by ጌታ » Tue Mar 22, 2022 2:36 pm
ይገርምሃል ሳላህ እንዲሸጥ በርትቼ እየጠለይኩ ነው፡፡ እያለ ያለው ከሲቲው ደብሩይን እኩል ክፈሉኝ ነው፡፡ ከሲቲ ተጫዋች እኩል ለመከፈል እንደሲቲ በተከታታይ ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ አለብህ፡፡ አንዳንዴ እኮ ጎበዝ ጎበዝ ሲሉን ይዞርብናል (እኛ ታዋቂ ሰዎች ቂቂቂቂቂ)
ሊቨርፑል ዋትፈርድን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሸንፍ ተገምቶለታል፡፡ አይዞን ዋትፈርድን አንፍራ.......ግን ይሄ ሰው ንቆ መግባት ይቅርባችሁ.......
ሁለቱም ቡድኖች በሚቀጥለው ዘጠኝ ጨዋታዎች በሚገጥሟቸው ቡድኖች ዋንጫው ይወሰናል፡፡ ከሁሉ የበለጠ ሲቲና ሊቬ ሚያዝያ ውስጥ በአንድ ሳምንት ሁለቴ ይገናኛሉ፡፡ ጉዋርዲዮላ ባለፈው ከፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ሳይፈሩን ከፍተው በማጥቃት ከሚጫወቱ 5 የሚሆኑ ቡድኖች ዋናው ሊቨርፑል ነው ብሎ ነበር፡፡ ይሄ ማለት እኔ ከሲቲ ጋ ያለው ግጥሚያ የሚያስፈራኝን ያህል እሱንም እንቅልፍ እንደሚያሳጣው ነው፡፡
ለማንኛውም ተሥፋችንን ሳናበዛ የሚሆነውን እንመልከት..........ፕሪሚየር ሊጉንና ሻምፒዮንስ ሊግን ካሸነፉ ሊቨርፑል ድረስ ሄጄ ላከብር ቃል እገባለሁ........ላንተ
ባልተያያዘ ዜና - የአርሰናሉ አርቴታ ባለፈው ኦባምያንግ ካገሩ አርፍዶ መጣ ብሎ ከቀጣው በኋላ ለባርሴሎና ሲያስረክበው አናዶኝ ነበር፡፡ ለክፋቱ አርሰናል ከዛ በኋላ የያዛቸው ሴጣን ለቋቸው ድል በድል ሆኑ - ሊቨርፑል እስኪያሸንፋቸው፡፡ በሌላ በኩል ኦባምያንግም ባርሴሎና ውስጥ እያማረበት ነው፡፡ መሄዱ ለአርቴታ እንደድል ቢቆጠርም አሁን ግን ይህን የመሰለ ተጫዋች በነጻ በመልቀቁ እየተወቀሰ ነው፡፡
ክሎፕ ሳካ ላይ ዓይኑን ጥሏል ይባላል፡፡ ልጁ እስከ 2024 ኮንትራት ቢኖረውም ክሎፕ ለሳላህ ወይም ማኔ መተኪያ ይሆነኛል ብሎ እያሰበ ነው......አሉ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!