- ስላሴ እና ፅንሰ ሀሳቡ
ሚስጥረ ስላሴ ምን ይሆን?
ከ ሀገር ውስጥ
መምህር ምህረት አብ ስላሴን አስመልክቶ በሚስጥራዊ ቡድኖች ላይ እንዲህ ሲል ስለስላሴ ነግሮናል "‹‹.. ዛፍ ከላይ ቅርንጫፍ፤ ከመሃል ግንድ፤ ከታች ስር.. ስላለው ሶሰት ዛፍ እንላለን?… አንልም.. አንድ ዛፍ.. አንዱ ዛፍ ግን ስንት ነገር አለው?..ሶሰት… እግዚአብሄር ስንት ነው?.. አንድ… አንዱ አምላክ ግን ስንት አካል አለው?.. ሶስት.. ታድያ ይሄ ምን ይከብዳል..››(4) በመሆኑም የምህረታቡ ትንታኔ መሰረት ስላሴ ማለት የእግዚአብሄር ሶስት አካላት ማለት ናቸው፡፡ እግዚአብሄርን የገነቡ ሶስት አካላት በሌላ ቋንቋ እግዚአብሄር ማለት አብ ሲደመር ወልድ ሲደመር መንፈስ ቅዱስ ………
ቀጣዩ መምህር ኪዳነ ማርያም ጌታሁን ናቸው ፡፡ምን ነበር ያልሉትአ ባቴ?
“ ስላሴ በስም በአካል በግብር(የኢኮኖሚው ግብር እንዳይመስልህ ተግባር ለማለት ተፈልጎ ነው) ሶስት ናቸው፡፡ስማቸውም አብ፣ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ ፡፡አብ አካል አለው ወልድ አካል አለው መንፈስ ቅዱስ አካል አለው፡፡በግብራቸው አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ነው፡፡……….ስላሴ ሶስት አካል ሶስት ስም ሶስት ግብር ስላላቸው ሶስት አማልክት ናቸው ማለት አይደለም፡፡ሶስቱም በባህሪ፣በህልውና፣ይህን አለም በመፍጠር እና በመግዛት አንድ ናቸው፡፡……”(5)
አባ ሳሙኤልም በበኩሉ የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ሶስትነት እና አንድነትን በተነተነበት ሂደቱ አብ ወልድ አይደለም ወልድ አብ አይደለም መንፈስ ቅዱስም አብም ወልድም እንዳልሆነ እና የሶስቱድም ርእግዛብሄርን እንደሚሰጥ በስእላዊ ስእላዊ በሆነ መልኩ ለመግለፅ በመፅሀፉ ሙከራ አድርጓል(6)
ይህን ሀሳብ በመደገፍ መምህር ታሪኩ አበራ እንዲህ ሲል አንድ በሉ ይለናል
“ እግዚአብሄር ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ነው፡፡አብ የምንለው የእግዛብሄር ልብ ወልድ የምንለው የእግዛብሄር ቃል መንፈስ ቅዱስ የምንለው ደግሞ እስትንፋስ ነው”(7)
መምህር ብርሃኑ ጎበና በበኩሉ፡-
“የእግዛብሄር አንድነት እና ሶስትነት የሚክዱ ጥቂቶች ሳይሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡እግዚአብሄር አንድ ሲሆን ሶስት ሶስት ሲሆን አንድነው” (8) አያይዞም “……ለሰው በነፍሱ ሶስትነት አለው፡፡ይሀውም ልብነት፣ቃልነት፣ህይወትነት ነው፡፡የሰው ነፍስ በልብነቷ የአብ ምሳሌ ናት፡፡በቃልነቷ የወልድ በህይወትነቷ የመንፈስ ቅዱስ …….”(9)
የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በስላሴ ስር የሚከተለውን ፅፏል
“እውነተኛ እና ህያው የሆነ አንድ አምላክ አለ በሶስት አካላት ስለሚኖር ስላሴ የሚለው ቃል የአንዱን አምላክ የስም የአካል የግብር ሶስትነት ያመላክታል……..አዲስ ኪዳን ግን በእግዚአብሄር ዘንድ ሶስት አካላት እንዳሉ ስማቸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ይገልጣል”(10)
በመሆኑም እነዚህ የተደማመሩ የኦርቶዶክስ እምነት መምህራንን አንድ ሚያደርጋቸው ስላሴ ሚለው ቃል የ አንድ አምላክ ሶስት አካላት ናቸው የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ግን ነውን? ተረጋጋ እንመጣበታለን፡፡
የስላሴ ትርጉም እና ይዘት እና አለማቀፍ ትርጓሜ
የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በተመለከተ ዊኪፒድያ እንዲህ ብሎናል
The Christian doctrine of the Trinity defines God as three divine persons or hypostases:[1] the Father, the Son (Jesus Christ), and the Holy Spirit; "one God in three persons". The three persons are distinct, yet are one "substance, essence or nature (11)
አንዳንድ ኦንላይን ዲክሽነሪዎችም እንዲህ ሲሉ ትንታኔን ሰጥተውታል
Trinity Theology In most Christian faiths, the union of three divine persons, the Father, Son, and Holy Spirit, in one God. Also called Trine.(12)
ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ በበኩሉ
"The Trinity is the term employed to signify the central doctrine of the Christian religion — the truth that in the unity of the Godheadthere are Three Persons, the Father, the Son, and the Holy Spirit, these Three Persons being truly distinct one from another."(13)
Professor of Theology and Religious Studies John T. Ford የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ በዚህ መልኩ ይተነትነዋል፡“Trinity. This word (from the Latin trinus, meaning “threefold”) refers to the central mystery of the Christian faith that God exists as a communion of three distinct and interrelated divine persons: Father, Son and Holy Spirit. The doctrine of the Trinity is a mystery that is inaccessible to human reason alone and is known through divine revelation only.”(14)
