የዲማ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጊዜ እና ሕይወት

Postby ምረቱ » Sun May 03, 2009 12:38 am

ጊዜ እና ሕይወት :

ሕይወት ገና በተሲዐት በቁም አንቀላፍታ
"'በጊዜ"" ተረታ ""ለጊዜ"' እጂ ሰጥታ
ዛቢያዋን- መሽከርከሪያ ምህዋሯን ስታ
ስታዘግም በሰው ምህዋር ""በጊዜ"" ባለፋንታ
እንበለ ሀገር; በሰው ቀየ-በሰው ቦታ;
""ጊዜ"" ግን ይሮጣል
የልቡን ይሰራል
ሕይወትን ገትሮ እንደጉድ ይበራል
ዘመን ይቆልላል::
እንዲያ እየከነፈ;
አንዳንዱን ያነሳል
አንዳንዱን ይጥላል
አንዳንዱን ይክባል
አንዳንዱን ይንዳል::
ሕይወት ብርቱ! እንደምንም ብላ ምህዋሯን ብታገኝ
""ጊዜ"" እንደሁ አይተዋት; መሽከርከሪያ ጊዜ እንደልብ አይገኝ::

ሚያዚያ 25, 2001 ዓ.ም

ቶሮንቶ
(ጊዜ ለባከነባቸው እና ለተፈናቀሉ)
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ያለፈ ዘመንም ይሆናል መስታወት

Postby ምረቱ » Sat May 23, 2009 12:57 am

ያለፈ ዘመንም ይሆናል መስታወት:

አንዳንዴ
ያለፍንበትን ዘመን
የኁአልዮሽ ስናጠነጥን
ከመስታወት ፊት ለፊት ቆመን
ትክለ ሰውነታችን እንደሚታየን
የወፈርነው; የከሳነው
ያማረብን ወይንም የጠቆርነው
ሁሉንም በውል እንደምናየው
ያለፈ ዘመንም ይሆናል መስታወት
ስብዕናችንን እንድናይበት
ዛሬም ሲደነግዝ-አለው መብራትነት::
የዘመን ዕይታ እንዳውም ይበልጣል
ገጽን እያሳየ መች ይሽነግላል
ሕይወትን መዝኖ ልክን ይናገራል::

ግንቦት 14,2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Heritage of Exile

Postby ምረቱ » Sun May 24, 2009 12:34 am

""ሰው ያላገሩና ሰው ያለቦታው ብሳና ይሆናል ሸንኮራ አገዳው"" በማላቀው ምክንያት ዛሬ ትዝ አለኝና እቺን ነገር ቋጠርኩ

Heritage of Exile:

When you find yourself
Far away from your nation's roof,
The sense of purpose
The dream you wish to realize,
The identity you cherish
Now seen as outlandish
And that sense of pride,
appears to fade and become weird.
Weird for the new land,
Weird in the face of a different crowed
And then you're judged,
""This guy is very weird.""
Often times judged on grounds of commonsense
Entrenched in society as if it is not nonsense
But never
take the judge or the judgment as a real life scale
It's just the heritage of exile.

May 24, 2009, Toronto
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የቀለም ውድነት

Postby ምረቱ » Wed Jun 10, 2009 12:55 am

የቀለም ውድነት:

ቀለም; ሆድ; መኝታው በብላሽ ተለምዶ
እነ አጂሮች አገር ሰው አለቀ ነዶ
አቅም የለኝም ላለ ለቀለም ለመክፈል
ምንም ችግር የለም
የባንክ አካውንቱ ኪሱ ተበርብሮ አራጣ ይሰጣል
ደሞ ወግ አይቀርም "እርዳታ' ይሉታል::
እንደዛች ያላትን ሁለት ዲናር እንደሰጠቺው
ያላትን አንጠፍጥፋ; ሲያጥራት ተበድራ ያስተማረችው
እምየ ኢትዮጵያ-ሀገሬስ ምን ትበል?!
እንዲያ እየተራበች ለዛ ሁሉ ማቲ;ለዛ ሁሉ ፍልፍል
የከፍተኛ ትምርት እንዲሁ ስታድል
ኢትዮጵያ ምን ትበል?
ወይ አንቺ እናት ዓለም
ጉዱን ብትሰሚ የሰለጠነውን የቱጃሩን ዓለም
የተማሪ ጥሬ-ስጋ እየበላ ገንዘብ እንደሚለቅም
ወይ ነጻ ዓለም!
ሰው ትምርት ሲራብ
ቅጥ ባጣ ዋጋ የሚቸበችብ!
ለነገሩ መጽሐፉ እንዳለው
ጽድቅ ለባለ ጠጋ አይቀልም
ግመልም በመርፌ ቀዳዳ አይሾልክም::

ሰኔ 1,2001 ዓ.ም

ቶሮንቶ

የማይመለከታቸው አገሮች አሉ-ስካንዴቪያን አገሮች በአብነት ይጠቀሳሉ::
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ማን ራሱን ጣለ?

