደነበር ነው።

እኔ፦ዋው! ይቀጥሉ በዚህ ላይ ጭቅጭቅ አላነሳም ግዜም አላባክንም ወቅቱም ስላልሆነ።...

በዓሉ፦ በጼ ሃይለ ስላሴ ደግሞ ብዙ ክርክር ኤርትራን በተመለከተ። ግብጽ፣ እንግሊዝ፣ ኢትዮጵያ እና እራስዋ ኤርትራም እራሴን አስተዳድራለው ብለው በዚህ ጉዳይ በጣም ተጨቃጭቀውበታል።

እኔ፦ ግብጽም ተመኝታ ነበር እንዴ?

በዓሉ፦ እንዴ ታዲያስ ከራሱዋ ግዛት ጋር አጣምራ የቀይ ባህር አውራጃዎች ጨምራ ማስተዳደር እንደምትችልና ሌላም ሌላም ምክንያት እያቀረበች ኤርትራ ለ እኔ ነው የምትገባው ብላ ነበር። እንግሊዝም "የሰራየ፣ የሃማሴን፣ የአካለጉዛይና ቀይ ባህር አውራጃ ለኢትዮጵያ ይሰጡ፤ ምዕራባዊ ቆላና ሰሜን ምስራቃዊው ቆላ ኤርትራ ከሱዳን ጋር አንድ ላይ ሆኖ በእኔ ይተዳደር" በማለት ትከራከር ነበር። በውሃላ የተባበሩት መንግስታት ጉዳዩን ከመረመረ በውሃላ በኢትዮጵያ 1942 ህዳር ወይም እ.ኤ.አ 1950 ታህሳስ ላይ ጉዳዩን ለድምጽ ውሳኔ አቅርቦ የድርጅቱ አባል ሀገሮች በሰጡት ድምጽ 46 ሀገሮች ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ትቀላቀል ብለው ሲደግፉ 10 አገሮች ተቃወሙ። 4 ሀገሮች ድምጽ ሳይሰጡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀላቀል በውሳኔ ቁጥር 390 ተወሰነ። ይሄ አይበቃህም?

እኔ፦ ኧረ ከበቂ በላይ ነው:: ይልቅስ ወደ ዋናው እንግባ እኔስ ለመግቢያ ያህል እንጂ ስለግዜው ሁኔታ እና ሰሞኑን ስለተነሳው ቶፒክ የመጽሃፍ ጉዳይ እንዲሁም ዛሬ እያዳመጥኩት ስላለው ስለፕሮፌሰር ተስፋ ጺዮን የሚሰጡት አስተያየትም ሆነ እድምታቸው ምን እንደሆነ እንዲነግሩኝም ነው:: ቀደም ብዬ እንዳልኩትም ስለአለም ኢኮኖሚንም በተመለከተ እፈልጋለው::

በዓሉ:- እንግዲህ ጀምረዋ!

ይቀጥላል
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Mar 25, 2009 7:33 pm

ሰላም 'password' :-

በዚህ አምድ በቅርቡ በተስፋዬ ገብረአብ ተጽፎ በቀረበው የ"ጋዜጠኛው ማስታወሻ" በተሰኘው ጽሑፍ ላይ አስተያዬት ሲሰጥ ነበር :: ከዚያ መጽሐፍም አልፎ በተስፋዬ ገብረአብ የቀድሞ ሥራዎች ላይም ተያያዥነት ያላቸው አስተያዬቶች ቀርበዋል :: የእኔ ጥያቄ

ተስፋዬ ገብረአብ "የቡርቃ ዝምታ" ብሎ በሠየመው ሥራው ከብርሃኑ ዘርይሁን ሥራዎች እና አቀራረብ ሊያመሣሥለው የሚችለው ምንድን ነው ?