የሐገር ውስጥ ኦርቶዶክስ ሰባኪያን ስላሴን የእግዚአብሄርን የገነቡ 3 አካላት መሆኑን በምሳሌ አስደግፈው ነግረውናል ይህም ሲባል እግዚአብሄር ማለት አንድ ወጥ አካል ሲሆን ሶስት የተለያዩ ክፍሎች አሉት ማለታቸው ነው፡፡ ልክ አንድ ዛፍ ግንድ ፣ስር እና ቅጠል እናዳለው ሁሉ፡፡ የግንድ ,የስር እና የቅጠል ድምር ውጤት እንደሆነ ሁሉ… እግዚአብሄርም አንድ አካል ሲሆን ያስገኙት ክፍሎች አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው ማለታቸው ነው፡፡ . የባህር ማዶ ምሁራን ግን በዚህ አይስማሙም ስላሴን ማለት የአንድ አካል 3 ክፍሎቸ ብለው ሳይሆን ሚተረጉሙት ሶስት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ነው ሲሉ ፅፈው ሲያበቁ ግና በስልጣን በሀይል በግዛት አንድ መሆናቸውን ጨምረው ፅፈዋል ፡፡ ወይም እነዚህ ሶስት የተለያዩ አካለት እያንዳንዳቸው አምላክ መመሆናቸውን ነግረውህ ሲያበቁ ግና ሶስት አምላክ ሳይሆኑ አንድ አምላክ መሆነቸውን ጨምረው ይነግሩሃል፡፡
ካቶሊክ ኢስሳይክሎፒዲያ በዚህ መልኩ የገለፀውን አንብብ" in the words of the Athanasian Creed: "the Father is God, the Son is God, and the Holy Spirit is God, and yet there are not three Gods but one God."(15)
ግራ ቢገባህም ሶብር አርግ!!!
ስላሴ እዚህ ላይ አያበቃም የቀሩ ሌሎች ፍልስፍና ዎች አቅፎ ይዟል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ዱዋሊሰዘም በሚባል የ እምባሻ ስም ይታወቃል፡፡ ይህ ፍልስፍና ከ አትናሲያን አቂዳ የሚለይ ሲሆን አንዱ ፈጣሪ በሶስት አካላት ተገለጠ የሚል ፍልስፍናን ይዞ ነው ብቅ ያለው ይህም ሲባል ልክ ውሀ ጠጣር ፣ፈሳሽ ፣ እና ጋዝ እንደሚሆነው ፈጣሪም እራሱን ሶስት ገልጾል የሚል እምነትን አንግበውተነስተዋል ማለት ነው ፡፡ ይህን ፅንሰ ሀሳብ አስመልክቶ Scott Dunham እንዲህ ቢል አይገርምም
“Modalism is a conception of the three persons of the Trinity not as distinctly subsisting persons, but as manifestations of the one God, whether the Father or a divine substance.” [16]
Xavier William እንዲህ ቢል አይገርምም
Sebellianism: Christian heresy that was a more developed and less naive form of Modalistic Monarchianism (see Monarchianism); it was propounded by Sebellius (c. 217-c.220), who was possible a presbyter in Rome…Sebellius evidently taught that the Godhead is a monad, expressing itself in three operations: as Father, in creation; as Son, in redemption; and as Holy Spirit, in sanctification.”(17)
እውቁ የመለኮት ጠበብት Samuel Hopkins እንዲህ ሲል ፅፏል
“…Sebellianism; which considers the Deity as but one person, and to be three only out of respect to the different manner or kind of his operations.”(18)
ሶስት አይነት ስላሴ
1. አዲሱ ስላሴ
2. ዱዋሊዝም ስላሴ
3. አትናስያን ስላሴ
Let us examine them ነው ሚባለው?
አዲሱ ስላሴ፡- ይህ የስላሴ አይነት የሀገር ውስጥ ሚሽነሪዎች የሚሰብኩት የ ስላሴ አይነት ነው፡፡ ይህም ሲባል ስላሴ ማለት 3 የተለያዩ እና ራሱን የቻለ አካል ያላቸው ሳይሆኑ ስላሴ ማለት የአንዱ እግዚአብሄር አንድ ወጥ አካል ሶስት ክፍሎች ናቸው የሚል ፍልስፍና ነው፡፡ በዚህ ስላሴ ፅንሰ ሀሳብ አራማጆች ከሚሰጡት ምሳሌ ውስጥ አንዱ በሚስጥራዊው ቡድን ቪድዮ ሲዲ ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን ይህም
መምህር ምህረተአብ እንዳለው "‹‹.. ዛፍ ከላይ ቅርንጫፍ፤ ከመሃል ግንድ፤ ከታች ስር.. ስላለው ሶሰት ዛፍ እንላለን?… አንልም.. አንድ ዛፍ.. አንዱ ዛፍ ግን ስንት ነገር አለው?..ሶሰት… እግዚአብሄር ስንት ነው?.. አንድ… አንዱ አምላክ ግን ስንት አካል አለው?.. ሶስት.. ታድያ ይሄ ምን ይከብዳል..››(19)
ሹፍ!!! ምህረተ አብ የስላሴን ፅንሰ ሀሳብ ከዛፍ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ነገረን፡፡ ነግሮንም ሲያበቃ እኛ እውነት ነው ስንል ሐሳቡን መረመርን ሁሉም እንደሚያውቀው አንድ ዛፍ አንድ ወጥ ሙሉ አካል አለው ይህ የዛፍ አካል የተለያዩ ክፍሎች አሉት ለምሳሌ ስሩ ብቻውን ዛፍ አይባልም፡፡ ግና የዛፉ አንድ ክፍል ነው ሚባለው ፡፡ ግንዱም ሆነ ቅጠሉም ዛፍ የሚባለው አንድ ወጥ አካል የተለያዩ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለብቻቸው ዛፍ አይደሉም፡፡ ዛፍ የሚባሉት የሁሉም ክፍሎች ጥምረት የሚያስገኘው ድምር ውጤት ነው ይህን እወነታ ስር ቅጠሉ እንኳ ያውቀዋል፡፡ በምህረተ አብ ሎጂክ መሰረት አንዱ አምላክ ልክ እንደዛፍ ሁሉ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ አንድም አብ የሚባለው ክፍል ነው ሁለትም ወልድ ሚባለው ክፍል ሶስትም መንፈስቅዱስ የሚባለው ክፍል በመሆኑም ይህ አንዱ አምላክ የሚገኘው ሶስቱ ክፍሎቹ ሲደመሩ ነው ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው እነዚህ የአንዱ አምላክ ወጥ አካል ሶስቱ ክፍሎች ካልተደመሩ አምላክ ሊባሉ ወይም አንዱን አምላክ ሊሰጡ አይችሉም፡፡ በመሆኑም እንደምህረተአብ ሎጂክ አብ ብቻውን አምላክ አደለም ማለት ነው፡፡ ወልድም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ብቻቸውን አምላክ አይደሉም ፡፡ ልክ ስር ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ግንዱ ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ቅርንጫፉም ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ሁሉ!!! የመምህር ታሪኩ አበራን ምሳሌም መመልከት ይቻላል፡፡ መምህር ታሪኩ አበራ ምን ነበር ያልከው?