Postby ምረቱ » Fri Jul 10, 2009 1:55 am

ማን ራሱን ጣለ?

ጉንጩን ሲበለጥጥ ሲያገጥ ባያየው
ክለብ ስላልወጣ ስላላጫፈረው
ያ ባለ ባዶ ደስታ-ለፌሽታ ቅርበት ያለው
የፌሽታው ብልጭታ ድርግም ሲል ውስጡ ኦና የሚሆነው
ፈለገና ጥራዝ ነጠቅነቱን ሊተረትረው;
""ምነው... ምነው ራስህን እንዲህ የጣልከው?!""
እስኪ ማን ራሱን ጣለ?!

ራሱንስ የትም የጣለ....በሰው ራስ የማለለ
የራሱን ኦናነት...በሰው ፌሽታ በሰው ራስ የከለለ
ወይንም ከናካቴው ራሱን ያልወጠነ
ጭራሽ በሱ ብሶ ተናጋሪ ሆነ
በሰው ላይ በየነ::

ባይሽቀረቀርም ስው ከላይ ባይዘንጥ
የሰው ራስ ባያይ; ፌሽታም ባይቀላውጥ
ያ ጥራዝ ነጣቂ ራሱን ሳያገኝ ራሱን ሳይለውጥ
ላይ ላዮን እያየ ምናል ''ራስ ጣልክ ብሎ"" አቦሰጥ ባይሰጥ
ራስ ያለው ከውስጥ::

ቶሮንቶ
ሐምሌ 2001
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Fri Jul 10, 2009 1:57 am

ማን ራሱን ጣለ?

ጉንጩን ሲበለጥጥ ሲያገጥ ባያየው
ክለብ ስላልወጣ ስላላጫፈረው
ያ ባለ ባዶ ደስታ-ለፌሽታ ቅርበት ያለው
የፌሽታው ብልጭታ ድርግም ሲል ውስጡ ኦና የሚሆነው
ፈለገና ጥራዝ ነጠቅነቱን ሊተረትረው;
""ምነው... ምነው ራስህን እንዲህ የጣልከው?!""
እስኪ ማን ራሱን ጣለ?!

ራሱንስ የትም የጣለ....በሰው ራስ የማለለ
የራሱን ኦናነት...በሰው ፌሽታ በሰው ራስ የከለለ
ወይንም ከናካቴው ራሱን ያልወጠነ
ጭራሽ በሱ ብሶ ተናጋሪ ሆነ
በሰው ላይ በየነ::

ባይሽቀረቀርም ስው ከላይ ባይዘንጥ
የሰው ራስ ባያይ; ፌሽታም ባይቀላውጥ
ያ ጥራዝ ነጣቂ ራሱን ሳያገኝ ራሱን ሳይለውጥ
ላይ ላዮን እያየ ምናል ''ራስ ጣልክ ብሎ"" አቦሰጥ ባይሰጥ
ራስ ያለው ከውስጥ::

ቶሮንቶ
ሐምሌ 2001
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ተስፋ የሚያስፈልገው...

Postby ምረቱ » Tue Jul 21, 2009 1:13 am

ተስፋ የሚያስፈልገው ተስፋ አስቆራጭ በሚመስል ሁኔታ ነው:

በትምህርት ቤቴ ቤተ መጽሐፍት ሰማይን ማየት በሚያስችለኝ
ቦታ ምቾት ባለው ወንበር ላይ ተቀምጫለሁ
የያዝኩትን ዳጎስ ያለ መጽሀፍ አነባለሁ
በተመስጦ ጉዳዪን እያኘኩ ገጾቹን ላፍ ላፍ አደርጋለሁ
አንዳንዴ ደሞ ንባቡን ትቼ እቆዝማለሁ
አይኔን ወደ ውጭ ልኬ ከምድር እስከ ሰማይ ማየት የቻልኩትን ነገር ሁሉ እማትራለሁ::