"የቡርቃ ዝምታ"ን በሚከተሉት ድረ-ገጾች ልታገኘው ትችላለህ ::

1. Ye+BurQa+Zemeta.pdf

2. የቡርቃ ዝምታ

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዛዙ » Sun Mar 29, 2009 10:45 am

ሀሪከን (ስልማ) በቅድሚያ እንዴት ነህ? እንደመሰለኝ ተስፋዬን ሽንጥህን ገትረህ የተከራከርክለት የጋዜጠኛው ማስታወሻን አንብበህ የቡርቃ ዝምታን ሳታነብ በፊት ነው:: እኔም ለአንድ ጓደኛዬ ሰለ 'ጋዜጠኛው ማረሳሻ' የጻፍኩት ኢሜል ከዚህ በታች ይነበባል ግን የቡርቃን ሳላነብ በፊት እንደጻፍኩት ልብ በሉ.... እዚህ እንዳለ ልለጥፍላችሁ

I think the book is a sort of a confession, a way of making amends for the damage he has done to Ethiopia by being on EPRDF's side during those horrendous wrongdoings he describes, rather than anything else. Most Efoita writings used to get on my nerves whenever I had a chance to skim through them, I couldn’t even think of buying an issue with my own money, as I remember, no matter how enticing the cover looked. I used to ask 'efoita for whom' much as Wendimu Chubero (the Dorze guy in the book) did. Yet, I remember my seething anger at reading somewhere on an issue of that magazine (which he mentioned in the book) featuring their fabricated version of a story ridiculing professor Mesfin that went back to his childhood in a pseudo-psychoanalytic garbage aimed at his explaining why he denies the existence of the Amhara as an ethnic group (not that I care about the professor any longer after he compromised his integrity in the form of his unholy interviews on VOA regarding the Kinjit split).

I particularly liked a few stories, that of his teacher Zimita, who shouted at him, most legitimately, 'Haven’t they fired you yet?' at a traffic red light; his revealing story of the telecommunications henchmen of EPRDF favoring Tigray, which seemed like a claim suspended on air but now is told by him as an actual fact; his revealing story of EPRDF's machinations against OLF to make them withdraw from the first regional elections, and their doggedness to stop at no moral frontiers or even political principles to ensure the continuance of their rule; OPDO's embarrassing record of not having any form of political orientation and the fact that their very existence in the political scene is driven by pure personal greed of the top guys; same goes for the impotent Amhara outfit named ANDM until lately headed by an Erit. Think of the guy Kassa Deme who, when asked to lend an Amhara cover for Bereket's interview about Eritrea's independence, didn't bother to read what it said but asked why he was not told to wear a tie when he was to be photographed! These are the guys that are running the show in ANDM at present.I also liked his disarming honesty in terms of his own capacity and his mockery on the ludicrous intellectual capacity of most EPRDF stooges. By the way, have you read Mulugeta Lule’s 'Atifto Metifat”' Tesfaye also copiously mentions him and his book in this writing and his tremendous respect for the veteran journalist (later owner of Tobia newspaper) is evident. It also seems that his style was seriously influenced by Mulugeta Lule's book, which was a previous expose of a pervious regime (Derg) at exactly the level of responsibility occupied by Tesfaye during EPRDF; the influence is evident in his love of reference to classical literature and history, his style of narrative, the prominent politicians referred to in his book, and even the choice of his vocabulary.The conflicting information he is willing to concede, however, makes one suspect of his true tendencies with regard to the nation of Ethiopia . For example, he denied that he was ever aware of his Tigrean heritage during the episode he recounted of 'Anley', the political education teacher who later became his sportswriter, and yet he later on admits that he chose to join the rebels because of 'his informed opinion of the rebels since childhood that was different' from his buddy soldier (Amde) from Gojam.I also found his crocodile tears about Gondar as less than honest, considering the brand and tone of the sarcastic stories he was running at the time in 'Efoita' in keeping with EPRDF's marginalizing policy of the major urban centers, and vis-à-vis the plight of the Amharic speaking Ethiopian at the time.It is furthermore virtually impossible that he could have escaped being identified by Shabia as a possible plant in EPRDF. I am sure of that because I was also approached by an Erit (who could have been a Shabia operative) in Wollo (a few years after these guys came to power) about clandestinely 'serving our nation' who mistakenly believed that I was an Erit because I was project manager at a company owned by an Erit. I was young and green and fresh out of college at the time, and I was in no mood for adventure, so I curtly rebuffed him by saying, 'I am an Ethiopian through and through, and if you insist on my origin, I am an Amhara', to which he replied that I should not be ashamed of my Eritrean heritage, and insisted on tracking me and talking to me on several occasions during my unruly young evenings in the small pubs of the small Southern Wollo town where I was working, until I rejected him repeatedly and he gave up. If it were these days, I would have played along in order to learn of his true intentions.So Tesfaye, being a full-blooded Erit in EPRDF, it is impossible that he was not approached by them and not cooperating with them in one way or another, which could be the reason that he finally fled when he was discovered. I was inspired to read his previous book 'ye Burqa zimita', to see how he had approached the Oromo problem, which I am sure will give me further insight into his true sentiment to the nation of Ethiopia as you and I know it. In a way of provocation, he mentions a letter from someone on why 'Chala Chube Chebete' was an alphabet learning tablet. I would doubt whether he didn't realize that it has more to do with the phonetic advantage of collating same-root letters in the same sentence than a stereotyping purpose of 'Chala' with 'Chube'. I found the deliberate mention of this reader’s comment poisonous at best.True, his motive is not crystal-clear and perhaps sinister but his story is revealing, and his Amharic is crisp. He also has a lot more up his sleeve than he is willing to concede. That is my conclusion. I think I will use material from this letter to send him my comments and hear what he has to say.