“እግዚአብሄር(አምላክ፣ቲኦስ) ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ነው፡፡አብ የምንለው የእግዛብሄር ልብ ወልድ የምንለው የእግዛብሄር ቃል መንፈስ ቅዱስ የምንለው ደግሞ እስትንፋስ ነው”(20)
መምህር ታሪኩ እንደነገረን እግዚአብሄር ወይም ደግሞ አምላክ በግሪኩ ደግሞ ቲኦስ ሚለው የተገነባው ከሶስት ክፍሎች እንደሆነ ነግሮናል አብ ማለት አምላክ ልብ ነው ወልድ የአንዱ አምላክ ቃል ነው መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የአንዱ አምላክ እስትንፋስ ነው፡፡ በዚህም አምክንዮ መሰረት ቃሉ ብቻ አምላክ ሊባል አይችልም እስትንፋም እንዲሁ አምላክ ሊባል አይችልም ልቡም በተመሳሳ መልኩ አምላክ ሊባል አይችልም ፡፡ ምክንያቱም አንዱ የአምላክ አካል አገነባቡ ከነዚህ ሶስት ክፍሎች በመሆኑ፡፡ ለየብቻቸው አምላክ አይደሉም፡፡ ልክ ስር ለብቻው ዛፍ እንዳልሆነ ሁሉ………….
የመምህር ብርሀነ ጎበናም ምሳሌ ይህን ፅንሰ ሀሳብ ያረጋግጥልናል ፡፡ እንዲህ ሲል የፃፈውን ማንበብ ይቻላል “……ለሰው በነፍሱ ሶስትነት አለው፡፡ይሀውም ልብነት፣ቃልነት፣ህይወትነት ነው፡፡የሰው ነፍስ በልብነቷ የአብ ምሳሌ ናት፡፡በቃልነቷ የወልድ በህይወትነቷ የመንፈስ ቅዱስ …….”
በመምህር ብርሀነ ጎበና ምሳሌም ከሄድን ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን ሰው የሚባለው አንድ ወጥ አካል ብዙ ውስጣዊ ክፍሎች አጣምሮ ይዟል፡፡ ከነሱም ውስጥ መምህር ብርሀነ ጎበና እንደነገረን ልብ ፣ ቃል ፣ ህይወት ሰው የተባለው አንድ ወጥ ሙሉ አካልን ያስገኙት የነዚህ ድምር ውጤት ነው፡፡ ቃል ብቻውን ሰው አይደለም፡፡ ልብ ብቻውን ሰው አይደለም እንዲሁም ነፍስ ብቻውን ሰው አይደለም፡፡
ቀጣዩ ጥያቄ እየሱስ ብቻውን አምላክ ነው ብለን ክርስትያኑን ስንጠይቀው አዎ ነው፡፡ ሲል ያለ እፍረት ሲመልስ ታየዋለህ ይህ ደግሞ ከላይ በቀረበው ሎጂክ መሰረት አያስኬድም ምክንያቱም ስር ብቻውን ዛፍ ሊባል እንደማይችል እየሱስ ብቻውን አምላክ ሊባል አይችለም ፡፡ ኖ አምላክ ሊባል ይችላል ለማለት የግድ ከሁለቱ ጋር ውህደት መፍጠር አለበት …..