አንዲት ነጭ ርግብ እየበረረች ተፋትልካ
ከመስታወቱ ተጋጭታ ለማጥመጃ የተቀመጠ የሚመስል የቆመ ሺቦ ላይ ብትሰካ
ልቤ በሀዘን ተነካ::
ሁለቱም ክንፎቿ በሽቦው ተቸነከረ
የውስጧም ውሀ ፈሰሰ ወደታች ተንቆረቆረ
አንዱ እንደኔ ያያት መስታዎቱን ነካክቶ ለማስበረር ሞከረ::

ልክ ሞቷን ለመጠባበቅ እንደመረጠች ነገር
እርግቧ አልቻለችም ትንሽ እንኳ ለመብረር መሞከር
ጸጥ አለች .
ግን ትተነፍሳለች::
ልጁ ተስፋ ቆርጦ ተመለሰ
የኔም እጀ ወደ መጸሀፌ ተመለሰ...ጠረጴዛውን ዳሰሰ
ንባቡን ብጀምርም እይታየ ትንሽ ደፈረሰ
ብዙ ደቂቃ ቢያልፍም አይኔ ከአንድ አንቀጽ አልፎ የትም አልደረሰ::

ያኔ ንባቡን መልሼ አቆምኩ
እርግቧን እያየሁ መቆዘሜን ቀጥልኩ::

እንዳንቀላፋች ናት
""ግን የታል የፈጠራት?
እውነት ሁሉንም የፈጠረው እግዚያብሔር ነው?"" እያልኩ
ከእግዜር ሙግት ጀመርኩ
ጥርጣሬየን አጠናከርኩ::

"'ሰውስ እሺ ሀጢያት ይሰራል ይባል
አሁን ይቺ ርግብ ምን ይወጣታል
በእውነት ፈጥሯት ከሆነስ እንዴት ዝም ይላል
እንዴት ሞት ይፈረድባታል??""
እያልኩ እንደሞተች ተስፋ በመቁረጥ
ግን ደሞ መሞቷንም በውል ለማረጋገጥ
መስታወቱን በጣቴ ብቆረቁር
እርግቧ ወደ ላይ ተነስታ መብረር
ወዲያው ደንግጨ ወይ እግዚያብሔር!!!
አፌ ተሳሰረ
ልቤም በጸጸት እና በእምነት ተሰበረ::
በእኔ ብሶ በእግዚያብሄር ስላዘንኩ
እጂጉን ተጸጸትኩ
ማንበቡንም ትቼ ወደ ቤት ተመለስኩ
ያሳለፍኩትን የጥርጣሬ ዘመን በአእምሮየ ከለስኩ
አንድ ነገር አወኩ!
ለካስ ተስፋ የሚያስፈልገው
ተስፋ አስቆራጭ በሚመስል ሁኔታ ነው:
ተስፋም እግዚያብሔር ነው::

በፈረንጆቹ በዲሴምበር ወር 2007 ላይ ትምህርት ቤት ያጋጠመኝ ነው::

ቶሮንቶ
ተጻፈ ዛሬ ሐምሌ 12, 2001 ዓ.ም
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

አለ አንዳንድ ሰዐት

Postby ምረቱ » Fri Oct 09, 2009 6:00 am

አለ እኮ አንዳንድ ሰዐት
ለራስ የሀሴት መለከት የሚነፉበት
ከራስ ጋር በሰላም በፍቅር የሚጫወቱበት
አሁንን የሚያጣጥሙበት
ነገር ዓለሙን ረስቶ
አሮጌ ፋይል ዘግቶ
ቀልብን ለሀሴት አመቻችቶ
በቃ ነገር ዓለሙን ትቶ
......ጉራንጉሩን ረስቶ
ልብ እና መንፈስን አስማምቶ
ትላንት እና ነገን ወርውሮ
አሁንን በአሁን አጥሮ
እንዲሁ... በአሁን መደመም
ትላንት ሳይታሰብ...ነገ ሳይታለም
እንዲህ ያለ ሰዐት አያስደስትም!