እንዲህ ያልኩት የቡርቃ ዝምታን ሳላነብ ነበር:: አሁን ግን እድሜ ለልጁነህ1 ከዚሁ ዋርካ ላይ ሊንኩን አግኝቼ አንብቤው ከትናንት ወዲያ ነው የጨረስኩት....... እላለሁ ደግሜ ደግሜ ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ጥሩ የሚመኝ አእምሮ ከልጅነቱ ጀምሮ እንዳልነበረው....አለዚያ ከወያኔ ጋር ተባብሮ እንዲህ አይነት መጽሀፍ አይጽፍም ነበር:: አሁን አብሮዋቸው ያጭበረበረውን ሰዎች በጥሩ አማርኛ ስላማልን አሪፍ ሰው ነው እሱ'ኮ ኢትዮጵያዊነት ያለው ነው አንለውም:: For once ከሙዝ ጋር እስማማለሁ:: ብራቮ ሙዝ እላለሁ

አክባሪያችሁ

ዛዙ
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby password » Sun Mar 29, 2009 10:50 am

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም 'password' :-

በዚህ አምድ በቅርቡ በተስፋዬ ገብረአብ ተጽፎ በቀረበው የ"ጋዜጠኛው ማስታወሻ" በተሰኘው ጽሑፍ ላይ አስተያዬት ሲሰጥ ነበር :: ከዚያ መጽሐፍም አልፎ በተስፋዬ ገብረአብ የቀድሞ ሥራዎች ላይም ተያያዥነት ያላቸው አስተያዬቶች ቀርበዋል :: የእኔ ጥያቄ

ተስፋዬ ገብረአብ "የቡርቃ ዝምታ" ብሎ በሠየመው ሥራው ከብርሃኑ ዘርይሁን ሥራዎች እና አቀራረብ ሊያመሣሥለው የሚችለው ምንድን ነው ?