የዛሬው ክርስትና መርህ ግን አብ ብቻውን አምላክ ነው፣ ወልድ ብቻውን አምላክ ነው ፣ መንፈስ ቅዱስ ብቻውን አምላክ ነው የሚል ነው ይህም በምህረታቡ ምሳሌ ሲተረጎም ስር ብቻውን ዛፍ ነው፣ ግንድ ብቻውን ዛፍ ነው ፣ ወይም ቅጠል ብቻውን ዛፍ ነው እንደመለት ነው ………….. ይህ እንግዲህ አዲሱ የስላሴ ስልት መሆኑ ነው፡፡
የሆነ ሆኖ ይህ ፅንሰ ሀሳብ ከ መፅሀፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል ወይም ይቃረናል፡፡ ምክንያቱም መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግርህ አብ እየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደዛፍ ስር እና ግንድ የተጣመሩ እና የተዋሀዱ አካላት ሳይሆኑ እራሳቸውን የቻሉ እና የተለያዩ መሆናቸውን ነው ሚነግርህ ማለትም አብ የአንዱ አምላክ ልብ እንደሆነ ሳይሆን ሚነግርህ አብ እራሱንየቻለ እንዲሁም ከወልድ የተለየ ሙሉ አካል እንደሆነ ነው ሚነግርህ፡፡ ወልድም የአንዱ እግዚአብሄር ክፍል እንደሆነ ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱስ ሚነግርህ እየሱስ የእራን የቻለ አካል እንደሆነ ነው ሚነግርህ በዚህም ስሌት መፅሀፍ ቅዱስን እንመልከተው፡፡
በመፅሀፍ ቅዱስ አብ ብቻውን አምላክ ተብሏል የሚከተለውን ምሳሌ መመልከት ትችላለህ
- " እኔ ወደ አባቴ እና ወደ አባታቹህ ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካቹህ ላርግ ነው ብለሽ ንገሪያቸው " (ዮሀ 20፡17)
ይህ ከላይ በአይንህ በብረቱ ያየሀው አንቀፅ በ እየሱስ አንደበት እንደተነገረ የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ ነግሮናል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት በሰማይ የሚገኘው አብ አምላክ ነው ወይም እግዚአብሄር ነው ማለት ነው፡፡ በምህረታብ ሎጂክ እና በታሪኩ ሎጂክ ብንስማማ እንዲህ ወደ ሚል ማጠቃለያ መድረስ መፍፁም አይቻለንም፡፡ ምክንያቱም ምህረተአብ እና ታሪኩ እንደሚሉን አብ የአምላክ አንዱ ክፍል እንጂ አምላክ አደለም፡፡ ልክ ስር የዛፍ ክፍል እንደሆነ እና ለብቻው ተለይቶ ሲመጣ ዛፍ ሊባል እንደማይችለው….
ይህንም ፅንሰ ሀሳብ ከመሰረቱ ለማቆም የሚያስችሉ ብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆችን ማቅረብ ይቻላል፡፡
- 1 ጴጥ 1፡3 “የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ይመስገን" ምን ማለት ነው? ፈለክም አልፈለክም የወልድ አባት እና አምላክ ይመስገን ማለት ነው……. በመሆኑም አብ ብቻውን አምላክ ተባለ እንጂ አምላክ እነ ታሪኩ እንደሚሉህ የሶስቱ ድምር አይደለም
- ኤፍሶን 1፡16 "የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና ክብር የሚገባው አምላክ(እግዚአብሄር)"
- ሮሜ 15፡5-6 "የእየሱስ ክርስቶስ አብት እና አምላክ ይመስገን"
- 2 ቆር 1፡3 "የእየሱስ ክርስቶስ አብት እና አምላክ ይመስገን"
ይህ ሁሉ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፅ በጉልህ እንዳስቀመጠው አብ ብቻውን አምላክ ወይም እግዚአብሄር ይባላል ፡፡ እግዚአብሄር ወይም አምላክ የሶስቱ አንድ መጠሪያ ስም ነው የሚለው መጫወቻ ካርድ ሚሽነሪዎች ስለማያዋጣቸው ቢቀይሩትሩት መልካም ነው፡፡…………
ሌላው እየሱስ እና አብ ልክ እንደ በዛፉ ምሳሌ እንደተጠቀሰው የተጣበቁ ሳይሆኑ የተለያዩ ነበሩ ለዚህም ምክንያታዊነት በመረጃነት ሚቀርበው መለኮታዊ ስትለው የምታንቆለጳጵሰው መፅሀፍ ነው፡፡ እነሆ መፅሀፍህ እንደነገረን ከሆነ እየሱስ በምድር ላይ ሳለ አብ በሰማይ ነበረ ፡፡ የሚከተሉትን አናቅፅት መመልከት ትችላለህ፡፡
- ማት 5፡45 "በሰማይ ላለው አባታቹህ ዘንድ ልጆች ትባሉ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ"
- ማት 6፡14 "ሰዎችን ይቅር ብትሉ በሰማይ ያለው አባታቹህ ይቅር ይላቹሀል
- ማት 6፡18 " ስትፆም በሰማይ ላለው አባትህ"
- ማት 6፡32 "ምን እንደሚያስፈል በሰማይ ያለው አባትህ ያውቃል
- ማት 7፡21 በሰማይ ያለው አባቴን ፍቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለን መንግስተ ሰማያት አይገባም"
እንዲሁም እየሱስ ያሰስተማረውን ፀሎት መመልከት ይቻላል፡፡አብ በሰማይ እንዳለ ግልፅ የሆነ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ስሌት ከተስማማህ ሚቀርብብህ ቀጣዩ ጥያቄ ወልድ የት ነው የነበረው የሚል ይሆናል? ለዚህም ጥያቄ ያለህ ብቸኛ ምላሽህ እየሱስ ይህን ሲያስተምር ምድር ላይ ነበር የሚል ብቻ ይሆናል፡፡ አብ በሰማይ ያለው አንድ አካል ከነበረ ወልድ በምድር ያለው ሌላ አካል ከነበረ የተለያዩ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ እናም በዛፍ ወይም በ ሰው መመሰሉ መሰረቱ ምንድ ነው? በሰማይ ያለው አብ አንድ በምድር ያለው እየሱስ ሁለት ሆነው ሳሉ እንደ ዛፍ የተጣበቁ አካላትስ አድርጎ ማቅረቡ ምን የሚሉት ፍልስፍና ነው? መሰረቱስ የትኛው የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፅ ነው? ይህ አዲሱ የስላሴ ስልት ሚሽነሪው ተራውን ተከታይ ለማሳት እየተጠቀመበት ያለ ስልት መሆኑን ለማወቅ እንግዲህ ነብይ መሆን አያስፈልግም!!!!!