ጥቅምት 2, 2002 ዓ.ም

ሀሚልተን
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

በረከት ነው መርገምት

Postby ምረቱ » Sat Nov 21, 2009 11:44 pm

ይቺ ከተጻፈች ቆየት ብላለች .... ወይ ታሪክ ነች ወይ ታሪክ ትሆናለች ...it's a matter of time

በረከት ነው መርገምት


ያኔ በጓድንኞች ሙድ እንዳልተያዘ
ፍቅር ያዘን ሲሉ እንዲያ እንዳልተሳቀ -እንዲያ እንዳልተፌዘ
የኔም ልብ በተራው ጊዜውን ጠብቆ በፍቅር ተከዘ::

ያውም በሰው ሀገር ስንት ሀሳብ ባለበት
ብዙ ውጣ ውረድ ድካም በሞላበት
ልቤ እሱን ረስቶ ለፍቅር ሲተጋ ሲያደርገው እንደ እምነት
ፍቅር እያሰበ ሌት-ከቀን ሲዋትት
ማነው የሚያስረዳኝ ነገሩ የገባው የተገለጸለት
ይኼ ፍቅር ማለት በረከት ነው መርገምት?

በሀሳብ ብትቃትት ፋታ ቢነሳህም
እንቅልፍም እያጣህ ብዙ ብታስብም
ፍቅር በመያዝህ ምንም አትጸጸት
የእግዚያብሔር ስጦታ ቢሆንስ በረከትየካቲት 20, 2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የሰው ዕብቅ

Postby ምረቱ » Sat Dec 12, 2009 10:28 pm

የሰው ዕብቅ
ስልጣኔ አዙሮት እራሱን የሳተ
በሰው ንፍዘት እየዋተተ
በነውር በሀጢያት እየተደሰተ
ራሱን ለሰዶምነት እየፈተተ
ሰልጥኛለሁ ይለናላ
ወደ ሰዶም እየሄደ ወደ ኌላ
ኧረ እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ጠብቅ
እንዳያረክሳት እንዲህ ያለ የሰው ዕብቅ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ለውብ ልጂ ከልብ በላይ ምን ይሰጣል?

Postby ምረቱ » Sat Dec 12, 2009 10:35 pm

አንዳንዴ የወደደ ሞኝ አይደል!
የመውደዴን ልክ ላሳይ ባስብ
ቀን ቀን ሳልጋደም በሀሳብ
ሌሊት ተኝቼ በምናብ
ሰርቼ ግድንግድ የፍቅር ግንብ
ልቤም ከትሞ በሷ ልብ
እኔ በሀሳብ ላይ;ሀሳብ በእኔ ላይ ሆነን
ሳስብ..ሳስብ...ሳስብ...
ምን አይነት ሀሳብ
.....የማይረግብ
አንዴ በስሟ ትንሽዬ መጽሀፍ ስጽፍ
አንዴ ወጣ ብለን ጥሩ የዕረፍት ጊዜ ስናሳልፍ
መውደዴ እስኪገባት አለቅም ብዬ ዓይን ዓይኗን ሳያት
ድምጽ አልባ ሆኘ በዐይኔ ስለፍቅሯ ሳዜምላት
ቁንጂናዋን አንድ ባንድ ሳሳያት
ራሴን ያለፈቃዷ ሾሜ እንደውበቷ ነገረፈጂ
የኔ"'ሚስ ወርልድ"" እሷ ነች ብዬ ላውጂ
የሷን ደስታ; የሷን ስኬት እንደምመኝ ልነግራት ስዘጋጂ
ለካስ ናት ፍቅር የማትፈልግ ቆንጆ ልጂ::

ልጠይቅ እንጂ ፍቅር የያዘው ሞኝ አይደል!
ለውብ ልጂ
ለባለ ፀዳል ከልብ እና ከፍቅር በላይ ምን ይሰጣል?!

ለፍቅር ሞኞች
ወይ ፍቅርን ይወርሳሉ
ወይ ፍቅርን ይከሳሉ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

አድዋ

Postby ምረቱ » Mon Mar 01, 2010 3:55 pm

ለአድዋ ድል መታሰቢያ የቋጠርኳትን ላካፍል:

ነገረ አድዋ...ጥልቅ; ምጥቅ
ጸአዳ ዝንት-ዓለም የሚያንጸባርቅ

የወራሪ የታሪክ ለምጥ
የአበሽ የታሪክ ጌጥ
የአበሽ ተድላ ሀሴት
የወራሪ የመንፈስ; የአካል ስብራት

አድዋ የቀን አውራ
የድል አባወራ
እንዳውዳመት ይዘከራ!