"የቡርቃ ዝምታ"ን በሚከተሉት ድረ-ገጾች ልታገኘው ትችላለህ ::

1. Ye+BurQa+Zemeta.pdf

2. የቡርቃ ዝምታ

ተድላ

ሰላም ተድላ፣

ይህ ከፍል የጋዜጠኛው ማስታወሻ የተሰኘው መጽሃፍ ስነጽሁፋዊ ይዘቱ የሚተችበትና ጥንካሪና ድክመቱን የምንወያይበት እንዲሆ በማለት ነው የከፈትኩት። የምወደውና የማከብረው ደራሲ ብርሃኑን የጠቀስኩት አንድም ደራሲ ተሰፋዬ ያበረታታኝ ነበር ብሎ ስላነሳው ሲሆን፣ ሁለተናው ምክንያቴ የከፍሉ ስም ተሳታፊ የሚስብ እንዲሆን በማለት እንጂ የሁለቱ ደራሲያ
ስራ ይመሳስላል ለማለት አልነበርም።

በተስፋዬ ገ /አብ የተደረሰው ''የጋዜጠኛው ማስታወሻ '' የተሰኘው መጽሀፍ

ተስፋዬ ... ብርሀኑ ያበረታታኝ ነበር ... ይላል ...

ገጽ 75 ላይ ደርሼአለሁ ... ብርሀኑ ላካ ተኪውን አዘጋጅቶልን ኖሯል ...

ጉርም ትረካ .... አስደናቂ ዘገባዎች ... ውብ ስነጽሁፍ

እያነበብኩት ነው ... ስጨርስ እመለሳለሁ ....

አስተያየቴን የሰጠሁት ገና ገጽ 75 ላይ እያለሁ ነበር። መንሻዬ የድርሰቱ ይዘት ወይም ተአማኒነት አልነበርም፣ የደራሲው አተራረክና ለልብ ሰቀላ የተጠቀመው የልቦለድ አጻጻፍ ዘዬ እንጂ ። ተስፋዬ ጎበዝ ደራሲ እንደሆነ ማንም የሚመሰክረው ነው፣ ይህ ችሎታ ከየት መጥ የሚለውን ጥያቄ ስንመልስ ነው እነብርሀኑ ዘሪሁን ብቅ የሚሉት። ተስፋዬ የቀደምቶቹን መጻህፍት ሳያነብ፣ አነሱን በአርአያነት ሳያይ ዝም ብሎ የዝቁዋላን ዳገትና ቁልቁለት ሲወጣና ሲወርድ ቢውል ይህን ችሎታውን ሊጎናጸፍ ይችላል ብዬ አላምንም። ለዚህ ነው ብርሀኑ ለካ ተኪውን አዘጋጅቶል ኖሮአል ያልኩት። ከነብርሀኑ የተማረው ቁዋንቁዋ፣ ከነበኣሉ የቀዳው ዘዬ፣ ከነዳኛቸው የወሰደው አወቃቀር ስልት ሳይኖር አንድ ወጣት ደራሲ የተዋጣለት ስራ ይሰራል ብዬ መገመት ያዳግተኛል።

ይህ ማለት ግን የደራሲው ስራ ከቀደምቶቹ ጋር ይመሳስላል ማለት አይደለም። የቀደምቶቹ ስራ ግን ላሁኖቹ ደረሲያን ስራ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው መካድ አይቻልም።

የቡርቃ ዝምታ አንብቤ የምለው ይኖርኛል። ከጅምሩ ''ነፍጠኞች ወዮላችሁ'' የሚለው የምእራፍ አንድ ርእስ ራሱ አስደንግጦኛል። ምእራፉ ትኩረት እንዲስብ ይሆን?
ደርሲ ከፖተለከ , ደብተራ ከኮተለከ....