አብ ማለት እግዚአብሄር ማለት ነው እሱም ከወልድ የተለየ አካል ነው ለምሳሌ ይህን ተመልከት
- ዩሐ 14፡1 “በኔም እመኑ በእግዚአብሄርም (ቲኦስ) እመኑ"
- ሐዋ 10፡38 “እግዚአብሄር እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው”
- ሐ.ስራ 2፡36 "እንግዲህ እግዚአብሄር እየሱስን ጌታም መሲህ እንዳደረገው እስራኤል ሁሉ ይወቅ"
- ሉቃስ 12፡8" እየሱስ እንዲህ አለ” ሳያፍር በሰው ፊት ለመሚመሰክርልኝ እኔም በእግዚአብሄር እና በመላእክት ፊት እመሰክርለታለሁኝ"
- 1ጢሞ 2፡5 “እግዚአብሄር አንድ ነው ፣ በመካከል ሆኖ እግዚአብሄር እና ሰውን የሚያስታርቀው አንድ እሱም ሰው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነው"
- ሉቃ 18፡18 “እየሱስም እንዲህ አለ ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ እግዚአብሄር ውጪ ቸር የለም"
- 1 ሐ.ስራ 7፡56 "እስጢፋኖስ ወደ ሰማይ ትኩር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሄር ክብር አየ ፣ እየሱስንም በእግዚአብሄር ቀኝ ቆሞ አየሁ ስለዚህ እነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅ በእግዚአብሄር በቀኝ ቆሞ አየሁት”
- ማር 16፡19 “ጌታ እየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ በ እግዚአብሄርም በቀኝ በኩል ተቀመጠ"
ይህ ለምሳሌነት ብቻ የቀረበ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሆን እየሱስ የእግዚአብሄር አንዱ ክፍል ነው ሲሉና አምላክ ሚባለው የሶስቱ አካላት ድምር ውጤት ነው ብለው እየተቀባበሉ የሚያስተጋቡትን ሁሉ ይቃወማል፡፡ ለምን? ለምን እንደሆነ በምሳሌ እንመልከተው….
ለምሳሌ ተመልከት 1ጢሞ 2፡5 " እግዚአብሄር አንድ ነው ፣ በመካከል ሆኖ እግዚአብሄር እና ሰውን የሚያስታርቀው አንድ እሱም ሰው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነው" ይልሀል ይህ እንግዲህ ቅር አለህም ጎረበጠህም የነ ምህረታብን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ይቃወማል፡፡ እነ ምህረትአብ---- እግዚአብሄር ማለት አብ ሲደመር እየሱስ(ወልድ) ሲደመር መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ሲሉ ቢነግሩንም መልኮታዊ ስትል ምታምንበት መፅሀፍ ግን እግዚአብሄር ማለት የ 3 ቱ ድምር ውጤት ሳይሆን አብ ብቻ እንደሆነ እና አንድ ብቻ እንደሆነ አልፎ ተርፎ ከእየሱስ ጋር እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ አካል እንደሆነ ጨምሮ ነግሮሐል፡፡ እየሱስ ባረገ ወቅት ከ አብ ውስጥ ገብቶ አንዱን እግዚአብሄር መሰረተ ወደሚል ምክንያታዊነት ሚያመራ ሎጂክ ቢያቀርቡም እንነምህረታብ መፅሀፍ ቅዱስህ ግን እየሱስ ባረገ ወቅት ከ እግዚአብሄር በቀኝ ቆመ ወይም ተቀመጠ ይልሀል መለኮታዊ ብለህ ምታንቆለጳጵሰው ፅህፍህ እየሱስ እና እግዚአብሄር ፍፁም የተለያዩ አካለት መሆናቸውን ታውቅ ዘንድ የግድ መንፈስ ቅዱስ እስጊገልፅልህ መጠበቅ የለብህም ምክንያቱም የ እየሱስ እና የ እግዚአብሄርን መለያየት ይገለፅልህ ዘንድ መፅሀፍህን ገልጠህ ማንበብ በቂና በቂ ነው፡፡
እየሱስ በምድር ሳለ እግዚአብሄር በሰማይ ነበር፡፡ የወንጌል ፀሀፊዎች እንደሚነግሩን ከሆነ እየሱስ እና እግዚአብሄር ሁለቱም ሰማይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎን ለጎን የተቀመጡት በእየሱስ እርገት ወቅት ነበር፡፡ እየሱስ ሲያርግ እና በእግዚአብሄር በቀኝ በኩል ሲሆን እግዚአብሄር ደግሞ በ እየሱስ በ ግራ በኩል ሆነ ...... አስተውለህ ከሆነ እየሱስ " እግዚአብሄር እና እራሱ" እንደሚለያዩ እዚ ምድር ላይ ሳለ ነግሮህ ነበር ፡፡ ተመልከት ሉቃስ 12፡8" እየሱስ እንዲህ አለ " ሳያፍር በሰው ፊት ለመሚመሰክርልኝ እኔም በእግዚአብሄር እና በመላእክት ፊት እመሰክርለታለሁኝ" እግዚአብሄር እና እሱ መለያየታቸውን በግልፅ ነገረህ ፡፡ ሲብስም ሉቃ 18፡18 " እየሱስም እንዲህ አለ ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ እግዚአብሄር ውጪ ቸር የለም" በነገራችን ላይ ሳልነግርህ ማላልፈው ነገር ቢኖር በብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆች ውስጥ ያገርህ ሰው የቋንቋ ቁማር እየተጫወተ መሆኑን ነው…. እንዴት ከተባለ ግሪከኛውን ቃል ቲኦስ ሲያሰኘው እግዚአብሄር ሲያሰኘው አምላክ እያለ መተርጎሙ እራሱ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል ለምን አላማ ተፈልጎ ነውም ያስብላል፡፡