የድል ብስራት
የድል ጥሪት
የመንፈስ ስንቅ ያበሻ አንጡራ ሀብት

አድዋ!
የወንድነት ድካ ያበሽነት ልክ ስፍር
የአበሽ የድል ገድል! የድል ስንክሳር
የድል ችቦ ክምር
የማይበገር ጀግና ትውልድ
የደም; ያጥንት ውልድ
ሲያስቡት መንፈስ እንደ ችቦ የሚያቀጣጥል የሚያነድ
የኛነታችን ማህተም የኛነታችን አሻራ
የመንፈስ መጽናኛ በሌሎች ጥቁር ሕዝቦችም ጎራ

አድዋ!

የአበሻነት እና ""የነጻነት"' የቃል ኪዳን ውል
የእምቢ ለሀገሬ እምቢ ለነጻነቴ ብሂል
የሚንበለበል ያገር ፍቅር ምስል
"ዋ ኢትዮጵያ! እኔ ላንቺ ልሙት እረ ልከንበል"
ይሄ ነው ያድዋ ትርጉሙ
ሃበሻ የጻፈው የሳለው በደሙ

ሰው ሲደመም ጡብ;ሲሚንቶ;ፌሮ ተስማምቶ ሰማይ ሊነካ ሲንጠራራ
አበሽ በዛቱ; በልቡ የማይፈርስ ሰማይ ጠቀስ የድል ክምር ሲሰራ
የሚታይ ከየትኛውም ስፍራ ...
እኛማ ለምን አንኮራ!!

አድዋ ትዕይንትም ነው
በአንድ በኩል ቀልበ ጡሊ የሰው አገር ሊወር የወበራ
በሌላ በኩል ገራገር አበሽ ግን ለነጻነቱ የማይመለስ ሞት የማይፈራ
ስንት የሴት ወንድ; ስንት የወንድ አውራ
ጎራዴ የያዙ እጆች የተፋለሙበት ከባለመትረየስ ጋራ
የስጋና የመንፈስ ስምምነት የ"ልሙት ለሀገሬ ፍካሬ'
የጽኑ ነብስ; ጽኑ ስጋ የመንፈስ ዝማሬ; የተጋድሎ ፍሬ
ያገር ፍቅር እና አልሸነፍ ባይነት
ወራሪን እንደ ሰንጋ የመተሩበት
ያበሻ ማንነት የታየበት
ዝንታለም የሚታወስ ትዕይንት

አደዋ!

የአድዋስ ቅዱስነት!!!
እንደ ክርስቶስ ስቅለት
ለሰው ልጂ ፍቅሩን እንደገለጠበት
አበሻ"ለነጻነት' ያለውን ቀናዒነት ያሳየበት
የደም; ያጥንት አስራት በኩራት ያስገባበት
የነጻነት የመጨረሻ ዋጋ-ህቅታውን ከነዛቱ የሰጠበት
የድል ጥሪት;
የአበሽ መንፈሳዊ ሀብት!!
የሀበሻ ኩራት!!

አድዋ የድል አውራ
እንደ አውደ ዐመት ይከበራ!!

ምረቱ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby Senayte » Wed Mar 03, 2010 4:16 am

ዋው ዲማ እንደዚህ ገጣሚ መሆንህን አላውቅም ነበር :: አይ ኖ ጥሩ ጸሀፊ እንድነበርክ /እንድሆንክ , ግን ግጥም..... ዋው ....ዛሬ ግዜ ስጥቼ ሁሉንም አንበብኳቸው ....በጣም ቆንጆዎች ናቸው ......ቀጥልበት ...ብሮ...
Senayte
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 241
Joined: Thu Nov 18, 2004 5:00 am
Location: Lieville.....

Postby ምረቱ » Thu Mar 04, 2010 7:06 am

Senayte wrote:ዋው ዲማ እንደዚህ ገጣሚ መሆንህን አላውቅም ነበር :: አይ ኖ ጥሩ ጸሀፊ እንድነበርክ /እንድሆንክ , ግን ግጥም..... ዋው ....ዛሬ ግዜ ስጥቼ ሁሉንም አንበብኳቸው ....በጣም ቆንጆዎች ናቸው ......ቀጥልበት ...ብሮ...


ሰላም ሠናይት

ስላነበብሽኝ እና ስለ ማበረታቻው አመሰግናለሁ::
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ቶድ » Fri Mar 05, 2010 12:19 am

በቅድሚያ የከብረ ሰላምታ ለዲማ!!!!!