ፓስ
Last edited by password on Sun Mar 29, 2009 12:23 pm, edited 2 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ዛዙ » Sun Mar 29, 2009 10:57 am

ሌላው የረሳሁት ነገር ከበዐሉ ግርማና ከብርህኑ ዘሪሁን ጋር መወዳደሩን ነው:: ይሄ ቀልድ ነው:: ከላይ በጠቀስኩት ኢሜል ላይ እንደጻፍኩት ግን ከሙሉጌታ ሉሌ ጋር ብናወዳድረው አይከፋም:: የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሱ አጻጻፍ ተጽዕኖ እንዳለበት (ከ'አጥፍቶ መጥፋት') ግን ለመጽሀፉ ከመረጠው theme ጀምሮ እስከአጻጻፍ ዘይቤና የቃላት አመራረጡ ድረስ ግልጽ ነው::
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby ሀሪከን2 » Sun Mar 29, 2009 11:57 am

ሰላም ዛዙ እንዴት ነህ
በነገራችን ላይ የቡርቃ ዝምታን ያነበብኩት የዛሬ ሰባት አመት ነበር ይህን አስተያየት ዋርካ ፓለቲካ ያለው ትሬድ ለጥፈህው ቢሆን ኖሮ ይበልጥ ስሜት የሚሰጥ ይመስለኛል

ዛዙ wrote:ሀሪከን (ስልማ) በቅድሚያ እንዴት ነህ? እንደመሰለኝ ተስፋዬን ሽንጥህን ገትረህ የተከራከርክለት የጋዜጠኛው ማስታወሻን አንብበህ የቡርቃ ዝምታን ሳታነብ በፊት ነው:: እኔም ለአንድ ጓደኛዬ ሰለ 'ጋዜጠኛው ማረሳሻ' የጻፍኩት ኢሜል ከዚህ በታች ይነበባል ግን የቡርቃን ሳላነብ በፊት እንደጻፍኩት ልብ በሉ.... እዚህ እንዳለ ልለጥፍላችሁ

I think the book is a sort of a confession, a way of making amends for the damage he has done to Ethiopia by being on EPRDF's side during those horrendous wrongdoings he describes, rather than anything else. Most Efoita writings used to get on my nerves whenever I had a chance to skim through them, I couldn’t even think of buying an issue with my own money, as I remember, no matter how enticing the cover looked. I used to ask 'efoita for whom' much as Wendimu Chubero (the Dorze guy in the book) did. Yet, I remember my seething anger at reading somewhere on an issue of that magazine (which he mentioned in the book) featuring their fabricated version of a story ridiculing professor Mesfin that went back to his childhood in a pseudo-psychoanalytic garbage aimed at his explaining why he denies the existence of the Amhara as an ethnic group (not that I care about the professor any longer after he compromised his integrity in the form of his unholy interviews on VOA regarding the Kinjit split).