ሹፍ!! አንድ እግዚአብሄር አለ ይህም እግዚአብሄር ደግሞ ጳውሎስ እንደነገረህ እየሱስ አይደለም እየሱስ ስራው ሰውን ከ ዚህ እግዚአብሄር ጋር ማገናኘት ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ማርቆስ ወንጌል ላይ እንደተነገረህ ይህ እግዚአብሄር ደግሞ በሰማይ ነበረ…. እየሱስ ዮሐንስ ወንጌል ላይ እንዲህ ብሏል
"ወደ አባቴ እና ወደ አባታቹህ ወደ አምላኬ(ወይም ወደእግዚአብሄሬና) እና ወደ አምላካችሁ(ወይም ወደ እግዚአብሄራቹህ) ላርግ ነው፡፡" በአንቀፁ ላይ የተጠቀሰው የግሪክ ቃል ቲኦስ የሚል ነው፡፡ ቀጥታ ትርጉሙ አምላክ ወይም እግዚአብሄር ፈጣሪ ማለት ነው ፡፡
የትኛውም ምሁር ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚስማማበት ነገር እዚጋር እንዳለ ላስታውስህ ፡፡ እሱም አምላክ ማለት የእግዚአብሄር ሌላ ስሙ ወይም ደግሞ እግዚአብሄር ማለት የ አምላክ ሌላ ስሙ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የፈለከው አንቀፅ ላይ ያለውን ቲኦስ የሚለውን የግሪክ ቃል አምላክ ወይም እግዚአብሄር ብለህ ብትተረጉመው ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ተቀያያሪ ስሞች በመሆናቸው………!! አይደለም ሚል ተከራካሪ በምሁራን ዘንድ መሳቂያ እና መሳለቂያ ከመሆን የዘለለ ትርፍን አያተርፍም….
በዚህ ከተስማማን ወደ ዋናው ርእስ ስመልስህ በወንጌሎች ውስጥ እጅግ በሚበዙ ስፍራዎች ውስጥ እግዚአብሄር እና እየሱስ የተለያዩ ወጥ አካላት መሆናቸው ተቀምጧል፡፡
ካስታወስክ እየሱስ የዘላለም ህይወትን አስመልክቶ እንደህ ብሎ ተናግሯል “የዘላለም ህይወትም፣ ብቻህን እውነተኛ አምላክ(እግዚአብሄር) የሆንከው አንተ እና የላከውን እየሱስ ክርስትቶስ ማወቅ ነው"(ዮሐ 17፡3) ብቸኛው አምላክ እግዚአብሄር ወጥ አካል ሲሆን ከ እየሱስ የተለየ አካል ነው፡፡ እግዚአብሄር ማለት 3 ሲደመሩ ነው የሚለው የሐገርህ ሚሽነሪዎች ተራ ብሂል አንድ ደረጃ ወደ ላይ እንደሚያስኬድህ በውድ ካልሆነ ደግሞ በግድ ማወቅ ይኖርብሀል!!! አንድ አምላክ አለ በሰዎች እና በአምላክ መሃል አንድ አስታራቂ አለ ይህም አስታራቂ እንግዲህ እየሱስ ነው ሲል ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በደንብ አስታውስ….. እንቀጥል……..
እንዳልኩህ እግዚአብሄር እና እየሱስ መለያየታቸውን አስረግጠው የሚያሳዩ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆች እጅግ ከመብዛታቸው የተነሳ አንባቢ ይቁጠራቸው በል እንጂ ቆትረህ አትዘልቃቸውም ፡፡ ወደ ጳውሎስ መልእክት ጎራ ብትል እንኳ ጳውሎስ እንዳለው አንድ እግዚአብሄር አለ አንድ ልጅም አለው ፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ---- ልጁ(ወልድ) በምድር------ ጭራሽ ፍፅም የተለያዩ አካላት እንደሆኑ ነው በግልፅ ያስቀመጠው ፡፡ ለማንኛውም አንቀፁ እንዲህ ይነበባል “እግዚአብሄር ለአንድ ልጁ(ወልድን) ሳይራራ ለኛ አሳልፎ ሰጠው"(ሮሜ 8፡32) ወይም በሰማይ ያለው እግዚአብሄር በምድር ያለውን እየሱስ አሳልፎ ሰጠው ብለህ መተርጎም ትችላለህ፡፡ በአንቀፁ መሰረት እነዚህ ሁለት ህልውናዎች የተለያዩ ሆነው ሳለ የነ ምህረታብ በዛፍ የመመሰሉ ሎጂክ ምንጩ መልስ ያጣ አእምሮ እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ እንዳልሆነ ደግሜ ደጋግሜ በእርግጠኝነት እነግርሀለው ….. በመሆኑም እግዛብሄር አንድ ራሱን የቻለ አካል እየሱስ እራሱን የቻለ ሌላ አካል ……... ሁለት ናቸው አንዱ በምድር ሌላው በሰማይ ይህ እኮ መፅሀፍ ቅዱስን ያነበበ ተራ ኢለመንገተሪ ተማሪ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ እንዴት መንፈስ ቅዱስ ይህን እንዳለገለፀላቸው ለኔ ራሱ ግርምት ሆኖብኛል!!!
ምሳሌ መጨመር ካስፈለገ መፅሀፍህ ውስጥ በሚከተለው መልኩ የተቀመጠውን አንብብ
"እግዚአብሄርን እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው"(ሐ.ስራ 10፡38) እግዚአብሄር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ድምር መጠሪያ ስም ቢሆን ኖሮ አንቀፁ "አብ እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው " የሚል ይሆን ነበር፡፡ ነበር ባይሰበር ልበልህና አልሆነም ፡፡ 1ዱ አምላክ ጳውሎስ እንዳለህ አንዱ እግዚአብሄር ነው እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ የቀባው …..
