የአዲስ አመት መልክቴ ለወንድሜ ለመካሪዬ ላስተማሪዬ ላክባሪዬ ላበረታቼ ለፓስዎርድ/ ለደራሲ መኮንን ገብረ ዝጊ ይድረስልኝ....
ይህ አዲስ አመት የጀመርከውን በሰክሰስፉል ሁኔታ የምታገባድድበት አዳዲስ ግኝቶችን የምታፈልቅበት እውቀት እንደ አባይ ፉዋፉዋቴ የምታፈልቅበት ባንተ ግኝት ሌላውን የምታስተምርበት ስምህ እስከህዋ ድረስ የሚናኝበት የጠና የብልጽግና አመት ይሁንልህ እያልኩ ስመኝልህ ለተከበሩት ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማዶችህ ይህ ሙሉ አመት የጠና የብልጽግና የሰርቶ መከበርያ የጥጋብ አመት እንዲሆንላቸው እመኛለሁ::
እንደምን አለኽልኝ ወንድምዬ?ከዋርካ ጠፋኽ...ይሻልሀል...ጊዜ ማባከን ነው....ከስንት ከብት ጋር ሳር ብላ አትብላ እያሉ መታገል ነው::የተሰጠውን ባግባቡ የማያመነዥግ የምታደልበው ከብት ጋር ከመዳረቅ እንዳንተ ጥፍት ማለት ሳይሻል አይቀርም::
ፓስ....ያንን ነገር አልጀመርኩም::ወኔ አጣሁ::ግን እቅዴ ካድማስ ማዶ ስራዬ ገና ምኑም ያልተጀመረ::እስቲ በዚህ አዲስ አመት ወነ እንዲኖረኝ ተመኝልኝና ልክ እንደኒውክልየር ፍንዳታ ነገሮችን ላፈነዳዳቸው::በውስጥ የታመቁ ኢለመንቶች አሉ....በውስጤ እየተብላሉ ነው እንዳላወጣቸው ወኔው ጎደለኝ ልበል?
በርድ እህታችን ደህና ነች?ካነበብሽኝ እህተ እንኩዋን አደረሰሽ የኔ ፍቅር::ይህ አዲስ አመት በቃ እንደፈለግሽው ይሁንልሽ::የተመኘሽው እጅሽ ላይ እየሆነ ደስታ ላይ ደስታን ይስጥሽ::
ወንድማችሁ ሾተል ነኝ