I particularly liked a few stories, that of his teacher Zimita, who shouted at him, most legitimately, 'Haven’t they fired you yet?' at a traffic red light; his revealing story of the telecommunications henchmen of EPRDF favoring Tigray, which seemed like a claim suspended on air but now is told by him as an actual fact; his revealing story of EPRDF's machinations against OLF to make them withdraw from the first regional elections, and their doggedness to stop at no moral frontiers or even political principles to ensure the continuance of their rule; OPDO's embarrassing record of not having any form of political orientation and the fact that their very existence in the political scene is driven by pure personal greed of the top guys; same goes for the impotent Amhara outfit named ANDM until lately headed by an Erit. Think of the guy Kassa Deme who, when asked to lend an Amhara cover for Bereket's interview about Eritrea's independence, didn't bother to read what it said but asked why he was not told to wear a tie when he was to be photographed! These are the guys that are running the show in ANDM at present.I also liked his disarming honesty in terms of his own capacity and his mockery on the ludicrous intellectual capacity of most EPRDF stooges. By the way, have you read Mulugeta Lule’s 'Atifto Metifat”' Tesfaye also copiously mentions him and his book in this writing and his tremendous respect for the veteran journalist (later owner of Tobia newspaper) is evident. It also seems that his style was seriously influenced by Mulugeta Lule's book, which was a previous expose of a pervious regime (Derg) at exactly the level of responsibility occupied by Tesfaye during EPRDF; the influence is evident in his love of reference to classical literature and history, his style of narrative, the prominent politicians referred to in his book, and even the choice of his vocabulary.The conflicting information he is willing to concede, however, makes one suspect of his true tendencies with regard to the nation of Ethiopia . For example, he denied that he was ever aware of his Tigrean heritage during the episode he recounted of 'Anley', the political education teacher who later became his sportswriter, and yet he later on admits that he chose to join the rebels because of 'his informed opinion of the rebels since childhood that was different' from his buddy soldier (Amde) from Gojam.I also found his crocodile tears about Gondar as less than honest, considering the brand and tone of the sarcastic stories he was running at the time in 'Efoita' in keeping with EPRDF's marginalizing policy of the major urban centers, and vis-à-vis the plight of the Amharic speaking Ethiopian at the time.It is furthermore virtually impossible that he could have escaped being identified by Shabia as a possible plant in EPRDF. I am sure of that because I was also approached by an Erit (who could have been a Shabia operative) in Wollo (a few years after these guys came to power) about clandestinely 'serving our nation' who mistakenly believed that I was an Erit because I was project manager at a company owned by an Erit. I was young and green and fresh out of college at the time, and I was in no mood for adventure, so I curtly rebuffed him by saying, 'I am an Ethiopian through and through, and if you insist on my origin, I am an Amhara', to which he replied that I should not be ashamed of my Eritrean heritage, and insisted on tracking me and talking to me on several occasions during my unruly young evenings in the small pubs of the small Southern Wollo town where I was working, until I rejected him repeatedly and he gave up. If it were these days, I would have played along in order to learn of his true intentions.So Tesfaye, being a full-blooded Erit in EPRDF, it is impossible that he was not approached by them and not cooperating with them in one way or another, which could be the reason that he finally fled when he was discovered. I was inspired to read his previous book 'ye Burqa zimita', to see how he had approached the Oromo problem, which I am sure will give me further insight into his true sentiment to the nation of Ethiopia as you and I know it. In a way of provocation, he mentions a letter from someone on why 'Chala Chube Chebete' was an alphabet learning tablet. I would doubt whether he didn't realize that it has more to do with the phonetic advantage of collating same-root letters in the same sentence than a stereotyping purpose of 'Chala' with 'Chube'. I found the deliberate mention of this reader’s comment poisonous at best.True, his motive is not crystal-clear and perhaps sinister but his story is revealing, and his Amharic is crisp. He also has a lot more up his sleeve than he is willing to concede. That is my conclusion. I think I will use material from this letter to send him my comments and hear what he has to say.

እንዲህ ያልኩት የቡርቃ ዝምታን ሳላነብ ነበር:: አሁን ግን እድሜ ለልጁነህ1 ከዚሁ ዋርካ ላይ ሊንኩን አግኝቼ አንብቤው ከትናንት ወዲያ ነው የጨረስኩት....... እላለሁ ደግሜ ደግሜ ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ጥሩ የሚመኝ አእምሮ ከልጅነቱ ጀምሮ እንዳልነበረው....አለዚያ ከወያኔ ጋር ተባብሮ እንዲህ አይነት መጽሀፍ አይጽፍም ነበር:: አሁን አብሮዋቸው ያጭበረበረውን ሰዎች በጥሩ አማርኛ ስላማልን አሪፍ ሰው ነው እሱ'ኮ ኢትዮጵያዊነት ያለው ነው አንለውም:: For once ከሙዝ ጋር እስማማለሁ:: ብራቮ ሙዝ እላለሁ

አክባሪያችሁ

ዛዙ
Last edited by ሀሪከን2 on Sun Mar 29, 2009 7:40 pm, edited 1 time in total.
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Mar 29, 2009 6:32 pm

ሰላም 'password' :-

ስለ ሚዛናዊ አስተያዬትህ አመሠገናለሁ ::