ፅንሰ ሐሳቡን ሳጠቃልለው ስላሴን በዛፍ የመመሰሉ ሎጂክ አእምሮ ስራ ሲፈታ የፈበረከው እንጂ ሰነዳዊ ማስረጃ ያለው ፅንሰ ሐሳብ አይደለም ፡፡ አብ ወልድን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን በ አንድ ወጥ አካል እና በተለያዩ ክፍሎች መመሰሉ ከራሱ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር በጭራሽ አያስኬድም ፡፡ ከላይ እንዳየነው አብ እየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ(ያልተጣበቁ) እና እራሳቸውን የቻሉ አካላት መሆናቸውን ነው፡፡ እነዚህ አካላትን አምላክ ናቸው ማለት ሶስት አምላክ አለን ብሎ ከመናገር የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡ የሆነ ሆኖ ያገር ውስጥ ሚሽነሪዎች አዲስ ፅንሰ ሐሳብ ፈጥረው የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ወደ አንድ አምላክ ፅንሰ ሐሳብ ለመቀየር ያደረጉት ሙከራን ሳላደንቅ አላልፍም ፡፡ ዘለሉም ፈረጡም ግን ይህ ፅንሰ ሐሳባቸው አዲስ ከመሆኖም ባሻገር ከለው መሰረታዊ ፅሁፍ ወይም መለኮታዊ ነው ሲሉ ከሚያምኑበት ሰነድ አንፃር ተቀባይነት እንደማይኖረው ወይም ውዳቂ አሳብ ከመሆን ባሻገር ሌላ ቦታ አይኖረውም፡፡ ይህ እንግዲህ አንዱ እና የመጀመሪያው የስላሴ ፅንሰ ሐሳበብ ሲሆን ወደ ሁለተኛው እናምራ ነው ሚባለው?
አትናሲያን ስላሴ፡- ይህ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ፍፁም የተለያዩ እና እራሳቸውን የቻሉ አካላት እንደሆነ ያምናል ማለትም አብ ወልድ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ አደለም ወልድም እንዲሁ አብ አደለም መንፈስ ቅዱስ አደለም፡፡ በአካል ይለያያሉ ወልድ ምድር ላይ ሳለ አብ ሰማይ ነበር … ይህ የስላሴ እምነት ምስሉ ከላይ የተመለከትከውን ይመስላል፡፡ ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ የአትናሲያንን አቂዳ እንደወረደ በዚህ መልኩ ቢገልፀው አይገርምም፡፡
" in the words of the Athanasian Creed: "the Father is God, the Son is God, and the Holy Spirit is God, and yet there are not three Gods but one God."(21)
ይህ ፅንሰ ሐሳብ እነምህረት አብ ከሚሉህ ስላሴ በእጅጉ ይለያል:: የነ ምህረተአብ እግዚአብሄር አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ተዋቅረው ልክ እንደ ዛፍ ተጣብቀው ያመጡት ውጤት ነው፡፡ ይህ ፎቶ ግን ሚነግርህ አብ እራሱን የቻለ አካል እና ከ ወልድ የተለየ መሆኑን እንዲሁም ወልድ ከ አብም ከ መንፈስ ቅዱስ የተለዩ መሆናቸውን ነው፡፡ ስለ ሆነም እንደ አትናሲያን አቂዳ መሰረት እነዚህ በምስሉ ላይ ምትመለከታቸው ሶስት ሳይሆኑ አንድ አማላክ ናቸው ……… ይህ ነው እንግዲህ አንድ ሲደመር አንድ ሲደመር አንድ እኩል ይሆናል አንድ ማለት …………………. ሶስት መሆናቸውን ለማወቅ መቁጠር ብቻ ይጠበቅብሐል፡፡
ዱዋሊዝም እና ስላሴ ፡- ይህን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ውግዘት የደረሰበት የስላሴ አይዲዮሎጂ መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ፅንሰ ሀሳብ አራማጆች እንደሚያምኑት ስላሴ ማለት በሶስት መልኩ ራሱን የገለጠ አምላክ ነው ሲሉ ያምናሉ ፡፡ አምነውም ሲያበቁ ምሳሌ ለመስጠት ሲሞክሩ ይስተዋላል ፡፡ ይህ ከሚያቀርቡት ምሳሌ አንዱ ምን መሰለህ ውሀ በሶስት ሁኔታ ይገለፅ የለ ይሉሃል አንተም መልሰህ አዎ ስትላቸው አንዱ ፈጣሪ በሶስት መልኩ ቢገለፅ ምና ለበት ይሉሀል፡፡ ይህ ፅንሰ ሐሳብ በ መፅሀፍ ቅዱስ ስሌት ሲለካ ተራ አሉባልታ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው ብዙሀን የክርስትና አንጃዎች ይህን ፅንሰ ሐሳብ መርምረውት ሲያበቁ አንድ ደረጃ እንደማያስኬዳቸው ሲገባቸው ወድያውኑ ውድቅ ያደረጉት ወደ ላይም ከፍ ሲሉ ይህን ፅንሰ ሃሳብ የተቀበለን ሁሉ በክህደት የፈረጁት፡፡ ይህ ፅንሰ ሀሳብ ውድቅ ለማድረግ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ መሆን አያስፈልግም አንዱን ወንጌል ብቻ ካነበብከው ይህ ፅንሰ ሐሳብ እንደማያስኬድ ትረዳለህ………………….