""ፍቅር እስከ መቃብር"" በታላቁና ስመ ጥሩ ደራሲ በዶክተር አዲስ አለማየሁ ..... በዲማ ጊዮርጊስ ዙሪያ ህይወትና ነፍስ ሲዘራበት ............ ዛሬ ደግሞ የታላቁን የአድዋን ድል በማስመልከት በተከበሩትና እጅግ በጣም በምናፈቅራቸው በእነዛ ስመ ጥር ቅድመ አያቶቻችን ስለተከፈለልን መስዋትነት ገድል ..... ባህሉንና ታሪኩን በሚወደውና በሚያከብረው በውድ ወንድማችን በዲማ ...... ""ነፍስና ህይወት"" በተዘራበት የግጥም መድብል የአድዋ ምድርና እንዳያልፉ ሆነው ስላለፉት ውድ ሰማዕታት አያቶቻችን ነፍስና ህይወት ሲዘሩ በማንበቤ ....... ከታላቁ አድናቆቴ ባሻገር ..... የዲማ ስም አሰያየሙ ... ""በተፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ"" ..... ተጨማሪ ህይወት የመዝራቱ ሚስጥር እንቆቅልሽ እንዲሆንብኝ እየጋበዘኝ ነው::

ወንድም ዲማ እጅግ በጣም ግሩም ግጥም ነውና የምትጽፈው ....... በርታ!!!!! በዚሁ ቀጥልበት!!!!!! ባሕላችንና ታሪካችንንም ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ..... የአንተን መሰል ወገን መፈጠሩ እሰየው የሚያስብል ነው!!!!!

በዚህም አጋጣሚ የታላቁን የአድዋን ድል በዓል በማስመልከት ለሁሉም ወገኖቻችን የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ..... የዛሬ 114 ዓመት ገደማ .... ውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን በዘርና በሐይማኖት ሳይከፋፈሉ ... በታላቁ በአድዋ ምድር ላይ ..... ከአራቱም የሐገራችን መዓዘናት በመሰባሰብ ስለከፈሉት መስዋትነት ...... የአድዋ ምድርና በተለይም የአድዋ ተወላጆቿ ስለኢትዮጵያ አንድነት እጅግ በጣም የከበደ ሀላፊነት ሊሰማቸው እንዲገባ ከፖለቲካ እጅግ በጣም የነፃ መልክቴን አስተላልፋለሁ:: እንደዚህም ስል ለአድዋ ልጆች ብቻ የተለየ መልክት ላስተላልፍ ፈልጌ ወይንም የአድዋ ልጆች የሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ውለታ አለባቸው ለማለት ሳይሆን ...... ወይንም በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የአድዋ ልጆች ናቸው ለማለት ፈልጌ አይደለም .... ወይንም ሌላው ኢትዮጵያዊ ምንም ተሰሚነት የለውም ለማለት ሳይሆን ወይንም ለአድዋ ልጆች ከሌላው ወገኖቼ የተለየ ብልጫ ለመስጠትም ሳይሆን (ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ነው!!!!! ምንም ጥርጥርም የለውም!!!!!!) ..... የታላቁ የአድዋ ድል የታሪክ መፃፊያ ደብተሩ የአድዋ ምድር መሆኑዋና ....... በአድዋ ላይ ስለተከፈለው መስዋትነት ...... እያንዳንዱ ውድ ወገናችን በዘር .. በፆታ ... በሀይማኖት ሳይከፋፈል ..... ከእያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ .... አንተ ትብስ እኔ ትብስ ተባብሎ ታሪክ የሰራበት አጋጣሚ ነበርና ...... ዛሬም!!!!!!!! አሁንም ቢሆን!!!!!!!! እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ!!!!!! ይህንን በዓል በማስመልከት በዘር የመከፋፈል ፖለቲካውን በመተው ....... በተለይም ነገ ለምንወልዳቸው ውድ ልጆቻችን መርዝ አዘል የቤት ስራ እንዳንሰጣቸው ....... አንድነታችንን ጠበቅ!!!!!!!!!! የምናደርግበት አጋጣሚ እንዲሆን ከአደራ ጋር መልእክቴን ለእያንዳንዱ ወገናችን በዚህ አጋጣሚ አስተላልፋለሁ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 4 guests