ወደፊት 'የቡርቃ ዝምታን' አንብበህ ስትጭርስ የምትሠጠውን አስተያዬት ለማንበብ ያብቃን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby password » Mon Mar 30, 2009 10:07 pm

የቡርቃው ዝምታን በማንበብ ላይ ነኝ። ገጽ 100 ደርሻለሁ፣ መጽሀፉን...አንብቤ እስክጨርስ የተከበረው የደራሲ ብርሀኑን ስም ከቡርቃው ዝምታ ድረሲ ጋር ተያይዞ እንዲቆይ ስላልፈለግሁ አንስቼዋለሁ። ብርሃኑ ብርሃንና ሰላም ከሚሰጡ እንጂ ጨለማና ጥፋት ከሚሰብኩ ጋር አይጠራም...

የቡርቃው ዝምታ ርካሽ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው... ኪነ ጽሁፍ ስላይደለ ዋርካ ስነጽሁፍ ፎረም ውስጥ የመገምገም ብቃት ሆነ ክብር አለው ብዬ አላምንም።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby sarandem » Wed Apr 01, 2009 7:58 am

"የቡርቃ ዝምታ" በማር የተለወሰ የዘረኝነት ትምክት የሞላበት መጽሀፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: ኢትዮጵያ ውስጥ ሚገኙ ብሄረሰቦች ተፈቃቅረው: ተቻችለው እንዲኖሩ ሚያደረግ ብዙ ነገር መጻፍ እየተቻለ ከታሪክ አጋጣሚዎች የሳሳውን ብልት እና ቁስል መርጦ እንዲያመረቅዝ ማድረግ የከፋፋይነት ባህሪ ነው:: ማንኛውም መሪ በዘመኑ መልካም እና መጥፎ ነገሮችን ይሰራል:: መጥፎ የሰራውን ነገር ብቻ መዞ አውጥቶ አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር ሚያናጭ ነገር መጻፍ አሳፋሪ ና ጸያፍ ተግባር ነው:: አጼ ሚኒልክ ልንመዝናቸው ሚገባው በዘመናቸው በነበረው የአለም ፓለቲካ አስተዳደር መሆኑ ሚዛናዊነት ነው:: እሳቸው እኔ እስከማውቀው ግዛታቸውን ለማስፋፋት በመላ ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሰው የቻሉትን ብሄር ወይም ግዛት አስገብረዋል :: ይህንን ሲያደርጉ የኦሮሞን ብሄር ብቻ ነጥለው አላስገበሩም:: በዚህ ጉዳይ ተጠቂ የነበሩ ሌሎችም ነበሩ ሆኖም እርሣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ምርጥ መሪ ሚያስብላቸው ብዙ አሪፍ ነገሮችን ሰርተዋል:: አዳዲስ ያስተዋወቁትን ቴክኖሎጂ ብንክድ እንኳን ለመላው የጥቁር መኩሪያ የሆነ የአድዋን ጦርነት በመምራት በድል ተወጥተዋል:: ይህንን ድል ለመጎናጸፍ ሚኒልክ መላ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ከጎናቸው አስተባብረው ነው አኩሪ ድል ያመጡት በዘመናቸው የነበሩት ምርጥ የጦር አበጋዞች ውስጥ በኢትዮጵያውነታቸው ምንኮራባቸው ከኦሮሞ ብሄር የተገኙ ጀግኖች እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ከፈተኛ መስዋትነት ከፍለዋል :: ካለተሳሳትኩ ራስ ጎበና :ደጃዝማች ባልቻ : ራስ ወሌ :ፊታውራሪ ሀ/ጊዮርጊስ ከኦሮሞ ብሄር የተገኙ ነበሩ :: ማንኛውም ሰው አማራ ወይም ኦሮሞ ልሁን ብሎ አልተወለደም:: ማንም ደሞ እራሱ ባልሰራው ነገር/የአንዱ ብሄር በመሆኑ ብቻ/ እንደጥፋተኝነት ሊያስቆጥረው አይገባም/:: በተቃራኒው እኔ የእንትን ምንትስ ዘር ነኝ ብሎም መኮፈስ ወይም የበታችነት ስሜት ላይ መውደቅም ቢሆን የአስተሳሰብ ድህነት ነው::