ማጠቃለያ ፡- በዚህ ፅሁፍ ላይ ለማስገንዘብ የፈለኩት ዋና ነጥብ ስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በእጅጉ ራስ ምታት በመሆኑ ሰበብ የተለያየ እና የተቃረነ ፅንሰ ሐሳብ ይነሳበት ዘንድ ምክንያት ሆኗል የመጀመሪያው አዲሱ ስላሴ ስልት ብዬ የሰየምኩት ሶስቱን አካላት ተጣብቀው ልክ እንደ ዛፍ አንድ አካል ሆኑ ሲሉ ማስተማር እንዲሁም ያለ እፍረት መፃፍ ለጀመሩት ያገራችን ሚሽነሪዎች ሲሆን ሐሳቡም ወዴት እንደሚጠያመራ እና ማጠቃለያው እንደማያምር ለማሳየት እና ለማስገንዘብ ነው፡፡ ሁለተኛው የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በ ሀገራችን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሲሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንደ ዛፍ የተጣበቁ አንድ ወጥ አካል ሳይሆን ሶስት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን የሚያትተው የስላሴ አካል ነው እንዴት እንደተለያዩ ማወቅ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለህትመት የበቃውን ፎቶ መመልከት በቂ ነው ፡፡ እንደዛፍ አንድ ወጥ አካል አለመሆናቸውንም ስእሉ ራሱ በቂ ምላሽ ነው፡፡ ሶስተኛው የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ግና ሞዳሊዝም በሚል ስያሜ የሚታወቀው ሲሆን በመሰረቱ ውግዝ የተደረገ ፅንሰ ሐሳብ ነው ፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ለአእምሮ የጎረበጠ መሆኑን ምሁራን በ አንድ ድምፅ ይስማሙበታል፡፡
Rev. J.F. de Groot ምን ነበር ያልከው?
“It remains impossible for human intellect how three people has one divine nature.”(22) “ለሰው ልጅ ጭንቅላት (ያለተመለሰ ነገር ቢኖር) እንዴት ሶስት አካላት በመለኮት አንድ ይሆናሉ (ሚለው ጥያቄ ነው)” The new catholic encyclopedia በበኩሉ “One should not speak of tritarianism in New Testament without series qualification …”(23) በኔው አማርኛ “ እንድ (ሰው) በአዲስ ኪዳን ስላሴን አስመልክቶ ሊናገር አይችልም (ብዙ) ማስተካከያዎችን (ካላስከተለበቀር)”አንድ እርምጃ በመራመድ C.F Bergson የሚተለውንብሏል ““To attribute son to God is to deny the perfection of God”(24) “ ለፈጣሪ ልጅ ማረግ የፈጣሪን ሙሉእነት ማጓደልነው”ሙስሊም ምሁራንም በበኩላቸው ይህን ፅንሰ ሀሳብ ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ ሲሉ አጣጥለውታል(25) ፡፡ The new catholic encyclopedia ምአክሎ ይህ ፅንሰ ሀሳብበ 4ተኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ መሆኑን አስረግጦ ከትቦልናል(26)
በሙስሊሙ ታሪክ ይህን ፅንሰ ሀሳብ በመቃወም ሼይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያህ (27) በመፅሀፋቸው እራሱን የቻለ መልስ ሲፅፉ ተማሪው አልሀፊዝ ኢስማኢል ኢብኑከሲር (28) በበኩላቸው የእየሱስን ኢስላማዊ ገፅታ አጥርቶ ሚያሳይ ዳጎስ ያለ ኪታብ አዘጋጀተውልናል፡፡ ምዕራፍ ሁለት በቅርቡ ይጠብቁን ………
Reference
4. ሚስጥራዊ ቡድን ቪድዮ፣ መምህር ምህረተአብ
5. ኪዳነማርያምጌታሁን፣ክርስቶስ ከቁርአን ጋር ምን አገናኘው፣1999፣2ተኛእትም ገፅ 78-79
6. አባሳሙኤል፣የሀይማኖት መቻቻል በኢትዮጵያ አለን ፣ቁጥር 1፣2000፣ገፅ 136
7. .መምህር ታሪኩ አበራ፣እየሱስ ማነው?፣3ተኛእትም፣2003፣ገፅ 5
8. መምህር ብርሀኑ ጎበና፣አምደ ሀይማኖት 11ደኛእትም፣2000 ገፅ 39
9. መምህር ብርሀኑ ጎበና፣አምደሀይማኖት 11ደኛእትም፣2000 ገፅ 42
10. የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበቃላት፣8ተኛእትም፣1998 ገፅ64
11. http://en.wikipedia.org/wiki/trinity
12. http://www.thefreedictionary.com/
13. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
14. Ford, J. T. (2006). Glossary of Theological Terms. Winnona, Minnesota: Saint Mary’s Press. p. 188
15. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
16. Dunham, Scott A. (2008). The Trinity and Creation in Augustine: An Ecological Analysis. Albany, New York: State University of New York Press. p. 41
17. William, X. (2006). Economics, Ethics, Religions & Superstitions. Lincoln, Nebraska: iUniverse. p. 234
18. Hopkins, S. (n.d.). The System of Doctrines Contained in Divine Revelation, Explained and Defended. Showing their Consistence and Connection with each other, Vol. 1. Boston: Isaiah Thomas and Ebenezer T. Andrews. p. 444
19. ሚስጥራዊ ቡድን ቪድዮ፣ መምህር ምህረተአብ
20. መምህር ታሪኩ አበራ፣እየሱስ ማነው?፣3ተኛእትም፣2003፣ገፅ 5
21. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
22. Rev. J.F. de Groot , Catholic teaching pp. 101
23. The new catholic encyclopedia ,1967 vol. 14 pp.295
24. C.F Bergson , the creative evolution pp. 16
25. Christianity original and the present , Muhammed Ibn Abdelah as Salim pp. 15
26. The new catholic encyclopedia ,1967 vol. 14 pp.299
27. Al Jewab As Saih Limen Bedele Dinul Mesih
28. Al hafith ibn katheer, the Islamic view of Jesus.
29. የተጠቀምኩት መፅሀፍ ቅዱስ KJV bible ሲሆንየ1816ቱእትም