ተስፋዬ የቡርቃ ዝምታ መጽሀፉ ላይ ዘርን መሰረት አድርጎ አንዱን ዘር ሲክብ አንዱን ዘር ሲያንቋሽሽ ብዙ ቦታ ላይ ታዝቤዋለሁ::

አንድ ደራሲ ምርጥ ከሚያደርጉት መመዘኛዎች ውስጥ ያለው አመለካከት ከአለም ሁኔታ ጋር ሚጣጣም ወይ ቀድሞ ሲገኝ እንዲሁም ለአንባቢው በመጽሀፉ ሚሰንቀው ብዙ ቁም ነገር መሆን ሲገባው ተስፋዬ ግን ለአንባቢው ያስተላልፈው ዋናው ጭብጥ በቀልን ጥላቻ በመሆኑ መጽሀፉን የዘቀጠ ያደረገዋል::

ተስፋዬ በቡርቃ ዝምታ መጽሀፉ ethnocentric person ነው የሆነብኝ::
በነገራችን ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ስለ ተስፋዬ መጽሀፍት እንዲሁም ስለ እርሷቸው የተጻፈውን እንዲህ ያስተባብላሉ::
ተስፋዬ ገ/አብ ከ ኦሮሞዎች በላይ ኦሮሞ መሆን ይፈልጋል ይሉታል:: ከገጽ 50 ጀምሮ አንብቡት
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby BRUKYIRGA » Fri Apr 03, 2009 2:47 am

የደራሲው ማስታውሻ የሚለው መጥሀፍ እንዴት እንደሚገኝ የሚያውቅ ካለ እርዳታሁ አይለየኝ
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby ShyBoy » Fri Apr 03, 2009 3:44 am

BRUKYIRGA wrote:የደራሲው ማስታውሻ የሚለው መጥሀፍ እንዴት እንደሚገኝ የሚያውቅ ካለ እርዳታሁ አይለየኝ

http://addisneger.zoomshare.com/files/YM.pdf
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ቀጭ » Fri Apr 03, 2009 11:18 pm

ShyBoy wrote:
BRUKYIRGA wrote:የደራሲው ማስታውሻ የሚለው መጥሀፍ እንዴት እንደሚገኝ የሚያውቅ ካለ እርዳታሁ አይለየኝ

http://addisneger.zoomshare.com/files/YM.pdf

አይናፋሩ ልጅ አመሰግናለሁ!
ቀጭ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Tue Mar 31, 2009 4:01 am

Postby BRUKYIRGA » Sat Apr 04, 2009 2:19 am

shyboy ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby ShyBoy » Sat Apr 04, 2009 6:04 pm

ቀጭ እና ብሩክይርጋ: ምስጋናውን ተቀብያለሁ:: ሆኖም ግን ኢንተርኔት ላይ የተለቀቀው እና ዋናው መጽሀፍ እንደሚለያዩ ብዙ ሰዎች ስለገለጹ ዋናውን መጽሀፍ የምታገኙት ከሆነ እሱን ገዝታችሁ እንድታነቡ እመክራለሁ:: እኔ ያነበብሁት ኢንተርኔት ላይ የተለቀቀውን ሲሆን አሁን ግን ያለሁበት አካባቢ ዋናው መጽሀፍ ገበያ ላይ ስለዋለ እሱን ገዝቻለሁ:: ገና በቅርቡ የገዛሁት በመሆኑ አላነበብሁትም.......ማንበቤ ግን አይቀርም::
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests